አቡነ ኤርሚያስ በቤተክርስቲያን ስም ክፉ ነገርን መቀስቀስና ምዕመናንን ማባላት አይገባም” አሉ

November 19, 2023

ሁለተኛው ዳንኤል ክብረት የአብይ አህመድ ተላላኪ አቡነ ኤርሚያስ በቤተክርስቲያን ስም ክፉ ነገርን መቀስቀስና ምዕመናንን ማባላት አይገባም” አሉ

 

https://youtu.be/QeXCaFdgqTU?si=LAdnrCmOg1sm1XbT

6 Comments

 1. ሀ) የሃይማኖት ተቋማት የእረኝነት ሳይሆን የለየለት ምንደኝነት ሰለባ ከሆኑ ዓመታት ተቆጠሩ!

  ለ) እንዲህ አይነት ከጨካኝ (ከገዳይና አስገዳይ) የፖለቲካ ሥርዓት ካድሬዎች (ባለሥልጣናት) መካከል ተቀምጦ እና ከእነርሱ ባልተናነሰ ግልብና አደገኛ ስሜት እየተናጠ አገር ማለት ሰው እንዳልሆነ ሁሉ የገዳዮችን የጦር ሃይል ተዳፈራችሁ በሚል እረኛው ነኝ የሚለውን ህዝብ የሚያጎሳቁል አባት ተብየ አኳኋን የሚነግረን የገጠመንና እየገጠመን ያለውን ውድቀት አስከፊነት ነው!

  ሐ) እነዚህን አይነቶች አሳፋሪና ወራዳ አባቶች ተብየወች ከቻሉ ንፅሃ ገብተው ይቅርታ እንዲጠይቁ ካልሆን ግን የጨበጡትን መስቀል አርክሰውታልና ቢያንስ ባለመሳለም እውነተኛ አማኝነትን ማሳየት የግድ ነው!

  ሐ) አዎ! የአድርባይነት ክፉ ልክፍትን/ሰብእናን በሃይማኖታዊ አልባስ እና በንዋየ ቅድሳት ሸፍኖ (ተኩላነትን በበግ ለምድ ለብዶ/ሸፍኖ) መከረኛውን ህዝብ የማታለሉን አስቀያሚ ሰብእና ፈፅሞ ማስቀረት ባይቻልም ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ በቋፍ ላይ ያለውን ትውልድ ጨርሶ ከማበላሸቱ በፊት መገታት አለበት!!

 2. አዎ! የዚህ መከረኛ ህዝብ መከራና ውርደት ፍፃሜ ካጣባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ በሃይማኖት ስም የተደላደለ ዓለማዊ አኗኗር በመፍጠርና በማመቻቸት ክፉ ደዌ በተለከፉ አባት ነን ባዮች (እበትም ትል ይወልዳል እንዲሉ) እና የዘመናችን የቴክኖሎጅ ውጤቶች ለህዝብ ደህንነትና እድገት ሳይሆን ለተንቦረቀቀ የግልና የቡድን የአኗኗር ስልት መሣሪያነት በሚጠቀሙ አክቲቪስትና ኮሜዲያን ተብየ ወገኖች ምክንያት ነው!

 3. ሰዎች፣ ሕፃናት ፣ እናቶች ፣ አባቶች ሲታገቱ ለማስለቅ ገንዘብ ሲለመንላቸው፣ ስርአት ሲጓደል በአያገባኝም ስሜት የዚህ የዚያ ክልል ችግር ነዉ የእኔ አይደለም በማለትና ቀደመን የቀበሌ እና የወረዳ የፍትህ እና የፖሊስ ተቋማትን በፌደራል ወይም በማእከላዊ መንግስት መንፈስ ባለማደራጀታችን ችግር ውሰጥ ገብተናል

  • ንዝንቦ ምንድነው የጻፍከው? ለማን ነው የጻፍከውስ? አንተ ያልከውን አደረጃጀት ለመፍጠርስ ማን ነው የሚችለው? የጸሀፊውና አስትያየት ሰጭዎች ያተኮሩት በአቡነ ኤርምያስ አፍ ወለምታ ነው አንተ ደግሞ ሌላ አለም ላይ ነህ። እንዲህ ከሰማይ ሰማያት አልፈው በህዋው ተንሳፍፈው እንዳንተ አይነት ጽሁፍ የሚለቁ ጫት የሚበሉ ሰዎች ናቸው ብትችል አትብላ ይቅርብህ። ህዝቅኤል ጋቢሳን መሰልከኝ።

 4. Regarding Abiy Ahmed’s Ploy To Use The Ethiopian Church Clergy To Ensnare And Destroy Fanno, Zemedkun Bekele Writes Thus:

  “…ስለዚህ መላው ዐማራ በሃይማኖት አባቶች በኩል የሚመጡበትን የመጨረሻ ኒዩክለር ቦንብ ከወዲሁ ሊያመክን ይገባል። ቀላል ነው። እምቢኝ፣ እምቢዮ፣ ጥፋ ከዚህ፣ አውግዝ፣ ደኅና ሰንብት ሊባል ይገባል። ራሱ ቤተ ክህነቱ ፋኖን የሚፈራበት ምክንያት አለው። ቤተ ክህነቱ የፋኖ መምጣት እርግጥ ከሆነ እንዲያውም ከአረመኔው አቢይ አሕመድ በከፋ ሁኔታ ፋኖን የሚታገለው ራሱ ቤተ ክህነቱና መጅሊሱ ነው።

  ……….። ቤተ ክህነቱ የወንበዴ፣ የሌባ፣ የሸርሙጦች መነሃሪያ ከሆነ ሰንብቷል። አስገድደው የደፈሩ ጳጳስ አሁንም በሥልጣናቸው እንዳሉ ነው። አስገድደው ያውም መነኩሲት አስገድደው በመንበረ ፓትርያርክ መኖሪያ ውስጥ የደፈሩ፣ የተደፈረችውም መነኩሲት ወልዳ ተቀምጣ ጳጳሱ እስከአሁን በሥልጣን ተቀምጦ እያየን፣ እየተመለከትን ከዚህ ወገን የሚመጣ ውግዘት ማንን ይጎዳ ብዬ ነው የምሳቀቅ? ዘራፊ፣ ነጋዴ፣ የፓርቲ ካድሬ ዘጭ ብሎ ቆብ አጥልቆ ቢያወግዘኝ እንዴት እሰማዋለሁ። ነፍሰ ገዳይ፣ በሻሸመኔ ምእመናንን በመትረየስ የስጨፈጨፈ ጳጳስ ላውግዝህ ቢለኝስ እሰማዋለሁ እንዴ? አዎ ፋኖ ሲመጣ እነዚህን በቤተ እምነት የተሸሸጉትን ወንበዴዎች በዥራፍ እየዠለጠ እንደሚያጠራቸው አሳምረው ያውቃሉ። እናም ከወዲሁ የመንግሥት መጠቀሚያ ኮንዶ* ወይም ሸንኮራ ሆነው ቢቀርቡ አያስደነግጠኝም።

  ስለዚህ ፋኖ ከዚያ አካባቢ የሚመጣን ገተት የራስ ምቾት ማስጠበቂያ፣ በቆብ ስር የተሸሸጉ ምቾት ያንገላታቸውን ባለ ቪ8 የደሀ ልጆችን ሰበካ እንዳይሰማ እመክራለሁ።”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Welkeit and Raya
Previous Story

አስቸኳይ ሕዝባዊ ጥሪ ወልቃይትን እና ራያን ለህዝበ-ውሳኔ (ሬፈራንደም) ማቅረብ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የታቀደ አደገኛ ሴራ ነው!

Ermias 1 1
Next Story

ከካህኑና ከሌዋዊው ደጉ ሳምራዊ የሰብአዊነት መገለጫ ሆነ፣ 

Go toTop