November 11, 2023
2 mins read

አቡኑ ጳጳሳት በእንጀራ ታነቁ!

orthodox Church

orthodox Church

ሰማእታት ቅዱሳን ይኸን ጉድ አላዩ!
እነ አቡነ ጴጥሮስ ይኸን አልታዘቡ፡
አድማሱ ጀምበሬ ይኸንን አልሰሙ፣
ፓትርያሪክ ጳጳሳት ለፋሽሽት ሲሰግዱ፡፡

ተምእመናን አስራት ደሞዝ እየዛቁ፣
አስራት አስገቢዎች በድሮን ሲመቱ፣
በእንጀራ ታፍነው ጳጳሳት ጪጭ አሉ!

በበጎቻቸው ደም ስልጣን አስከብረው፣
ተበግ አራጆች ጋር ሲያድሩ ተወባርተው፣
የደመ-ነፍስ ያህል ስግጥጥ እንኳ አይላቸው፡፡

ለሕዝብ መድህንነት ሲሰቀል ጎልጎታ፣
ለራሱ ድሎት ሲል ጳጳስ ሕዝብ አሰዋ፡፡

ጴጥሮስና ጳውሎስ በቄሳር ሲቀሉ፣
የዛሬ ጳጳሳት ሹመት ተቀበሉ፡፡

ተመሐል ደረት ላይ መስቀል አንዠርገው፣
ተራስ ቅላቸውም ያማረ ቆብ ደፍተው፣
ለአባይ ሲታዘዙ ትንሽ አይከብዳቸው፡፡

ገዳማት ተቃጥለው ባህታውያን ሲያልቁ፣
ፓትርያሪክ ተባይ አቡኑ ጳጳሱ፣
ተአቃጣዮች ጋራ ግብር ይበላሉ፡፡

እንዲናገር ቢያዝዝ ነፍስ እስተንፋስ ያለው፣
የደም የስደት ጎርፍ በዓይን ብረት አይተው፣
ጳጳሳት ጪጭ አሉ በቀፈት ታፍነው፡፡

አማሮች ተአሕዛብ ተአውሬ ሲፋለሙ፣
በአማራ አስራት መፅዋእት የሚንፈላሰሱ፣
እንጀራው አንቋቸው ጳጳሳት ጪጭ አሉ፡፡

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ህዳር ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

1 Comment

  1. ሁለቴ አይሞቱ ጳጳስ ሲሆኑ ሙተዋል ደፈር ብለው ፋሽዝምን ቢያወግዙ፤የልጆቻቸውን ግድያ ቢያወግዙ፤የቤተ ክርስቲያን ቃጠሎን ቢያወግዙ በእርግጥ የሃይማኖቱ የበላይ ጠባቂ ልባቸው ወደ ሌላ ቢሆንም ከስር ያሉት ጠንከር ብለው ሃይማኖቱን ቢያስከብሩልን።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ሃይማኖታችን የቅድሚያ ትኩረትና ርብርብ የሚባል ነገር አያውቅም እንዴ?

187083
Next Story

ዳናኤል ክብረት፦ የማህበረሰብ ስጋት የሆነው የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ| ABC TV ልዩ ዝግጅት

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop