December 8, 2023
2 mins read

አርበኛ ሁን ካህን!

arbegna 1 1 1

arbegna 1 1 1

መጣፉ ያዝዛል እንድትገጥም ሰይጣንን፣
ተሕዝብ እንድትነቅለው ነግንገህ ቁንጮውን፣
ሳትውል ሳታድር አርበኛ ሁን ካህን!

ፈለግን ተከል የጴጥሮስ አድማሱን፣
ክፉ አምስት ዘመን ዳግም ሲመጣብን፡፡

እንኳንና ሕዝቡ እንዳትገዛ ምድር፣
በግዝት መሀላ በጸሎት ውል እሰር፣
ጭራቅ አገር ወሮ ተኝተህ ላታድር፡፡

ከበሮ ደልቀህ እምቢልታውን ነፍተህ፣
ፀናጽል አፋጭተህ መቋሚያህን ሰብቀህ፣
አዋጅ! አዋጅ! ብለህ ሞረሽ ክተት ጠርተህ፣
ክላ ዲያብሎስ በል ተአገር ሳያጠፋህ!

ሰሜን እስተ ደቡብ ቀጥ ብለህ ቆመህ፣
ተምስራቅ ምዕራብም አግድም ተያይዘህ፣
የወልድን ምልክት መስቀል በአንገት አስረህ፣
እንደ ጉም አብነው ሳጥናኤልን ገፈህ፣
ተመልካች አትሁን ሲጨስ ሲነድ ሕዝብህ፡፡

ዜማውን አዚመህ ቅኔን ተቀኝተህ፣
ጸበልን እረጭተህ በመስቀል ደልዘህ፣
አስወጣ ዲያብሎስ ዛሩን አስጎርተህ፡፡

እግዜር ተሳጥናኤል እንዳልታረቀ አውቀህ፣
ማተብ ታላሰረ ሽምግልና አቁመህ፣
ቃል አባይ ከሀዲን ዳግም ማመን ትተህ፣
መንን ወደ ጫቃ ጥራኝ ፋኖ ብለህ፡፡

ለምተዋት ዓለም ነገ ለማትኖር፣
ሥጋህ አሸንፎ ነፍስ አትግባ ሲኦል፡፡

እግዜርና ታሪክ ጥሪ ሲያቀርቡልህ፣
አደጋ ሲወድቁ አገርና ሕዝብህ፣
እንድታድናቸው በሥጋ በደምህ፣
አርበኛ ሁን ካሀን እንደ ቅድመ አያትህ፡፡

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Tesfaye Gebreab
Previous Story

እዉን መዘክር ለተስፋየ ገብረአብ?

Amhara
Next Story

አማራ ያለው አማራጭ አንድ ብቻ ነው – ማሽነፍ !! (እውነቱ ቢሆን)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop