ከማይቀር ታሪካዊ ስህተት እና ክህደት ራሳችን እና አገራችን እንታደግ !

ኢትዮጵያን የምንል ኢትዮጵያዊ የሆን ሁሉ ማወቅ ያለብን ስለመሆኑ ከአሁን ጊዜ በላይ የተሻለ ዕድል ሊኖር አይችልም ፡፡

ይህ ዕድል ደግሞ ለኢትዮጵጵያን ብቻ ሳይሆን ከዚህ በተቃራኒ ላሉት ፤ለሚገኙት ፀረ.-ኢትዮጵያ መልክ እና ቅርፅ  ይዘዉ የነበሩት እና ያሉት ሁሉ ሊያስቡበት ይገባል ፡፡

ባአሁኑ ስዓት ሶስቱን የኢትዮጵያዊነት ምልክቶች ኢትዮጵያ፣ኢትዮጵያዊነትን፣ ዓማራ እና የዓማራ ህዝብ ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነት አርማ እና መለያ  ፋኖ ለያይቶ መመልከት  ታሪክን ወደ ኋላ አለማወቅ ወይም መካድ ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያ እንደ አገር ከምትታወቅበት ህዝቡም እንደ ህዝብ ከኖረበት ጀምሮ ካለፉት ሶስት ሽ ዓመታት ጀምሮ የማይነጣጠሉ መሆናቸዉን ከማያዉቀዉ ይልቅ የሚያዉቀዉ ብዙ መሆኑ እየታወቀ  ሆኖ ዕዉነቱን አለመናገር መፍትሄ ሊያስገኝ አይችልም፡፡

ነገር ግን ለአገር እና ለህዝብ የሚበጀዉ እና ዘላቂ መፍትሄ የሚመጣዉ  ዕዉነትን እና ታሪክን መረዳት እና አገርን እና ህዝብን ለማዳን እና ለመታደግ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ሠፊዉን የዓማራን ህዝብ ለይቶ ለማሳየት መሞከር  ታሪክ ማወናወከር ብቻ ሳይሆን ታሪክን ተሳስቶ ማሳሳት እና ክህደት መሆኑን መረዳት አለብን፡፡

ለግል እና ለቡድን ጥቅም እና ስም ሲባል  በተለያየ ሰበብ አስባብ ህዝብን በራሱ አገር የመኖር ተፈጥሯዊ  መብት በማሳጣት ይባስ ብሎ አርሶ አደሩ ጥማድ እንዲፈታ ፣ሞፈሩን እንዲሰቅል በማድረግ እና ህዝብን እና ትዉልድን በመለያየት የሚደረግ የክፋት እና የግል ፍላጎት ኮተት መቆም አለበት ፡፡

ኢትዮጵያም እና ኢትዮጵያዊነት ከማንኛዉም የስርዓት እና የፖለቲካ አመለካከት በፊት የነበሩ እና ወደፊትም የሚኖሩ ታሪክ እና ትዉልድ በቅብብሎሽ የሚቀጥል ነዉ ፡፡

እናም ዛሬ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያ እና ዓለም ሁሉ ሊያዉቁት እና ሊረዱት የሚገባዉ ኢትዮጵያ ፣ኢትዮጵያዊነት እና ዓማራን ለይቶ ለማሳያት ለሚፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያ ማለት ህዝብ መሆኑን ሊያስተምሩ ይገባል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የእኛ “መንግስት” - ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ  ህዝብን ፣ አገርን እና ራስን  እና ተፈጥሯዊ  መብት  ለመከላከል በሚደረግ የህልዉና ጥያቄ  እና ትግል በሰከነ ሁኔታ መረዳት እና መግባባት እንጂ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ለማንም የሚረባ አይሆንም ፡፡

ኢትዮጵያዊነትን መጥላት እና የኢትዮጵያን ህዝብ ችግር መግፋት እና ማጥላላት  ጥላቻን መዝራት እና ማስፋፋት ከመሆን ባሻገር ለሁላችን በሚሆን ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጦ የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህመም እና የመከራ ቀንበር ጫና መረዳት ያስፈልጋል፡፡

የህዝብን ብሶት ማጥላላት እና ማለባበስ አገር እና ህዝቦች አንድነት የሚፈይድ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ጠላቶች ሳይቀሩ የሚያዉቁትን ዕዉነታ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ሊረዱት ይገባል ፡፡

ሁላችንም የሰዉ ልጆች ፣ኢትዮጵያዉያን እና የዓለም ህዝቦች ከታሪካዊ ስህተት እና ክህደት ፀፀት ግርፋት ለመዳን የኋላ ታሪካን እና ዕዉነት መመርምር ያስፈልጋል፡፡እናም ሁላችንም ከማይቀር የታሪክ ስህተት እና ክህደት ለመዳን ከዕዉነት እና ትዉልድ እንዳንጣላ ከመሳሳት እና ክህደት እንታቀብ ፡፡

“አንድነት ኃይል ነዉ” !

 

Allen

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share