ሃገራዊ ፖለቲካና የብሄር ፖለቲካ፣ የዛሬ 31 አመት በ“አማራ ህዝብ ከየት ወዴት” መጽሃፍ ውስጥ – አንዳርጋቸው ፅጌ

ከዚህ በታች በምስሉ የምታዩት ጽሁፍ የተወሰደው የዛሬ 31 አመት ከጻፍኩት “የአማራ ህዝብ ከየት ወዴት” የሚል ርእስ ከሰጠኋት ትንሽዬ መጽሃፍ ነው።

አሁን ባለንበት ወቅት የአማራ ህዝብ የሚያደርገውን ትግል በጥርጣሬ የሚመለከቱ አሁንም በኢትዮጵያ ውስጥ ትግሉ ህብረ ብሄራዊ መሆን አለበት የሚሉ ሰዎች እያየሁ ነው። ወደ ብሄር ፖለቲካ መውረድ መውጫ ወደ ሌለው አዘቅት መግባት ነው የሚል ክርክር እያቀረቡም ነው። ከዛም አልፎ የኢትዮጵያ ህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች የወደቁት በአመራራ ችግር ስለሆነ እኛ የተሻለ አመራራ የምንሰጠው ሃገራዊ ፓርቲ እናቋቁማለን እያሉ ነው። እንዲህ አይነቶቹን ፓርቲዎች ወይም ድርጅቶች ለማቆም እንቅስቃሴ የጀመሩም አሉ። እኔ በግሌ እንኳን ሶስት የተለያዩ አካላት እንዳሉ አውቃለሁ።

በጣም የሚገርመው ይህ “የአማራ ድርጅት ወይም ሃገራዊ ድርጅት የማቆምና ያለማቆም” ጥያቄ ልክ እንደዛሬው የዛሬ 31 አመት ተነስቶ ነበር። ይህን በተመለከተ ከላይ በጠቀስኳት ትንሽ መጣጥፌ ያስፈርኩት ጽሁፍ ለዛሬው መዋዛገቢያ ለሆነ ጉዳይ የራሱን መልስ ሰጥቶ ነበር።

እንደገና እየተነሳ ያለውን አጀንዳ ከስሜት፣ ከስድብና መጯጯህ ውጭ ከፍ ያደርገዋል ብዬ ስላሰብኩ በቁምነገሩ ላይ ለማሰላሰል የሚፈልግ ሁሉ እንዲያነበው እዚህ ላይ አውጥቼዋለሁ።

ያች ትንሽ መጣጣፍ የተጻፈችበት ዘመን ገና ከተማሪው ንቅናቄ የተሳሳተ የጨቋኝ ብሄር ገዥ መደብና የተጨቋኝ ህዝብ የፖለቲካ ትርክት ያልተላቀቅሁበት ዘመን በመሆኑ በርካታ ስህተቶችን አስተናግዳለች። እድሜ፣ ልምዴና እውቀቴ እየጨመረ ሲሄድ ስህተቶችን ማረም ችያለሁ። ሰከን ካልኩ በኋላ በጻፍኩት “ነጻነትን የማያውቅ ነጻ አውጭ” በሚለው መጽሃፌ ላይ እነዚህን ስህተቶች በሚገባ አርሜያለሁ።

ከዚህ ውጭ አንድ ሰው እውነታን በሚገባ እንዳያይ፣ ስሜት፣ ገንዘብና ስልጣን ካልጋረደው እንዴት በቀላሉ መጪውን ዘመን ማየት እንደሚችል ይች ትንሽ መጽሃፍ የራሷን ትምህርት ትሰጣለች።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እረ በመድሃኔ ኣለም ይብቃዎት ኢንጂነር ግዛቸው! 

እኔ ያችን መጻሃፍ የጻፍኩት የወያኔንና የኦነግ ጥምረት በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ የነበረውን ስቃይ በቅረበት በማየቴ ነበር። ወያኔ ስልጣን በያዘ ማግስት፣ በበደኖ፣ በአርባጉጉ፣ በአርሲና በሌሎች ቦታዎችም በአማራው ላይ ከባድ ጭፍጨፋ ተካሂዷል። ወያኔ በአማራ ህዝብ መሬት ላይ ለማለፍ ሲል ደብቆት የነበረው የአማራ ህዝብ ጥላቻና ፍራቻ ስልጣን ከያዘ በኋላ ሃገራዊ ፖለቲካው የሚመራበት ፍልስፍና አደረገው። ይችን መጽሃፍ የጻፍኩት መጪው ዘመን ለአማራ የከፋ ይሆናል ብዬ በማሰቤ ነበር።

ሆኖም ግን ይች መጽሃፋ ትልቅ ተቃውሞ የገጠማት ከአማራና ከጉራጌ ልሂቆች ነበር። ተቃውሞውም “አማራውን የወያኔ የዘር አመለካከት ከረጢት ውስጥ ልትከተው ነው” የሚል ነበር። በመጽሃፌ ለዚህ ጉዳይ መልስ የሰጠሁ ቢሆንም የሚሰማኝ አልተገኘም። መልሱ ከዚህ በታች በምስሉ የምታዩት ነበር። በጊዜ ተሰባስበን ቢሆን ኖሮ የአማራም፣ የኢትዮጵያም የመከራ እድሜው ያጥር ነበር።

አላስፈጊ ከሆነ ብዙ መስዋእትነት በኋላ የአማራ ህዝብ ነቅቷል። የዛሬው ምልከታዬ ላልነቁት ጥቂት አማሮችና የአማራ ህዝብ ለህልውናው መከበር የሚያደረገውን ትግል ለመደገፍ ለተቸገሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውን ነው።

6 Comments

  1. የአማራ ምሁራን ትልቅ ስህተት ዶክተር አስራትን ያለመከተላቸው ነበር::ያኔ መደራጀትና አንድነት ቢኖር ኖሮ ይህ ሁሉ ወገን ዛሬ አይጨፈጨፍም ነበር:: ዛሬም አልመሸም:: የፋኖን ትግል በመደገፍ አማራን ነፃ ከማውጣት ውጪ አማራጭ አይኖርም::አትግደለኝ አታፈናቅለኝ የሚል የህዝብ ሀይል አሸናፊ ነው

  2. ይችን ፖርቱጋል የሠራትን ግምብ ያለህፍረት የራስህ አስመስለህ ትለጥፋታለህ፤ ትንሽ አታፍርም?

  3. እናንተ ቅጠል ጎዝጉዛችሁ ስተኙ እኛ ከፖርቹጋል ግንበኛ አስመጥተን ማሰራትም እኮ ቁምነገር ነው።

  4. Zemede/Andy ተው እንጅ ተከባበሩ እንደ እንቁራሪት ፈንድተህ ትሞታለህ እንጅ ኢትዮጵያውያን የደረሱበት እደርሳለሁ ብለህ አታስብ። ዘር ማንዘርህ አሁንም ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን አትርሳ ኢትይጵያ ከሌለች ከፓለስታይን የከፋ እጣ ይደርስሃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share