March 30, 2024
6 mins read

ፋኖን ለምን ትደግፊያለሽ? ለምትሉኝ መልስ መስጠት እፈልጋለሁ

ዶ/ር ትእግስት መንግስቱ

GJ25A74WAAAubrAይህ የሚያሳዝን ዘመን መጥቶብን ኢትዮጵያዊ ነኝ ብቻ ማለት አልበቃ ብሎ ዘር መቁጠር ጀምረናል ባንድ ወቅት ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለ ሁሉ አማራ ነው  እየተባለ መታወቂያው ላይ እንዲፃፍለት የወያኔ መንግስት አዞ ነበር፡፡

አብይ አባቱ ኦሮሞ : እናቱ አማራ መሆኗን ነግሮናል:: ነገር ግን የአማራ ሴት ጡት ያልጠባ ይመስል ይህንን ህዝብ እንዴት እንደሚያንገላታው እያየን ነው:: የናት ጡት ነካሽ የሚለው አባባል ትዝ አለኝ::

እኔ ራሴን ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዬ ነው የማምነው:: ልጅ ሆኜ እናቴ ጎጃሜ መሆኗን እሰማለሁ ; የአባቴ ቤተሰቦች ከአዲስ አለም እንደመጡ አውቃለሁ : ነገር ግን አንድም ቀን አማራ የሚለውን ቃል ሲነገር አልሰማሁም :: ያደግኩት ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን መፈክር እየሰማሁ ነው:: ለኔ ይህ መፈክር ብቻ ሳይሆን ጥልቅ የሰመጠ እምነት ነበር::

ራሻ ሄደን ከሌላ ኢትዮጵያኖች ጋር ስንገናኝ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ እናቴ አማራ እንደሆነች የተነገረኝ:: የአባቴ እናት ብዙዬም የሸዋ አማራ ነበሩ:: አያታቸው ወልዶ አማኑኤል ከምኒልክ ጋር በአድዋ የተዋጉ ጀግና:: ለጀግንነታቸውም አዲስ አለም ምኒልክ መሬት ሸለ ሟቸው ::የወልዶአማኑኤል የልጅ ልጅ ( የአባቴ አጎት ) ድረስልኝ የሁለተኛ አለም ጦርነት ጀግና አርበኛ ነበር  ጣልያንን ሲዋጋ ተይዞ በአደባባይ የተሰቀለ::

ለሀገራቸው መሰዋትነት የከፈሉ አርበኞች ኢትዮጵያ ኖች , አረንጋዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን ይዘው ከተዋጉ  ዘር በመፈጠሬ እኮራለሁ:: ወያኔ መጥቶ በብሄረሰቦች እኩልነት ስም ሃገራችንን ከፋፈላት የብሄረሰቦች መብት ማስከበሪያ ሳትሆን የተረኛ ፖለቲካ ማረማመጂያ ሆነች:: ወያኔ መጥቶ ዘመኑ የትግሬ ነው ብሎ ሌላውን ሲረግጥ ቆየ:: ለውጥ መጣ ብለን ደስ ሲለን አብይ መጣ : አሁን ደሞ ጊዜው የኦሮሞ ነው ተባልን:: ከወያኔ ጊዜ የባስ እንጂ የተሻለ አልመጣም:: ግርድፍን አባርሬ እንትፎን አመጣሁ ነዉ የሆነው::

ኢትዮጵያንና አረንጋዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን ሲያይ የሚያመው ጎጠኛ ኢትዮጵያን እስከመራ ድረስ ኢትዮጵያኖች ከዚህ ከአዙሪት የተረኝነት ጎጠኛ ፖለቲካ አንላቀቅም ፉኖ አነሳሱ የ አማራን በደልና ጭፍጨፋ ለማስቆም ቢሆን መድረሻው ግን ይህን የተረኝነት ፖለቲካ ላንዴና ለመጨረሻ አስቁም : ኢትዮጵያኖች ከማንኛውም ብሄረሰብ ቢወለዱም እንደፈለጉ በየትኛውም በኢትዮጲያ ክፍል እየተዘዋወሩ : ሳይገደሉ : ሳይፈናቀሉ: መብታቸው ተጠብቆላቸው: መመረጥም  መምርጥም መብት አግኝተው እንዲኖሩ; ሃብት አፍርተው ; ቤተሰብ እያስተዳደሩ ሊኖሩ እንዲችሉ ለማድረግ ነው::

መንግስት ፅንፈኛ ጃውሳ ወሮበላ እያለ ሊያጥላላ ቢሞክሮም ነገር ግን ተግባር ከቃል በላይ ነው:: ማነው የሚዘርፈው : ማሳ የሚያቃጥለው: እርጉዝ የሚገለው የመንግስት ታጣቂዎች ወይንስ ፋኖ? ማነው ገበሬውን የሚያንገለታው? ማዳበሪያ በትርፍ የሚሸጠው?

ማነው አምቡላንስ በድሮን የሚመታው? ለብዙ አመታት የናፈቅነውን እና ማሳካት ያቃተንን የብሄረሰቦች እኩልነትን በ አንዲት ኢትዮጵያ ሊያሳካ የሚችለው ፋኖ ብቻ ነው ብዬ ስለማምን ነው የምደግፋቸው

አብይ ‘እግዚአብሄር *እያለ ጆሮራችንን ያደነቁረናል ነገር ግን ፍርሃተእግዚአብሄርን በተግባር የሚያሳየን ማነው? ፋኖ የለቀቃቸውን ምር ብኞች መንግስት ይገላል ያንገላታል::

አሁን ነው ሰዓቱ

ሁሉም ተረባርቦ ፋኖን መደገፍ ያለበት:: ትግሉን ለማሳጠርና መስዋትነቱን ለመቀነስ ፋኖን የምደግፈው አማራ ስለሆንኩ ብቻ አይደለም  

ፉኖን የምደግፈው ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩ ነው ፡በአንዴት ኢትዮጵያና በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ስለማምን ነው  

ደል ለፍኖ

ድል ለኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ትቅደም  

እናሸንፋለን

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

Go toTop