የዩቲዩብ አፈና፤ ያማራ ሕዝብ አሸናፊነት ብሥራት

August 2, 2023

Fano 3 1 1 1“በመጀመርያ ይንቁሃል፣ ቀጥለው ይዘልፉሃል፣ ከዚያም ይፋለሙሃል፣ በመጨረሻ ትረታቸዋለህ::”

“First they ignore you, then they ridicule you, then  they fight you, then you win”

 ማህተማ ጋንዲ (Mahatma Gandhi)

 

ወያኔና ኦነግ አማራን አከርካሪውን ሰብረነዋል እያሉ ይታበዩ ስለነበረ ሽንታም ምናምን እያሉ ይንቁት ነበር።  የናቁት አማራ ማንገራገር ሲጀምር ደግሞ ነፍጠኛ ምናምን እያሉ ያሸማቅቁት ጀመር።  ከማንገራገር ወደ መወራወር ሲሻገር ደግሞ ድምጹን ሲሰሙት ብቻ መርበድበድ ጀመሩና ለማፈን ይሯሯጡ ጀመር።  ከዚህ በኋላ የሚቀራቸው ደግሞ ኮለኔል ፈንታሁን ሙሐባ እንዳለው በፋኖ እምሽክ እየተደረጉ የሽንፈት ጽዋቸውን መጎንጨት ብቻ ነው፣ ምንም እንኳን ጨርሰው እስኪመሽኩ ድረስ ከፍተኛ መስዋእትነት ቢያስከፍሉም።

የጠላትህን ድምጽ በመፍራት ያፈንክ ወይም ለማፈን የሞከርክ ቀን፣ በጠላትህ የመሸነፍህን አይቀሬነት ለጠላትህ ታብሥራለህ፣ ለወዳጆችህ ደግሞ ታረዳለህ።  ወያኔና ኦነግ እያደረጉ ያሉትም ይሄንኑ ነው።

ወያኔና ኦነግ ያማራን ድምጽ ለማፈን የሚሞከሩት አማራዊ ዩቲዩቦችን (YouTube) በመዝጋት መሆኑ ደግሞ የዩቲዩብን ምንነት ባጠቃላይ ደግሞ ያሜሪቃን መንግሥት ምንነት ላማራ ሕዝብ ቁልጭ አድርጎ በማሳየት ላማራ ሕዝብ ትልቅ ትምሕርት አስተምሮታል።  ካሁን በኋላ ያሜሪቃ መንግሥት ባጠቃላይ ደግሞ ምዕራባውያን ስለ አንደበት ነጻነት (free speech)፣ ዲሞክራሲ (democracy) እና ሰብዓዊ መብት (Human right) የሚያወሩትን ተረት ተረት እውነት ብሎ የሚቀበል አማራ ካለ፣ እሱ አላዋቂ ሳይሆን ጥሬ መሐይም ነው።

ያሜሪቃ መንግሥት ስለ ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ቀን ከሌት የሚያላዝነው፣ የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት አፍቃሪ ሁኖ ሳይሆን፣ ብሔራዊ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ፍቱን መሣርያወች ሁነው ስላገኛቸው ብቻ ነው።  ፍቱን መሣርያወች የሆኑለት ደግሞ በግዙፍ ሚዲያወቹ (CNN, BBC ወዘተ.) እና በሆሊወድ (Hollywood) አማካኝነት የፕሮፓጋንዳ የበላይነትን ስለጨበጠ፣ ትርክቶችን (narration) ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመቆጣጠር የማይፈልገውን ሰይጣን አስብሎ የሚፈልገውን መልዓክ በማስባል በመደዴው ሕዝብ እንዲመረጥ የማድረግ አቅሙ ከፍተኛ ስለሆነ ነው።

ያሜሪቃ ዲሞክራሲ በዘረኝነት (racism)፣ በጀሪማንደሪንግ (gerrymandering) እና በመሳሰሉት የተጨመላለቀ፣ ውስጡ ለቄስ የሆነ ዲሞክራሲ ነው።  የዲሞክራሲው አብዛኛው ክፍል ደግሞ እጅግም ረብ የሌለው፣ በእንቶ ፈንቶወች ላይ የሚያተኩር ቢከፍቱት ተልባ የሆነ የይስሙላ ዲሞክራሲ ነው። ስለዚህም፣ ያሜሪቃ መንግሥት ዲሞክራቲክ ነው ቢባል፣ ዲሞክራቲክነቱ ላሜሪቃ ሕዝብ ብቻ ነው፣ ለዚያውም ደግሞ እንደሚጋነነው ሳይሆን በተወሰነ ደረጃ ብቻ።

ካሜሪካ ውጭ ግን ካሜሪቃ መንግሥት የበለጠ የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጠላት ባለማችን ላይ አይገኝም።  ለምሳሌ ያህል ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት አፍሪቃ ውስጥ ሥር ሊሰዱ ያልቻሉበት ዋናው ምክኒያት፣ ሥር ከሰደዱ አፍሪቃ ላፍሪቃውያን (African for Africans) ሁና ያሜሪቃ ጥቅም ስለሚቀርና፣ ይህ እንዳይሆን ደግሞ ያሜሪቃ መንግሥት የሱ ቡችሎች የሆኑ አምባገነኖችን ባፍሪቃውያን ላይ በቀጥታና በተዛዋሪ ስለሚጭን ነው።

በወያኔ ዘመን መለስ ዜናዊ ያሜሪቃ ቡችላ እንደነበረ ሁሉ፣ በኦነግ ዘመን ደግሞ ጭራቅ አሕመድ ያሜሪቃ ቡችላ ነው።  ስለዚህም፣ አሜሪቃ የቡችላዋን የጭራቅ አሕመድን እድሜ በተቻላት መጠን ለማስረዘም የምትችለውን ያህል ትጣጣራለች።  የዩቲዩቡ አፈናም የዚሁ ጥረት አካል ነው።

ሳሞዛ ውሻ ቢሆንም፣ የኛ ውሻ ነው፡፡”

“Somoza may be a son of a bitch, but he’s our son of a bitch”

President F. D. Roosevelt (about the brutal dictator of Nicaragua)

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

አበበ ፈለቀ በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት

አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች

January 29, 2025
Go toTop