የጸጋዬ ገብረ መድኅን አፈር ትናገር!

/

ፀጋዬ ወ-ገብረ መድኅን ዘ-ትውልደ አምቦ፤
ቅኔን የዘረፈ በሰምና ወርቅ አጅቦ፤
አገር ጠብቆ ወገን አቀራርቦ፤
አርጓል በገነት ቀስተደመና ደርቦ።

አምቦ የፀጋዬ አፈር ትናገር፤
ስለእውነት ትመስክር፤
አፈሯ አንድ ነው ወይስ ዥንጉርጉር፤
እውን ታፈራለች ጣፋጭ ከመራር?

የኦሮሚያ አፈር ማን ቀየረሽ፤
የነአብዲሳ አጋን ዘር ማን በረዘሽ፤
ጽንፈኞች አበላሹሽ፤
በዘረኝነት አከረፉሽ፤
ማን ይሆን የሩዋንዳን አፈር የዘራብሽ፤
ማነው በእርኩስ መንፈስ የቀየጠሽ፤
ምነው ከነአቢቹ መማር ተሳነሽ።

የፀጋዬ አፈር መልሽልን እባክሽ፤
ማን እረግሞ ማን አወገዘሽ፤
መልካም ዘር እንዳይበቅልብሽ::

ጥሬ ከሆንሽ እንጠርጥርሽ፤
ሐቁን ሳናውቅ ከምናማሽ፤
ንገሪን እውነቱን እንወቅልሽ፤
ሐቁን አውቀን ዝም እንበልሽ።

የኦሮሚያ አፈር ደጓ አፈራችን፤
ግራ ተጋብተሽ ግራ አታጋቢን፤
አማራ ጠሉን የአማራ ስም ሰጠሽልን፤
ምነው አምቦ አፍራሽ ከገንቢ ደቀልሽብን፤
በምን ቀመር ከፀጋዬ አፈር እሬት በቀለብን?

የፀጋዬ አፈር ውዷ እናታችን፤
እባክሽ ተለመኝን፤
ስሚው እሪታችን፤
ሳጥናዬልን ውሰጅልን፤
አሜኪላን ንቀይልን፤
የፀጋዬ አፈር ፀጋን መልሽልን።

ፀጋዬን የወለደሽ አፈራችን፤
ደግነሽና ክፉ አታናግሪን፤
ክፉ ወልደሽ ክፉ አታርጊን፤
ፈጥነሽ መልሽልን!
ከሀጢዓት አንጭን፤
እንደ ጸጋዬ ገብረ መድኅን፤
ቀስተደመናን አልብሽን፤
በግ መስሎ ማኖር ሰለችን፤
መራራን መሸከም በቃን፤
የጸጋይ አፈር ተለመኝን፤
መረራን አስወግጅልን፤
ከሃጢአት አጽጅን፤
እንደ ጸጋዬ ገነትን ስጭን።

ሰማነህ ታ. ጀመረ፤
ኦታዋ፤ ካናዳ
ታሕሳስ 2016 (ተሻሽሎ የቀረበ)

የጸጋዬ ገብረ መድኅን አፈር ትናገር!

ፀጋዬ ወ-ገብረ መድኅን ዘ-ትውልደ አምቦ፤
ቅኔን የዘረፈ በሰምና ወርቅ አጅቦ፤
አገር ጠብቆ ወገን አቀራርቦ፤
አርጓል በገነት ቀስተደመና ደርቦ።

አምቦ የፀጋዬ አፈር ትናገር፤
ስለእውነት ትመስክር፤
አፈሯ አንድ ነው ወይስ ዥንጉርጉር፤
እውን ታፈራለች ጣፋጭ ከመራር?

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማሮች ጥያቄ - ገለታው

የኦሮሚያ አፈር ማን ቀየረሽ፤
የነአብዲሳ አጋን ዘር ማን በረዘሽ፤
ጽንፈኞች አበላሹሽ፤
በዘረኝነት አከረፉሽ፤
ማን ይሆን የሩዋንዳን አፈር የዘራብሽ፤
ማነው በእርኩስ መንፈስ የቀየጠሽ፤
ምነው ከነአቢቹ መማር ተሳነሽ።

የፀጋዬ አፈር መልሽልን እባክሽ፤
ማን እረግሞ ማን አወገዘሽ፤
መልካም ዘር እንዳይበቅልብሽ ::

ጥሬ ከሆንሽ እንጠርጥርሽ፤
ሐቁን ሳናውቅ ከምናማሽ፤
ንገሪን እውነቱን እንወቅልሽ፤
ሐቁን አውቀን ዝም እንበልሽ።

የኦሮሚያ አፈር ደጓ አፈራችን፤
ግራ ተጋብተሽ ግራ አታጋቢን፤
አማራ ጠሉን የአማራ ስም ሰጠሽልን፤
ምነው አምቦ አፍራሽ ከገንቢ ደቀልሽብን፤
በምን ቀመር ከፀጋዬ አፈር እሬት በቀለብን? የፀጋዬ አፈር ውዷ እናታችን፤
እባክሽ ተለመኝን፤
ስሚው እሪታችን፤
ሳጥናዬልን ውሰጅልን፤
አሜኪላን ንቀይልን፤
የፀጋዬ አፈር ፀጋን መልሽልን።

ፀጋዬን የወለደሽ አፈራችን፤
ደግነሽና ክፉ አታናግሪን፤
ክፉ ወልደሽ ክፉ አታርጊን፤
ፈጥነሽ መልሽልን!
ከሀጢዓት አንጭን፤
እንደ ጸጋዬ ገብረ መድኅን፤
ቀስተደመናን አልብሽን፤
በግ መስሎ ማኖር ሰለችን፤
መራራን መሸከም በቃን፤
የጸጋይ አፈር ተለመኝን፤
መረራን አስወግጅልን፤
ከሃጢአት አጽጅን፤
እንደ ጸጋዬ ገነትን ስጭን።

ሰማነህ ታ. ጀመረ፤
ኦታዋ፤ ካናዳ
ታሕሳስ 2016 (ተሻሽሎ የቀረበ)


     የጸጋዬ ገብረ መድኅን አፈር ትናገር!

2 Comments

 1. አቶ ሰማነህ አዎ ሰማንህ! ግጥምህ፡

  1. የፀጋዬ አፈር ብሎ ነገር የለም። ፀጋዬ የራሱ የሆነ አፈር የለውም፡፡ ኢትዮጵያ የምትባል የሚወዳት አገር ግን ነበረችው፡፡
  2. ሁለተኛ ጽጋዬ አምቦ ይወለድ እንጅ በስጋውም፣ በመንፈሱም ሆነ በአስተሳሰቡ ኦሮሞ አልነበረም፡፡ ኦሮሞ ነኝ ብሎም አያውቅም፡፡ ፈረንጅ ትንሽ የጥቁር ዘር ያለበትን ሁሉ ጥቁር ይላል፡፡ አንተም በአያቱም ሆነ በምንጅላቱ የኦሮሞ ስም ያለውን ሁሉ ኦሮሞ እያልክ ነው፡፡ የኦሮሞ አይነት ሥም ጃፓንም አለ፡፡ ጃፓን ኬኛ አይነት ነገር ነው፡፡
  3. የኦሮሚያ አፈር የሚባልም የለም፡፡ የኦሮሚያ አፈር የሚባለውን እስቲ በካርታ አሳዬን! ኦነግ አባ ጭጓሬ አስመስሎ የሳለውን የኦሮምያ አፈር ልትለው ነው?
  4. እንደ አለፈው አምሳ ዘመን ሁሉ አሁንም የያዝከው ልመና ነው፡፡ ለምነህ የጨረስክ ወይም የታከትክ አትመስልም፡፡ በልመና አገር ተመስርቶም ሆነ ክብር ተጠብቆ የኖረበት ቦታ በምድር የለም፡፡ ከሃምሳ አመቱ ትግልህ አንድም ታልተማርክ የምንለው እግዜር ምህረቱን ያውርድልህ ነው፡፡
  5. እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአብይ አህመድ ጭራቅ አገዝዝ ደጋፊና አትንኩት ባይ ሰው ነበርክ፡፡ አሁን ከዚያ ብዙ የራክ አትመስልም፡፡ አርቆ አሳቢ ለመምሰል መሞከረህ እኛን ስንቱን የታዘብነውና የሚያነበውን ሕዝብ መናቅ ወይም መጃጃል ነው፡፡

  አቶ ሰማነህ! እኛስ ሰማንህ፡፡ እባክህ አንተም በፈንታህ ስማን፡፡ አመሰግናለሁ

 2. ነገረኛና ተንኳሽ ተናካሾች ባሉበት ምድር ሰው በራሱ እይታ አስቦ መኖር አይችልም። አሁን ማን ይሙት ግጥሙ ሽፈራው ከሰጠው አስተያየት ጋር ይገናኛል? ጠ/ሚሩ ወደ ስልጣን ሲመጣ የዘፈኑለት፤ ያወደሱት፤ እጅና እግሩን ለመጨበጥና ለመሳም የተመኙና የተሳካላቸው አሉ። ያ በራሱ እነርሱን አያስወቅስም። ሰውዬው በጣፋጭ አንደበቱ ብዙዎችን ያኔም ዛሬም ያማታልና። ሰው አቋሙን የመለወጥ መብት አለው። ትላንት ጠ/ሚሩ ደግፏልና አሁን አይንህ ላፈር ማለት የፓለቲካ ውስልትና ነው። እንኳን የሃበሻው ያስረሽ ምችው ፓለቲካ ይቅርና ዘመን ጠገብ የሆኑ ያለ እኛ ማን አለ የሚሉን ስመ ዲሞራሲ አራማጆችም ተቻችለው ነው ለመኖር የቻሉት።
  የእኛ ጉዳይ ችግሩ ብዙና ውስብስብ ነው። አሁን ደግሞ እድሜ ለኢንተርኔት ውሸቱና እውነቱ ተዳቅሎ ይሰራጫል። የጨነቀን እውነትን ከውሸት መለየት ነው። በዚህ አለቅጥ ዘምኛለሁ በማለት ጾታ የለኝም በሚለው ጭምልቅ ትውልድ ውስጥ የነጻነት መስፈሪያው የራስ በልቶ ማደር ብቻ ሆኗል። ሎሬት ጸጋዬ አውስቶ ዛሬ ያለንበትን የብሄር የስካር ፓለቲካ ልክ አይደለም ማለቱ አውቂነት እንጂ ለኩነኔ አያበቃም። ግን ብዙ ኦሮሞዎች እላያቸው ላይ የመከራ ዝናብ እየወረደባቸው ኦነግና የአሁኑ ሸኔ አማራን ሲያርድ ሰውን ለማትረፍ ጥረዋል። አብረውም ተገለዋል። ግን ምድሪቱ በጠበንጃ አንጋቾችና ጊዜ በሰጣቸው ስለምትነዳ ዛሬም ይኸው ግድያው ማፈናቀሉ ማፈኑ፤ ማሰሩ ቀጥሏል። ለዚህ ነው የኢትዮጵያ ፓለቲካ በወረፋ የመገዳደል ፓለቲካ ነው የምንለው። ይህ በኦሮሞ ህዝብ ስም የሚደረገው ግፍ በትግራይና በኤርትራ ህዝብ ስም ለዘመናት ከተፈጸመው በደል አይለይም። የጎሳ ፓለቲካ፤ የቋንቋ ትግል ለማንም ለምንም ጠቅሞ አያውቅም። ጸጋዬ የወደዳትን ያችን ኢትዮጵያ ሁሉ ሃገሬ ነው ብሎ እንዲቀበላትና እንዲኖርባት ጸጉር መሰንጠቃችን በመተው ለሰላም፤ ለህብረትና ለአንድነት የተቻለንን ሁሉ እናድርግ። ገና የነጮቹ 2024 ብዙ ያሳየናል። ዝግ ብሎ የአለምን የፓለቲካ አሰላለፍና አፍሪቃዊውን ሰቆቃ መረዳት ተገቢ ነው። ሱዳን ትፍረከረካለች ብሎ ያሰበ ሰው ነበረ? አሁን ግፍና ረሃብ በምድሪቱ ስንቱን እየጨረሰ ዓለም ሁሉ አይኑ ለምን ከፍልስጤማዊያን ጋር ቆመ? የሱዳናዊው ህይወት ከፍልስጤሙ ያንሳል? ይህ ነው ሊያበግነን የሚገባው ሰው በቆዳው መለየቱ፤ በሃይማኖቱና በዘሩ መመዝበሩና መሰደዱ፡ እይታችን አለም አቀፋዊ፤ ብሎም አህጉራዊ ሆኖ የጥቁር ህዝቦችን መራራ ግፍ የሚታገል ይሁን። እቤቱ በራፍ ላይ ቆሞ የክልል ባንዲራ የሚያውለበልቡ የቁም ሙቶች ለእኔ በድኖች እንጂ ነፍስ የዘራባቸው ሰዎች አይደሉም። እናስብ። ከመካረር በጎ ነገርን ፈልገን አንድ በሚያደርገን ነገር ላይ እንስራ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share