ለፋኖ ጣፊለት! – በላይነህ አባተ

በአገርሽ ተከብረሽ መኖርን ተፈለግሽ ፣
ጡርቂና መለኮ መከተሉን ትተሽ፣
ሳትውይ ሳታድሪ ቆንጆ ፋኖን ምረጭ፡፡

ባንዳና ከሀዲን ዛሬውኑ ፈተሽ፣
ከፋኖ ዝናር ላይ ዋይ ተጠምጥመሽ፡፡

አሳማ ሆዳሙን በእርግጫ አፈንድተሽ፣
ተፋኖ ደረት ላይ ተጣበቂ ዘለሽ!

በብአዴን ካድሬ ምራቅሽን ተፍተሽ፣
የፋኖን ክንድ ያዥ የኔ መድህን ብለሽ፡፡

ባንዳ ካህንና ሆዳም ቄስ ተፈታሽ፣
ደግሞና ደጋግሞ እግዜር ይባርክሽ፣
ሳጥናኤል ይሁዳን ትተሽ በመሄድሽ፡፡

የይሁዳ ጳጳስ እጅ መሳም ትተሽ ፣
የፋኖ ቄስ መስቀል ይሁን መሳለሚያሽ፡፡

አድር ባዩን ምሁር በመጥረጊያ አባረሽ፣
ፋኖን ግባ በይው ቀይ ምንጣፍ አንጥፈሽ፡፡

እንደ ጀግናዋ ሴት እንደ ቅድመ አያትሽ፣
በኩራት ተራመጅ ፋኖውን አግብተሽ፡፡

ደረቱ የሰፋን መለኮ ተይና፣
ልቡ የተነፋ ተከተይ ጀግና፡፡

አሙለጭላጭ ደንደሳም ተሚቆም ተጎንሽ፣
ተያዘ እማይለቀው ምርኩዙ ያድርግኝ፡፡

በሆዱ እሚሳብን ቀርጮውን ተይና፣
ቆፍጠን ብሎ እሚሄድ ተከተይ አንበሳ፡፡

ቀጣፊ ቀላማጅ ከሀዲውን ትተሽ፣
በቃሉ አዳሪውን አድርጊው ትራስሽ፡፡

አሳማውን ጅቡን ጆፌውን አባረሽ፣
ለአንበሳው ለነብሩ ክፍት ይሁን በርሽ፡፡

የሰፈር አውደልዳይ ዘረጦውን ትተሽ፣
ጫካ ተሚያገሳው ሂጂ ተከትለሽ፡፡

የፋሽሽትን ሎሌ አርገሽ እግር አጣቢ፣
ከደም መላሹ ጋር በአደባባይ ዋይ፡፡

በኩራት በክብር በአገር እንድትኖሪ፣
ጀግኖች ልጆች ወልደሽ እንድታሳድጊ፣
ቆንጆ እንደ አያቶችሽ ፋኖን ምረጭ!

ልፍስፍስ እያለ ባልሽ ታስቸገረሽ፣
ለፋኖ ጣፊለት ና! ጥለፈኝ ብለሽ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
መጀመርያ ጥቅምት ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም.

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለሚመለከተው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share