ዳኔል ክብረት አማካሪ ወይንስ ተሳዳቢ? ከዶ/ር መንግስቱ ሙሴ – ዳላስ/ቴክሳስ

ዳኔል ክብረት የተባለ የኦሮሞ ብልጽግና ፕሮፖጋንዲስት ቀጣሪ እና አሳዳሪወችን ለማስደሰት እንዲህ አለ “ጃውሳው ቀንጭሮ እንዲቀር የሚያደርጉት አያሌ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ምክያቶች አሉ፡፡ ሑከት ፈጣሪ ኃይል ከመሆን ባለፈ የመከላከያንና የሕዝቡን ጠንካራ ምት ቀልብሶ ወደ ውጤት አይሻገርም፡፡”

መቸስ በአገራችንን ቃላዋቂ የሚሉት አባባል አለ። ቃል አዋቂ ማለት ከእውን አለም ይልቅ የተነገረውን የሚያስተጋባ ማለት ሲሆን ይህ የ”ቃላዋቂነት” አባባል ለዚህ የብልጽግና ፕሮፖጋንዲስት የሚስማማ ቃል ሆኖ አገኘሁት። ከላይ ከዳኔል ክብረት መጣጥፍ እንደወሰድሁት ዳኔል እየቃዠ ያለ ሰው ሆኖ ተሰማኝ። ፋኖ ለዳኔል ክብረት አሳዳሪ ደመወዝ ከፋዮችም ሆነ ለራሱ ሁከት ፈጣሪ የሚለው ቃል አይመጥነውም። በዚያውም ደግሞ የመከላከያን ምት መመከት ብቻ አይደለም ሱሪውን እያስፈታ ያነገተውን ትጥቅ እያስወረደ እየነዳው ለመሆኑ ይህ ፕሮፖጋንዲስት የመንግስትን ደህንነት እስኪነግሩት መጠበቅ አይገባውም በቀጥታ ቋሪት ደጋዳሞት ቢደውል የአለፈውን ሳምንት የውጊያ ውሎወች የደጋዳሞት አርሷደሮች ይነግሩታል። ዳኔል “የሕዝቡን ጠንካራ ክንድ” የሚል ቃል በዚህች አጭር ፕሮፖጋንዳ ጽሁፉ አስገብቷል። ይህን ያነበበ አንድ የደጋዳሞት አብሮ አደጌ ድንቄም ከሕዝብ ድጋፍ ብሎ ይሳለቅበት እና የቀን ቅዠት ውስጥ ያለው ዳኔል ስለየትኛው ሕዝብ እንደሚያወራ ግልጽ ባይሆንም ስለአማራው ከሆነ ይህችን የባንዳ ካድሬወች ማደናቆር ወደጎን ያርጋት እና እውነታው ግን በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው እራስን ከጥፋት ለማዳን እና ብሶት የወለደው ተጋድሎ ፍጹም ሕዝባዊ መሆኑን ይረዳው።

 

ዲያቆን ዳኒ ወረድ ብሎ በተራ ቁጥር አንድ ላይ እንዲህ አለ። “1.ብሶት እንጂ ግብ የለውም፦ ጃውሳው በለውጥ ሂደት ላይ የተፈጠሩትን ችግሮች ለዲስኩሩ ማቀጣጠያ ይጠቀማል። መነሻው ግን የዝርፊያ እና የሥልጣን ፍላጎት ነው።” የጣጣፍ አቃቂር እና ማደናቆር ይሏል እንዲህ ነው። ብሶት እንጅ ግብ የለውም ይላል። እዚህች ላይ አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ዘመኑ 1961 ዓም ነው። እኔም የ 5ኛ ክፍል ተማሪ ነበርሁ እናም በአንዷ የሰንበት ቀን ቋሪት ላይ ባምላኩ አየለ (አባ ጊዮን) ከስርአተ ቅዳሴ በኋላ ሕዝቡን ሰብስቦ በየተራ በጎጃም ላይ የተሾሙ የንጉሱን እንደራሴወች መበደላቸውን ዘርዝሮ ለሕዝቡ አስረዳ። ከጠላት ወረራ በኋላ ጎጃምን የገዙት ደጃዝማች ከበደ ተሰማም ሆኑ ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁስላሴ በድለውናል።ከዚህ በኋ በቃን መሪወቻችንን ንጉሱ አንድ በአንድ ወስደው በግዞት አጥፍተዋቸዋል የሰሩን በደል ሳያንስ አሁን በመሬታችን ላይ $0.50 ሳንቲም ግብር ጥለውብናል ጎጃም ይህን ግብር ይሁን ብለህ የከፈልህ ጥቁር ውሻ ውለድ በሚል ሕዝቡን አንድ አረገው።ደጋዳሞትም ሆነ መላው የጎጃም ሕዝብ ከነጻነት በኋላ የተጠራቀመ በደሉን በልቡ ይዞ ኖሮ እንደዚህ ያለ መሪ ሲያገኝ ምሀላ ገብቶ ለበን መውዜሩን ወለወለና ባምላኩ አየለን (አባ ጊወንን) መሪ አርጎ ተከተለ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ችግሩን ሁሉ በአቶ ኃይለማርያም ላይ በማሳበብ በስልጣን መዝለቅ አይቻልም; የኢትዮጵያ የችግሮቿ ምንጭ እራሱ ኢህአዴግ/ወያኔ ነው

 

በዚያች በአንዷ የ 1961 ዓም ቋሪት እና ልጃንበራ የተቀሰቀሰውን የአርሷደር እንቅስቃሴ የትም አይደርስም ብለው የናቁት የንጉሡ እንደራሴ ደጃዝማች ፀሐዩ እንቁስላሴ (አርበኛ) ደጋግመው የፈጥኖ ደራሽ ጦር ወደ ደጋዳሞት ቢልኩም፤ በደጃዝማች ፀሐይ ደጋግሞ የተላከው ጦር የእውሐ ሽታ ሆኖ ቀረ። ከዚህ በኋላ ድንጋጤ የተሰማቸው እንደራሴ የንጉሡ ቀራቢ ስለነበሩ በደጋዳሞት ጦርሰራዊት እንዲላክ ጠይቀው ጣያቄአቸው መልስ አግኝቶ ጦር ሰራዊት ተላከ። ከቀናት ውጊያ በኋላ የተላከው ጦርሰራዊት በመቸነፉ ፈርጥጦ ፉነተሰላም ገባ የሚል ወሬ በጠቅልአይ ግዛቱ ተዛመተ። ሌላው የመንግስት ፕሮፖጋንዳ ደግሞ ንጉሡ ከፍተኛ ጦር ማስገባታቸውን እና በአየር መደብደባቸውን የሚነግር ነበር።

 

የንጉሡ እና የደጃዝማች ፀሐዩ ጦር የደጋዳሞት ሕዝብ ላይ መዝመቱን የሰማው የሞጣ፤ የብቸና እና እና ከፊል የባህርዳር አውራጃወች በይፋ መሸፈታቸውን አሳወቁ። የፖሊስ ጣቢያወች እና የፍርድቤቶች በነዚያ አውራጃወች በሕዝብ ተያዙ። ያንዘመን የአውሮፕላን ትራንስፖርት በብዙ ስለማይታወቅ እና ሕዝቡም ስለማይጠቀም አገር አቋራጭ የነበሩት አውቶቡሶች ጭምር ተቋረጡ። ከአባይ ድልድይ እንዳያልፍ ሆኖ የመንግስትም ሆነ የግል አውቶሞቢል ተገታ። በመጨረሻ ማቻክል እና ጎዛምን አመጹን ሲቀላቀሉ የንጉሱ እንደራሴ እና ጎጃምን ለሁለት አስርት አመታት የገዙት ፀሐዩ እንቁስላሴ መንገድ ስለተዘጋባቸው በአንድ ሌሊት ከአዲስ አበባ ሄሊኮፕተር ተልኮላቸው ትቂት ተከታዮቻቸውን ይዘው ማርቆስን ለቀው ሄዱ። ያንዘመን የጎጃም ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ ደብረ ማርቆ ስለነበር ፀሐዩ እንቁስላሴ ማርቆስን በሌሊት ከለቀቁ በኋላ የጎጃም ሕዝብ ለትቂት ለአጭር ግዜ ቢሆንም በራሱ ሰወች ተዳደረ።

ንጉሱ በግርማ ሞገሳቸው እና በኃይል እገዛዋለሁ ያሉት ጎጃም ሆ ብሎ ተነስቶ ስለረታቸው ሌላ እስትራቴጅ አወጡ እናም የሐገረ ስብከቱን ጳጳስ ኑሯቸው አዲስ አበባ የነበሩትን መስቀል አሸክመው በመላክ ከሁለት አመት አጥፊ ጦርነት በኋላ አመጹን ማቆም ተችሏል። አላማው ያኔም ስልጣን አልነበረም የግብር ጭማሪ ነበር። የሕዝብን ቁጣ የተቀበሉት ንጉሠ ነገስት የ .50 ሳንቲሟን ግብር አነሱ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዕዉነት ሲገለፅ ለትብብር እና አንድነት የሚበጂ ነዉ  !  

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ነው። ይህ የብልጽግና ፕሮፖጋንዲስት ሕዝብን እየሰደበ ብሶት ቢኖረውም ግብ የለውም ይለናል። የአማራ ሕዝብ የኢትዮጵያ እምብርት ነው። እንደሌሎች ወንድሞቹ/እህቶቹ የአንባ ገነን ጭካኔ ሰለባ ሆኗል። ለአለፉት 32 አመታት በየአካባቢው ተገድሏል። ያፈራውን የሰራዉን ቤቱን እየተነጠቀ በሐገሩ ስደተኛ ሆኗል። በተለየ ደግሞ በወለጋ በመተከል ያላቋረጠ ጀኖሳይድ አብይ አህመድ ስልጣን ከያዘ ቀን ጀምሮ ተካሄዶበታል። በነዚህ አካባቢወች ብቻ በመቶሽሆች ተሰደዋል በአስርሽሆች ተጨፍጭፈዋል። ይህን ነው ካድሬው የኦሮሞ ብልጽግና ፕሮፖጋንዲስት “ብሶት” የሚለን። ይህን ፍጅት የመኖር አለመኖር አደጋ መገታት አለበት እናም ግቡ ይህ አደጋውን መቀልበስ ነው።

ሕዝብን የሚሳደበው የኦሮሞ ብልጽግና ካድሬ እንዲ አለ፦ “ጃውሳው ግብህ ምንድን ነው? ቢባል ምላሽ የለውም። ልክ መኪና እንደሚያሳድድ ውሻ ነው። ውሻው መኪናውን ቢይዘው ምን እንደሚያደርገው አያውቅም።” ይህ ተራ ስድብ በሕዝብ ላይ የተወረወረ ነው። የአማራ ሕዝብ ስልጣን አልጠየቀም በእርግጥ የማይወክለኝ ሕገመንግስት ይነሳልኝ ብሏል። አትግደሉኝ እንደሌላው ዜጋ ኢትይጵያን አብሬ ዳር ድንበሯን አስጠብቄአለሁ የመኖር መብቴ ይከበር ነው ያለ። ለመሆኑ ይህ ካድሬ የዚህ ስርአት ዋና እምብርት ጸረ አማራነት እና ጸረ ኢትዮጵያዊነት መሆኑን ያውቃል? አዎ ስርአቱ በህወሓት እና በኦነግ የተመሰረተ ስርአት ነው። የአማራ ሕዝብን በጠላትነት ፈርጀው ዘር ተኮር የሆነ ሕገመንግስት 1991 ዓም ሲጽፉ እና አስተዳደራዊ ክልሎችን ሲያካልሉ ሁለቱም ይህን ሕዝብ ያላካተተ ይሁንታውን ያልጠየቀ ብሎም ከታችም ከላይም መሬት ቆርሰው በመውሰድ ወደፊት ብንገነጠል በሚል ስሌት የራሳቸውን ግዛት ያስፋፉበት እና አማራ በሚኖርበት ሁሉ እንዲሳደድ አቅድ አውጥተው ለ32 አመታት የሰሩ ናቸው። የኦሮሞ ብልጽግና ፕሮፖጋንዲስት ካድሬ ዳኔል ክብረት ካላወቀ እሱ እንዳለው ፋኖ የአማራ ሕዝብ ነው። እንቢተኝነት ሳይሆን የመኖር የአለመኖር አደጋ የፈጠረው እራስን ከጥፋት ለማዳን የተነሳ ተጋድሎ ነው። ግቡን ይህን በአማራ ላይ የተቃጣውን Existential threat የመቀልበስ ወይም የማስቆም ተጋድሎ ነው። የአማራ ሕዝብ ለአመታት በሰላማዊ ሰልፍ እና በየአደባባዩ የመኖር መብቱ እንዲከበርለት ጠይቋል። የዚያ ጥያቄ ምላሽ “አሃዳዊነትን ናፋቂ” ወይንም የድሮ መንግስታትን ናፋቂ የሚሉ ስላቆች ሆነው አግኝቶታል። ለሰላማዊ ጥያቄወቹ የተሰጠው መልስ ንቃቻ እና ስድብ ብሎም ግድያ እና እስራት ነበር። ዘረኛ ጸረ አንድነት ኃይላት ሁሉም በሚባል የሚስማሙበት አማራ መኖር እንደሌለበት ነው። የጋራ ጥያቄወችን ሲያነሳ ትምክህተኛ ይሉታል። ግላዊ ጥያቄወችን ሲኡያነሳ አሮጌውን ስርአት ናፋቂ ይሉታል። ይህ ነው የአማራ የፋኖ ነፍጣዊ ተጋድሎን ያስነሳው። ግቡም በማንነቱ የመኖር ዋስትናውን የማስከበር እንጅ የሌሎችን የመንጠቅ አይደለም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለእነርሱና ለእኛ !!!

የኦሮሞ ብልጽግና ፕሮፖጋንዲስቱ ካድሬ ዳኔል ክብረት ወረድ ብሎ ተራ ቁጥር ሁለት ባለው ላይ እንዲህ ይላል።

 

“ከማዕከል ጋር የተጣላ ጠባይ፦ የአማራ ክልል ሕዝብ በታሪኩ የኖረው የማዕከላዊ ሥልጣን ማዕከልና ደጋፊ ሆኖ ነው። ከማዕከላዊ ሥልጣን ራስን ማግለልና ራስን የሀገር ባይተዋር አድርጎ መቁጠር የክልሉ ሕዝብ ባህል አይደለም።” ይህ አባባሉ በጣም አስቂኝ ነው። የአማራ ሕዝብ እና ፋኖ ማህከልን የማፍረስ አላማ ይዞ የተነሳ ሳይሆን ማህከልን ለማፍረስ በተነሳው ኦነጋዊው መንግስት ላይ የተነሳ እራስን የመከላከል ተጋድሎ ነው። ከላይ ያነሳሁት የ 1961 ዓም በደጋዳሞት ተቀስቅሶ መላ ጠቅላይ ግዛቱን ያጥለቀለቀው የግብር ጭማሪን በመቃወም በንጉሠ ነገስቱ ላይ ተነስቶ የነበር ወታደራዊ አመጽ ማህከልን አልተቃወመም በመሆኑም ንጉሡ ጥያቄውን በቀጥታ ሲመልሱት ቆመ። ዛሬም የተነሳው ይባስ ብሎ በኦነግ አላማ ዙሪያ የተሰባሰቡ እንደነሌንጮ ባቲ፤ ሌንጮ ለታ ወዘተ አይነቶች ማህከልን ተቃዋሚወች የያዙት ስልጣን እና የእኛ የሚሉትን አጠናክረው ለመገንጠል የሚሰሩበት ማህከል ነው። ፋኖ ይህን የተገንጣይ መንጋ የገጠመ እና ሊያጠፉት በእጅ አዙር በአማራ ሕዝብ እና በኢትዮጵያ ላይ የተነሳውን የጥፋት ዘመቻ ለመግታት የተነሳ ተጋድሎ ነው። የኦሮሞ ብልጽግና ፕሮፖጋንዲስቱ ካድሬ ዳኔል ክብረት 7 የሚሆኑ ተመሳሳይ ትርኪ ምርኪ ሀሳቦችን የፋኖ ምክንያት በሚል አቅርቦ ተሳድቧል። አስተሳሰብን መቃወም መብት ነው ግን ከላይ እንዳሳየሁት መሳደብ ግን ክብረ ነክ እና ወንጀል ነው። ይህ ክብረነክ ደግሞ የጅምላ ሲሆን የበለጠ አሳዛኝ ያረገዋል።

ባጭሩ ዳኔል እና የእርሱ አሳዳሪ ደመወዝ ከፋዮቹ እና መሰል የጠባብ ብሔርተኛ መንጋ የጅምላ ስድብን በተለይ በአማራ ላይ የሚወረወር የጅምላ ስድብን ለአለፉት 32 አመታት የተለመደ በመሆኑ ብዙ አያስደንቅም። የሚያሳዝነውም ሆነ የሚያስደንቀው አይንን ጨፍኖ እና ጆሮን ደፍኖ ለነሱ አፈቀላጤ የሆነ ይህን የመሰለ ወራዶች ስራ እና ተግባር ነው።

3 Comments

  1. የማንበብ፣ የመፃፍ እና በሰላ አንደበት የመናገር ክህሎትን በብስለትና በትዕግሥት ማጤን ለሚሳነው ምን ያህል ሊያሳስት የሚችል አደገኛ ሰብእና እንደሆነ ለመረዳትና ለማስረዳት ዳንኤል ክብረት እጅግ ግልፃ ማሳያ ነውና ትውልዱን የበለጠ ሳይበክል ከምር በቃህ መባል አለበት!!!

  2. ዳንኤል ህዝብ ዳግም ባያምንህም አሁን ካለህበት የስጋ ክብረት የመንፈስ ድህነት አይበልጥብህም ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ ሲጠላህ ምን ይሰማሃል እስላሞች የመጽሃፍ ምርቃት ሂደህ እራስህን ያዋረድከውን አስበው እራስህ ስራህን ገደል ውስጥ ከትተኸዋል፡፡ አንዴ ስትሰልም አንዴ ስትከረስትን እንዴት ይሆናል? በዚህ ላይ ቤተሰብ አለህ ያንተ ውርደት የነሱ ነው እልሁን ትተህ ወደ አቅልህ ተመለስ አሸናፊ አትሆንም፡፡ መጽሃፍህን የገዛንህ ስብከትህን ያዳመጥን እንዲህ አካልቦ ለውርደት ያደረስህን ደፍረህ ብትነግረን መልካም ነበር የሚገርመው በውጭ ሃገርም ቦታ የሌለህ ሰው ሁነሃል፡፡ ተይዘሃል አምላክ ይርዳህ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share