በኢትዮጲያዊያን ላይ ሰቆቃ የሚፈጽመው የአብይ አህመድ ምንደኞች ይጋለጡ

የህዝባችን ሰቆቃ ሳይገዳቸው ለስልጣን ለዝና ለዩ ጥቅም ወይም በዘር ከወያኔ እስከ ኦነግ ብልጽግና የሚያሸረግዱ የሃይማኖት መሪ ሆኑ ምሁር ተብዬ ያለምንም ርህራሄ መጋለጥ ይገባቸዋል::

የምንወደው ዘ-ሐበሻ ይህን ሃገራዊ ተጋዳይነት የሚደነቅ ነው ይበል ያሰኛል  ወንድማችን  አልዩ ተበጀ ቀጥልበት:: በያልንበት ያሉት መምከር ካልተመለሱ ማግለል የምንችልባቸው ብዙ መድረኮች አሉ:: ከእነዚህ ህሊና ቢሶች አንዱ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም በተደረገው ጥረት ተገቢ ተግሳጽ ቀርቦለት በሚዋደቁት የፋኖ ወጣቶች ላይ ልቅ አፉን ስለቀጠለ በየሆቴሉ በየመናሀሪያው ፊት የሚነሱት የቁርጥ ቀን ልጆች ተነሰተዋል:: ወደፊትም መቃብሩ ላይ የሚቆም ቅን ኢትዮጲያዊ እስከማይጠፋ ድረስ ማጋለጡ ማራቁ ይቀጥላል:: የሃይማኖት መሪዎቹም ባለፈው ጉደኛይቱ አዳነች አበቤን ያሞካሹት ካህን ከእጃቸው ስጋወደኑ ያለመቀበል ድረስ መመናን በመትጋት ላይ ሲሆኑ የጰኔጠቆስጤው ፓስተር ጻድቁ አብዶ የወንጌላዊት ቄስ ደረጀ ቄስ  በያልነበት በተለይ የአሜሪካ ፓስተሮች ለምእመናንም በማሳወቅ ላይ ነን ልክልካቸውን ነግረናል:: የግፈኛው አብይ አፈቀላጤነቱን ካላቆሙ በሚቀጥለው ምርጫ ይነሱ ዘንድ ምእመናኑን በመቀስቀስ ላይ ነን::

የድንቅ ሃገር ወዳድ ሙፍቲህ ኢንድሪስን የተረከቡት ሃጂ ቱፋም በቀጥታ የተነገራቸው ሲሆን ቅን ሙስሊም ኢትዮጲያዊያን የመጅሊስ ጉባኤ ላይ በተለይ ወለዮቹ የሚያቀብሩብት ብዙ ብርቱ ጥያቄዎች መኖራቸውን ያለሁበት ግሩፕ Interfaith Coalition በማህበራዊ ሚዲያ እየተገረው ነው ቅን ሙስሊሞች ትናንት ድምጻችን ይሰማ በጋራ ያሰማን በርቱ:: አሜካኖቹና የአውሮፓ ህብረት የተፈጸመው ዘር ማጥፋት አብይን ከስልጣን የሚያስወግድ በመሆኑ አብይ ከወደቀ ሃገሪቱ ትፈርሳለች በጥገና ለውጥ ይካሄድ ያሉ የሚደራደሩ የሁሉም ፓልቲካና ማህባራት ተወካዮች ምቃውም ይኖርባቸዋል

የሰው መብት አስከባሪዎች ቆይታ ጉብኝት በዚሁ ስጋት የታገደውን ይህን በብርቱ ላቀረቡት የኣውሮፓ ህብረት በዚያ ያላች ሁ በተለይ ብራሰልስ ለሚታረደው ህዝባችን ሞግቱ:: የተገፋው የኢትዮጲያ ህዝብ በተለይ ያቸንፋል ጨቁዋኝ ፈሮንን ባህር ያሰመጠ ት እቢተኛው ናቡከደነጾርን ሳር ያስበላ ጌታ በግፈኞቹ የኦሮሙማ መሪዎች ላይ ይፈርዳል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  እዚህም አዚያም ጩኸቱ ተበራክቷል . ... ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ (ጋዜጠኛ)

ኢትዮጵያ በነጻነትና በአንድነት ለዘለዓለም ትኑር!!

ደጎን ሞረቴው

2 Comments

  1. ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው አቶ ዳንኤል ክብረትን ረስተውት ነው? አረጋዊ በርሄ፤ሌንጮዎችን፤ዲማ ነገዎን፤መራራ ጉዲና፤በየነ ጴጥሮስ የመሳሰሉትን ጨምረው ቢከኩልን፡፡

  2. ሰው አልማርያምን ይቀየማል? ጸጉሩን ሳየው ቀደም ሲል በአሜሪካ ፋኖነትን ለመጀመር ሳያስብ አልቀረም፡፡ እስቲ በዚህ እድሜ እንዲህ ብድግ ብሎ ጸጉርን ማጎፈር መብት ነው? ወይስ የጤንነት ወይስ የኢትዮጵያ አምላክ አቅጣጫውን አስቶት? ጸጉሮቹ ሳይሳሱ ቀደም ብሎ ቢሆን አንድ ነገር ነበር፡፡ እንደው ትምህርት ሲበዛ አናት ላይ ሳይወጣ አይቀርም የሚባለው እውነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ አያቴ ይቅርብህ ድቁና ተማር ያለችኝ አሁን ት ዝ አለኝ፡፡ ፕሮፌሰር ማሞ ሙጨም ጸጉራቸው እንደ ጥላ ሁኖ ሰው ባጠገባቸው ለመሄድ አንደ ሜትር ያስፈልገው ነበር፡፡ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለዚህ አልታደሉም እንጅ ሹሩባ ይሰሩት ነበር፡፡ ለሹሩባው ባይታደሉም ወጣትነትን በቋንቋቸውና በሸሚዛቸው ሊያሳዩ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ እነ ሎሬት ጸጋዬ አይነት የሃገር አድባር ወስዶ እነዚህን ይልቀቅብን? ዶር ብርሃኑ ባለፈው አሰብን ለማስመለስ በግልግል እንደቀሩ ሰማሁ እንዲህ አይነቱስ ድፍረት ሊመሰገን ይገባል ናፖሊዎን ነው ሁል ጊዜ አሳማ ሁኖ ከመኖር አንድ ቀን አምበሳ ሁኖ መሞት ይሻላል ያለው? እንደው ፈረንጅ ካልጠቀስን ያወቅን አይመስለንም እንጅ ፊታውራሪ ጎሹ ጥዋት ማታ የሚተርቱት ተረት ነበር ግን ማን ይጥቀስላቸው? አይ የኛ ነገር፡፡

    በር ወደ ኋላ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share