ኢትዮጵያን ያለ ኢትዮያዉያን ማሰብ እንዴት ይሆናል ?

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን ከዓማራ ህዝብ ነጥሎ በማሳየት በትዉልድ መካከል የክህደት  ሳንካ መፍጠር እና ታሪክ ማወናከር ከደደቢት በረኃ የሚመዘዝ የጥላቻ ዘመቻ አካል ነዉ ፡፡

በአገራችን ኢትዮጵያ የቀደመ ክብር ፣ ምግባር እና ተግባር ከታሪክ ጋር ለማጥፋት ኢትዮጵያዊነት ጠላትነት ሆኖ እንደ ወንጀል ተወስዶ በዉስጥ እና በዉጭ ጠላት በተለይም ለሶስት አስርተ ዓመታት ከፍተኛ መድሎ በህዝብ ላይ ተፈፅሟል፡፡

ለዚህም ላለፉት ግማሽ ክ/ዘመን ኢትዮጵያን ብለዉ ኢትዮጵያዊነትን ማተብ ያጠለቁ ሁሉ ማንነታቸዉ ፣ ዕምነታቸዉ እና አመለካከታቸዉ እየጠፈረጀ ዓማራ፣ ትምክህተኛ፣ ትናንትን ናፋቂ እና አድናቂ፣ ለአገር እና ለህዝብ ያደረጉት መልካም ተግባር እንደወንጀል የሚቆጠር የሌላ ዓለም ፍጡር ሆነዉ መሳደዳቸዉ፣ መዋረዳቸዉ፣ መሞታቸዉ፣ መቸገራቸዉ እና በአገራቸዉ መፃተኛ መባላቸዉ ሳይወዱ በግድ ከመሞት መሰንበት በማለት ዓሜን ብለዉ ተቀብለዉ የረጂም ጊዜ መከራ ቀንበር መሸከም ግድ ሆኒባቸዋል ፡፡

በዚህ ላይ ብዙ ማለት የሚቻል ነገር ግን በዉስጥም ሆነ በዉጭ ይህ ሁሉ መከራ እና ስቃይ እንዲቀበል የሆነ ኢትዮጵያዊ የዓማራ ህዝብ በራሱ አገር የመኖር ተፈጥሯዊ ከብሩን እና መብቱን እንዲያጣ ከመሆኑ በላይ ሲሞት እንኳ አሞሟቱም ሆነ ሞቱ ሠባዊነት ባለዉ ሁኔታ እንዲገለፅ  ሆኖ አያዉቅም ፡፡

በአንድ ወቅት በቀድሞዉ ደቡብ ኢትዮጵያ በአሁኑ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በጋምቤላ ክልል አዋሳኝ በተለይም 2006 / 2007 ዓ.ም. በተቀነባበረ እና አስቀድሞ በታሰበ ሁኔታ በአካባቢዉ ኗሪ ኢትዮጵያዉያንን በተለይም ስመ ዓማራ ላይ ከፍተኛ ዕልቂት እና መፈናቀል ተካሂዷል ፡፡

በዚህ ጊዜ አንድ የቴፒ ከተማ ኗሪ ወንድሜ ምንድን ነዉ እየሆነ ያለዉ ብየ ስጠይቀዉ እና ለምን ሠዉ ይሞታል ስለዉ  …….አይ ዓማራ ነዉ አለኝ ፡፡

ይህ ወንድሜ ያለዉ ከክፋት እንዳልሆነ ይልቁንስ ካለማወቅ እና በመላ ኢትዮጵያ አይደለም በዓለም ዕየተለመደ ያለ ኢትዮጵያዊ ዓማራነት ቁርኝት እና ዉህደት ለማጥፋት የተሰጠ መጠሪያ መሆኑን ባለመገንዘብ ነዉ ፡፡ አንባቢም በዚህ ልክ እንዲረዳኝ አስባለሁ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ የማን ናት? - ከአንተነህ መርዕድ

ወንድሜ ያለዉ የሚሞተዉ ዓማራ ነዉ እንዲሞትም ስለተፈለገ ነዉ ከየት መጣ ያልተባለ ጦርነት የተከፈተበት ማለቱ ነበር ፡፡ ልክ ነዉ ዉጡ ስለመባሉም እና ያን ባለተቀበሉት እና አቅመ ደካሞች ላይ ሞት ማወጂ የብሄር እንጂ የሠዉ ሞት አይደለም ፡፡

ዓለም በኢትዮጵያ ላይ ስለ ሠባዊ መብት እና የሠዉ ልጆች ሠባዊ ቀዉስ ትርጓሜ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት -ዓማራነት ላይ ሲደርስ የብሄር እንጂ የሠዉ ሞትም ሆነ ሠባዊ መብት ጥሰት አለ ብሎ በተግባር ቀርቶ በቃል ያለዉ ካለ እርሱን ላለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት ማንም ያየ የለም ፡፡

ዓለም ቀርቶ ያአገር ዉስጥ የማህበረሰብ እና ሠባዊ ደህንነት እና መብት ተቆርቋሪ እና ተባባሪ ነን የሚሉት አካላት ስለ ምጣኔ ቀዉስ እና ከመዉቀስ ባለፈ ያደረጉት ያሉት ቢኖር ተመጣጣኝ ቢሆን ከማለት ያለፈ የለም ፡፡ ተመጣጣኝ ስንት እንደሆነ በቀመር ተሰልቶ እንደ ተቀመጠ ሁሉ ዞትር አንድ ሀረግ መምዘዝ በአገር እና በወገን ቁስል ከመታከም እና ከማዝገም ሊለይ አይችልም ፡፡

ኢትዮጵያዊንም ሆነ ዓማራነት በማንም ምኞት እና ፍላጎት የተገኙ ሳይሆን በደም እና በአጥንት የጠመሰረቱ የህይወት ዋጋ የተገኙ እና ከአገር አልፈዉ በዓለም የሚታወቁ ሆኖ ሳለ በአገራቸዉ መገለላቸዉ ለዕዉነት እና ማንነት እንዲስቡ እና አንዲሰባሰቡ ምክነያት ሆኗል  ፡፡

ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝብ የሰዉ ልጆች መነሻ እና መዳረሻ ስትሆን ኢትዮጵያዊነት ዓማራነት ከአፍሪካ አልፎ በዓለም መጠሪያ ሆኖ የሚገኘዉ በኢትዮጵያዊነት ተስፋፊነት ሳይሆን ዓለማቀፋዊ ዕዉነትነት ያለዉ በመሆኑ ነዉ ፡፡

እንግዲህ ኢትዮጵያዊነትን ዓማራነት ፤ የዓማራን ሞት ከሠባዊነት ወደ ብሄር ፣ ዓማራ የሚለዉን  “አምሀራ “, የኢትዮጵያዉያንን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ሠንደቅ ዓለማ  የዓማራ፣ የኢትዮጵያዉን እንጀራ የዓማራ…..በማለት ኢትዮጵያን እና ዓማራን ነጣጥሎ ለማሳየት እና ጠላትነት ማድረግ መፈረጂ እና መገለል ያስከተለዉ በደል ዓማራ ራስን ማዳን ኢትዮጵያን መታደግ መሆኑን ከመከራ ዘመናት እንደማር ሆኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወቅታዊ መልዕክት ለለውጥ ኃይሉ  (ሰው ዘ ናዝሬት)

አማራ ብሎ ከኢትዮጵያዊነት መነጠል እና ከኢትዮጵያ ከፍታ ማዉረድ ወይም ብሄርተኛ ብሎ ነገር ማጉላላት የማይሆን እና የማይቻል ነዉ ፡፡ ሁለቱም ኢትዮጵያ እና ዓማራ ስያሜም ሆነ ፤ ሁነታቸዉ ፈልገዉ ሳይሆን በተፈጥሮ ያገኙት ነዉ እና ማንኛዉም ህያዉ ፍጡር በግማሽ ነብስ መኖር እንደማይቻለዉ ሁለቱም አይነጣጠሉም ፤ አይከፋፈሉም ፤አንዱ ያለ ሌላዉ መሰብ ብቻ ከምንም በላይ ሠዉ ካለመሆን ብልጠት የተሞላበት ከንቱ ምኞት የሚመነጭ ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያም ሆነ ኢትዮጵያዊነት እና ዓማራነት ዓለም ሲኖር የነበር ማንነት መሆኑን ብዙ መጥቀስ ለታሪክ እና ለዓለም ትተን ዓማራ ማለት በላቲን ምንጊዜም (አልፋ እና ኦሜጋ)፤ግርማ ሞገስ ፣ዘላለማዊ……ሲሆን በአፍሪካ የወንድ ልጂ መጠሪያ መሆኑን ሲታወቅ በአገራችንም “አማረ  ” የሚል ስያሜ ከ“አበበ   ” ባላነሰ ይጠራል ፡፡ እዚህ ላይ አማራ በአማርኛ እንዲህ ነዉ እንዲያ ነዉ አልልም ….. ይህም ለታሪክ እና ስነፅሁፍ ሊቃዉንት መተዉ ይመረጣል፡፡

ዓማራ በቦታ ስያሜ ካልን በኢራቅ ጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የሚገኝ ወደብ  ዓማራ ይባላል ፡፡

ከዚህም በላይ ጥንታዊ እና አርቆ አስተዋይ አያት ቅድመ አያቶቻችን ሩቅ ምስራቅ ድረስ ሄደዉ እየሩሳሌም ይዞታ “ዴር ሱልጣንን ” ገዳም ይዘዉ ገድመዉ ይዘዉልን ለእኛ አስረክበዋል ፡፡

አዚህ ላይ ነዉ ዓማራ ወይም ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደ ሆነ እና ግማዱ ዉስብስብ እና ረቂቅ መሆኑን የሚሳየን ፡፡ በቆዳ ስፋት ከስራኤል ያነሰ ፤ በሁሉም ረገድ ከስራኤል የተሸለ ህዝብ በዓለም ላይ የለም ግን አስራኤል ዉጡ ፤ልቀቁልኝ ብላ ታዉቃለች ….?

ርግጥ ነዉ አረቦች በተለይም ግብፅ ዉስጥ እንደምታደርገዉ ከዴር ሱልጣንም ለማፈናቀል በተለይም ከዘመነ ኢህዴግ ጀምሮ ተዘናግታ አታዉቅም ፡፡ ከዚህ ሌላ በዓለም የተለያዩ አገራት ዓማራ በሚል መጠሪያ ያላቸዉ ግዛቶች ፣ቦታወች ፣ ድርጂቶች….ብዙ አሉ እና እነዚህ ሁላ የኢትዮጵያን የቀደመ ዕዉነት እና ማንነት በሚጠሉት የዉጭ ታሪካዊ ጠላቶች ፊታዉራሪነት፤አስተባባሪነት  እና በዉስጥ ኢትዮጵያ-ጠል ተባባሪነት የስያሜ ለዉጥ እንዲደረግ ለምን አልተደረገም…….?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ልብ የሚነካ ግጥም፡ 'የህጻኑ ጥሪ' መታሰቢያነቱ ለ እስክንድርና በግፍ ለታሰሩ ወላጆች (በድምጽ)

ከላይ እንደ ተጠቀሰዉ  ሠዉ እየሞተ ብሄር ነዉ ፤ ዐማራ ሳይሆን አምሀራ ፣ ኢትዮጵያ ሳይሆን …..እኛ እና እኛ ብቻ….ብሎ ከማደናገር እና ታሪክ ከማወናከር በላይ ምን አይነት ከኢትዮጵያዊነት ሠገነት መገልበጥ ሳይሆን መፈጥፈጥ እንደሆነ መረዳት አለብን ፡፡

ኢትዮጵያዉያን ከረፈደም ቢሆን አገር ማለት እኛ ነን ብለዉ በህይወት የመኖር የነፃነት እና የህልዉና ጥያቄ ሲያነሱ ብሄርተኝነት እና ከኢትዮጵያ ማማ እና ከፍታ መዉረድ መሆኑን ለሚያስተጋቡ ይብላኝላቸዉ እንጂ ከአገር እና ከስም በፊት ቃል እና ሠዉ ነበር ፡፡

ለሠዉ ልጂ ድህነት እና ህይወት ሲል መድኃኒት ዓለም ዕየሱስ ክርስቶስ ዓምላክ ሆኖ ሳለ ሠዉ የሆነዉ ዓለምን ለማዳን እንጂ ስም ለመቀየር አይደለም ፡፡

እኛ ኢትዮጵያዉያን ዕዉነትን መሸሽ ብንለምድም ከዕዉነት ማምለጥ ግን አንድንም ዓለም ሠባ አገራት በነበሩበት ጊዜ ሆነ ከዚያ በፊት ሠዉ ስለነበር ቃል ሠዉ ሆኖ የሠዉን ባህሪ ተላብሶ ዓምላክ የሠዉን ልጂ የኃጢያት ቀንበር በመስበር ከባርነት ነፃ እንዲወጣ የተሰደበበት፣ የተዋረደበት፣ የተሰደደበት እና የሞተለት የሰዉ ልጂ ነዉ ፡፡

ዓለም ከሰዉ ልጂ በኋላ ስሟን ማግኘቷ በምሳሌ ሲታይ ከአስራኤል በፊት ዐይሁድ ነበሩ ፤ ከደች/ሆላንድ አስቀድሞ ደቾች ነበሩ ፣ ከአቢስንያም በፊት አበሾች ነበሩ እና ሠዎች ወይም ዜጎች በሌሉበት የምትኖር ዓለም ሆነ አገር የለችም ፡፡

እናም ስለ ኢትዮጵያ ስንናገር ስለ ኢትዮጵያዉያን መከራ እና ስቃይ እንዳላየ ማለፍ ከሆነ ስለ አገር እና ሠዉ ሳይሆን ስለ ግል ጥቅም መኖር ወይም ነዉር ለመሰወር መጨነቅ ነዉ ፡፡

“አንድነት ኃይል ነዉ !”

 

Allen!

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share