October 15, 2023
5 mins read

ኤርትራና ሲንጋፖር – አብራሃም ለቤዛ

455563 1 1ኤርትራ ከሲንጋፖር ጋር ለመተረክ የፈለግኩት ከሰሞኑን የኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ተቀማጭ አማባሳደር ከሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስተር  Mr. Yap Ong Heng ጋር ተገናኙና ተወያዩ የሚል ዜና ነው፡፡  ነገር ነገር ያነሳዎል እንዲሉ ለመተረክ የፈለግኩት ስለሁቱ አገሮች ግንኙነት ሳይሆን የምስራቅ አፍሪካ ሲንጋፖር እንሆናለን ይል ስለነበረው የኤርትራዊያን ቅዠት ነው፡፡

የኤርትራ መንግስት ከኢትዮጵ ለመገንጠል በሚያደርገው ጥድፈት ዋዜማ ኤርትራን የምስራቅ አፍሪካ ሲንጋፖር እናደርጋታል ይል ነበር፡፡  የየደቡብ ምስራቅ ኤሺያ አገሮች በአጭር ጊዜ ከድህነት ስለወጡ ለብዙ የአፍሪካ አገሮች መቅኛ ነበሩ፡፡  ፈጣን እድገትና ልማት ግን ትክክለኛ  የፖሊሲ አቅጣጫ በመያዝ የሚመጣ እንጂ በማለም ብቻ የሚሆን አይደለም፡፡  የኤርትራዊን የምስራቅ አፍሪካ ሲንጋፖር የመሆን ምኞት የመጣው ራሳቸውን ከሌላው ሀባሻ የኢትዮጵ ህዝብ እንዲሁም ከትግሬ ወንድሞቻቸው ለይተው ማየታቸው ነው፡፡ የ60 ዓመት የጣሊያን ቅኝ ገዢ ፖሊሲ በኤርትራዊያን ላይ ይኸ አስተሳሰብ እንዲጫን አድረጎል፡፡ ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ “Ethiopia and Eritrea- The Federal Experience”  በሚለው ጥናታዊ ፅሁፋቸው ኤርትራዊያን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ዳግም የሄዱበት መንገድ እኛ የተለየን ነን ፤ ከሃበሻ እኛ የሰለጠንን ነን፤ እኛ ከተገነጠልን በፍጥነት እንበለፅጋለን የሚለው አስተሳሰብ ስለሰረፀባቸው ነው ይላል፡፡

የሆነው ግን ኤርትራ የአፍሪካ ሲንጋፖር ሳይሆን የአፍሪካ ሰሜን ኮርያ ሆነ፡፡ የሃበሻ ምቀኝነት እንዲሉ ለዚህ ደግሞ የወያኔ ኢተዮጵያ ኤርትራን በማሳጣት ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጋለች፡፡

የደቡብ ምስራቅ ኤሽ አገሮች ሲንጋፖር ፤ ማሌዥያ፤ ቬትናም፡ታይላድ ፤ኢንዶኔዢያና ፊሊፒንስ ሲሆኑ ፤ በአጭር ጊዜ ከድህነት በመውጣታቸው ምክንያትም የኤሽያ ታይገር የሚል የዳቦ ስም ወጥቶላቸዋል፡፡  የወያኔዎ ኢትዮጵያ ልማታዊ መንግስትን በመከተል የደቡብ ምስራቅ ኤሽ አገሮች መንገድ እከተላለሁ ብትልም፤  ነገር ግን የኢትዮጵያ ፖሊሲ በጎሳ ፖለቲካ ፤ የጋራ መግባባት የሌለው ፖለቲካ ሃይል እና በሙስና የተጨማለቀ ፖለቲካ ሃይል የተተበተ ስለሆነ የደቡብ ምስራቅ ኤሽያ አገሮችን ፈለግ መከተል አልቻለችም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለራሷ የአፍሪካ ላይዮን የሚል የዳቦ ስም አውጥታለች፡፡ ለከታታይ 14 ዓመት (2005-2019)  በሁለት ዲጂት ያደገ ኢኮኖሚ ባለቤት የሚል የተለመደ የወያኔዎች የአፍ ማሞሻ ጥቅስ ነበር፡፡

ፅንፈኛው ጃ-War  መሃመድ   የኦሮሞ ፖለቲከኛም በሲንጋፖር ኢኮኖሚ እምርታ እንደሚማክና ሲጋፖር እየተማረ እናዳጠናዉም በተደጋጋሚ ይገልፃል፡፡ ችግሩ የሲንጋፖርና የደቡብ ምስራቅ ኤሽያ አገሮች ሲንጋፖር አገሮች መመንደግ ሳይሆን እነሱ የሄዱበትን  እኛ እንዳንሄድበት  ራሳችንን አድርገናል፡፡ የእኛ መንገድ ማለት በህገመንግስታችንም ሆነ በኢኮኖሚ ፖሊሲያችን ኢትዮጵያዊነት በዜጋነት እንዲደራጁ አንፈቅድም፡፡  የብሄር ፖለቲካ ይዘን እንደ ዝንጀሮ መንጋ ባለች ሃብት (ክምር) ላይ ሰፍረን መበዝበዝ እንጂ ምርታማነትና ዕድገትን አናመጣም፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop