በደብረማርቆስ ከተማ ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው | የስልጣን እድሜአቸው አብቅቷል። ኢትዮጵያዊነት የሚያሸንፍበት ጊዜው ቅርብ ነው”

October 19, 2023

https://youtu.be/7_LRRBo7CtE?si=wqtswcr-3MvpPU0k

https://youtu.be/LdWo_9v0Gi4?si=xI8LbuphhZRLYWS5

 

2 Comments

  1. የኛ ነገር የሚያሳዝን ነው በምድረ አሜሪካ ታከለ ኡማ ያን ሁሉ ግፍ ሰርቶ ህዝብ አንድ ሁኖ ትንሽ ሳንቲም አዋጥቶ ሶስት ሰው ጉዳዩን ይዞ ፍርድ ቤት በገተረው ነበር ዛሬ በቂ መረጃ እጃችን ላይ ያለ እነ ስብሃት ነጋ፤ሰየ አብረሃ፤የጻድቃን ቤተ ሰቦች፤ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ኧረ ስንቱ ይጠቀሳል ደም ያፈሰሰ ትግሬ ሁሉ ከተጠቂው ጋር እየተጋፋ ማኪያቶ ይጠጣል በፋኖ ትግል ደረት ከምናሳብጥ በየሃጉሩ ያሉትን ነብሰ ገዳዮች ኮሚቴ አቋቋሞ ሰቅዞ መያዝ ያስፈልጋል፡፡ በውጭ አገር ነብሰ ገዳዮችን እጅ እየነሱ በሃገር ቤት አዛውንቱን አቶ ታዲዮስ ታንቱን እመጫትዋን መስከረም አበራን፤ፓርላማው ውስጥ አንድ የሚጮህልንን ክርስቲያን ታደለን አስበልቶ ወደ ሌላ መሄድ በጣም አሳዛኝና ብሄራዊ ኩራታችንን የሚያኮስስ ይሆናል፡፡ በውጭም ሆነ በውስጥም እንደአይታጠፌ እስክንድር ነጋ ካልተሆነ ሁሉም ነገር የአንድ ሰሞን ጫጫታ ይሆናል አብይም ለዚህ በሚገባ የተዘጋጀበት ይመስላል፡፡

  2. በአውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ምድር ላይ የሚርመሰመሱት በደርግ፤ በወያኔና ሻቢያ እልፍ ሰው ያስበሉና የበሉ ናቸው። የሚያስገርመው ለማያቋርጥ መከራ የዳረጉንና በሰው እንባ ያሾፉ የዘር ፓለቲከኞች ዛሬም በሰላም በውጭና በሃገር ውስጥ መኖራቸው ነው። በሃበሻዋ ምድር ፍትህ ኑሮ አያውቅም። አሁን እንሆ በፋኖና በድህነቱ መንግስት መካከል የሚደረገውም የመኖርና ያለመኖር ትንቅንቅ በሌላ ወሬ እየተተካ ትላንት ለእውነት ድምጽ የሆኑን ሰዎች ከአይንና ከጀሮ ተሰውረው እያለ አሁን ደግሞ የወደብ ጉዳይ ትኩስ ወሬ ሆኗል። ይህ ከቁራሽ በተረፈችው ሃገር ውስጥ ያለውን የፓለቲካ ግርግርና የኑሮ ውድነት አቅጣጫ ማስለወጫ እንጂ ኤርትራም ሆነች ኢትዮጵያ ለጦርነት የሚያበቃቸው ጉዳይ የለም። ትላንት እንካችሁ ብሎ ወያኔ ያስረከባቸውን ሃገርና ድንበር አሁን አምጡ ማለት እብደት እንጂ ብልሃት አይደለም። ግን ልብ ያለው ሰው የፓለቲካውን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ አሰላለፍ ሊያስተውል ይገባል። ዓረቡና ነጩ ዓለም እንድንገዳደል ያኔም አሁንም ይፈልጋሉ። ጋላቢው ሃይል እነርሱ ናቸው። ኤርትራ በቻይና በሩሲያና በሌሎችም ሃገሮች ይፋዊይና ይፋዊ ጉብኝት ያደረገችው የምግብ ዘይት ፍለጋ አይደለም። ባጭሩ ሻቢያም ታጥቋል። የድህነቱ መንግስትም አለኝ ይላል እንግዲህ ፈረንጆች እንደሚሉት dé·jà vu ነው። ይዋጣላቸው እንዳንል ያኔም አሁንም የሚሞተው የድሃ ልጅ ነው። ግን የአፍሪቃ መሪዎች ጦር ለመምዘዝ የሚቸኩሉትን ያህል ግማሽ ሃይላቸውን ለሰላም ቢያደርጉ ይህ ሁሉ መቀጣቀጥ ባልኖረም ነበር። ወያኔ ሃዘን ቀን ብሎ አውጆ የፓለቲካ ቅስቀሳ ቀን ሲያደርገው ላየ እነዚህ የፓለቲካ ውሾች ዛሬም ጦር መዛዥና ያዙኝ ልቀቁኝ ማለታቸው የቁም ሙቶች እንደሆኑ አመላካች ነው። ለነገሩ ወያኔና ሻቢያ ያለ ባሩድ ጢስ በሰላም ኑሮው አያውቅም። ሲገድሉ፤ ሲገደሉ ሲያፍኑና ሲታፈኑ ነው የኖሩት። ትርክታቸው ውሸት፤ ገድላቸው ከንቱ ነው። ግን እንደ ገደል ማሚቶ የተባለውን እያስተጋቡ በሃገርና በውጭ ያሉ ጭፍን ደጋፊዎቻቸው ብለውና በላት እንጂ ለምን ብሎ የሚጠይቅ የለም። እጅግ የሚዘገንን ጊዜ ላይ እንገኛለን።
    ግን ከላይ ሃሳብ ሰጭው እንዳለው ድምጽ የሆኑን ሲታሰሩ፤ ሲገደሉ፤ ሲሰወሩ እነርሱን እየዘነጋን ወደፊት መጓዝ አንችልም። በሚቻለው ሁሉ ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ መሆን የዛሬ ቋሚን ግድ ይላል። የ 70 ዓመት አዛውንትን እስር ቤት ወርውሮ የኢትዮጵያ ልዕልና ገለ መሌ ቢሉት ፍሬ ቢስ ነው። መታወቂያው እየታየ ወደ አዲስ አበባ አትገቡም የሚሉን የጊዜው የኦሮሞ አለቆች አብሾ እንደጠጣ ሰው አብደዋል። አንዴ እሬቻን ቀይ ባህር እናከብራለን ሲሉን በሌላ በኩል ጠ/ሚሩ የቆየ ታሪክን እያላተመ ካድሬዎቹን ያነቃቃል። ግን እኮ ይህን ሸፋፋ የፓለቲካ አካሄድ በፊትም አይተነዋል። ፍጻሜው የሮም አወዳደቅ ነው። ለዚህና ለዚያም ነው የሃበሻ ፓለቲካ የመገዳደል ፓለቲካ ነው የምንለው። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

391607191 10158405958714649 1343776512103938949 n
Previous Story

የአብይ አሕመድ ኦነግ/ኦሕዴድ ወራሪ አረመኔ በምሥራቅ ሸዋ በረኽት ወረዳ በድሮን ከ20 በላይ ንጽሐን ዐማራ ገበሬዎችን አስጨፍጭፏል

Next Story

አደንዛዥ እጾችና የሚያሳብዱ ሱሶች!

Go toTop