June 3, 2023
11 mins read

የሰንሹ የጦርነት ጥበብ ላማራ ሕዝባዊ ግንባር፤ ማጥቃት መከላከል ነው

National Army Amhara Special Force 1 1

በጥበበኛ አዛዥ የሚመራ ጦር ሳይታሰብ ግድቡን ጥሶ በሚጎርፍ ደራሽ ውሃ ይመሰላል፡፡  ደራሽ ውሃ ከፍተኛ ቦታን እየለቀቀ፣ ወደ ዝቅተኛ ቦታ እያዘቀዘቀ፣ ዝቅዝቅ በመጉረፉ በሚያገኘው እየጨመረ የሚሄድ እንድርረት (increasing momentum) እንቅፋቶቹን እየጠራረገ ረባዳን ያጥለቀልቃል፡፡  በጥበበኛ የጦር አዛዥ የሚመራ የጦር ሠራዊትም የጠላትን ጠንካራ ጎን እየራቀ፣ ደካማ ጎኑን እሰነጠቀ፣ እየጎለበተ በመትመም፣ የጠላት ጦር ያልሰፈረበትን የጠላት ግዛት እንበለ ውጊያ በመቆጣጠር ይንቦራቀቅበታል፡፡  ደራሽ ውሃ ወደ መዳረሻው የሚወንዘው አወናነዙን ከመሬቱ አቀማመጥ ጋር እያዛመደ ፍጥነቱን፣ ስፋቱንና ጥልቀቱን በመለዋወጥ እንደሆነ ሁሉ፣ በጥበበኛ የጦር አበጋዝ የሚመራ ሠራዊትም ወደ ግቡ (goal) የሚያመራው የጠላቱን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ትልሙን (strategy) እና ስልቱን (tactic) እንዳስፈላጊነቱ በመለዋወጥ ነው፡፡”  ሰንሹ (Sun Tzu)

 

ጦርነት ማለት በሽወዳ (deception) ላይ የተመሠረተ መጨፋጨፍ ማለት ነው፡፡  በመሆኑም ዋናው የድል ቁልፍ የሽወዳ ክሂሎት ምጥቀት ነው፡፡  የአጉል ጀብደኝነት ትርፉ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ነው፡፡  ስለዚህም ጠንካራ ስትሆን ደካማ፣ ደካማ ስትሆን ጠንካራ፣ ሩቅ ስትሆን ቅርብ፣ ቅርብ ስትሆን ሩቅ፣ ዝግጁ ስትሆን አልዝግጁ፣ አልዝግጁ ስትሆን ዝግጁ መስለህ ለጠላትህ ታይ፡፡  ጠላትህን እንቁ አሳይተህ እነቀው፡፡”  ሰንሹ (Sun Tzu)

 

መንደርደርያ

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል፣ የአማራን ሕልውና ለማስቀጠል ከኦነግና ከወያኔ ጋር የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ይገኛል፡፡  በዚህ የሞት ሽረት ትግል ላይ ደግሞ ሁሉም ፋኖ አማራ ሁሉም አማራ ፋኖ በመሆን እንደክሂሎቱ የበኩሉን ተጋድሎ ማድረግ አለበት፡፡  ከነዚህም ተጋድሎወች ውስጥ ደግሞ አንዱና ዋናው የአማራን ሕዝብ ተፈጥሯዊ የጦርነት ጥበብ በጦርነት ሳይንስ ማዳበር ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ ባማራነቱ የተካነውን እድሜ ጠገብ የጦርነት ጥበብ በሌሎች አገሮች (በተለይም ደግሞ በቻይናና በሩሲያ) የጦርነት ጥበቦች ካዳበረው፣ ማናቸውንም ጦርነት ባሸናፊነት የመወጣት እድሉ ከፍተኛ እንደሚሆን እሙን ነው፡፡  የቻይናው የጦርነት ሊቅ ሰንሹ (Sun Tzu) የጦርነት ጥበብ (Art of War) በተሰኘው ድንቅ መጽሐፉ ላይ በስፋት እንዳብራራው ደግሞ፣ የጦርነትን ጥበብ የተካነ፣ ትጥቁ እጅግም የሆነ ሠራዊት፣ እስካፍንጫው የታጠቀን ሠራዊት በቀላሉ ድል እንደሚመታ ነው፡፡  የዚህ ጦማር ዓላማ ደግሞ ከሰንሹ የጦርነት መርሖች ውስጥ አንዱ የሆነውን የማጥቃትና የመከላከል መርሕ መዘርዘር ነው፡፡

የኦነግ ሠራዊት ጨለማን ተገን አድርጎ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉትን ሕጻናትን፣ አረጋውያንና ደካሞችን ከማረድ በስተቀር፣ በዕድሜ ዘመኑ አንድም ቀን ድል ማድረግ ቀርቶ በቅጡ ተዋግቶ የማያውቅ፣ በትንሽ ብትር የሚንኮታኮት እንኩቶ፣ በፍንጥቅ እሳት ዐመድ የሚሆን ገለባ ሠራዊት ነው፡፡  እንዲህም ሆኖ ግን ጠላት አይናቅምና ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ባልተጠነቀቀበት ቦታ ላይ በድንገት ከተፍ ብሎ መከታተፍ ያስፈልጋል፡፡  በተለይም ደግሞ ማንም አይነካኝም ብሎ በመተማመን ተኮፍሶ በሚንጎባለልበት ቦታ ላይ (ለምሳሌ ያህል ወለጋ ላይ) ተሰውሮ ገብቶ እንብርቱን ወግቶ ቅንብቻውን ማስተንፈስ የግድ ነው፡፡ ጭራቅ አሕመድ ጃንደረባወች ተመስገን ጡሩነህና ደመቀ መኮንን የሚያሰማሯቸውን የአማራ ለምድ የለበሱ ብአዴናዊ የመስመር መኮንኖች በማስወገድ፣ ጭራቁን የግንኙነት መስመሮች መበጣጠስ ይዋል ይደር መባል የለበትም፡፡  የሰንሹ ትምህርት የሚያስተምረውም ይህንኑ ነው፡፡

የሰንሹ የማጥቃትና የመከላከል መርሖች

  1. ድልማድረግ በራስ ሁኔታ፣ ድል መደረግ ደግሞ በጠላት ሁኔታ ይወሰናል፡፡  ስለዚህም ጠቢብ የጦር አዛዥ በራሱ በኩል ሊያከናውናቸው የሚገባውን ሁሉ በጥንቃቄ አከናውኖ አመችውን ጊዜ ነቅቶና ተግቶ በትእግስት ይጠባበቃል፡፡  ታላቆቹ ጦረኞች ትዕግስትና ጊዜ ናቸው፡፡  ጊዜ የሰጠው ቅል ዲንጋ ይሰብራል፡፡  
  2. ኢተረችነትበመከላከል ችሎታ፣ ረችነት ደግሞ በማጥቃት ችሎታ ይወሰናል፡፡  ጠላት ሲበረታ ተከላከል፣ ሲደክም አጥቃ፡፡
  3. ጠቢብየጦር አዛዥ የሚያጠቃው መጠቃት ያለበትን እንጅ ለማጥቃት ሲል ብቻ አያጠቃም፡፡
  4. ጠቢብየጦር አዛዥ የሚከላከለው መካላከል ያለበትን እንጅ ለመከላከል ሲል ብቻ አይከላከልም፡፡
  5. ጠቢብየጦር አዛዥ ሲያጠቃ የሚከላከል፣ ሲከላከል የሚያጠቃ ያስመስላል፡፡
  6. ጠቢብየጦር አዛዥ ሲያስፈልግ እንደ እሳተ ገሞራ ከምድር ይፈነዳል፣ ሲያስፈልግ ደግሞ እንደ መብረቅ ከሰማይ ይበርቃል፡፡
  7. ጠቢብየጦር አዛዥ ሲያስፈልግ እንደ ንፋስ ይፈጥናል፣ ሲያስፈልግ ደግሞ እንደ ተራራ ይቆማል፡፡
  8. ጠላትህ ሲጠናከር ሽሸው፣ ሲዳከም አጥቃው፡፡  በግንባርህ ሲመጣብህ በጀርባው፣ በቀኝህ ሲመጣብህ በግራው እየተዟዟርክ አዋክበው፡፡  አወይ አተኳኮስ ወይ ደፋር መሆን፣ ሲሄድ መቀለቻ ሲዞር ግንባሩን፡፡ጠላትህ ሲረጋጋ ባሉባልታ አሸብረው፣ ሲያርፍ በትንኮሳ አዋክበው፡፡  ካጋም እንተጠጋ ቁልቋል ረፍት እየነሳህ፣ እዚህም እዚያም እየበሳሳህ፣ ዘላለም አስለቅሰው፡፡
  9. ጠላትህትይዝብኛለህ ብሎ የማያስበውን፣ ከያዝክበት ደግሞ ባስቸኳይ ሊያስለቅቅህ የግድ  የሚያስፈልገውን ቦታ ሳይስበው በድንገት ያዝበትና ሥራህን ቶሎ ሠራርተህ  ያስበው በድንገት በመውጣት ትሄድበታለህ ብሎ በማያስበው መንገድ ትሄድበታለህ ብሎ ወደማይገምተው ቦታ በፍጥነት ሂድ፡፡
  10. እንደመብረቅ በድንገት በርቀህ እንደ አውሎ ንፋስ በድንገት ንፈስ ፡፡  መብረቅ ድንገት ይበርቃል እንጅ ከየት በኩል እንደሚበርቅ አይታወቅም፡፡  አውሎ ንፋስ በድንገት ነፍሶ የሚጠራርገውን ይጠራርጋል እንጅ ከወዴት እንደሚነፍስ አስቀድሞ አይታወቅም፡፡  ሲበርቅ ቢጨፍኑ ከመወጋት አይድኑ፡፡
  11. ጠንካራ ስትሆን ደካማ፣ ደካማ ስትሆን ጠንካራ፣ ሩቅ ስትሆን ቅርብ፣ ቅርብ ስትሆን ሩቅ፣ ዝግጁ ስትሆን አልዝግጁ፣ አልዝግጁ ስትሆን ዝግጁ መስለህ ለጠላትህ ታይ፡፡  ጠላትህን እንቁ አሳይተህ እነቀው፡፡
  12. ማጥቃትህስኬታማ እንደሚሆን እርግጠኛ ልትሆን የምትችለው ጠላትህ የማይከላከለውን ስታጠቃ ብቻ ነው፡፡  መከላከልህ ስኬታማ እንደሚሆን እርግጠኛ መሆን የምትችለው ጠላትህ የማያጠቃውን ስትከላከል ብቻ ነው፡፡  በማጥቃት የተካነውን መከላከል፣ በመከላከል የተካነውን ማጥቃት ትርፉ ትልቅ ሽንፈት ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop