ቀይ ባህር አዲሱ ቁማር! – ላይነህ አባተ

October 15, 2023

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

yt76778tu7yugj 1 1

በመላእክትነት ተመርጦ የነበረው ሳጥናኤል እግዚአብሔርን ከድቶና ክርስቶስን ወደ ተራራ ወስዶ ከተማ እያሳዬ በንብረት ሊደልለው ሞከረ፡፡ የሳጥናኤል ተከታዮች ደግሞ ከዓለም በፊት እግዚአብሔርን እያመለከ የኖረውን አማራ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኢትዮጵያ ሱሴ ወዘተርፈ በሚሉ የቁማር ካርታዎች ሲያታልሉ ኖሩ፡፡  አማራ ክርስቶስን ስላለሆነ  ተታለለ፡፡

በቁማር መጫዋቻ ካርታ መደለሉ የሰለቸው አማራ ራሱን ለማዳን እንደ ቅድመ አያቶቹ ቆርጦ ሲፋለም  ደሞ እንደተለመደው ቀይ ባህር የሚል የቁማር ካርታ ይዘው ብቅ አሉ፡፡

ሳጥናኤል አዙሮ የሚያይበት አንገትና ይሉኝታ እንደሌለው ሁሉ ተከታዮዎቹ ጭራቆችም ትናንት የሰሩትን ዞር ብለው የሚያዩበት አንገት፣ እንደ አቡጀዲ የሸረከኩትን ውሽት የሚያፍሩበት ህሊናና ይሉኝታ የሳጥናኤል ያህል እንኳ የላቸውም፡፡

አማራ የኢትዮጵያ ግዛት ከራስ ካሳ እስከ ሞያሌ፤ የባህረ ነጋሽ ሰዎችም ወንድምና እህቶታችችን ናቸው ሲል እነዚህ የሳጥናኤል ተከታዮች ኢትዮጵያ የባህረ ነጋሽ ቅኝ ገዥ፣ ሰዎቹም የተለዩ ስለሆኑ ይገንጠሉ ብለው ያሳደገቻቸውን ኢትዮጵያን ከአርባ አምስት  ዓመታት በላይ ወጉ፣ ሕዝቡን በድድ አናከሱ፡፡ አማራ ሕዝባችንን አትከፋፍሉ አገሪቱንም ወደብ አልባ አታድርጉ ሲል በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ልጆቻቸውን በከንቱ በማስጨርገድ ወደብ አልባ አድርገውና ከዓለም በፊትም ኢትዮጵያ ወደብ አልባ እንድትሆን ድምጥ ሰጥተው የሚያሳፍር ወራዳ ሥራ በታሪክ ማህደር ጣፉ፡፡ ትንሽ ቆይተው በዘረፉት የኢትዮጵያ እንጀራ ሲጣሉ ደሞ የባህረ ነጋሽን ሰዎች በላንባ ዲና እየፈለጉ በወረንጦ ነቅለውና ንብረታቸውን ገፈው አባረሩ፡፡ በለማተቡ አማራ በአደራ ንብረታቸውን የጠበቀላቸው የባህረ ነጋሽ ሰዎች በኋላ ንብረታቸውን ተረከቡ፡፡

ቁማርተኛ ጭራቆች ዛሬም እንደ ወትሮው አዙሮ የሚያዩበት አንገትና ሊያፍሩ የሚችሉበት ህሊና ወይም ይሉኝታ ስለሌላቸው ቀይ ባህር የምትል ማታለያ ቁማር ይዘው ብቅ አሉ፡፡ ዳሩ ዛሬም በዚህ የሳጥናኤል ተከታዮች  ቁማር እንደገና ተጠልፎ የሚወደቅ  የእንግዴህ ልጅ የሆነ የአማራ ምሁር  ያጣሉ አይባልም፡፡ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኢትዮጵያ ሱሴ በሚሉ ይሁዳዊ ሰባኪያን የተንዘላዘሉና የተከንከረፈፉ ጁላጅል ምሁራን በወደብ ስብከትም እንደ ገለባ ተጠርገው የአማራን ሕዝብ ማሳሳቱን አይቀጥሉም አይባልም፡፡

የወቅቱ የአማራ ጥያቄ ቀይ ባህር፣ ወደብ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ልማት፣ ጅኒጃንካ የሚል ድስኩር ሳይሆን የህልውናና የአገሩ ባለቤትነትን የማረጋጋጥ  ጥያቄ ብቻ ነው፡፡ አማራ ጊዜውን፣ እውቀቱን፣ ንብረቱንም ሆነ መንፈሱን ማዋል ያለበት ለራሱ ህልውና ብቻ ነው፡፡ አማራ እንደ ማርያም ጠላት በሚዋከብበት በዚህ ክፉ ዘመን የራሱ ልጅ እየተራበ ሌላውን አጎርሳለሁ የሚል፣ የራሱ እያረረበት የሌላውን የሚያማስል የእንግዴህ ልጅ ነው፡፡ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ኢትዮጵያ ሱሴ እያሉ የአማራ ምሁራንን ሲያጃጅሉ የኖሩት ቁማርተኞች ዛሬ ደሞ ቀይ ባህርና ወደብ የሚባል የካርታ ጨዋታ የጀመሩት አንድም እንደዚህ ዓይነቱን የእንግዴህ ልጅ ሙልጭ አድርገው ቁማር ለመብላትና የአማራን ዘር የማጥፋቱን ሴራ ለማጧጧፍ ሁለትም በምዕራባውያን ጌቶቻቸው ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው  ነው፡፡

ዓባይን ማን መቼ ይገድበው? http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2014/06/Abay.pdf

ፈንድ ፈንዳጅ ዲያስጶራ እባክህ ስማ! ለዘራፊዎች የማይነጥፍ ጥገት መሆንህ ይብቃ!   – https://amharic.zehabesha.com/wp-content/uploads/2022/08/%E1%89%A6%E1%8A%95%%E1%8B%B3%E1%8C%85.pdf

ጥቅምት ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

1 Comment

  1. ይህ የቀይ ባህር ፓለቲካ የጊዜው የድብ ድብ የቁማር ጫወታ ነው። ድሮ ያኔ ገና ሻቢያና ወያኔ የከተማ ሰዎች ሳይሆኑ ስንት ተብሎ ነበር። የተባለው ሁሉ ግን የልጆች ጫወታ ሆኖ ፈራርሶ በስፍራው ሁለቱ አማጽያን ሃገር ገዢ ከሆኑ በህዋላ የሆነው የነበረው እልቂትና የፓለቲካ ጠረባ በከፋ መልኩ በዘርና ከዚያ ወገን ጋር ነበርክ በሚል የብቀላ በትር ተተክቶ ዛሬ ላንበት የድንበር ገተር የብልጽግና ፓለቲካ ደርሰናል። የሃገሬ ሰዎች ያልሞተ ሰው የሚሉት እንዲህ ያለውን የአፓርታይድ የፓለቲካ ሸፍጥ በማየት አታድርስ ምነው ቀደም ብለህ ወስደኸኝ በሆነ ብለው እንባ ያፈሳሉ በምሬት። ያልሞተ ሰው ይገናኛል መባሉ ቀርቶ ዛሬ ምነው ሞቴ ቀደም ባለ ይህን ሁሉ ሳላይ የሚሉ እልፍ ናቸው።
    ሰው አውሬ ከሆነ ቆይቷል። የአሁኑ የሰው ባህሪ ግን አውሬን ያስንቃል። አንድ በመከራ ከአፋር ወደ ጅቡቲ ከጅቡቲ ወደ የመን የተሻገረ ወገን ሲናገር – የመን ከደረስን በህዋላ የደረሰብኝ ድብደባና ቅሚያ ሁሉ የተፈጸመው በሃበሻ ነው ይለናል። እንዴት ሲባል እናንተ ናችሁ ትግራይን መከራ ውስጥ የከተታችሁት ከአማራ ጋር ሁናችሁ በማለት አማራና አፋሮችን አልፎ ተርፎም ኦሮሞዎችን እየለዪ ቀደም ብለው የተሻገሩት የትግራይ ተወላጆች ከየመኖች ጋር በመመሳጠር ያሰቃዪን ነበር በማለት ከምሬት ጋር እንዴት ብሎ ወደ ኢትዪጵያ መመለስ እንደሚችል በመጠየቅ እንባውን ያፈሳል። ክፋታችን ተንኮላችን መራኮታችን መገዳደላችን ምቀኝነታችን ድንበር ተሻጋሪና ዘርና ቋንቋ ተኮር በመሆኑ ለተሻለ ግብና ዓላማ ራስን አዘጋጅቶ ሰርቶ ለመኖር አልተቻለም። ሁሌ እንቅፋት ፈጣሪዎችና ያልሆነውን ሆነ በማለት ነገር ቆስቋሾችና አራጋቢዎች እንደሆንን መከራን ዘርተን በመከራ ውስጥ እኛም እናቀላፋለን። አንድ ቀልደኛ ዝም በል እባክህ ሰው የዘራውን ያጭዳል ቢሉት እንዴ እሱም እኮ ከበቀለ ነው እንዳለው ነው። ፌዝና ቁምነገር ቧልትና ተረቱ ሁሉ አደንዛዥና ውዥንብር ፈጣሪ ነው።
    ስለ ቀይ ባህር ጉዳይ መከራከር፤ ጥያቄ ማንሳት፤ ለምን እና እንዴት ብሎ መጠየቅ የሃገሪቱ የፓለቲካ አቀማመጥና ወደብ አልባ መሆን የሚፈጥረው ጉዳይ እንጂ ጦርነት ማስጀመሪያ ጥሪ አይደለም። ግራም ነፈሰ ቀኝ እውነት በጠፋበት ዓለም የተባለውን በማጋነን፤ ወይም የራስን የፈጠራ ታሪክ በመለጠፍ ሰውና ሃገር ማጋጨት በፊትም ያለ ዛሬም የሚኖር የፓለቲካ ሸር ነው። ኤርትራም ሆነች ከቁራሽ ተራፊዋ የሃበሻ ምድር ጦርነት ሳይሆን አብሮ መኖር፤ መረዳዳት ነው የሚያስፈልጋቸው። ረሃብ፤ ሞት፤ መሰደድ መቼ ነው የሚቆመው? እንዲቆምስ ምን ማድረግ አለብን ብሎ ራስን ለሰዎች መብትና ሰላም እንደማሰለፍ የጋማና የቀንድ ከብት ይመስል በየወገኑ እየተሰለፉ የምጽዓት ከበሮ መምታት ሰውነት ሳይሆን እንስሳነት ነው። ስለ ቀይ ባህርና ወደብ ጥያቄ አንስቶ መፋለም በምድረክ ላይ ጦርነት ቀስቃሽ አይደለም። በግጭትና በጉልበት ወደብ አገኛለሁ ማለት ግን የቁም ቅዥት ነው። እዚያም እሳት እንዳለ ማወቅ ግድ ይላል። ስለሆነም ገዥዎች ሁልጊዜ ራሳቸውን በስልጣን ላይ ለማቆየት የሚጠቀሙበት ዘዴ ለሃገርህ ለድንበርህ ለሃይማኖትህ ወዘተ በማለት ሰውን ከህዋላ እየገፉ እሳት ውስጥ በመማገድ እንደሆነ ታሪክ ፍንትው አርጎ ያሳየናል። በኤርትራም ሆነ በሃበሻዋ ምድር በዚህ የሂሳብ ስሌት ውስጥ ራሱን አሰልፎ የሚሞት ጅል እንጂ ጀግና አይደለም። ማን እየሞተ ማን ይኖራል? የአንዲት ሃገር ነጻነትስ የሚለካው በምን ይሆን? በስመ ነጻነት ባርነትን ያመጡ ስንት ሃገሮች አሉ? የቀይ ባህሩ የአሁን የፓለቲካ ጥያቄ ሽርፍራፊ ሳንቲም በዪቱቭና በሌላውም መድረክ ለሚለቅሙ የሩቅ ደም አፍሳሾችና የፓለቲካ ተቆራቋሾች ይጠቅም እንጂ ሌላ ትርፍ የለውም። ቁማርተኞች የበሉትን እንጂ የተበሉትን አይናገሩም። እልፍ አስገብሮ ድርብ እልፍ አገኘሁ ይላል። አይጣል ነው የሃበሻ ፓለቲካ – የውሻ ፓለቲካ ዝንተ ዓለም መነካከስ። ያልፍለት ይሆን? አይመስለኝም። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

455563 1 1
Previous Story

ኤርትራና ሲንጋፖር – አብራሃም ለቤዛ

387181783 4479238222301554 7255492896229777268 n
Next Story

የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በኢትዮጵያ [በትግራይ] ተሰማ…!!

Go toTop