For Immediate Release –
ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. June 2, 2023
እኛ ስማችን ከታች የተዘረዘርን፣ በተለያዩ አህጉራት የምንገኝ ድርጅቶች፣ የፋሽስቱ ኦሮሙማ ብልፅግና መንግሥት፣ ወለጋ በሚኖሩ ዐማራዎች ላይ እያደረሰ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ አልበቃ ብሎት፣ ሰሞኑን በምሥራቅ ጎጃም በደብረ ኤልያስ ሥላሴ ገዳም ከ200 በላይ መነኮሳትን በፍፁም ጭካኔ፣ በከባድ መሳሪያና በገጀራ ጨፍጨፎ የዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል መፈፀሙን አጥብቀን እናወግዛለን።
ይህ ዘውጋዊ ፋሽስት መንግሥት በዐማራው ህዝብ ላይ አረመኒያዊ ወረራ ከፍቶ፣ ንፁሀንን ረሸኗል፣ ገዳማትንና ቤተክርስቲያናትን አውድሟል፣ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን አፍርሷል፣ ከ19 በላይ መስጊዶችን ደምስሷል፣ ባለፈው አርብና ዛሬ ግንቦት 25 ቀን ባንዋር መስጊድ ለጸሎትና ለስግደት በሄዱ ሙስሊሞች ላይ አፋኙ አገዛዝ ተኩስ በመክፈት ብዙ ስዎችን ገሏል፣ አቁስሏል፣ የዐማራው ገበሬ የአፈር ማዳበሪያ እንዳያገኝ ከልክሏል፣ እንዲሁም በፈጠራ ክስ በማንነታቸው ምክንያት ብቻ አፍኖ ከ30 ሺህ በላይ ዐማራዎችን በእስር እያሰቃየ ይገኛል።
ፋሽስቱ መንግሥት ባለፉት አምስት የሰቆቃ አመታት በዐማራው ህዝብ ላይ በወለጋ፣ በመተከል፣ በሰሜን ሸዋ፣ በደሴ፣ በጎንደርና በጎጃም የፈፀመውና እየፈፀመ ያለው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ሳያንስ፣ ህወሓት ከከፈተችበት ጦርነት ገና ባላገገመው፣ በዐማራው ክልል ላይ ብዛት ያለው ሠራዊት በማዝመት ንፁሀኑን ህዝብ እየጨረሰ ይገኛል። በተለይም ዋነኛ ፋሽስታዊ ትኩረቱን ነባር የእምነት ተቋሞችን በማጥፋት ላይ አነጣጥሮ፣ በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስና የእስልምና ተከታዮች ላይ ከባድ አረመኔያዊ ጥቃት እያደረሰ ይገኛል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ለማዳከምና ብሎም ለማጥፋት ባለው እቅድ መሠረት በጎጃምና ሸዋ ገዳማትንና አብያተ ክርስቲያናትን እያወደመ ይታያል። በአሁኑ ሰዓትም ምሥራቅ ጎጃም በሚገኘው ደብረ ኤልያስ ገዳማት ላይ፣ በከባድ መሳሪያ ለተከታታይ ቀናት በመደብደብ፣ ገዳሙ ውስጥ ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተመስክሯል። ብዙ በገዳሙ የሚኖሩ መነኮሳትና ፀበል ሊጠመቁ የሄዱ ምዕመናን ተገድለዋል፤ ብዙዎችም ቆስለዋል። በተጨማሪም፣ ሰሞኑን ከ19 በላይ የሚሆኑ መስጊዶችን በማፍረስ በሙስሊሙ ማህበረስብ ላይ ሃይማኖታዊ ዘመቻ እያካሄደ ይገኝል።
በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በአብይ፣ በሺመልስና አዳነች አበቤ እብሪተኛ ትዕዛዝ፣ ማንነትን መሠረት ያደረገ፣ ዐማራና ከኦሮሞ ውጭ የሆኑ ነገዶችን በመለየት፣ ከ100 ሺህ በላይ ቤቶች በማፍረስ፣ ቢያንስ ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ በክረምት ሜዳ ላይ እንዲወድቁ አድርጎአል። ከዚህ ተከትሎም፣ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት ከትምህርት ገበታቸው እንዲሰናከሉ ተደርጓል። ይህ ፋሽስታዊ አምባገነን መንግሥት በሁሉም ትብብር በቅርቡ ካልተወገደ፣ ህዝቡንም ከመጥፋት፣ አገርንም ከመውደም መታደግ አይቻልም። ስለዚህም፣ ይህን ውድቀቱን ለማፋጠን የሚከተሉትን ጥሪዎች እናቀርባለን፡-
1. በዐማራ ክልል የተሰማራው ወራሪ ሠራዊት በአስቸኳይ እንዲወጣ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት፣ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራትና ሌሎችም ለፍትህ የቆሙ ኢትዮጵያዊ ወገኖች፣ በሕዝባዊ እሚቢተኝነት የማያቋርጥ ግፊት እንዲያደርጉ፤
2. በገዳማት ቤተክርስቲያን እንዲሁም መስጊዶች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ሁሉም የእምነት ቤቶች በህብረት እንዲያወግዙና፣ የፋሽስቱን መንግሥት የወንጀል ድርጊቶች ለዓለም አቀፍ የእምነት አቻዎቻቸው እንዲያስረዱ፤ የሃይማኖት አባቶችም፣ ይህንን አገር አፍራሽ፣ ሃይማኖት አርካሽ፣ የሆነ መንግሥታዊ የሽብር ወንጀል ዝም ብለው ማየታቸውን ትተው ድምፃቸውን እንዲያሰሙና መንፈሳዊ ተግሳፅ በመንግሥት ላይ እንዲያደርጉ፤
3. ማንነትን መሠረት አድርጎ ከመቶ ሺህ በላይ ቤቶችን የማፍረስ ወንጀልን እንዲሁም በፈጠራ ክስ በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ ዐማራዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ዘግናኝ የእስር ቤት ስቃይ. ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባገኘው መድረክ ሁሉ እንዲያወግዙ፤
4. በውጭ የምትገኙ ድርጅቶችና፣ ኢትዮጵያዊ ግለ-ሰቦች፣ አረመኔው መንግሥት በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ወንጀል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅም ሆነ፣ ለተጀመረው የኢኮኖሚ ዕቀባ፣ የምታደርጉትን አስተዋፅኦ በተፋፋመና በተቀነባበረ መንገድ እንድትቀጥሉ፤ በተለይም ፋሽስቱን መንግሥት እየጎዳው ባለው ከውጭ የሚላክ ገንዘብ ማቆም፣ የዳያስፕራው ወደ ኢትዮጵያ ለእረፍት አለመሄድ፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አለመጠቀም፣ ኢትዮጵያ ኢንቨስት አለማድረግ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ትብብራችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤
5. በመጨረሻም የዘውጋዊው ፋሽስት መንግሥት መሪዎች እያደረሱ ባሉት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ፣ የእምነት ነፃነትን አለማክበርና በራስ ህዝብ ላይ ጦርነት ማወጅን በመሳሰሉት ዓለም አቀፍ ወንጀል ተከስሰው ለፍርድ እንዲቀርቡ የማያቋርጥ ጥረት እንዲደረግ እናሳስባለን። አፋኙን የአብይ መንግሥት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከስልጣን ማስወገድ አማራጭ የለውም!!!
ፈራሚ ድርጅቶች
SIGNATORY ORGANIZATIONS
1. Abba Bahrey Forum
2. Adwa Great African Victory Association (AGAVA)
3. All Shewa Ethiopian People Multipurpose International Association
4. Amhara Association in Queensland, Australia Amhara Dimtse Serechit
5. Amhara Wellbeing and Development Association
6. Communities of Ethiopians in Finland
7. Concerned Amharas in the Diaspora
8. DC Task Force
9. Embilta Forum
10. eT-Hub
11. Ethio-Canadian Human Rights Association
12. Ethiopian American Development Council (EADC)
13. Ethiopian Community Association of Greater Cincinnati (ECAGC)
14. Ethiopian Dialogue Forum (EDF)
15. Freedom and Justice for Telemt Amhara
16. Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause
17. Global Amhara Coalition (GAC)
18. Gonder Hibret for Ethiopian Unity
19. Major Lemma Woldetsadik Memorial Foundation
20. Network of Ethiopian Scholars (NES)
21. Radio Yenesew Ethiopia
22. Selassie Stand Up, Inc.
23. The Ethiopian Broadcast Group
24. Vision Ethiopia (VE)
25. Welkait, Tegede, Telemt, Setit Humera Global Amhara Unity Association
26. Worldwide Ethiopian Civic Associations Network (WE-CAN)
Well, expressing one’s position in approval or disapproval of ideas and actions by a ruling group and its supporters is the right thing to do as far as it reflects the very hard reality on the ground like a very age-old ugly if not tragic political system of our own !
Yes, it is quite right to make viable and vivid recommendations whenever we express our statements as either approving or disapproving one’s behaviors and actions . But words by themselves are nothing but words ! Sadly enough, we are terribly accustomed to this type of political thinking and behavior!
Our recommendations must not be just lousy or good for nothing type of words or even just intentions . They must be consequential if they are not taken seriously by those who are primarily responsible for what went wrong and what is going wrong over and over again. Our recommendations must have biting teeth, not just barking mouths!
I wish the above statement by 26 bodies with very attractive names could be different from our very lousy and bit going no where types of words with which we came across for so many years !
I am sorry to say but I have to say that we are not out of the very ugly political vicious cycle of thinking and behavior yet. It must be bitterly painful . But that is what it is until we honestly search what is wrong with our own inner souls as human beings created in an image of our creator with a very great purpose of life !
Needless to say, the right and wise thing is first to admit our own horrible ways of doing things for nothing, though it is not easy , and do something that could make a difference as far as the very disastrous way of political thinking and doing things is concerned !
It is painfully sad if not tragic to say that our statements (meglechas) are becoming nothing but good for nothing , boring and misleading ! No doubt that this is a very dangerous political mentality of being satisfied with empty words of political statements , not actionable words !
The very ugly political mentality of just talking the talk , but not walking the walk and claiming we feel satisfied desperately needs to change !