June 2, 2023
2 mins read

ይኸ ግድየለሽ ግድያና ጭፍጨፋ፣ ታሪካዊ ቅዱሳት መካናትን ከመድፈርና ከማርከስ ዐልፎ በጦር መሣርያ ማውደም ላንዴና ለመጨረሻ መወገዝና በቃ ማለት ያለበት ጉዳይ ነው

genocide 1 1 1

በየማኅበራዊ መገናኛው የምንሰማው እውነት ከሆነ – ሐሰት የሚወራበት ምንም ምክንያት ያለ አይመስለኝም፣ የዐቢይና እሱ የፈጠረው የብልፅግና መንግሥት ከፋሽስቱ ኢጣልያንም የከፋ መሆኑን በተደጋጋሚ አረጋግጧል ማለት ትክክለኛ አገላለጽ መሆኑ የሚካድ አይመስለኝም። ታዲያ እነዚያ “አሁንስ ይብቃ” (No More) እያሉ ይጮኹ የነበሩት አፎች የት ገቡ። “ባዕድ ኀይል በአገራችን ጉዳይ አይግባ” ሲሉ ላንቃቸው እስከሚበጠስ ጮኹ፤ ዓለምንም ከጫፍ እስከጫፍ አነቃነቁ። አሁን ታዲያ ይኸው መንግሥት አገሪቷን በጭፍኑ ሲያጠፋ፣ ሲያወድም፣ ከሩዋንዳ በከፋ እንጂ በማያንስ መልክ ሕዝብን ሲያፈናቅልና ሕፃናትን ለጅብ እራት ሲዳርግ፣ ቅዱሳትንና ታሪካዊ መካናትን አላንዳች ርኅራኄ ሲደመስስ፣ ጆሯቸው ዳባ ለብሶ፣ አፋቸውም ተደፍኖ መቅረቱ ምን ይባላል።

ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የቤተክርስቲያኒቷ ጳጳሳትስ ለምን ዝምታ መረጡ። በሥልጣናቸው ሲመጣ ብቻ ነው ወይ እሳት ለብሰው፣ እሳት ጐርሰው፣ ምእመናኑን ከጐናቸው አሰልፈው፣ መንግሥትን መግቢያ መውጫ የሚያሳጡት፤ ሰማዕትነትን የሚመኙት። እንዴት አያፍሩም። “ኢትዮጵያዊ እንደመሆኔ የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል” ብለው ስለአገራቸውና ስለሃይማኖታቸው በኢጣሊያን ጦር ተኳሽ ቡድን ብርቅ ሕይወታቸውን የሠውት ያ ታላቁ  አቡነ ጴጥሮስ ዛሬ በሕይወት ቢኖሩ እንደነዚህ ዐይነቶቹን አባቶች ምን ይሏቸው ይሁን።
ኢትዮጵያዊ መሆን እጅግ በጣም በሚያሳፍርበት ወቅት ነን ያለነው። የማያፍር ልበደንዳና ካለ፣ ሰው መሆኑ ራሱ አጠራጣሪ ነው ማለት ይቻላል።
ኀይሌ ላሬቦ


Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop