ለተከበርከው የጠለምትና የአዳርቃይ ሕዝብ ሆይ

ከዓለም አቀፍ የአማራ ማንነት ድጋፍ ኮሚቴ

ህዳር 26 2016 ዓ/ም

ጀግናው የጠለምት ሕዝብ ሆይ በጸረ አማራው፣ ክፉና መሰሪ የትህነግ ቡድን ላለፉት በርካታ ዓመታት በማንነትህ ሲገድሉህ፣ ሲያሰቃዩህ፣ ሲያስሩህና ለዘመናት ተውልደህ ባደክበት ቀዬ እንደመጤ ኢስባዊ በሆነ መንገድ አፈናቅለው ለስደት ሲዳርጉህ፣ ለም በሆነው መሬትህ ላይ ግን ከትግራይ የራሱን ሕዝብ አምጥቶ በማስፈር ተጠቃሚ አድርገዋቸዋል፣ ተፈጥሮዓዊ ሃብቶችን(እምነ በረድ፣ እጣን፣ ወርቅ…ወዘተ)ዘርፈው ወደ ትግራይ በማጋዝ አገራቸውን አበልፅገዋል፣ የአገሬው ተወላጅን የበይ ተመልካች አድርገውታል፣ እናቶችን ያልምንም ሃፍረት አስገድደው ደፍረዋል፣ የሕዝቡ ስነ-ልቦና አዛብተዉታል፣ ከመላው አማርኛ ተናጋሪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንዳይግባባ አማርኛ ቛንቛ እንዳይማር ተከልክሏል ፣ በምትኩ ትግርኛ ቛንቛ በቀዳሚነት እንዲነገር ሰፊ ስራ ሰርተዋል።

በጠለምት ሕዝብ የተፈፀመው ይህ ነው የማይባል በደልና ግፍ ደምና አጥንትህን ገብረህ የአገኘኽውን ነጻነት የኦሮሙማና የትህነግ ቡድን በመተባበር ሕዝበ-ውሳኔ በሚል ማደናገርያ እንደገና ለባርነት ቀንበር ሊዳርጉህ ወስነዋል። ይህን ለማስፈፀም በአቶ ሸጋው ውቤ የሚመራ የአከባቢው ተወላጅ ባንዳዎች ቡድን ያለምንም ሃፍረት በይፋ ሕዝቡን ያለፍላጎቱ ሕዝበ-ውሳኔ ማካሄድ እንዳለበት ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩበት ይገኛሉ።

ጠለምት ምንም በማያሻማ ታሪክ የጎንደር ክፍለሃገር መሆኑን ዓለም ያወቀው ሃቅ ሆኖ ሳለ ማንነትህን ሳትወድና ሳትፈቅድ በግዴታ ሕዝበ ወሳኔ በሚል እንቆቅልሽ እንድትለውጥ የሚደረገው ድራማ እምቢኝ አሻፈረኝ የምን ሕዝበ ወሳኔ በማለት ከአሁን ቀደም በጉልበትህ ያረጋገጥከዉን ማንነትህን በሕዝበ ወሳኔ  ትርክት ታሪክህን፣ ማንነትህን፣ ነጻነትህንና ዳር ድንበርህን አሳልፈህ መስጠት የለብህም።

ለማንነትህና ለደምበርህ ሆ ብለህ በመነሳት የሃገሬው ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሕገ-መንግስታዊ መብቱ እንዲረጋገጥለትና ለ40ዓመታት ሙሉ የታገለለት አላማ ወደ ሆነው ወደ ነባር አስተዳደሩ ወደ ጎንደር ህጋዊና ፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲሰጠው ለፈደረሺን ምክር ቤት ያቀረብከዉን ጥያቄ ተግባራዊ እንዲሆን ከመጠየቅ ዉጭ የማይታሰብ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጥላቸው። ይህ ሳይሆን ቢቀርና ጠለምትን ከአገሬው ተወላጅ ባለፈ ለወያኔ ሰፋሪዎች ለሕዝበ ዉሳኔ ድርድር ለማቅረብ ቢሞከር ታሪክና ትውልድ ይቅር የማይለው ስህተት ከመፈጸም ባሻገር አከባቢዉን የጦርነት ቀጠና እንዲሆን የማድረግ ውሳኔ ከመሆን እንደማያልፍ ማሳሰብ እንወዳለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሞት የስብሐት ነጋ በርን እያንኳኳ ነው (ሁኔ አቢሲኒያዊ ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ)

የጠለምት፣ የወልቃይት የጠገዴ፣ የሁመራና የራያ ወረዳዎች ወደ ትግራይ የተካለሉት 1ኛ/ በሕዝበ ዉሳኔ ሳይሆን ፖለቲካዊ ውሳኔ በመሆኑ 2ኛ/ እነዚህ ክልሎች ወደትግራይ የተካለሉት ህገ-መንግስቱ ከመጽደቁ ቀደም ብሎ በመሆኑ። 3ኛ/ እነዚህ ወረዳዎች ታሪካዊ፣ ባህላዊና ስነልቦናዊ ግንኙነታቸው ከጎንደር ክፍለ ሃገር ጋር በመሆኑ ህዝበ-ውሳኔ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም።

የጠለምት የአማራ ማንነትና የወሰን ይገባኛል ጥያቄ ላለፉት በርካታ ዓመታት ለፌደረሺኑ ምክር ቤትና ለአማራ ክልል አስተዳደር በተደጋጋሚ ያቀረበ ቢሆንም ምላሽ አላገኘም።  በተለያዩ ድህረ-ገጾች እንደምንሰማው፣ በነዚህ ታሪካዊ የአማራ ክልሎች ወያኔ ባለርስቱን አባሮ የራሱን ሰዎች እንደገና አምጥቶ በማስፈርና ክልሉን በትግራይ አስተዳደር ስር አድርጎ አዛዥና ናዛዥ በሚሆንበት መድረክ  ሕዝበ–ውሳኔ  ይደረግ ማለት ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ግልፅ መሆኑ እየታወቀ አንዳንድ የአከባቢው ተወላጆች በማወቅም ሆነ ባላማወቅ ሕዝበ-ውሳኔ ቢካሄድ የአገሬው ሕዝብ ያሸንፋል ብለው የሚያስቡ የዋሆች ሕዝቡን ወደተሳሳተ መንገድ እየመሩት ስለሆነ የማንነት ጥያቄ የቀረበበትን ጉዳይ በቀጥታ ለመፍታት አለመፈለግንና የአማራን ደም ወያኔን ለማባበያ እየተጠቀመበት መሆኑን አውቃችሁ ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት ከመስራት ብትታቀቡና ከሕዝባቹህ ጎን በመሰለፍ አገራዊ ግዴታችሁን ትወጡ ዘንድ ለማሳሰብ እንወዳለን።

በእንዲህ አይነት ሁኔታ የሕዝብ ድምፅ ውሳኔ የሚለው የመፍትሄ ሃሳብ ሳይጀመር ውጤት እንደማይስጥ በመገንዘብ መንግስት የጠለምት፣ ወልቃይት ጠገዴ፣ የሁመራና ራያ ሕዝብ ጥያቄ ሊፈታ የሚገባው የሕዝቡን ማንነት፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ሕዝባዊ ስነ-ልቦናን መሰረት አድርጎ በማየት አሁን ባለበት የአማራ ክልል አስተዳደር እንዲቀጥል የፈደሬሽኑ ምክርቤት አስቸኳይ ዉሳኔ እንዲስጥበት ላማሳሰብ እንወዳለን፡፡

በመጨረሻም አንዳንድ ከጀግናውና ስመጥር የጠለምት ሕዝብ አብራክ ተፈጥረው ለሆዳቸውና በጊዜአዊ ጥቅማ ጥቅም ተደልለው ታሪካዊቷን ጠለምትን በህዝበ-ውሳኔ ሰበብ ለትግሬ ወራሪ ሃይል አሳልፈው ለመስጠት ደፋ ቀና ለሚሉት እነ ዲያቆን ሸጋዉ ውቤና ግብረ-አበሮቹ የብልጽግና ተላላኪዎችና ዘመናዊ ባንዳዎች እንዲሁም በወያኔ የአስተዳደር ዘመን የነበሩ አሁንም በብልፅግና አስተዳደር ውስጥ ሆነው የሚሰሩና ከትህነግ ጋር በድብቅ ግንኙነት ያላቸው አስመሳዮች የትህነግ አላማ የሆነዉን ህዝበ-ዉሳኔውን ለማስተግበር ከፍተኛ ስራ እየሰሩ መሆናቸዉን በተጨባጭ ደረስንበታል። በመሆኑንም ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡና ሳይረፍድ ከሕዝባቸው ጎን በመሆን ታሪካዊ ግዴታቸው ይወጡ ዘንድ ከወዲሁ ላማስጠንቀቅ እንወዳለን። ከዚህ እኩይና መሰሪ ተግባራቸው የማይታቀቡ ከሆነ ግን ታሪካዊ የጠለምት ሕዝብ ጠላት መሆናቸውንና ለልጅ ልጆቻቸው መጥፎ ታሪክ አውርሰው የሚያልፉ መሆናቸውን ሊገነዘቡት ይገባል እንላለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአደዋ ድል በተሃድሶና በኢንላይተንሜንት መነፅር ሲታይ ! -  ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብርና በነፃንት ትኑር

አማራነን እንጂ አማራ እንሁን አላልነም

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share