ፍሬ አልባ ደረቅ ዛፍ ላይ ድንጋይ ማባከን ለምን ?

#image_title

ዕንግዳ ተቀባዮች እንደነበርን መረሳቱስ ፡፡ ዛሬ ላይ ይህ ዕንግዳ ተቀባይነት ታሪክ ቢሆንም በአዴን ላይ መኖሩ የሚደንቅ ባይሆንም የሚጠበቅ ነዉ ፡፡

አሁን ደግሞ የትህነግ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ባ/ር መገኘት እና መነጋገር ለምን እንደ ድንቅ እና ብርቅ መናፈሱ የሚገባ አይደለም የምን መደናነቅ ነዉ ፡፡

በልቶ ዝም የሚል ጌታዉን የሚክድ ሎሌ አይኖርም እና በአዴን መቀሌ የብዙዎች ኢትዮጵያዉያን እና አማራ  ደም እና መቃብር ረግጦ መቀሌ ተገኝቷል፡፡

የሆነዉ ግመል ሰርቆ አጎንብሶ መሄድ የለም እና  ጌታዉን የሚያገለግል ህዝብን የሚገለገል በባርነት የተያዘ ምንዱባን ላይ መፍረድ የደረቀ ዛፍ ፍሬ አልባ ዛፍ ላይ ድንጋይ ማባከን ለበጎ አይደለም፡፡

ይህ ኢትዮጵያን በማዉድም እና አችና በማክሰም  ኢትዮጵያን በማድማት ትግራይን ማልማት ለሰላሳ ዓመታት መሰራቱ እና ይህም በበአዲን ጉዳይ አስፈፃሚነት መሰራቱን እንዴት ተዘንግቶ ነዉ ብሎ መጠየቅ እና ታሪክን ወደ ኋላ ማወቅ እንዴት ይዘነጋል ፡፡

በአዲን በምናብ የሚያስተዳድረዉ የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ (ሠም-ኢትዮጵያ) ከነሰያሜዉ ሳይቀር ዓማራ ክልል ብሎ የተሰጠዉን እንደወረደ ያለምንም ቀቅድመ ጥያቄ ፈራ ተባ ሳይል ዓማራ እያለ የዓማራን እና የኢትዮጵያን ሙሉ ጥቅም እና ታሪካዊ ዳራ አሳልፎ ለመስጠጥት ቀደምት ተባባሪ መሆኑን ዓለም ሲያዉቀዉ የጎንደርን እና የወሎን ግዛቶች አሳልፎ ለመስጠጥ መጠራጠር  ሰዉ አለመሆን ነዉ ፡፡

ይህ በኢትዮጵያ እና ህዝቦች ኪሳራ በተለይም በዓማራ ህዝብ ነፃነት እና ህልዉና በተከፈለ ዋጋ ለትህነግ /ኢህአዴግ አሳልፎ መስጠት የበአዴን መገለጫ ነዉ ፡፡

ከኢህአዴግ መስረታ (1982) ጀምሮ በኢትዮጵያዉያን ደም እና ህይወት በተከፈለ ሁለንተናዊ መስዋዕት ወርቅ በጨርቅ የመለወጥ ፣ በክልሉ ከወረዳ አስከ ክልል ርዕሰ መስዳደር በቀጥታም ሆነ በሌላ ሁኔታ የሰሜን ምዕራብ ግዛቶች በኢትዮጵያዉያን ዓማራዎች አመራር ስር ሆነዉ ያዉቃሉ ወይ ፡፡ ለመሆኑ ኢህአዴግ ወይም ብአዴን ህልዉናዉን በአስራ ዘተኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ካጣ በኋላ በነቢብ እጂ በሀሳብ እና በተግባር አለ ወይ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ‹‹የኦሮሙማን ጠቅላይ ጦር ሠፈር አውድም!!! የሜ/ጀኔራሎቹ የደም መሬት! Bombard the Orommuma Headquarter!››

ማነዉ ኢትዮያን ለትህነግ የግል ንብረት አሳልፎ የሰጠ ፣ ማነዉ የኢትዮጵያ ህዝባዊ ብሄራዊ ጦር (ምድር፣ሰማይ ፣ባህር..) እንዲከስም ፣ የዓማራዉ ህዝብ ሶስተኛ ዜጋ እንዲሆን ….ያደረገዉ ብሎ መጠየቅ እና ማወቅ ዛሬ ሳይሆን ከሀያ ዓመት በፊት መታወቅ የመበረበት ነዉ ፡፡

ኢህአዴግ እያለ  ብአዴን ምን የተለየ ሚና ይጠበቅበታል ፡፡ ዕዉነት ብአዴን ለአቅመ  ራስን መቻል የበቃ እና በቦታዉ ቢኖር የቀደመዉን ትተን የዛሬዉን እንይ  ትህነግ አገር ወሮ ፣ አገር ገድሎ ፣ ህዝብ በድሎ …..ከነሙሉ ጥቅሙ እና ስሙ የክልሉን መከለሳከያ (የትግራይ መከላከያ) በአባልነት ያለበት ፣ የወረራዉ ፊዉታራሪ የነበሩት የወታደር አዛዥ ምክትል አስተዳዳሪ በሆኑበት  የሽግግር መንግስት ሲመሰርት ብአዴን በጭንቅ ጊዜ የኢትዮጵያን ፣ የዓማራን እና የኢህአዴን ህልዉና  ከጥፋት እና ከሞት የታደገ የዓማራን ህዝብ ፤ልጆች (ልዩ ኃይል፣ ፋኖ ፣ መከላከያ…..) ወዘተ በማዳከም ህዝቡን እና ልጆችን አመድ አፋሽ ማድረግ ነበረበት ወይ ፡፡ አትፈርዱ ብአዴን በዕዉነት ኖሮም ፤ታይቶ አይታወቅም እና አትፈረዱ “ድንጋይ የሚወረወረዉ ፍሬ በያዘ ዛፍ ነዉ እና” ድናጋይ ማባከን ነዉ፡፡

ብአዴን ህዝባዊ እና ብሄራዊ ጀግኖችን ( ሙሉዓለም አበበ፣ ዶ/ር ዓምባቸዉን፣ ጀ/ል አሳምነዉን፣ አስማረ ዳኘ……) እና የራሱን አጋር ጓዶች ወደ ጎን ትቶ ለአገር እና ለህዝብ ጠንቆች ሙሾ አዉራጂ  ማህበር በአድረ ባይነት እና በበታችነት አስተሳሰብ ለተጠፈነ ገ ድርጂት  ፍሬ አልባ ዛፍ መሆኑን ዘንግቶ ድንጋይ መወርወር ከንቱ የዕንቅልፍ ሩጫ ነዉ ፡፡

“ከፍሬያቸዉ ታዉቋቸዋላችሁ ፡፡”

“የጦር የጦር ለታ አንተን ያሉ ሁሉ ፣

ዓማን ቢሆን ነዉ ወይ ጥለዉህ የበሉ ፡፡”

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ላልተወሰነ የቆይታ ዘመን የተቆቆመ ድርጅት!!!

 

አንድነት ኃይል ነዉ !

Allen T. Silassie !

 

 

5 Comments

  1. የጌታቸው በባህርዳር መገኘትና የአዲስ አበባዋ ከንቲባ ግማሽ ቢሊዪን ብር ታቅፋ መቀሌ ለእርዳታ መድረሷ የወያኔን አስተሳሰብና ስብዕና አይለውጥም። የሚሞተው ይሞታል፤ የተራበው ይራባል፤ የሚዘርፈው ይዘርፋል። ብቻ ነገርየው ሁሉ ውሃ ወቀጣ ነው። ያኔ እናቶች ዶ/ር ደብረጽዪን ተው ጦርነት ይቅር እያሉ ሲለምኑት ሰምቶ ቢሆን ኑሮ ዛሬ ትግራይ ወደ ኋላ 50 ዓመት ባልተመለሰች ነበር። ግን ሃበሻ ጦረኛ ነው። ሰላምን አያውቅም። መግደል መገዳደል እንደ ጀብድ ይቆጥራል። ዶ/ር ተስፋዬ መኮነን ባይለየኝ ከስፓንሽ ቋንቋ ወደ አማርኛ በመለሰው ” ቀይ አንበሳ” በተሰኘው መጽሃፍ ላይ ጸሃፊው ኮ/ሌ አልሃንድሮ ዴሌ ባዪ ያሰፈራቸው ነገሮች ሁሉ አሁን የምናያቸው ናቸው። እንዲያውም ዶ/ር ተስፋዬ ለምን የመጽሃፉን አርዕስት እንደ ቀየረው አልገባኝም። የመጽሃፉ ርዕስ “አንድ ነጭ በጥቁሮች የሰቆቃ ምድር” ነበርና የሚለው። ይህ አሁን ራሱ የሃበሻይቷ ምድር ከ80 ዓመት በላይ በህዋላ ያለችበትን የሚያሳይ ነውና። ምድሪቱ ዛሬም የጠበንጃ አንጋቾች፤ የዘረኞች፤ የባለተረኞች ናት። ሰቆቃውም ከቀድሞው ቢብስ እንጂ አልተሻለውም። ሃበሻ የውስጥ ፍርሃቱን በጭካኔና በጡቻ ሸፍኖ ነገን አያለሁ የሚል ከንቱ ፍጡር ነው። ይህ አልበቃ ብሎ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን ዛሬ ልክ እንደ ድንጋይ ዘመን ተምረናል የምንል ደንቆሮዎች የራሳችን መኖሪያ ይዘን በጎጆ ውስጥ የሚኖሩ ወገኖቻችን እንዲጫረሱ ከውጭና ከውስጥ በመሆን እሳት የምንቆሰቁስ የቁም ሙታኖች ነን። የተጻፈን ሁሉ እንደ እውነት፤ በሶሻል ሚዲያ ሰው ለፍጆታ ያዘጋጀውን የፓለቲካ ወጥመድ ሁሉ ልክ ነው ብለው እየተጋቱ ዛሬ የራሳቸውን ኑሮ በጥብጠው፤ ትዳራቸውን አፍርሰው እንቅልፍ አልባ የሆኑ ሃበሾች ቁጥር እልፍ ነው። ሰልፋቸውም በዘርና በቋንቋ የተሰመረ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ አይነት ነው። አብሮ መኖር በዓለም ዙሪያ ድሮ ቀረ። ኦ ለካ የመማሪያ መጽሃፋችንም አርዕስቱ ያ ነበር። አይ ጊዜ!
    ወያኔ ለትግራይ ህዝብ የማይጠቅም አሞሌ ነው። ዝንተ ዓለም በትግራይ ህዝብ ስም እየማለ ስንቶችን መቃብር እንደከተተ፤ ለረሃብ እንደዳረገ፤ ስደተኞች እንዳደረጋቸው ልብ ያለው ያስተውላል። ግን ለዚህ ሁሉ ገመና ተጠያቂው የአማራ ህዝብና የኤርትራ መንግስት ነው ይሉናል በፕሮፓጋንዳቸው። ማን ነበር መቀሌ ላይ ሆኖ ወደ ኤርትራ ሮኬት የተኮሰው? ማን ነበር 3 ጊዜ ተከበናል በሚል የውስልትና ፓለቲካ እልፍ የድሃ የትግራይ ልጆችን አስጨርሶና ሌሎችን ጨርሶ ዛሬ ተው እንደተባለ ውሻ ጭራውን እግሮቹ ውስጥ ከቶ ስለ ሰላም ስምምነት የሚያወራው? ለመሆኑ የትግራይ መሪዎች ዛሬ ሱዳን ላይ የተፈጠረውን መከራን ያኔ መተንበይ ይችሉ ነበር? ጭራሽ። ከ100 ሺህ በላይ የትግራይ ስደተኛ ያለባት ሱዳን ዛሬ ሰው ሁሉ ነፍሴ አውጭኝ በማለት የሚራወጥባት ሆናለች። ትላንት ለወያኔ ሙሉ ጥብቅና የቆመው የአሜሪካ መንግስት ዛሬ ስለ ሱዳን አልፎ አልፎ ከሳውዲ ጋር እንዲህና እንዲያ አደረገን ይላል ለወያኔ እንዳላዘነው አላላዘንም? ተመድም በየቀኑ አልተሰበሰበም ለምን ይሆን? የሰው ልጅ ህይወት እኩል አይደለምን? ግን ልክ እንደ ሃበሻ ዘረኞች የአሜሪካ መንግስትም መርጦ አልቃሽ ነው። ለጫነው ፈረስ ብቻ ነው የሚቆረቆረው ለፈረሱ ሳይሆን ለጭነቱ።
    አሁን እንሆ WFP and USAID የእርዳታ ምግብ በኢትዮጵያ ተሰረቀ በሚል ሰበብ እርዳታ አቁመናል ብለዋል። ይህ ግን በሂሳብ የተሰላ የኢትዮጵያን መንግስት ለማሽመድመድ ከአቀድት አንድ የሴራ ወጥመድ ነው። ልክ ነው እርዳታ ይሰረቃል፡፡ ይሸጣል፤ ይለወጣል። ይህ ደግሞ በኢትዪጵያ ብቻ የሚሆን ሳይሆን በሁሉም ሃገሮች የሚፈጸም ተግባር ነው። እኔ የእርዳታ ስርቆቱ ትክክል ነው እያልኩ አይደለም። ግን የተጀመረው ዛሬ ሳይሆን ድሮም ነበር ነው። ወያኔ ለተዋጊዎቹ ብስኩት ሲሰጥ፤ ነዳጅ ሲሰርቅ አሁን በቅርቡ ደግሞ ከመጋዘን ያለውን ሁሉ አሟጦ ሲወስድ፤ የእርዳታ መኪኖችን በዚያው ሲያስቀርና ለጦርነቱ ማጓጓዣ ሲያደርግ ዝም ያሉት አሜሪካኖችና አውሮፓውያኖች አሁን ላይ ጩኸት ማብዛታቸው አሜሪካን ተከትለው ለፓለቲካ ጫወታ ሜዳ መግባታቸውን ያሳያል። እኔ የዶ/ር አብይ መንግስት ያኔም አሁንም ደጋፊ አይደለሁም። ግን አሜሪካኖችን ለማስደስት ዶ/ሩ የሚያደርጉት ማንኛውም እሺታ ሁሉ ለእነርሱ እንቢታ ነው። ያኔ ወያኔን ተመልሶ እንዲገባ ስፍራ አመቻችተው ውጣ ሲሉት እምቢኝ ስላለ መበቀል ይፈልጋሉ። ሴራው የረቀቀና ጉዳዪን ለመረዳት የንስር አይኖች የረጋ ጭንቅላት ይጠይቃል።
    ባጭሩ በደረቀና ፍሬ በሌለው ዛፍ ላይ ድንጋይ ውርወራው የሚያሳየው ነጋም መሸም የሃበሻው ገመና እየቆየና መልኩን እየቀያየረ ሲለው በብሄር፤ ሲከፋው በቋንቋ፤ ሳይሆን በሃይማኖት እየተደገፈ ነጻ አውጭ ነኝ/ግምባር ነኝ እያለ ሰውን ደም መቀባትና መግደል እንጂ ለህዝባችን እዚህ ግባ የሚባል እፎይታ አያመጣም። ድሮ ድሮ ሰው ሰው እያሌ አያቴ “አምላኬ ጧሪ ቀባሪ አታሳጣኝ፤ የማታ እንጀራ አትንሳኝ” ይሉ ነበር። አሁን አሁን የጸሎታቸው ጥያቄ መሰረታዊነት እየገባኝ ሂዷል። ዋ ቆዳው የነጣ ሁሉ የጣሊያን ክልስ አይደለም። ዛሬ ልክ ነው ብለን ደም የምናፈስበት፤ ሰው የምናፈናቅልበት፤ ራሳችን መከራ ውስጥ የምንከትበት ሃሳብ ሁሉ ነገ ፉርሽ ሊሆን ይችላል። የጥቁር ህዝቦችን እንባና ጭቆና የሚገታና የሚሟገት እንጂ ዘረኛና ጎጠኛው ለእኔ እሳር ከሚለቅሙ እንስሶች የተሻለ ነው ብየ አላምንም። ዛሬ በአፍሪቃዊቱ ቱኒዚያ፤ በግብጽ፤ በሌሎችም ሃገራት በቆዳቸው ቀለም የተነሳ በጥቁሮች ላይ የሚደርሰውን ግፍ ያውቃሉ? ወይስ በደረቀና ፍሬ በሌለው ዛፍ ላይ ቤትዎ በራፍ ላይ ቆመው ድንጋይ ይወረውራሉ? በቃኝ!

    • Tesfa, all what you said make sense. But, the bottom line is: not all Ethiopians (as you call it Habeshas) wanted to kill each other. Only those who are in power who do not have imagination how to govern this complex country resolve for self destruction by antagonizing communities. Think how Ethiopians reacted when Abiye came to power. he could have done anything to make positive change but he wasted it by going back to his small group. Please don’t blame the mass for few power mongers.

      • I have no qualm when I say, Habeshas are war liking people and cruel. the fact is we are. I blame the silent majority as well as those who are terrorizing our people day an night without any remorse. To me, There is no difference between the two. One kills and the other witnesses in silence. Therefore, I stand firm with my comments.

  2. ይገርማል ጌቾ እንኳን አፍሮ ጥቁር መነጽር አድርጓል ያኛው ነው እንጅ ፈጣጣ እነ ነውር ጌጡ። ያንን ሁሉ ጥፋት ካደረገ በኋላ በዚህ መልኩ ያስተናግዱታል ማፈሪያዎች። አይ አማራ ተዋርድሃል

  3. There is no use whining about ADP.
    If the guard to your house was hired by the thief to begin with, he will open the door to the thief anytime the thief orders him to. So why be surprised? You did not go find and employ ADP. ADP was created and hired by TPLF and OLF. ADP will, therefore, keep obeying their orders. As long as you do not pay the sacrifice to rid of this employee of the enemy, and as long as you keep regarding it as your zebegna, you will be slaughtered, plundered and dehumanized.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share