በአሁኑ ሰአት አማራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ዩኒፎርም በለበሰ የኦሮሙማ መንጋ በየቀኑ እየተገደለ፣ እየታረደ፣ የእማራ ሴቶች በመንጋው እየተደፈሩ፣ አማራው ንብረቱ፣ የህይማኖት ቦታወቹ፣ በአለም የተመዘገቡ የታሪክ አሻራወቹ፣ ከተማወቹ፣ መንደሮቹና፣ የገበሬው የእህል ክምሮቹ ጭምር ….ወዘተ በድሮን በታንክና በመድፍ እየወደሙ ነው ያሉት፡፡ ከዚህ በባሰ ሁኔታም አማራው ዘሩ እንድጠፋና ትውልዱ እንዳይቀጥል ለማድረግ በኦብይ አህመድ የዘር ማጥፋት አዋጅ “GENOCIDE ታወጆበታል፡፡ አወቆትም ይሁን ሳያወቀው ይህንኑ የአብይ አህመድ የዘር ማጥፋት አዋጅ በይፋ ያረጋገጠው ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ባለፈው ማክሰኞ (11/28/2023) በናዝሬት ከተማ በተደረገ ስብሰባ ላይ ነው፡፡
የአገሪቱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ እምብርት የሆነችውና እንደዚሁም ከኒውዮርክና ከጀኔቫ ቀጥላ ሶስተኛዋ አለም አቀፍ የድፕሎማሲ ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ ለአገሪቱም ፖለቲካና ኢኮኖሚ መፍለቂያ ምንጭ ናት፡፤ የደም ስር ናት፡፤ ማንኛውም በዱሮው እሳቤ የግራም ሆነ የቀኝ ፖለቲካና በአሁኑ ዘይቤም የዘር ፖለቲካ መፍለቂያ የሆነችው አዲስ አበባ ማንኛውም ነገር ታስቦ፣ ተጠንስሶ፣ ተደቁሶ፣ ተለውሶ፣ የሚቀመረውና የሚዘወረው በዚህቹ የአገሪቱ መዲና በሆነችው ከአድስ አበባ ውስጥ ነው፡፡
አዲስ አበባ ውስጥ መንግስታዊ ዝርፊያው ተጧጡፎ ቀጥሏል፡፡ ይህ ዝርፊያ የብር፣ የመሬትና የሌሎች ሀብቶች ዝርፊያን ብቻ ሳይሆን የዶላርንም የውጭ ምንዛሬ የጥቁር ገበያ ንግድ የያዘ ዝርፊያ ነው፡፡ ዘረፋው የሚመራው በአብይ አህመድ የበላይነት ሲሆን በከተማዋ ውስጥ ያለው ዘረፋ የሚመራው በአዳነች አበቤና ኩባንያው ነው፡፡ የውጭ አገር ገንዘቦች የጥቁር ገበያ ዘረፋው የሚመራው ደግሞ በአህመድ ሽደ ታከለ፣ ኡማና ኩባንያው ነው፡፡ እዚህ ላይ “ኩባንያው” ስንል ቱባ ቱባ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የናጠጡና በአጭር ጊዜ በዘረፋ አብጠውና ደልበው አየር ላይ የሚንሳፈፉ ዘመን አመጣሽ ነጋደወች ጭምር ያሉበት አደገኛ ስብስብስን ማለታችን ነው፡፡ ሁሉንም የዝርፊያ ሽክርክሪቶች በበላይነት የሚቆጣጠራቸው በጥራቃው አብይ አህመድ ነው፡፡ አብይ ዘረፋወቹን ልክ እንደ አገር ፕሮጀክት ከላይ ሆኖ ይመራቸዋል፣ ያዛቸዋል፣ይቆጣጠራቸዋል፡፡ በተለይ የውጭ ምንዛሬ የጥቁር ገበያው ንግድ በመንግስት ደረጃ ድብቅና ስውር እቅድ ተይዞለት የሚመራ ሲሆን ብሩ እየታተመ ለተቀባዮቹ በባንክ እንዲከፈል ይደረጋል፡፡ ዶላሩም በውጭ እየተሰበሰበ እዚያው ስርጎ እንዲቀር ይደረጋል፡፡ በብዙ ቢሊዮኖች ዶላሮች ከሚቆጠረው ከዚሁ ከውጭ ምንዛሬው ጥቁር ገበያ ንግድ ውስጥ ወደ አገሪቱ አለም አቀፍ ሂሳብ ጠብ የሚትል አንዲት ሳንቲም የለችም፡፡ ሁሏም በአብይ አህመድ ዉሳኔና ምደባ ወደ ኦሮሙማ ፕሮጀክቶች የሚዞረው ከዞረ በኋላ ቀሪው እንደየአግባቡና እንደየሁኔታው ወደየሚመለከታቸው ባለስልጣናትና ባለሀብቶች አካውንት ውስጥ ይገባል፡፡ በውጭ አገር ማለት ነው፡፡ በዚህ ንግድም ነው አብይ አህመድ በፊት የትግራይን አሁን ደግሞ የአማራን ህዝብ መግደያ ድሮኖችና ሌሎች ከባባድ መስሪያወችን የሚሽምተው፡፡
እስካሁን ድረስም ህዝብ መግደያ መሳሪያ ድሽቃም ይሁን ድሮን እየተሸመተ ያለው ከአረብ ኢምሬትስ “በሁለቱ መሪወች የተለየ አግባብ” ከሚመጣ ገንዘብ ነው፡፡ከዚያ ውጭ ያለው ሌላውም ከጥቁር ገበያ ከሚመጣ የዶላር ንግድ ነው፡፡ አሁን ላይ የአገሪቱ ኢክስፖርት የተመናመነ ሲሆን ዱሮ ከድያስፖራው ይጎርፍ የነበረውም ሬሚታንስ ማለትም ከዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን በህጋዊ መንገድወደ አገር ይላክ የነበረው ገንዘብ ነጥፏል፡፡ምክንያቱንም ስንጠይቅ የኦሮሙማ የዘረኝነት ፖለቲካና መንግስታዊዩ የጥቁር ገበያ ንግድ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ድያስፖራው ከጥቂቶች የአብይ አህመድ ደጋፊወች በስተቀር ሁሉም በሚባል ደረጃ ስርአቱን ለማስወገድ የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ ተስማምቷል፡፡ ለዚሁም እውነተኛነት ከመገለጫወቹ ውስጥም አንዱ የሬሚታንሱ መንጠፍ ነው፡፡ አብይ አህመድ አገሪቱን ወደ እዳ ተሸካሚነት ስለከተታት አሁን ላይ የእርሱን መንግስት አምኖ ዶላር በሬሚታንስ የሚልክ ዲያስፖራ፣ ዶላር የሚያበድር የውጭ ባንክም ሆነ አለምአቀፍ አበዳሪ ድርጅትና አገር የለም፡፡
በአገር ውስጥ በተለይም በአድስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚደረገውን ዘረፋ ለማሳያ ያክል ብቻ በአጭሩ እንደሚከተለው እንቃነው፡፡ ዘረፋውን በአዲስ አበባ ከተማ የምታሽከረክረው በቅጽል ስሟ “የዝርፊያዋ ንግስት “በሚል ስም የምትታወቀው አዳነች አበቤ ነች፡፡ ይህች ሴት ባለ ብዙ ፈርጅ ወንጀለኛ ናት፡፡
አዲስ አበባን ራሷ ትዘርፋታለች፣ ከተማዋን መልሳም በኦሮሙማ መንጋ ታዘርፋታለች፡፡ ክህግ ውጭ የከተማዋ ከንቲባ ተድርጋ ተሹማ ከተማዋን ከኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ጋር “ድንበር ተካለልኩ“ በማለትም የከተማዋን ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ መንደሮች፣ ገበያወች፣ ህንጻወች፣ ወረዳወች፣ ንኡስ ከተሞችና ቀበሌወችን ወደ ኦሮሚያ እንዲካለሉ አድርጋለች፡፡ ይህ አድራጎት ኦሮሙማ በተወገደ ማግስት የሚፈርስና የማይጸና ቢሆንም ድርጊቷ በራሱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በተደረገ ሰው መፈጸሙ ከባድ ወንጀል ነው፡፡
የከተማውን የታሪክ አሻራወች ማጥፋት ሆን ብላ የተያያዘችው ሌላው ተግባሯ ነው፡፡ ምሳሌ (ለገሀርና አንበሳ ፋርማሲ)፣ በቢሊዮን ብሮች የከተማ ቦታወችን በስውር ትቸበችባለች፡፡ የራሷ ህጋዊ ሰውነትና መተዳደሪያ ቻርተር ያላትን አዲስ አበባን በዚህ ልክ ስትዘርፋትና ስታዘርፋት ለይስሙላ እንኳን ቢያንስ ቢያንስ ያንን በኦሮሙማ የታጨቀ “የከተማዋ ምክር ቤት” የሚባለውን “”የሾቀ”” ስብስብ ፈቃድ አትጠይቅም፡፡
በጣም አስቂኝም ዝነኛም ከሆኑት ዘረፋወቿ መካከል “”ቢሮዬን በ2 ቢሊዮን ብር አሳደስኩ” የሚለውና “”200 አውቶብሶችን በሶስት ቢሊዮን ብር ገዛሁ”” ያለችበት ሁለቱ ኮሜድወቿ ማንንም ሰው ፈገግ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ ባለፈ የመዝረፊያ ርእሶችን እየቀያየረች ዘረፋው ውስጥ ስትዋኝ ህዝብ ይነቃብኛል የሚል ጭንቀትም ፍራቻም የለባትም፡፡ በጣም ዝርዝር ቢመስልብንም የዝቅጠቷን ልክ ስለሚጠቁመን ለምሳሌ ያህል ብቻ ከሌሎቹ ለይተን እነዚህን ሁለት የዝርፊያ ሰንሰለቶቿን አጥርተን እንመልከት፡፡ እነርሱም የተማሪወች ምገባና በከተማዋ መግቢያ በሮች ላይ ስለተሰሩት መደብሮች ነው፡፡
የተማሪወች ምገባ፦
ይህ የዝርፊያ ሰንሰለት በውስጡ በጎ እሳቤ ያለው ቢመስልም አሰራሩ ብልሹና ለዘረፋ የተመቻቸ ብቻ ሳይሆን ለዘረፋ የተዝጋጀም ጭምር ነው፡፡ እቅድ፣ ቁጥጥር ስርአትና ተጠያቂነት የለውም፡፤ እነማን ናቸው ምግቡን እንዲያቀርቡ የተመረጡት?? እንዴት ተድርገውስ ነው የተመረጡት?? ምን ምን ነበሩ የምርጫ መስፈሪያወቹ?? እነማንስ ተወዳደሩ?? የትኞች በምን መመዘኛ ተመርጠው ነው ምገባውን የሚያካሂዱት?? በምን ምዘና?? ጭራሹኑስ ለአቅርቦቱ ውድድር ነበረ ወይ?? በዚህ ዙሪያ በጥቅሉ ለሚነሱት ጥያቄወች ለህዝቡና ለምክር ቤቱ ይፋ መደረግ የነበረባቸው አሰራሮች በሙሉ ለአዳነች በጥያቄ ቢቀርቡላት ለሁሉም መልሷ ዜሮ ነው፡፤ ለምን ቢባል ዉሳኔው የራሷ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ ገፍቶ እንዴት የሚለውን ጉዳይ ማንስ ምን አግብቶት ሊጠይቅ??
የአዲስ አበባ መግቢያ መደብሮችና ሱቆች፦
በአዲስ አበባ በሁሉም የመግቢያ በሮች ያሉትን ሱቆች/መደብሮች ለኦሮሞወች መነገጃ ብቻ ታስበው ነው የተዘጋጁት፡፡ ሲጀመር ከኦሮሞ ተወላጅ ሌላ ለአዲስ አበባ ህዝብ የግብርና ምርቶችንና ሸቀጦችን ሌሎች ዜጎች ማቅረብ አይችሉም፡፡ ሲቀጥል ደግሞ ሁሉም ማከፋፈያወች የተያዙት በኦሮሞ ተወላጆች ብቻ ነው፡፡ ሸማቹ አዲስ አበቤ እውነቱን ያውቀዋል፡፤ ታዲያ እናንተ ይህንን ምን ትሉታላችሁ???
በኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ይፋ ወደተደረገው ወደ አብይ አህመድ የአማራን ዘር የማጥፋት እቅድ ልመልሳችሁ፦ ከዚያ በፊት ግን ሽመልስ አብዲሳ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ የህዝብ ቁጥር የኦሮሞው ህዝብ ቁጥር ነው ስላለና፤ ይህም የውሸት ትርክት በብዙወቹ የኦሮሙማ መንጋወች በኩልም እይየተደጋገመ ስለሚገለጽ ይህ እርምት እንዲደረግበት በማስፈለጉ የሚከተለውን እውነትነት ያለውን መረጃ ማሳወቅ ግድ ይላልና እነሆ፡፡
ሁሌም የፈለገውን ሳይደብቅና ሳያመዛዝን በመናገር የሚታወቀው ሽመልስ አቢድሳ በኢትዮጵያ ውስጥ በህዝብ ብዛት ትልቁ የህዝብ ቁጥር የእኛ የኦሮሞወች ነው ከማለት ባለፈም አማራን ከሁለተኛነት ደረጃው ዝቅ አድርገን ወደ አናሳነት እናወርደዋለን ብሏል፡፡
ወደ አናሳነት ማወረዱ በተግባር የሚታይ ይሆናል፡፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በህዝብ ብዛት ግን አሁንም ዱሮም ትልቁ ቁጥር የአማራ ህዝብ ነው፡፤ የሽመልስ አብዲሳ አባባል መነሻው መርዘኛው መለስ ዜናዊ ያኔ ከ32 አመት በፊት አማራን የበታች አድርጎ ያቀረበውን የተፈበረከ የቁጥር መጠን ይዞ ነው፡፡ ያ አይሰራም፡፡ ያንን ቁጥር ወያኔና ኦሮሙማ እስካሁን ድረስ ለበጅት ምደባ፣ ለድምጽ ቆጠራና ለምዝበራ ተጠቀማችሁበት፡፡ ነፈዙ፣ አጋሰሱና ተገንዞ ከነነፍሱ የተቀበረው ብአደን ምንም አላላችሁም፡፤ ምንስ አግብቶት ምን ይላል??? ከዚህ በኋላ ግን አይሰራም፡፡ ያ ቁጥር ለወያኔ የፖለቲካ ቁማር ስኬት ሲባል በወያኔ የተቀመረ ቁጥር ነበር፡፡ ቁጩ ቁጥር ነበር፡፡ ስለሆነም ኦሮሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሁሉም ህዝቦች የበላይ ነው የሚለው አባባል የተሳሳተ መነሻን ያነገበ ነው፡፡
ሀቁ ይህ ነው፡፡ በኦሮሚያ ውስጥ አሁን ይኖራል ከሚባለው 34 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ 10 ሚሊዮኑ አማራ ሲሆን ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችም ኦሮምያ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ይህ ደግሞ በራሱ ወያኔ ህገ መንግስትም ቢሆን ህገ መንግስታዊ ነው፡፡ለሽመልስ አብዲሳ ስሌት ማስተካከያ ይረዳ ዘንድ \ አስር ሚሊዮኑን አማራ ወስዶ አዲስ አበባ ውስጥ ይኖራል ከሚባለው ሰባት ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ቢያንስ ስድሳ ከመቶው(60%) አማራ ስለሆነ ያንን ቁጥር በአስር ሚሊዮኑ ላይ አስልቶ መደመር ያስፈልጋል፡፡ ከዚያም እስከአሁን ድረስ ችግር አለባቸው በሚባሉት የአማራ መሬቶች ውስጥ ማለትም በወልቃይት፣ በራያ፣ በመተክል፣ በደራ፣ በአጣየና አሁን በቅርቡ የኦሮሞ ልዩ ሀይል በጨፈለቃት በምስራቅ ሸዋ ምንጃር በምትገኘው ”አውራ ጎዳና” ከተማ ውስጥ ያለውን አማራ ጨምሮ ማስላት ግድ ይላል፡፡ እንደገናም አሁንም ኦሮሙማ “ሰሜን ኦሮሚያ እናደርጋታለን እያለ የሚቃዡባትን ደቡብ ወሎ” ጨምሮ እንዳለ አማራውን በድፍን ወሎ፣ ሸዋ፣ ጎጃምና ጎንደር ያለውን አማራ አብሮ መደምር ያስፈልጋል፡፡ ይህ ድምር በግምት ከ56 ሚሊዮን በላይ ወይንም በዚያ አካባቢ ነው የሚሆነው፡፤ ይህ ነው የአማራ ህዝብ ቁጥር ብዛት፡፡
ኦሮሙማ “ይህ ትክክል አይደለም፤ አሁንም እኛ ኦሮሞወች ነን ትልቅ ቁጥር ያለን” በሚለው አቋም የሚጸና ከሆነ መፍትሄው በመረጃ ማረጋገጥ ነው፡፡ ይህንኑ ለማረጋገጥም ሀቀኛ፣ ተአማኒና የውጭ ታዛቢወች ጭምር ያሉበት ነጻ የሆነ የህዝብ ቆጠራ በአገሪቱ ውስጥ አካሂዶ ማረጋገጥ ነው፡፡ ያኔ በእኩልነት መርህ አብሮ መኖር የሚፈልግ ሁሉ እውነቱን ያውቃል፡፡ በዚህም ሆነ በዚያ አማራው ለየትኛውም አማራጭ ስር ነቀልና ቆራጥ ዝግጅት እያደረገ ነው፡፤ ህልዉና ነዋ!!!አሁን ላይ “ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም” የሚለው አሳዛኝ ሰቆቃ እንዳይደገም ነው የአማራው ተጋድሎ መነሻ ነጥብ፡፡
አሁንም ተረኛው ኦሮሙማ ከዚህ የባሱ ጸረ አማራ እቅዶችን ነድፎ ጸረ- አማራና ጸረ- ኢትዮጵያ የጥፋት ጉዞውን ከወያኔ በባሰ ደረጃ አክርሮ ቀጥሎበታል፡፤ የዘር ማጥፋት አዋጅ ማወጅ ብቻ አይደለም ወደትግበራም ገብቷል፡፤ ሙሉ ሀይሉን ከመላዋ አገሪቱ ነቅሎና በአማራ ህዝብ ላይ አሰማርቶ ህዝቡን ጧት ማታ እየቀጠቀጠው ነው፡፡ ለምድን ነው አብይ አህመድ ይህንን የሚያደርገው የምንል ካለን መልሱ አብይ አህመድ “የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ በድል እንዳይጠናቀቅ ለማድረግና ህዝቡም ከፋኖ ጎን እንዳይቆም ለማድረግ ነው” መልሱ፡፡
ከዚህም አልፎ ተርፎ አብይ አህመድ ህዝቡን በማስራብ፣ በፋኖ ስም በዲያስፖራ የተደራጁ የብአደን ፋኖወችን በማደራጀት፣ በእስረኛ ስም በየእስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የብአዴን “ታሳሪ ፋኖ” ተብየወችን በማደራጀት፣ በህዝቡ ውስጥ ብአደን በፋኖ ስም ያደራጃችውን በዝርፊያ ላይ የተሰማሩ “የብአደን ፋኖ” ተብየወችን በማደራጀት… ወዘተ አብይ አህመድ በረቀቀ ስሌት እየተጓዘ ነው፡፡
አልተሳካለትም እንጅ አብይ አህመድ መሬት ነክሶ፣ ደሙን አፍስሶ፣ አጥንቱን ከስክሶ ከህዝቡ ጋር ሆኖ ኦሮሙማን የሚፋለመውን ፋኖ ለመበከልና ለመከፋፈል ያልፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡አብይ አህመድ ከዚህም አልፎ ተርፎ ኦሮሙማወች“”ሰማዩም የእኛ ነው በሚሉባት አዲስ አበባ ውስጥ”” በ”ሰላም እንፈልጋለን “ስም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ “አማን” በሚል አህጽሮተ የሚጠራ ‘የአዲስ አበባ ማህበራዊ ንቅናቄ” በሚል ተደራጀን የሚሉ ሀይሎችን ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ እነዚህን የአብይ አህመድ ምርጥ የአድርባይ አብዮተኞችንና የኦሮሙማን አጀንዳ በጀርባ አጀንዳነት አዝለው የተሸከሙ ግለሰቦችን አብይ አሰባስቦ ‘’የተቃውሞ ሰልፍ”” ተብየውን ሰልፍ በማስደረግ የፋኖን ሁለገብ ተጋድሎ ለማኮላሸት ሰፊ ጥረት እያካሄደ ነው፡፡ አብይ ፋኖን በአማራ ህዝብ ለማስጠላት የሚያደርገው ከንቱ ጥረት በዚህ ብቻ አያቆምም፡፡ አገራዊ ድርድር በሚል ስም በይፋ ያደራጀው ኮሚሽን እየከሸፈበት ስለሆነ በፋኖ ስም የተደራጁ የዲያስፖራ፣ የእሰር ቤትና ብአደን ያደራጃቸውን የይስሙላ ፋኖወችን በማደራጀት በየአውደው ዉጊያው እየተዋደቀ ያለውን ፋኖ እንዲያማልሉ፣ እንዲያዘናጉ እየከፋፈሉ “ድርድር ይሻለናል” በማስኘት ወድርድር ወደሚለው የማዘናጊያ ወጥመዱ ለማስገባት ሰፊ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ ወጥመድና ሴራ የአማራን ህዝብ የህልውና ታጋድሎ ለማምከን መሆኑን መሬት ነክሶ የሚዋጋው ፋኖና የፋኖ ደጀን የሆነው ሰፊው የአማራ ህዝብ ነቅተውበታል፡፡ ይህም ሁሉ ሆኖ አብይ አሁንም “”ይሄዉና በፋኖ ምክንያት ህዝቡ በረሀብ ተጠቃ፣ በበሽታም ተጎዳ ስለሆነም ህዝቡ ፋኖን ተፋው ፣ አልፈልግህም አለው’” ለማስባል ብዙ ርቀቶችን ሄዶ የአማራን ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ለማኮላሸት፣ ለመበረዝና ለመከለስ ብዙ ጥረቶችን እያደረገ ነው፡፡ የዚህ ድራማ ቁልፍ ተዋናዮቹም የከሰረው ዲያቆን ድንኤል ክብረትና ቀንደኛው እጅግ በጣም ተፈላጊው ወንጀለኛ ተመስገን ጥሩነህ ናቸው፡፡ ደግነቱ እነዚህ ሁሉ ረቂቅ የሚመስሉ የኦሮሙማ ተንኮሎችና ድብቅ ሴራወቹ በተግባር ሜዳው ላይ በየአውደ ዉጊያወች ላይ ለሚዋደቀው ፋኖና ለሰፊው የአማራ ህዝብ በጣም ግልጽ ሆነውለታል፡፤ ይህም ማለት የኦሮሙማ ፋኖን የመከፋፈልና አዘናግቶ የመምታት ሴራወቹና ዉጥኖቹ በሙሉ እንዳሉ አብይ አህመድ ሳያውቀው ፋኖን ይበልጥ ቆራጥና ይበልጥ ጥንቁቅ እንዲሆን ረድተዉታል ማለት ነው፡፡
በዚህም ሆነ በዚያ የአማራው ህዝብ የህልውና ተጋድሎ መከራ ቢደራረብበትም በፋኖ የአማራ ልጆቹ ጽናትና አይበገሬነት በየእለቱ ወደ ድል እየገሰገሰ ነው፡፤ ህዝቡም በወንጀለኛው ተመስገን ጥሩነህ ደላላነት በቀን አበል ብዙ ሽህ ብሮች እየተከፍሏቸው ከተገዙት እጅግ በጣም ጥቂት ከሆኑ ሆዳም አማራወች በስተቀር ህዝቡ መቶ በመቶ ከፋኖ ጋር ቆሟል፡፡ ፋኖም የአማራ ህዝብ ብቸኛ አለኝታው መሆንኑ ህይወቱን በመክፈል በተግባር አረጋግጧል፡፡ ፋኖ ከእንግድህ ወዲያ በነዚሁ አይነቶቹ የአማራ ሆዳሞች ላይ የማያወላውል እርምጃ እንደሚወስድም ከውዲሁ አስጠንቅቋል፡፡ ይህ ማስጠንቀቂያና በሆዳም አማራወች ላይ መወሰድ የነበረበት የተግባር እርምጃ በብዙወቻችን በኩል ዘግይቷል የሚል ስሜት ቢኖርም ወሳኞቹ በየግንባሩ በአመራሩ ላይ ያሉት ፋኖወች ዉሳኔ ስለሆነቭጉዳዩን ለእነርሱ መተው ይሻላል፡፡ ይገባልም፡፡
“”ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው —- አስቀድሞ መምታትፊርማቶሪዉን ነው”” ይል ነበር የአገሬ አርበኛ፡፤ ያኔ “ፊርማቶሪ” ማለት ጠላት የነበረውን የጣሊያን ጦር እየመራ የሚያመጣ፣ ነገር አመላላሽ፣ አስጠቂ የሆነ የራስ ወገን የሆነ ሰው ለማለት የተጠቀሙበት ነው፡፡ ልክ እንደ አሁኖቹ የብአደን ተላላኪወች ማለት ነው፡፡ ሁሉም እንዲያውቀው የሚያስፈልግ ሀቅን በይፋ ማሳወቁ ለማንም ይበጃል፡፡ ለጠላትም ለወዳጅም፡፡
ይህም የአብይ አህመድ የጊዜ መግዣ የሆነው አገራዊ ድርድ፣ ምክክር የወልቅይትና ራያ የሪፍረንደም ማጃጃያ ድራማ….. ወዘተ ሁሉም ስልቶቹ ባዶ ቱሪናፋወች ናቸው፡፡ጊዜ መግዣወች ናቸው፡፡የኦሮሙማ ስልጣን ማራዘሚያ ቅያሶች ናቸው፡፡ የአገራዊ ድርድሩ ከሁሉ አስቀድሞ በቅድሚያ የአብይ አህመድን ከስልጣን መወረድ ያረጋገጠና እንዲፈጠር የሚፈለገውም ኮሚሽን የሁሉንም የአገሪቱን ሀይሎች ይሁንታ በቅድሚያ ማግኘት ያለበት መሆን ቀዳሚ ግደታ ነው፡፡ እንደዚሁም አብይ አህመድ ወልቃይትንና ራያን ከአማራው እጅ ፈልቅቆ ወስዶ “”የፕሪቶሪያው ስምምነት”” እያሉ ወያኔና ኦርሮሙማ በጋራ በሚያናፉት ድሪቶ ስምምነታቸው መሰረት ለወያኔወች እንዲያስረክባቸው የሚደረገው የቂል ስራ ከ600 ሽህ በላይ የትግራይ ወጣቶችን አስበልቷል ለሚባለው ለሀወሀት መሳቂያ ከመሆን አያልፍም፡፡ አንዳቸውም የአብይ አህመድ ስልቶችና የጊዜ መግዣ ቁማሮቹ አልሰሩለትም፡፡ ወደፊትም አይሰሩለትም፡፡ ምክንያቱም ኦሮሙማ ብቻውንም ሆነ ከወያኔ ጋር ተጣምሮ በሁለቱም ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎች ከሚገባው በላይ የተገፋውንና በግፍ የታረደውን የአማራን ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ማሸነፍ አይችሉምና ነው፡፡ ይህንን የተገፋ ህዝብን ማሸነፍ ያለመቻልን እውነታ አብይ አህመድ አሜሪካ ከአፍጋኒስታንና ከቬትናም ህዝብ የነጻነት ትግል ወቅት ካጋጠማት ውርደት መማር ያልቻለ እንሰሳ ነው፡፡
አገሪቱ አሁን ላለችበት አጣብቂኝ ብቸኛው መፍትሄ የስርአት ለውጥ ብቻ ነው ፤ አለበለዚያ ኣገሪቱ ወደማይቀረውና አሁን እየተጀመረ ወዳለው የእርስ በእርስ ጦርነቱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መግባቷ የማይቀር ስለሆነ አማራው ይህንኑ አውቆ በስፋትና በቁርጠኝነት ሰፊ ዝግጅት በማድረግ ፍልሚያውን እስከ ድል ድረስ መግፋት አለበት፡፤ እኔ ከዚህ ወገን ነኝ፡፡
አማራ ያለው አማራጭ አንድ ብቻ ነው – ማሽነፍ!!!