አስቸኳይ ሕዝባዊ ጥሪ ወልቃይትን እና ራያን ለህዝበ-ውሳኔ (ሬፈራንደም) ማቅረብ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የታቀደ አደገኛ ሴራ ነው!

For immediate release

ኅዳር ፰ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. (Hidar 8, 2016 E.C)

November 18, 2023

ወልቃይትን አስመልክቶ ጥቅምት ፳፰ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. (28, 2016) ወይም በNovember 8, 2023, ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የተሰጠው “የህዝበ-ውሳኔ” ሬፈራንደም (Referendum) አቅጣጫ ኢትዮጵያውያንን ለተባባሰ እልቂት የሚዳርግ የተሳሳተ ውሳኔ እንጅ ዘላቂ ሰላም እና መፍትሄ ማያመጣ በመሆኑ በአስቸኳይ ውሳኔው እንዲሻር እንጠይቃለን።

በድሮንና በከባድ መሳሪያ የዓለም አቀፍ የጦር ህግጋትን በመጣስ የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት እያደረሰ ያለው ጨፍጫፊው የአቢይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን ጦርነት ከማቆም ይልቅ ከትሕነግ ጋር በመተባበር በአማራና በትግራይ ህዝብ መካከል የማያባራ የዘላለም ዕልቂት ለመፍጠርና እየተጠናከረ የመጣውን የአማራው ህዝብ የህልውና ትግል ለመቀልበስ ታሪካዊ ማንነቱና አጽመ እርስቶቹ የሆኑትን ወልቃይትንና ራያን ለትግራይ ለማስረከብ “ህዝበ-ውሳኔ” የሚል ሴራ ይዞ መጥቷል። እንደሚታወቀው ሁሉ በጥላቻ፣ በራስ ወዳድነት፣ አምባገነንነት፣ አላዋቂነት አንዲሁም በአክራሪነት ላይ የተመሰረተው የትህነግ ማኒፌስቶ አንዱ ዓላማ ወልቃይትንና ራያን በመቆጣጠር፣ ተዝቆ የማያልቀውን የተፈጥሮ ሃብትና እጅግ ጠቃሚ መልክዓምድር በመጠቀም “የታላቋን ትግራይ” ምኞት ለማሳካት ነው። ዘረኛው የኦሮሞ ብልጽግና መንግሥትም ሆነ ተባባሪዎቹም “ህዝበ-ውሳኔ” የሚሉትም ትግራይን ለማስገጠልና እንዲሁም አማራን በማጥፋትና በማሳነስ ኦሮሚያ የምትባል ሌላ አዲስ አገር

የማዋለድ ትልቁ ድብቅ ሴራ አካል መሆኑ መታወቅ አለበት።

ለአማራው ትግል የቀይ መስመር የሆኑትን ወልቃይትን እና ራያን ለትህነግ አሳልፎ ለመስጠት የሚደረገውን እሽቅድድም የአማራ ህዝብና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በፍጹም አይቀበሉትም። በአማራው ላይ የተደረገው መጠነ ሰፊ ወረራና የዘር ማጥፋት ዘመቻ፣ በዋናነት ወልቃይትን እና ራያን ለህወሐት ለማስረከብ መሆኑን በደንብ በመገንዘቡ ህዝቡ ማንነቱን እና ርስቱን ለመጠበቅ ተስማምቶ የክተት አዋጅ አውጆ እራሱን እየተከላከለ ይገኛል። አማራ በእነኝህ ቦታዎች ላይ የማንነት እና አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ከማንሳት ባለፈ ህዝበ-ውሳኔ ለማድረግ ተስማምቷል ተብሎ የቀረበው ሃሳብ ፍጹም ሃሰት መሆኑን ልናስገነዝብ እንወዳለን። የአማራ ህዝብ ህዝበ-ውሳኔ እንዲደረግ አልጠየቀም፣ ጠይቆም አያውቅም። የአማራ ህዝብ ባልተወከለበት፣ እንዲሁም በወራሪ ኃይል ተይዞ፣ ነጻነቱ ተገድቦ፣ እየተገደለ፣ እየታፈነ፣ እየታሰረ፣ ሴት ልጆቹ እየተደፈሩ ባለበት በዚህ አፓርታይዳዊ ስርዓት ውስጥ ሆኖ ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ ተስማምቷል መባሉ አገሪቷ ምን ያህል በሴራ ፓለቲካ እንደተተበተበች ትልቅ ማሳያ ነው።

ትሕነግ አዲስ አበባን በ1983 ዓ.ም. ከተቆጣጠረ በኋላ ከወሰዳቸው ዓበይት የጥፋት እርምጃዎች አንዱ የሀገሪቱን ነባር የአስተዳደር ካርታን መለወጥ ነበር። በምትኩም ቋንቋን መሰረት ወዳደረገ አከላለል ተሸጋግሮ አዲስ ካርታ መስርቶ፣ ብዙ የማንነት ጥያቄዎችን እንዲነሱ ሁኔታውን አመቻችቶ የጎሳ ግጭቶች ሥር እየሰዳዱ እንዲሔዱ ትሕነግ አሻራውን አውሏል።የህወሓት ሕገወጥ መሬት ስልቀጣ፣ የትግራይ ተስፋፊነት ለብዙ ዓመታት የታሰበበት፤ በእቅድ የተሰራበት ዘላቂ እንዲሆን በአዲስ ሰፋሪዎችና በጦር መሳሪያ ኃይል የተደገፈ ነበር። በህወሓት አፓርታይድ ስርዓት ለአርባ አራት አመታት በወልቃይት ሕዝብ ላይ የተፈፀመበት ግፍ ወልቃይትን የአማራ የበደል ማዕከል አድርጓታል። የወልቃይት ህዝብ ለማንነቱ፣ ለመብቱ እና ለህልውናው የታገለው እና የሚታገለው መሬቱን፣ ንብረቱን ለቆ እንዲወጣ እና መተዳዳሪያ አጥቶ በስደት እንዲኖር በመደረጉ እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶቹ ተገፈው አፈናዉና እልቂቱ ስለበዛበት መሆኑ ይታወቃል። እሰካሁንም ድረስ ህወሓቶች በወልቃይትና ራያ ላደረሱት ኢሰብአዊ እልቂትና ወንጀል ለፍርድ አልቀረቡም። የንጹሃን ዜጎችን ሰብዓዊ መብት የረገጡ ወንጀለኖች ለፍርድ ሳይቀርቡ እና የህዝቡ የማንነት ታሪካዊ ጥያቄ በአግባቡ ሳይመለስ በጓሮ በር በተደረገ ስምምነት “ሕዝበ-ውሳኔ” ወይም ሬፈረንደም ለማድረግ መታሰቡ በህወሓትና በፋሽስቱ የአብይ አህመድ አፓርታይዳዊ ስርዓት አገር ለማፍረስ የታቀደውን ሴራ በግልጽ ያሳያል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአርባ ምንጭ የባልደራስ አመራሮች እገታን በተመለከተ የፓርቲው ድርጅታዊ መግለጫ

የአማራ ማንነትን ለማስከበር መስዋዕትነት የተከፈለባቸው የአማራ ህዝብ አፅመ ርስቶች ወልቃይት ጠገዴ፣ ሁመራና ጠለምት ከጎንደር ራያ አላማጣ፣ ኮረም፣ ወፍላ፣ መሆኒ፣ ዋጃ ከወሎ አሁን ያለው የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ከመፅደቁ 4 አመት በፊት ህወሓት ስልጣኑን ተጠቅሞ በግድ ወደ ትግራይ ጠቅሏቸው ለ29 አመታት አማራዎችን በአፓርታይዳዊ አገዛዝ ሲያሰቃያቸው ሺህወችን ጨፍጭፎ፣

ከጭፍጨፋው የተረፉትን ማንነታቸውን አሳጥቶ በቋንቋቸው እንዳይማሩ እንዳይናገሩ፣ አምልኮ እንዳይፈፅሙ፣ ደስታቸውንም ሆነ ሀዘናቸውን በአማርኛ እንዳይገልፁ አድርጎ አስጨንቆ ይዟቸው ከቆየ በኋላ ራሱ በለኮሰው ጦርነት አማራው ለነፃነቱ ባደረገው ተጋድሎ ርስቶቹን በደሙ ማስመለሱ እንዲሁም ምንም እንኳ በመንግሥት በጀት ባይሰጠውም ከሕወሐት ወረራ እና ጭቆና እራሱን ነፃ አውጥቶ ራሱን እያስተዳደረ መሆኑ እየታወቀ “ጥያቄ የሚነሳባቸው ቦታወች” በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት መሰረት ችግሩ ይፈታል የሚለው ሃሳብ ፈፁሞ ተቀባይነት የሌለው መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። እንዲሁም፣ ወያኔ ወልቃይትን ጠቅልሎ ወደ ትግርይ ክልል ያስገባው ኅገ መንግስቱ ሳይፀድቅ በፊት በፖለቲካ ውሳኔ ብቻ ነው። በተጨማሪም፣ ይህ ኅገ መንግሥት ሲረቀቅም ሆነ ሲፀድቅ አማራውን ያገለለ ስለነበረ አማራው ያልተሳተፈበት ህገ መንግሥት ከመሆኑም በሻገር ይህ ኅገ መንግሥት እንዲለወጥ በተደጋጋሚ ጥያቄ ካነሳ አመታት አልፈዋል፤ በዚህም የተነሳ አማራውን በማግለል በተቀረፀ ህገ መንግሥት አማራ ሊዳኝበት አይችልም። የወልቃይትና ራያ አማራነት እና የአማራ አፅመ እርስትነት የህዝቡ ፅኑ እምነት ከመሆኑ አልፎ ብዙ የታሪክ ምስክርነት ያለው በመሆኑ የትኛውም ምድራዊ ኃይል ከአማራ ባለቤትነት ሊያዋጣው አይችልም።

በትህነግ ወረራ ሰለባ የነበሩት የአማርንና የአፋርን ህዝብ ያላካተተው በፋሽስቱ የአብይ አህመድ አገዛዝና በህወሓት መካከል የተደረገው የፕሪቶሪያ ድብቅ ስምምነት ወይም ሴራ ወልቃይትን ለህወሐት ለመስጠት መሆኑ በግልፅ መታወቅ አለበት። ህወሓት የጀመረውና ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያለቀበት ጦርነት ሰላምን ከማምጣት ይልቅ ሌላ ጦርነት በአማራው ላይ ለመክፈት ዋነኛ ምክንያትም ሆኖአል። ከዚህ የይስሙላ ሰምምነት በተቃራኒ ትህነግ ታጣቂዎቹን አማራና ኤርትራ አዋሳኞች ላይ አሰፈረ እንጂ አንድም የትህነግ ታጣቂ ትጥቅ አልፈታም። እንደ አቶ ጌታቸው ረዳ አባባል በትግራይ በአሁኑ ሰአት 250,000 ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ይገኛሉ። በመሆኑም አሁን ሊተገበር የታቀደው ትህነግ በ1984 በሽግግር መንግሥቱ ጊዜ በኃይልና በፖለቲካ ውሳኔ አካባቢዎቹን ወደ ትግራይ ከልሎ ፥ነባሩን ነዋሪ አሳዶ፣ አስሮና ገድሎ ያሰፈራቸውን ሰዎች በጦርነቱ የተፈናቀሉ ነባር ነዋሪዎች በሚል መልሶ በማስፈር ህዝበ ውሳኔ በሚል የሕዝብ ማደናገሪያ ሰበብ አካባቢዎቹን ለህወሓት አሳልፎ ለመስጠት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል (Genocide) መንግስት ሙሉ ኃላፊነቱን ሊወስድ ይገባል!!! (መኢአድ)

በመሰረቱ የፕሪቶሪያ የሁለትዮሽ ስምምነት በኦሮሞው የብልጽግና መንግሥትና በትሕነግ መካከል ብቻ በመደረጉ አማራና አፋር ባልተሳተፉበተና ባልተወከሉበት ድርድርና ስምምነት መሰረት የተደረገ የፖሊቲካ ውሳኔ አይመለከታቸውም፣ ሕጋዊ መሰረተም የለውም። እውነታው በጥቅሉ ሲታይ፣ የወልቃይትንና ራያን ጉዳይ ህገ መንግሥቱም ሆነ የሴራ ስምምነት አይፈታውም።

ለኢትዮጵያ ዘላቂው መፍሔው ቋንቋን መሰረት አድርጎ የተዋቀረው ህገ መንግሥት ተወግዶ ሁሉን በእኩልነት የሚያሳትፍ ህገ መንግሥት ሲመስረት ብቻ ነው። ህወሓት ያዋቀረው የጎሳ ፌደራሊዝም ተወግዶ ሁሉንም የፌደራል አወቃቀር መርሆዎችን እና የዜጎችን መብት ዋነኛ መሰረት ያደረገ የፌደራል ስርዓት ሲዘረጋ አሁን የሚታየው የዘር ጭፍጨፋ፣ የድንበር ይገባኛል ጥያቄ እና አገር የማፍረስ ወይም የማዋለድ ተግባር ይወገዳል። ይህን ከማድረግ ይልቅ ከፋፋዩ “ህዝበ ውሳኔ” ሥራ ላይ ከዋለ በእርስ በርስ ጦርነት ኢትዮጵያን በማፍረስ ለህዝባችን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለምስራቅ አፍሪካና ለመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት የሚያስከትል ይሆናል። ስለዚህ ይህን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የታቀደውን አደገኛ ሴራ ለማምከን የአብይ አህመድን አፓርታይዳዊ አገዛዝ በህዝብ ትግል ማንበርከክ ስለሚጠይቅ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ለተግባራዊነቱ እንድንተባበር የሚከተሉትን ጥሪዎች እናስተላልፋለን፦

  1. በአማራ ህዝብ ንፁሐን ዜጎች ላይ በድሮንና በከባድ መሳሪያ ታጅቦ እየተካሔደ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ባስቸኳይ እንዲቆም እና ውራሪው የአብይ አመድ ስራዊትም ዛሬነገ ሳይል ክልሉን ለቆ እንዲወጣ እንጠይቃለን፣
  1. ወልቃይትንና ራያን “ለህዝበ-ውሳኔ” ሬፈረንደም ማቅረብ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የታቀደ አደገኛ ሴራ መሆኑን በመገንዘብ መላው የአማራ ህዝብ ከሌሎቹ ኢትዮጵያዊ ወገኖች ጋር በመቆም በዚህ ሕግ-አልባ አፓርታይዳዊ አገዛዝ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲያሰማ ጥሪ እናቀርባለን፣
  1. የመላው የአማራ ህዝብ ፥ በኃይልና በግፍ ተወስደው የነበሩትን እና ከፍተኛ መስዋዕት በመክፈል ያስመለሳቸውን ወልቃይትና ራያን አማራዊ ማንነታቸውን ማስከበር ይኖርበታል።
  1. መላው የኢትዮጵያም ህዝብ በወልቃይትና ራያ ላይ የታቀደው ‘ህዝበ-ውሳኔ’ አንድን ማህበረሰብ ከሌላው ጋር ለማቃቃር እና አገር አፍራሽ ውሳኔ በመሆኑ እንዲያወግዘው
ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጫ

እንጠይቃለን፣

  1. እኩይ ኃይሎች ህዝቡን ለመከፋፈል ያልተቋረጠ ጥረት እንደሚያደርጉ ታውቆ በአንድነት ለማይቀረው ትግል መሳተፍ ይገባል፤ በመሆኑም የአማራ ህዝብ ፋኖ የያዘውን ትግል በመቀጠል ሌሎች የህብረተሰብ አካሎችን ለትግሉ በማስተባባር፣ ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር፣ እና ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር ትግሉን በአሸናፊነት መወጣት ይኖርበታል፣
  1. አገርህን ለመጠበቅ ቃል ኪዳን የገባሃው መለዮ ለባሽ፣ ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለማዳን ትግሉን በመቀላቀል ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መስዋዕት መክፈል ውዴታህ ሳይሆን ግዴታህ መሆኑን በመረዳት ከገዥው ስርዓት አገልጋይነት በመላቀቅ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማሰከበር፣ ህዝቧንና ሰላሟን ለመጠበቅ ሲል እየተዋደቀ ከሚገኘው ከፋኖ ጋር በመሰለፍ ቃል ኪዳንህን እንድታከብር ጥሪ እናደርጋለን።
  1. በአፋኙ አብይ አህመድ አገዛዝ እስር ላይ የሚገኙ ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ በአማራነታቸው ብቻ የታሰሩ የፓለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፣
  1. በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ እርስ በርስ በመናበብ አማራው የራሱን ህልውና በማስከበር ኢትዮጵያን ከዚህ አፓርታይዳዊና ፋሺስታዊ ስርዓት በማላቀቅ ፍትሐዊ ስርዓትን ለማምጣት የሚያደርገውን ትግል ከአሁኑ በበለጠ ለመደገፍ እንዲነሳሳ ጥሪ እናቀርባለን። በሀገር ውስጥ ህይወታቸውን ለሚሰውት፣ ያለፍርድ በእስር ቤት ለሚንገላቱት፣ ለተፈናቀሉትና በርሃብ ለሚሰቃዩት፣ በፍትሕና በነፃነት እጦት ለሚንገላቱት ድምፅ በመሆን፣ ከዓለም አቀፉ ማኅብረሰብ ድጋፍ ለማግኘት በዲፕሎማሲም ጠንካራ ሥራ በመሥራት በወልቃይትና በራያ የታቀደውን ሴራ በማጋለጥ አገራችንን ከመፈራረስና ከመበታተን ለማዳንና ብሎም የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት ጠንክሮ እንዲሰራ እንጠይቃለን።

አማራው በክንዱ ህልውናውን ያስከብራል፣ ኢትዮጵያንም ከዚህ አስከፊ ስርዓት ነፃ በማውጣት ፍትሐዊ ስርዓት ያመጣል።

ፈራሚ ድርጅቶች

SIGNATORY ORGANIZATIONS

  1. Abba Bahrey Forum
  2. Adwa Great African Victory Association (AGAVA)
  3. Amhara Dimtse Serechit
  4. Amhara Wellbeing and Development Association
  5. Communities of Ethiopians in Finland
  6. Concerned Amharas in the Diaspora
  7. DC Task Force
  8. Embilta Forum
  9. Ethio-Canadian Human Rights Association
  10. Ethiopian American Community
  11. Ethiopian Community Association of Greater Cincinnati (ECAGC)
  12. Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause
  13. Global Amhara Coalition (GAC)
  14. Global Ethiopian Scholars Initiative (GESI)
  15. Hibre Hizb
  16. Major Lemma Woldetsadik Memorial Foundation
  17. Network of Ethiopian Scholars (NES)
  18. Radio Yenesew Ethiopia
  19. Selassie Stand Up, Inc.
  20. The Ethiopian Broadcast Group
  21. Vision Ethiopia (VE)
  22. Welkait, Tegede, Telemt, Setit Humera International organization
  23. Worldwide Ethiopian Civic Associations Network (WE-CAN)

 

3 Comments

  1. Great article based accurate historical facts. We only have one country and we can’t give it up for butchers.

  2. በጥቅሉ አብይ አህመድ ይህንን ማሳካት አይችልም፡፤ በኦሮሙማ መንጋ የታጨቀው “የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት” የሚለው የመንጋወቹ ስብስብ አስቀድሞ በፋኖ ተሽመድምዷል፡፡
    የህወሀት ድብቅ እቅድም ቢሆን የማይሰራ ነው፡፤
    የወያኔ እቅዱ ይህንን ይመስላል፡፡ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት መሬቶቹን በአብይ አህመድ በኩልለማኘት እሰከመቸረሻው ድረስ መጣር፡፡ ይህ ሳይሳካ ቢቀር በአብይ አስታክኬ ሰራዊቴ ተበትኗል ትጥቄንም አስረክቤያለሁ ብሎ በመዋሰት “”በድብ እዳ”” መልክ አማራን ወርሮ ወልቃይትንና ራያን መልሶ መውሰድ የሚል ነው፡፡
    በአሁኑ የአማራው ህዝብ ቁርጠኛ አቋምና ዝግጅት ወያኔ ይህንን መሰሉን እቅድ ሊያደርገው ቀርቶ ሊያስበው አይችልም፡፡ ካሰበውና ካደረገውም እብዴት ነው የሚሆነው፡፡ አንድ ሚሊዮን የትግራይ ወጣቶችን በአብይ አህመድ ተልካሳ ሰራዊት ያስበላ የወያኔ እቅድ ይታያችሁ በቆፍጣናው ፋኖ ምት ምን ሊደርስበት እንደሚችል፡፡
    ነገሩ “”አይሆንምን ትተሽ ይሆናልን ያዥ”” ነውና በአማራው በኩል በቂ ዝግጅት መደረግ አለበት፡፡ ወልቃይቴው ራያ ራዩማው በጠቅላላ አማራው ያፈረጠመ ዝግጅቱን ምን ጊዜም መላላትና መዘናጋት የለበትም፡፡
    ይህ በንዲህ እንዳለ ሪፍረንደም ለሚለው ቀደዳ መልሱ “”አይሳካም”” ነው፡፡ እንዴት እንደሚያሳኩት እናያለን፡፡፡

  3. ታማኝ በየነ ነው መሃመድ እንዲህ ያለ ችግር ሲመጣ ሼል ውስጥ ይደበቃል የሚወጣበትን ጊዜ ያውቅበታል ቀበሮ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share