አብይ፣ አምሳያ ይሁዳ

/

አንተ የመስቀል ስር ደላላ፣ ስምህ የተባለ ይሁዳ

መች ፍቅር ታውቃለህና ወዳጆችህን ደጋግመህ ክዳ፡፡

የቃልኪዳን ቀለበት አስርሃል፣ ሃብልም አጥልቀህ ነበር ለጓዶችህ

ያው ለአመልህ ነው እንጂ መቼና የት ፍቅር ታውቀለህ?

ትምላለህ በፍቅር አምላክ ስም፣ ሃገር በአማን እንዲውል

ልበ አካይስት አፈ ቅቤ፣ የተፈጠርክ በይሁዳ አምሳል፡፡

ፈጥረሃል የትርምስ ሃገር ዜጋ ወጥቶ የማይገባበት

በሰፈርከው ቁና ትሰፈራለህ ለአንተም ይሆናል የውርደት ሞት፡፡

ጌታውን ያሰቀለ ይሁዳ ህይወቱን እንዳበቃ በገመድ

ቆይተን ደግሞ እናያለን መጨረሻህን ያንተን መንገድ፡፡

ትንቢቱ እንዲህ ይል ነበር የተነገረው ስለ ይሁዳ

ወየሁለት ለእሱ፣ወየሁለት ለቤተሰቡ፣ ለዛ አምላኩን ለከዳ፡፡

“ሴይጣን በቀኙ ይቁም፣ጸሎቱ ሃጢያት ትሁንበት

ሹመቱን ሌላ ይውሰደው፣ ዘመኖቹም ይሁን ጥቂት

ባለዳም ያለውን ይውሰድ፣እንግዶችም ድካሙን ይበዝብዙት

መታሰቢያው ከምድር ይጥፋ፣ትታሰብ ሃጢያቱ በጌታ ፊት፡፡”

ቢጫ ፍኖት አሳይተህ በሃገር ስም ምልሃል

የፈጣሪን ስም እየጠራህ በህዝብ ደም ቀልደሃል፣

የሰላም ኖቤል ተሸላሚ የጦርነት እልቂት መሃንዲስ

ምድሪቱን በደም ያጨቀየህ ከጦርነት ሌላ ምን አለህ ውርስ?

በጦርነትና ረሃብ መስቀል ላይ ሀገርህን ወስደህ የሰቀልክ

ያውም እቅፍ አድርገህ ስመህ አሳለፈህ ለሞት የሰጠህ፣

እንግዲህ ማን እንበልህ? እንዲል ስም ይወጣል ከቤት

በአለም ተስተጋብቶ ይሰማል፣ ከበሮው ይመታል ጎረቤት፡፡

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮ ቫንኩቨር፣ ካናዳ

 

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  አድዋን በግጥም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share