August 4, 2023
4 mins read

ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን ብቻ ናት !

Ethiopia unite 2 1

ለዓመታት ኢትዮጵያ ለዜጎቿ የመከራ እና የስቃይ የደም መሬት ሆና መባጀቷ ያለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት በጥቁር ታሪክነቱ የሚዘከር መሆኑን የደረሰበት እና የሚያዉቅ ያዉቀዋል ፡፡

ያልተነካ ግልግል  ሲያዉቅ የጠገበም የተራበ ስለመኖሩ አያወቅም እና እንዲሁ በቁስል ላይ እንጨት መሰግሰግ መቆም አለበት ፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ ዕምብርት የግዛት  አካል በሆኑት ጎንደር ፣ጎጃም ፣ ወሎ እና ሸዋ ላይ እየሆነ ያለዉ የዓመታት የግፍ እና ሰቆቃ ዕባጭ የጥላቻ እና የምቀኝነት ሰንኮፍ ዉጤት ነዉ ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ አስኳል አንድ አካል የሆነዉ የኣማራ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ፣ በማንነቱ እና በልዑላዊነቱ የማይደራደር ሆኖ ሳለ በነበሩት የዘመናት ጭቆና እና መድሎ ለምን ያለ አንድም ተቋም ፣ድርጂት እና አካል አልነበረም አሁንም የለም ፡፡

ይህም ያሳሰባቸዉ ቅን የቁርጥ ቀን የችግር ጊዜ ደራሾች ኢትዮጵያዉያን በሰከነ እና ሠላማዊ መንገድ ለምን በማለታቸዉ የህይወት መስዋዕት ለህዝብ እና ለአገር ሲሉ ከፍለዋል ፡፡ ዕድለኛ የሆኑት በህይወት ከመሞት መሰንበት ብለዉ ስደትን መርጠዉ ሌሎችም  በአገራቸዉ ስለ አገራቸዉ መወገናቸዉ ዕስር ቤቴ ሆነዋል ፡፡

ዕዉነት ለፍትህ እና ለዕኩልነት መናገር እና መቆም አሁን ለደረስንበት ሁኔታ የሚያበቃን ነበር ወይ ፡፡ ህዝብ እና አገር ከስርዓት እና ከአደር ባይነት ወገንተኝነት በላይ መሆናቸዉን ተረስቶ ለስርዓት እና ለአድር ባዮች ሲባል ህዝብና አገር እንዲህ ያለ መሪር ዋጋ ለዘመናት መክፈል ነበረባቸዉ ፤አለባቸዉ ወይ የሚል አንድ ከመቶ ሚሊዮን ጠፋ ብሎ የሚጠይቅ አለመኖሩ የሚያስተዛዝብ ነዉ ፡፡

ዛሬ የዓማራ ህዝብ የሚያሰማዉ ዕሮሮ የዘመናት የጭቆና  እና አድሏዊ  ብሶት እንጂ ድንገት አለመሆኑን አለመረዳት ያለዉን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረት የሚያወሳስብ መሆኑን መገንዘብ ነብይነት አይጠይቅም ፡፡

የህዝብን እና የአገርን ችግር ከስሩ ተርድቶ በሆደ ሠፊነት እና በአስተዋይነት ለመፍታት ስህተትን መረዳት እና ይቅር ባይነትን መቀበል ይጠይቃል፡፡

የዓማራ ህዝብ ስለ ብሄራዊ አንድነት ፣ ሠላም  እና አብሮነት የሚያስተምረዉ ሳይሆን እየኖረ የሚያሳየዉ ሲጠይቅ ዘመናት ተቆጥረዋል ፡፡ ዛሬ ላይ ከሁላችን የሚጠበቀዉ ከኋላ ታሪካችን እና ስህተታችን ተምረን ከምንም ከማንም በላይ ህዝብ እና አገር ትክክል ናቸዉ በማለት ታሪካዊ እና ወቅታዊ ግዴታችንን መወጣት ብቻ ነዉ ፡፡

ከዚህ ዉጭ ለቡድን እና ለስርዓት ጥቅም እና ከንቱ ዉዳሴ አገር እና ህዝብ እንዲማቅቁ እና አንዲጨነቁ ማድረግ በበደል ላይ በደል መጨመር ይሆናል ፡፡ ለኢትዮጵያዉን የማትሆን አገር ለማንም ልትሆን አትችልም ፤አይፈቀደም ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !

Allen!

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop