“ኢትዮጵያ መንፈስ ናት” ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ – የፊልም ጸሐፊ እና ዳይሬክተር ፣ የሐዋርድ ዩንቨርሲቲ መምህር ክፍል ፩ እና ፪

February 7, 2024

3 Comments

 1. “ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በዚህ ሁሉት ክፍል ድንቅ ውይይታቸው “…የራሱን ሀገር ታሪክ ንቆ የተነሳ….የማያውቀዉን ሀገር ልለውጥ የሚል፣ አዋቂ እኔ ብቻ ነኝ የሚል….ኢትዮጵያን ወደፈለግኩት አቅጣጫ እየገረፍኳት እወስዳታለሁ የሚል….” እያሉ የገለጹት ትውልድ ፍሬ መሆናችንን ያሳያል።
  ምናልባትም የህመማችንን ምንጭ ማወቁ፣ ወደ ፈውሱ ሊወስደን ይችላል።”

  አንዳችም ጠብ የሚል የሌላት ትክክል ገለጻ። እነዚህ ኢትዮጵያን የሚያዩአት በዚያች በለመዱት ሸውራራ መነጽራቸው ሲሆን፣ መፍትሔ እያሉም እያቀረቡ ያሉት ሐጠውቀጠው እነሱ የሚፈልጉትን እንጂ አገራችን የምትሻውን አይደለም። ማለትም አራተኛ ዙር ዕልቂት “ሀ” ብሎ መጀመር።
  ኀይሌ

 2. You guys , I really do not understand why and how you keep blaming that generation whereas you keep behaving and doing not only the same but much more worse as far as what is gong on in the country is concerned
  !

  The professor keep saying that Ethiopia a spirit whereas you highly educated ones are terribly failing and Ethiopia’s spirit essence has been and is being incredibly damaged!

  LIs it not better to walk not merely talk or show not simply tell ! Why you guys try hard to have a well thought , well digested, well organized forum and come up with a kind of recommendation or road map of how we can get of the very miserable situation because of the very idiot and brutal ruling gangsters of a deadly politics of ethno-centrism ???

 3. የውሻ ፓለቲካ ሁልጊዜ መጮህና መናከስ ነው። ራሱ የረገጠውን ምድር ሳያውቅ በፈጠራ ትርክት ሰክሮ ሌላውን እያወናበደ ራሱም ተወናብዶ ጭራሽ ዓለምን በጠራ መነጽር ሳያያት በደንበር ገተር የሚያልፍ የጎሳ ፓለቲከኞች ስሪት ነው። አሁን ከላይ የተሰጡት ሁለት አስተያየቶች የሚያስገርሙ ናቸው። ግን ልብ ላለው ሰውን በማሰቃየትና በንጽሃን ደም እጅ ለተነከረ የጎሳና የቋንቋ ዳንኪራ መቺዎችና ፍርፋሪ ለቃሚዎች እውነትን ማየት ስለማይፈልጉ ሁሌ በሌላው እንዳሳበቡ፤ ታሪክን እንዳጣረሱ ዝንተ ዓለም ሲነክሱና ሲያናክሱ ይኖራሉ።
  ፕ/ሩ እድሜ ያስተማረው፤ በመከራ ውስጥ ያለፈ፤ በእሳት የተፈተነ ኢትዮጵያዊ ነው። ከላይ የተባሉትና ከአሁን በፊትም ሙያውንና ስብዕናውን ለማጥላላት መሞከሩ ሆን ተብሎ በእቅድ ከሚዘረገፈው የዘርና የቋንቋ ፓለቲካ የእሬት ክምር የተዘገነ ነው። ሰው የሰውን ሃሳብ በሃሳብ እንደመሞገት መረጃ በሌለው ያስረሽ ምቸው ፓለቲካ ሰውን ማጠልሽት ሃበሻው የተካነበት ሙያው ነው። እናንተ የዛሬ መቶ ዓመት ይህ በደል በዚህ ደረሰብኝ የምትሉ ጨለማዎች ለምን ዛሬ ላይ በብሄር ነጻነት ስም ሰዎቻቹሁ ከሰውነት ወደ አራዊት ሲለወጡ ዝም ትላላችሁ? ግን የመገዳደሉና የመወነጃጀሉ ፓለቲካ ላፍታም እንኳን እንዳያባራና ህዝባችን በሰላም ወቶ እንዳይገባ ትላንትም ዛሬም ወደፊትም ደንቃራዎቹ እኛው የዘርና የቋንቋ ሰካራሞቹ ነን። ግን ለምን ስለ ዓለም ጥቁሮች ህዝብ ነጻነት አንታገልም? ለምን አፍሪቃን አንድ ለማድረግ አንሰራም? እንዴት ሆኖ? እንደ ደ/አፍሪቃው አፓርታይድ በየክልሉ የራሱን ባንዲራ በራፉ ላይ ቆሞ ሃገሬ ይሄ ነው ብሎ ሰንደቁን ለሚያውለበልብ የህሊና ድውያን ዓለም ያለችው አፍንጫቸው ሥር ስለሆነ ነው።፡ በእርግጥም ኢትዮጵያ መንፈስ ናት። ስንቱን እሳት አሳለፈች? ዋ ይህ ቀን ያልፍና የፓለቲካ አሻጥሮች የሚያፍሩበትና የሚደበቁበት ጊዜ ይመጣል። ከዘመናት በፊት እውቁ አርበኛ ገሪማ ታፈረ እየተሾመ የሚመጣው ሁሉ ህዝቡን በጉቦና በእጅ መንሻ በማስቸገሩ እንዲህ ብለው ነበር።
  ሁሉ በሽተኛ ሁሉ ራሴን ባይ
  ደህና ሰው ባገሬ ላይገኝ ነው ወይ። ለመሆኑ እኝህ ሰው ማን ናቸው? በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

188575
Previous Story

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የገጠማት አንዱ ፈተና ጦስ መውጫ የታጣለት ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› አዙሪት ነው!

188611
Next Story

ኮ/ሉ ዛሬ በይፋ ፋኖን ተቀላቅሏል | የአረጋ ከበደ ልዩ ጠባቂዎች ከአርበኛ ዘመነ ጋር ያደረጉት ቆይታ | አረጋ አዳነች በጎንደር ታላቅ ቅሌት ተከናነቡ | ፋኖን ሊይዙ ሂደው እጅ ሠጡ | አባዱላ “ፋኖ እንደ ህውሃት አናዘውም”

Go toTop