March 6, 2024
3 mins read

ዱሩ ቤቴ !! ( አሥራደው ከካናዳ )

Fano 1 1

Fano 1 1እገባለሁ ጫካ – እገባለሁ ዱር፤
የበደልን ገፈት – ስጋት ከምኖር፤
አትገባም ወይ ጫካ – አትገባም ወይ ዱር፤
ተቀጥላ ዜጋ – ሆነህ ከመኖር ::

ትናንትም ተበዳይ – ዛሬም ጦም አዳሪ፤
የበይ ተመልካች – የጅቦች ገባሪ፤

የሃብቱ ተመጽዋች – ያገሩ ባይተዋር፤
የመብት ተነፋጊ – የባንዳዎች ገባር
ሁለተኛ ዜጋ – ሆኜ ከመኖር፤
እገባለሁ ጫካ – እገባለሁ ዱር ::

ባዕድ አምላኪዎች – ታሪክ ከላሾችን፤
ዘረኛ ጎሠኛ – አንድነት አፍራሽን፤
የ ’ድገት እንቅፋቶች – የኋሊት ጎታችን፤

አትፋለምም ወይ – አትገባም ወይ ከዱር፤
አንገት እየደፋህ – ዘወትር ከመኖር ::

አትሰማም ወይ ጥሪ – አትሰማም ወይ ጩኸት፤
ደሙ ሲተነፍግ – ሲንቀጫቀጭ አጥንት
በደም ተለውሶ – ባጥንት ያጠሩትን፤
አሳልፈህ ስትሰጥ – የጦቢያ መሬትን ::

ያ’ገሬ ቁልቁለት – ያ’ገሬ ተራራ፤
ጥንትም ያልተበገርክ – ለጠላት ወረራ፤

ለወገንህ ኩራት – መመኪያ ስለሆንክ፤
አብረኸኝ ተሰለፍ – ጠላት ለማንበርከክ ::

ዱሩ ቤቴ ብዬ – በቃ ወጥቻለሁ፤
በደልን በዓርነት – ፍቄ እመለሳለሁ ::

ወንዙ ጥም ቆራጬ – ደኑ ብርድልብሴ፤
አሸዋው ምንጣፌ – ድንጋዩ ትራሴ፤

ቅጠል ፍራፍሬ – ስራስር በልቼ፤
ሰንደቅ አበቅላለሁ – ነፃነት ዘርቼ ::

የዱር አራዊቶች – ሳትቀሩ ተነሱ፤
እምዬ ኢትዮጵያ ! – እያላችሁ አግሱ፤

ነብርና አንበሳ – አብሩ ባንድላይ፤
ከጣሊያን የባሰ – መቷል አገር ገዳይ ::

ጀግናው ጫካ ገባ – እሰይ በይ ምድሪቱ፤
እጅግ ቢበዛበት – የበደል ገፈቱ

ጉብል ከዱር ገባች – ዕልል በይ መሬት፤
ትግልን አርግዛ – ለመውለድ ነፃነት፤
በ’ኩልነት ጸንቶ – እንዲሰምር አንድነት ::

 

ጎበዝ ! « ጅቡ ከሚበላህ ጅቡን በልተህ ተቀደስ !! »

 

ለሥር ነቀል ለውጥ፤ በአንድነት በመነሳት፤ ነፃ ሕዝብ እንሁን !!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

ነፃነት፤ እኩልነትና ወንድማማችነት ይለምልም !!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ !!

የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ( 06/03/2024 ) እኤአ

ለአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ተዘጋጅቶ ሳይላክ የዘገየ ::

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Fano
Previous Story

ለፋኖ ጣፊለት! – በላይነህ አባተ

189171
Next Story

ፋኖ የተቆጣጠራቸው ቦታዋች የተደረገ የህዝብ ውይይት | “ዋና ዋና አዛዦች በአስቸኳይ ይታሰሩ” አብይ በመጨረሻም ጄነራሉን ጉድ አደረጉ| 15 ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው መኮንኖች ጠፉ | አብይ አህመድ በአሜሪካን ሊሸለም ነው፥

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop