April 8, 2024
10 mins read

እራሳቸው ፈተና የወደቁ፤ ፈተና ፈታኞች !!  (አሥራደው ከካናዳ)

ምስሎች : ከባንክሲ የመንገድ ላይ የጥበብ ሥራዎች የተዋስኳቸው::

Adanech Abebe 1 1 1

መንደርደርያ :

  • « The only thing we have to fear is fear itself. »        Franklin D. Roosevelt

«  ልንፈራው የሚገባ ነገር ቢኖር፤ እራሱን ፍራቻን ብቻ ነው »   ፍራንክሊን ሩዝቬልት

  • « Only when we are no longer afraid do we begin to live »    Dorothy Thompson
    « ፍራቻን ስናስወግድ ብቻ ነው መኖር የምንጀምረው »
  • « Hate is the consequence of fear; we fear something before we hate it…» Cyril Connolly

« ጥላቻ የፍርሃት ውጤት ነው፤ ከመጥላታችን በፊት፤  የሆነ ነገር እንፈራለን (ሌላውን መፍራት እንጀምራለን)… »    ሲሪል ኮኖሊ

 

መግቢያ :

ለመሆኑ የፈተና ዓላማና ግቡ ምንድነው ?!  ፈተናን ማን ለማን ይሰጣል ?!  የፈተና መለኪያ መሳሪያዎች ምንድናቸው ?!  ፈተና መቼና እንዴት ይሰጣል ? ፈተናውን ለማለፍ፤ መስፈርቶቹ ምንድናቸው ?!  መስፈርቶቹስ እንዴትና በማን ይወሰናሉ፤ በፈታኝና ተፈታኝ መሃከል ያለው ግኑኝነት ምን መሆን አለበት……….. ወዘተ.

በመጀመሪያ አንድ አገር፤ ከሁሉም አገራዊ ጉዳዮች በማስቀደም፤ የትምህርት ፍልስፍና (Educational Philosophy) ሊኖራት ይገባል::

ከዚያም፤ የትምህርት ፍልስፍናዋን  (Educational Philosophy) በሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ ቀመሮች ላይ በመንተራስ፤ የህዝቧን ታሪካዊ ፈለግ፤ የማህረሰባዊ ትስስርና የአኗኗር ልምድ በማጤን፤ ጤናማ የሆነ ሥርዓተ ትምህርት መቅረጽ (መንደፍ) ይኖርባታል ::

በአንጻሩ በአገራችን ኢትዮጵያ፤ ቀደም ብሎ ህወሃት፤ አሁን (የኦህዴድ/ኦነግ) ጥምር ብልጽግና ተብዬ የነደፉት ሥርዓተ ትምህርት፤ ሆን ተብሎ ትውልድን የአይምሮ ሰንካላ አድርጎ የሚገድል፤ አገርን አመክኖ ለማፍረስ የተወጠነ በመሆኑ፤ ይኸው አሁን ያለንበት አገራዊ የትምህርትና የትውልድ ውድቀት ላይ ደርሰናል ::

እነዚህ እራሳቸው የኢትዮጵያዊነት ፈተናን፤ ተፈትነው ደጋግመው የወደቁ፤ የዘረኝነት፤ የጎሠኝነትና የጥላቻ ፖለቲካ ሰባኪዎች፤ ለአዲስ አበባ ህዝብ፤ ብሎም ለመላው የኢትዮጵያ፤ ህዝብ፤ ፈተና የመስጠት የዕውቀት ችሎታ፤ የሞራል ብቃትና  የሰብአዊነት ሚዛን የማይደፉ፤ አርቆ ለማስተዋል የማይችሉ፤ ዳፍንታሞች በመሆናቸው፤ ህዝብ በአንድላይ በመነሳት በቃ ሊላቸው ይገባል ::

የአዲስ አበባ ሕዝብ ! ብሎም  መላው የኢትዮጵያ  ሕዝብ ሆይ ! !

  • እንዴት ውርደትን አሜን ብለህ ለመቀበል፤ እነዚህ የዘር ፖለቲከኞች የሚሰጡህን ፈተና ለመፈተን ትሰለፋለህ ??!!
  • በዘረኝነትና በጎሠኝነት፤ ከዜሮ በታች በእጅጉ የዘቀጡ ሲያዋርዱህ፤ ጥቃቱ አንገፍግፎህ በቃ ! የምትላቸው መቼ ነው ?!
  • ለመሆኑ: ከዜሮ በታች እስከ ስንት ዲግሪ ሴንትግሬድ ድረስ: ሲያዋርዱህ ነው ጥቃቱ የሚያንገፈግፍህ ?!
  • መቼነው እነዚህ አርቆ ለማስተዋል የማይችሉ፤ የፖለቲካ ዳፍንታሞችን፤ ከጀርባህ ላይ አሽቀንጥረህ በመጣል ነፃ ህዝብ የምትሆነው ?!

 

  • የአዲስ አበባ : ብሎም  መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ! ውርደትህ የሚያበቃው፤ በህዝባዊ እምቢተኝነት መሆኑን በመረዳት፤ ተባብረህ በአንድነት ተነሳ !  ያለ ፍላጎትህ በግድ የጫኑብህን፤ የዘርና የጎሣ ፖለቲካ፤ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከትከሻህ ላይ አሽቀንጥረህ ጣል !!

ማሳረጊያ

በሰው ልጆች የአኗኗር ሂደት ውስጥ፤ ሦስት ዓይነት የማህበራዊ ግንኙነቶች ያሉ ሲሆን እነሱም :

  1. የእኔየእኔ ነው
  2. 2. የእኔ የእኔ ነው፤ ያንተም የእኔ ነው
  3. 3. የእኔ ያንተ ነው፤ ያንተም የእኔ ነው የሚሉት ሲሆኑ፤

ከነዚህ ውስጥ፤ በቁጥር 1 እና 2 ያሉት ሁለቱ፤ ጤናማ ያልሆኑ ግንኙነቶች ሲሆኑ፤

አንዱ ብቻ፤ በቁጥር 3 ያለው፤ ለሰው ልጆች ጤናማና፤ አብሮ በጋራ የመኖር መሠረት የሆነ ሲሆን፤ እሱም: የእኔ ያንተ ነው፤ ያንተም የእኔ ነው የሚለው : የጋርዮሽና የመተሳሰብ ማህበራዊ ግንኙነት ነው ::

ህወሃት ለ27 ዓመታት፤ ያሰፈነው ሥርዓት፤ « የእኔ የእኔ ነው፤ ያንተም የእኔ ነው » የሚለው የዘራፊነት፤ የሌብነትና የንቅዘት (የሙስና) ሥርዓት ነበር :: ህወሃት ጠፍጥፎ የፈጠራቸው አሽከሮቹ የ(ኦህዴድ/ኦነግ)ጥምር ብልጽግና ተብዬዎች፤ ከጌቶቻቸው ውድቀት፤ ምንም መማር የማይችሉ ደንቆሮዎች በመሆናቸው፤ ያንኑ የፈጣሪያቸው የህወሃትን የቀማኛ ሥርዓት በከፋ መልኩ « ሁንዱማ ኬኛ በማለት » መቀጠሉን መርጠዋል::

የዘረኝነትና የጎሠኝነት ሥርዓታቸውን ዕድሜ ለማራዘም፤ በገዛ ወገኖቻቸው ላይ፤ በድሮንና በጦር አውሮፕላኖች፤ ቦንብ የሚያዘንቡ ህሊና ቢሶች፤ የኢትዮጵያን ህዝብ፤ የኢትዮጵያዊነት ካባውን አውልቀው፤ የዘረኝነትና የጎሠኝነት ቡቱቱ ለማልበስ፤ የሚያደርጉትን ደባና ሸፍጥ፤ ሕዝብ በአንድነት በመነሳት አምቢ ሊላቸው ይገባል ::

ዘረኝነትና ጎሠኝነትን እያራገቡ፤ እኛን እርስ በርሳችን በማባላት፤ እነሱ በሌብነት፤ በንቅዘት (በሙስና) ተሰማርተው፤ የአገር ሃብት እየዘረፉ ያዘርፋሉ ::

አይምሯቸው በዘረኝነት በመበከሉ፤ አርቆ የማሰብ ችሎታቸው ተገድቦ፤ የገዛ ወገኖቻቸውን የሚያርዱ፤ የሚያፈናቅሉና እንዲሰደዱ የሚያደርጉ፤ በሌብነት የሰለጠኑ፤ የአገር ሃብት ዘራፊዎች፤ በንቅዘት ወይም በሙስና ማጥ ውስጥ ተዘፍቀው፤ አጉል አጉል የሚሸቱ ነቀዞች፤ ፍትህ ተረግጦ፤ ዜጎች ያለ ፍርድ ወህኒ ቤት እየታጎሩ፤ ዜጎችን በየቦታው በጠራራ ፀሓይ ፤ በጥይት የሚገሉ ወንጀለኞች ፤ የድሃ ወገኖቻችንን ቤት እያፈረሱ፤ ሜዳ ላይ የሚበትኑ፤ ዜጎችን እያፈኑ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከድሃው ህዝብ የሚጠይቁ፤ የጠራራ ፀሐይ አጋሚዶዎችን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቃ ! ሊላቸው ይገባል ::

ጎበዝ ! ልብ ከሸፈተ ከተማም ጫካ ነው !! የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፤ ፋኖ ይመጣል እያላችሁ ከመጠበቅ፤ እራሳችሁ ፋኖ ሁኑና፤ ትግሉን በመቀላቀል፤ የድሉን ቀን እናፋጥን !! የመከራውን ቀን እናሳጥር !!

አጠያፊዎችን መጠየፍ ወንጀል አይደለም !!

ፍርሃት፤ ዝምታና አድር ባይነት ወንጀል ነው!!

ሳይዘገይ በአንድነት በመነሳት ነፃ ህዝብ እንሁን !!

የፈራ ይመለስ !! ድል ለፋኖ !!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

በሥር ነቀል ለውጥ፤ ወደ አዲስ ተስፋ !!

ነፃነት፤ እኩልነትና ወንድማማችነት ይለምልም !!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ !!

መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ( 06/04/2024 ) እኤአ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

Go toTop