በጎንደር ከተማ ለጥቃት የገባው የአገዛዙ ኃይል የአጸፋ ምላሽን መቋቋም ሲያቅተው የህዝብ መገልገያ ተቋማትን እንደ ምሽግ እየተጠቀመ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ!

August 3, 2023

በጎንደር ከተማ ለጥቃት የገባው የአገዛዙ ኃይል የአጸፋ ምላሽን መቋቋም ሲያቅተው የህዝብ መገልገያ ተቋማትን እንደ ምሽግ እየተጠቀመ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ!

ፋኖዎቹ ሀብቴ ወልዴ፣ ሰለሞን አጠናው፣ ውባንተ አባተና ተሾመ አበባው የቴዎድሮስ ብርጌድ፣ የገብርዬ እና የዘርአይ ሻለቃ መሪዎች በወቅታዊ ጉዳይ ያስተላለፉት!

ፋኖዎቹ ሀብቴ ወልዴ፣ ሰለሞን አጠናው፣ ውባንተ አባተና ተሾመ አበባው የቴዎድሮስ ብርጌድ፣ የገብርዬ እና የዘርአይ ሻለቃ መሪዎች በወቅታዊ ጉዳይ ያስተላለፉት!

1 Comment

  1. ሃገር እናቆማለን እያሉ ሃገር ማፍረስ ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን ያኔም አንድ ሰውና አንድ ጥይት እስኪቀር እንፋለማለን ተብሎ ነበር። የሆነውን ግን ሌላ ነው። በወያኔ የ 27 ዓመት አገዛዝና በ 3 ጊዜ ተደጋጋሚ ወረራ የፈራረሰው ገና ሳይጠገን ሌላ እሰጣ ገባና ጦርነት በአማራም ሆነ በሌሎች ክልሎች መለኮስ የራስን ቤት እሳት ለኩሶ ለእሳት አደጋ መከላከያ ድረሱልኝ እንደማለት ነው። ከተማ ያዙ፤ እከሌን ገደሉ፤ እከሌ ከፋኖ ጋር ተቀላቀለ ገለ መሌ መባሉ ሁሉ የልጆች ጫወታ ነው። ሲጀመር የሃበሻ የፓለቲካ ግሩፕ አንድ ሆኖ በሃሳብ ተስማምቶ የዘለቀበት ጊዜ በታሪክ የለም። እየተከፈለ፤ እየተሰነጠቀ፤ እያፈነገጠ ስምና ይዘቱን በመቀየር ወይ ይከስማል አለዛም ፍሬ አልባ ሆኖ ይቀራል እንጂ። የዛሬውን የሃገር ገመና በብሄር ጥያቄ ሰበብ ጣራ ላይ ያወጡት ሻቢያ፤ ወያኔ፤ ኦነግ፤ ኢህአፓ ወዘተ ሁሉ ከዚህ ግባ የሚባል ነገር ለቆሙለት ዓላማና ሃገር አላደረጉም። የነጻነት ትርጉሙ ባንዲራ ማውለብለብ ከሆነ ሁሉ በየደጃፉ የክልልና የብሄሩን ብሎም የሃገር ባንዲራ በራፉቸው ላይ ሆነው ያውለበልቡታል። የህዝብ የመናገር፤ የመጻፍ፤ የመሰብሰብ መብት ግን ዛሬም የለም። 12 ዓመት ሙሉ ተቸግረው፤ ለፍተው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለመግባት ፈተና ላይ የተቀመጡ ተማሪዎች ሁሉ ከፈተናው ገበታ ላይ በዚህ ግብግብ ምክንያት ፈተናው እንዲቆም ተደርጓል። የሞተው የፈረሰው፤ መንገድ በመዘጋቱ ረሃብና ጠነው መክፋቱን እነዚህ ጠበንጃ አንጋችና ሃገር አተራማሽ ሃይሎች አይነግሩንም። የሚነግሩን ከተማ ያዝን፤ እከሌን እነዚያን ከእስር አስፈታን ነው። ሲጀመር ጦርነት የፓለቲካ መፍትሄ ሆኖ አያውቅም። መነጋገር እንጂ! በምንም አይነት የሂሳብ ስሌት የህዝባችን መከራ ለማራዘም ካልሆነ በስተቀር ፋኖ ከሰለጠነ ሰራዊት ጋር ተዋግቶ ለውጥ ያስገኛል ብዬ አላምንም። ይህ በውጭና በሃገር ውስጥ አማራ ጠል ሃይሎች የአማራን ህዝብ የበለጠ ለማዳከም የሚደረግ ታላቅ ሴራ ነው። በዚህ ጦርነት የደስታ ታንቡር የሚመቱት ወያኔና ኦነግ በሰውር አንድ ሃይል በመሆን አማራን ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቀራመት ዝግጅት ላይ ናቸው። በዚህ ላይ የውጭ ሃይሎች እሳት እያቀበሉ ግጭቱ እንዳያባራ የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ማሰብ አስቸጋሪ አይሆንም። ባጭሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እንዳይኖር ይጥሩ የነበሩ የታሪክ ጠላቶቻችን ዛሬም ቢሆን አላረፉም። ዋ ወንዝ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው እንደሚባለው ዝም ብሎ ተራራ ላይ ቆሞ እየፎከሩ መታኮስና እልህ መጋባት በህዋላ ሃገር አልባ አድርጎ ልክ እንደ ሶሪያ፤ ሶማሊያ፤ የመንና ሌሎች ሃገሮች ሃገር አልባ እንዳንሆን እፈራለሁ።
    በማጠቃለያው ፋኖም ሆነ ሌሎች ታጣቂ ሃይሎች በሃበሻ ምድር የሚርመሰመሱ ሁሉ ቆም ብለው ማሰብ ያለባቸው ተኩሰው መግደላቸውን ሳይሆን ከሟች ጀርባ ያሉትን ዘመዶች፤ ቤተሰብና ልጆች ነው። መገዳደል የሚጎዳው ሟችን ብቻ ሳይሆን ከጀርባው ያሉትን ዘመድና አዝማድ ጭምር ነው። ስለሆነም ግጭቱን በማቆም የፓለትካ ጥያቄዎችን በማቅረብ ነገሮች በቶሎ ካረገቡ መተላለቁ ለማንም አይጠቅምም። በኢንተርኔት የሚነዛው ግማሽ እውነትና የፈጠራ ወሬም የሚጎዳው ህዝባችን እንጂ ለሽርፍራፊ ሳንቲም የሚሰሩትን የወሬ ቱልቱላዎች አይደለም። ጦርነት ይቁም!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

75 80
Previous Story

ሰበር ዜና #ጎንደር #ጎጃም #ወሎ #ሸዋ 75%-80%ቱ ከብልፅግና አገዛዝ ነፃ ወጥተዋል ፋኖ ድልን ተቀዳጅቷል

Ethiopia unite 2 1
Next Story

ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን ብቻ ናት !

Go toTop