ከሰሞኑ በብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ላይ የደረሰው እንግልት አንጀቴን በላው።

ዶ/ር በቀለ ገሠሠ (drbekeleg@gmail.com)

1ኛ/ መግቢያ፣

የአብይ መንግስት እንዴት በዚህ መልኩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ሊደፍራት ቻለ?

አማራንና ኦርቶዶክስን ማጥቃት በነስብሃት ነጋ ወያኔ/ኢህአደጎች ተጀምሮ ዛሬ ደግሞ በነርሱ ተተኪዎች እጅ ተባብሶ ይገኛል።

ነገር ግን እነዚህ የጥቃት ዒላማ የተደረጉት አካላት እንደሌሎቹ ቅን ዜጎች ለአገር ነፃነት፣ ሥልጣኔና ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማድረግና ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነት ከመክፈል በስተቀር  ምንም ያደረሱት የተለየ ወንጀል የለባቸውም።

ከተቀሩት የሀገራችን ነገዶችና እምነት ተከታዮች ጋራ ተቃቅፈው ከመኖርና ጥረው ግረው ከማደር በስተቀር ያደረሱት ምንም የተለየ ችግር የለም። ነገር ግን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የውስጥና የውጪ ጠላቶች ተባብረው የሚያደርሱት ጥቃት እጅግ በጣም ያሳዝናል፣ ያሳፍራል። በህብረት ተሰልፈን ማስቆም ይኖርብናል።

2ኛ/ ኢትዮጵያን ለማፍረስ  ኦርቶዶክስን የማጥቃት ወንጀል፣

በብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ- ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ላይ በኢትዮጵያ መንግሥትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ የደረሰባቸው እንግልት እጅግ በጣም አሳዘነኝ፣ አሳፈረኝ። ለስብሰባ በሰላም ገብተው እንዳይወጡ መከልከላቸውና ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸው እጅግ በጣም ያሳዝናል።

የቀድሞዎቹ መሪዎች የአማራንና የኦርቶዶክስን አከርካሪ ሰበርን ብለው አቅራሩብን፣ ግን በእግዚአብሔር ኃይል የገዛ አከርካሪያቸው ተሰበረ።

ዛሬ ደግሞ ርዝራጆቻቸው በአብያተ ክርስቲያናት፣ ገዳማትና መስጊዶች ላይ ከፍተኛ ጥቃት በማድረስ ላይ ይገኛሉ።  ቅዱስ ሲኖዶሱን እያፈረሱና እየከፋፈሉ ናቸው።

ታቦታት አርበኞቻችንን ተከትለው ዘምተውና ባርከው ነው ነፃነታችንን ያስከበሩልን። በአዲስ አበባ እነብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ በኢሉባቦር እነ አቡነ ሚካኤል፣ ወዘተ፣ በከፈሉት የህይወት መስዋዕትነት ነበር ሕዝባችንን ያተባበሩና ለነፃነት ድል ያበቁን።

ይህ ሁሉ ዛሬ የሚታየው አሳፋሪ ጥቃት ምስጋና-ቢስነት ብቻ ሳይሆን ትልቅ ኃጢያትም ጭምር መሆኑ ባይረሳ  ይሻላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለወልቃይት፤ ሐምሌ-05 ምስክር ትሁን! - በሙሉዓለም ገ/መድኀን

3ኛ/ ኢትዮጵያን ለማፍረስ አማራን  የማጥቃት ወንጀል፣

ደጋግመን እንደገለጽነው፣ ጭቁን የአማራ ህዝብ በወለጋ፣ በቤኒሻንጉል፣ በሻሸመኔ፣ በአጣዬ፣ ወዘተ  በአረመኔዎች እጅ ተጨፈጨፈ፣ ከኖሩባቸው የገዛ ቀዬዎቻቸው ተፈናቀሉ፣ ተሰደዱ። አሁን ደግሞ የአማራ ክልል በሚሉት ህዝብ ላይ ድሮን፣ ዲሽቃና መትረየስ እያዘነቡ ይገኛሉ።   ንብረቶችንና የእህል ክምሮችን ያቃጥላሉ። በአዲስ አበባ ብዙ መቶ ሺ ቤቶች በግፍ ፈርሰው ወገኖች በጎዳና ላይ ተጣሉ።

ውድ ሀገራችንን በመልክአምድር/ ጂኦግራፊ ሳይሆን በነገድ ከፋፈሉ። ነገር ግን በአንድ ክልል ተከልሎ የሚኖር ነገድ እንደሌለ ግልጽ ነው።  ከፋፍለው ለመግዛት ብቻ ሳይሆን ዘርም ለማጥፋት ያመጡብን ትልቅ መርዝ መሆኑን ሁላችንም መዘንጋት የለብንም።

4ኛ/ መፍትሄው ምንድን ነው?

አሁንም  ሁኔታዎቹ ከመባባሳቸው በፊት መፍትሄው በጋራ መቆም፣ መታገልና ለሰላም መጸለይ ነው ።

4.1 የኃይማኖት አባቶች እዉነትን መስክሩ፣ ለሆድ ሳይሆን ለመስቀሉና ለቁራናችሁ ክብርና ቅድሚያ ስጡ፣ ካለዚያ መልሶ ያቃጥላችኋል፣ ህይወትም አጭር መሆንዋን አትርሱ።

4.2. ምሁራን በትምህርታችሁ ሠርታችሁ መኖር ትችላላችሁ። ካንድ እንጄራ የሚያልፍ የለም። ልጅ ሆኜ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቴ ጋሸ ናርዶስ ተድፋዬ የሚባል አስተማሪዬ የሰጠን ምክር ሁሌ አይረሳኝም፣
‘Come forward and receive Light,
Go back and Shine it’ ይል ነበር። ትምህርት የብርሃን መፈንጠቂያ እንጂ የጭለማ መሣሪያ መሆን ከቶ አይጠበቅበትም።

4.3. ይህ ችግር የአማራና የኦርቶዶክስ ብቻ አይደለም፣ የሁሉም ንጹሕ ዜጋ ነው። ከውድ ሀገራችን መፍረስ የሚያተርፍ ማንም ዜጋ አይኖርም። ተያይዞ መጥፋትን ብቻ ነው የሚያስከትል። ስለዚህ በውስጥም ሆነ በውጪ የምንገኝ ተቆርቋሪ ዜጎች በታላቅ ህብረት ለሰላምና ለፍትሕ መታገልና መጸለይ  የሚጠበቅብን  መሠረታዊ ኃላፊነት ነው። ወጣቶች በተለይ በአንድነት መበርታት ይኖርባችኋል፣ የዛሬው ብቻ ሳይሆን የነገውም ህይወታችሁ ይስተካከል ዘንድ በርቱልኝ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ችግሩን ሁሉ በአቶ ኃይለማርያም ላይ በማሳበብ በስልጣን መዝለቅ አይቻልም; የኢትዮጵያ የችግሮቿ ምንጭ እራሱ ኢህአዴግ/ወያኔ ነው

5ኛ/ መደምደሚያ፣

አብያተ ክርስቲያናትን፣ ገዳማትንና መስጊዶችን ማቃጠል ለሰይጣን በር መክፈቻ ብቻ ነው።

ገበሬ ወጥቶ እንዳያርስና ነጋዴ ዞሮ እንዳይነግድ ማድረግ፣ ንብረት ማቃጠል፣ ወዘተ፣  ከፍተኛ ድህነት እንጂ ብልጽግና ሊያመጣ እንደማይችል እንዴት ማስተዋል አቃታቸው?

ፈጣሪያችን ሁሉን የተፈጥሮ ሀብት አሟልቶ የፈጠራትን ሰፊና ቅድስት ሀገር  ድሃ አድርጎ ማስቀረት ለምን እንደመረጡ ከቶ ሊገባኝ አልቻለም፣ መጥኔ ይስጣቸው።

ወጣት እንዳይማር ሆነ እንዳይኖር መከልከሉ የሚያመጣውን የዛሬና የነገ መዘዝ እንዴት መገንዘብ አቃታቸው?

ይህን ሁሉ ለማስቆም በከፍተኛ ህብረት ከፍተኛ ጥትረት ማድረግ ይጠበቅብናል።

የምስኪኖች አምላክ ቅዱስ ፈጣሪያችን ይጨመርበት።

4 Comments

  1. የዘ-ሐበሻ መድረክ አዘጋጆች፣
    መረጃዎችን በዴቂቃዎች ውስጥ በማስተላለፋችሁ ታላቅ ምስጋና ይገባችኋል፣
    በርቱልን።

  2. ጴጥሮስ ጴጥሮስን
    ጴጥሮስ እንደ ጴጥሮስ መሆኑ ቢሳነው ሰይፉን ስላሳዩት የተመዘዘውን
    “የአቤል ደም” አለ በእርቅና ይቅርታ ሕዝቡ እንዲተዉት የሚወገዘውን
    ፈጣሪውን ክዶ ደብር ለየሚያነደው ይቅርታ አርጉ ማለት ጲጥሮስን ላይመጥን
    ጴጥሮስ ጴጥሮስን ሁን! በኢትዮጵያ ምድር ጥቁሩም ሙሶሎኒ እንደ ነጩ አይሰልጥን

  3. It appears that someone is very creatively building the credibility of the clergy and certain high profile ANDM cadres as a preparation to use them as mediators and negotiators.
    DEMEKE ——- LEQEQE
    GEDDU ——— KAGER KOBELELE
    ABUNE PETROS ——— TEKELEKELU
    TAYE BOGALE ———
    TINGIRTU ————-
    ETC…

    Are you getting ready to be hoodwinked by another round of confuse and convince from the foxy Oromumma gang?

  4. እንደ ዶ/ር በቀለ ገሰሰ ያሉ ፒ ኤች ዲዎች ይገርማሉ፡፡ ምነው ባታናግሩን

    አብይም ሆነ ሎሎች የቀድሞ ኢሀዴግ ያሁኑ ፒፒ የመጣነው አማራና ተዋህዶን ለመስበር ነው እያሉ 33 ዓመት ተናገሩ፡፡ እነዚህን አምነው እኒህ አሁን ቅልጥ ታለው ከተማ የመጡት ጳጳስም አብይ ሙሴ ብለው ለእንጀራ ዜግነታቸውን የቀየሩለንት አሜሪካ ትተው አብይ በገዛላቸው ትኬት አዲሳባ ገብተው አብይን አገለገሉ፡፡ ምእመናኑ ዠልጦ አውርዶ ወደ መጣበት በሻሻ ሊሰደው ሲልም የሕዝቡን ቁጣ አብርደው አብይን አዳኑ፡፡ ከተጠቀመ በሁዋላ እንደ ኣገዳ መጦ ተፋቸው፡፡ እርሳቸው ግን ምን ተጎዱ እና ነው ዶ/ር በቀለ “አንጀቴን በሉኝ የሚለው?” እንደ እውነተኛው አቡነ ጴጥሮስ አገሪቱ ለፋሽሽት እንዳትገዛ ገዝተው ተሰው? የፋኖ የነፍስ አባት ሆነው እንደ አምስቱ ዘመን ካህናት ቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ አደሩ? ቀልጥ ታለው ከተማቸውና የዜግነት አገራቸው ገብተው መንፈላሰሳቸው ጉዳት ይሆን?

    ዶ/ር በቀለ ከጉራ ፈርዳ አማራ ሲባረር፣ በወልቃይት፣ በራያ፣ በመተከል፣ በወለጋ በሸዋ ሲታረዱ “አንጀቴን በሉኝ ” ብለው አያውቁም፡፡ ከእነዚያ ሁሉ ሰዎችን በሽንጣም አውሮጵላን ኒዮርክ መጥተው ፎቅ ላይ የሚያድሩት ካህን አንጀቷቸውን በሏቸው! አንዳንድ ፒ ኤች ዲዎች ምን ዓይነት አንጀት ነው ያላቸው?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share