በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱ እንዳሳሰበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽ ገለፀ

ኮሚሽኑ ዛሬ ከጀኔቫ ባወጣው መግለጫ በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክልሎች ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት መባባሱ በጣም ያሳስበናል ብሏል። በአማራ ክልል በኢትዮጵያ ወታደሮች እና በክልሉ ፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት እና በጎርጎሪያኑ ነሃሴ 4 ቀን የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ ሁኔታው በእጅጉ መባባሱን ኮሚሽኑ አመልክቷል። ከሀምሌ ወር ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 183 ሰዎች ሞተዋል ሲልም፤ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ቢሮ ቀደም ሲል ያወጣውን መረጃ ጠቅሷል።

እንደ ኮሚሽኑ፤ ባለሥልጣናቱ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር እንዲያውሉ፣ የሰዓት እላፊ ገደብ እንዲጥሉ እና ሕዝባዊ ስብሰባዎችን እንዲከለክሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰፊ ሥልጣን ሰጥቷቸዋል።

በዚህ ህግ 1,000 በላይ ሰዎች ከመላው ኢትዮጵያ መታሰራቸውን ዘገባዎች ደርሰውናል ያለው ኮሚሽኑ ፤ ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ የፋኖ ደጋፊዎች ተብለው የተጠረጠሩ የአማራ ብሄር ተወላጅ ወጣቶች መሆናቸውን አመልክቷል። እንደ መግለጫው ከነሃሴ ወር መጀመሪያ ጀምሮ በጅምላ ከቤት ወደ ቤት ፍተሻ እየተካሄደ ሲሆን የአማራ ክልልን ሁኔታ ሲዘግቡ ቢያንስ ሶስት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ታስረዋል። እስረኞቹ ምቾት በሌላቸው የእስር ማቆያ ማዕከላት ውስጥ እንዲቀመጡ መደረጋቸውንም ገልጿል።

ባለሥልጣናቱ የጅምላ እስራት እንዲያቆሙ፣ ማንኛውም ነፃነት መነፈግ በፍርድ ቤት እንዲታይ እና በዘፈቀደ የታሰሩትን እንዲፈቱ እንጠይቃለን ያለው መግለጫው፤ የእስር ሁኔታዎች ዓለም አቀፍ ደንቦችን እና ደረጃዎችን የሚያከብሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለባቸውም ብሏል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጽህፈት ቤት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ – ሁሉንም የእስር ቦታዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቆጣጣሪ አካላት እንዲፈቅዱ ጠይቋል። የታራሚዎች ደህንነት ፣ፍትሃዊ የፍርድ ሂደት እና ዋስትናን ጨምሮ ሰብዓዊ መብቶቻቸው ሙሉ በሙሉ ሊጠበቁ ይገባልም ብሏል ኮሚሽኑ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከሁለቱም ወገን በጦርነቱ ሰበብ ለሞቱት ከ600 ሺ በላይ ዜጎች አካላቸው ለጎደለ ተጠያቂው ማነው? - ሴና ዘ ሙሴ

መግለጫው አይይዞም ፌደራል ሃይሎች በተወሰኑ ከተሞች መኖራቸውን እና የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ገጠራማ አካባቢዎች እያፈገፈጉ መሆኑን በመግለጽ፤ ሁሉም ተዋናዮች ግድያ፣ሌሎች መብት ጥሰቶች እና ጥቃቶችን እንዲያቆሙ እና ቅሬታዎች በውይይት እና በፖለቲካ ሂደት እንዲፈቱ ጠይቋል።

በሌላ በኩል በአጨቃጫቂው የምዕራብ ትግራይ አካባቢም ከ250 የማያንሱ የትግራይ ተወላጆች በአማራ ፖሊስ፣ በአካባቢው ባለስልጣናት እና በአካባቢው ታጣቂዎች መታሰራቸውን ክስ ሰምተናል።ያለው መግለጫው ፤ ታሳሪዎቹ በትግራይ ጊዜያዊ ክልል አስተዳደር ወደ ሚተዳደሩ አካባቢዎች በወልቃይት ታጣቂዎች መወሰዳቸውንና ከዚያም በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በማጣራት ተደርጎ ታሳሪዎቹ ወደ ምዕራብ ትግራይ እንዲመለሱ ወይም በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አካባቢ እንዲቆዩ ምርጫ እንደተሰጣቸው በመግለጫው አመልክቷል።

የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ወንጀሎች እየቀጠለ ባለበት በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታም አሳሳቢ መሆኑን ተመልክቷል።

ስለሆነም በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና ጥሰቶች በፍጥነት፣በገለልተኛነት እና ብቃት ባለው ሁኔታ ተጣርተው አጥፊዎች በህግ መጠየቅ እንዳለባቸው ኮሚሽኑ አሳስቧል።

DW

1 Comment

 1. The same and terribly boring and toothless barking – very abused diplomatic words of “we are deeply concerned “ !
  Yes, it is a a very good for nothing diplomatic business or game to just complain and blame both sides ( the killer and the victim)!

  Needless to say, as it is absolutely true that as matter of reality that issue external factors are determined by the very principled way of doing things, goal oriented vision , sound planning, well- led action, unbreakable organization, and of course wise and dedicated leadership of the internal actors , not the other way round !

  We Ethiopians have failed repeatedly and shamefully in getting our country the country of true democratic system. Sadly enough, we expect from external actors of international politics to be the determinant factors of our own fate!

  So, let’s give the first focus on how to put our home in order by kicking out those deadly ruling elites of ethnic – politics , and make our dreams for the emergence and development of a truly democratic system!
  Anything less than this is painfully stupid political thought and behavior !!!

  I am not saying that world politics has nothing to do with our National fate and interest . Not at all! What I am saying is feeling good with reports of the above kind and feeling disappointed with any other unfair reports without doing our own home work which is a determinant factor is terribly wrong and must be taken seriously !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share