አንድ ወር ያለፈው የአማራ ክልል ጦርነት – ግርማ ካሳ

“ህዝብ ደብረ ማርቆስን ከተቆጣጠረ፣ ደብረ ኤሊያስ ህዝብ ላይ እየተኮሱ ያሉ መሄጃ አይኖራቸውም፡፡ እጃቸውን ይሰጣሉ”

ዘረኛውና ተረኛው የአብይ አህመድ ኦነጋዊ አገዛዝ በአማራ ማህበረሰብ ላይ በይፋ የከፈተው ጦርነት አንድ ወር አለፈው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ውጊያ የተደረገው በዋናነት በሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎና በስሜን ሸዋ ይፋት ነበር፡፡

#image_title

ባለፉት አንድ ሳምንት አገዛዙ ትኩረት ሰጥቶ ውጊያ የከፈተባቸው አካባቢዎች አምስት ናቸው፡፡ እነርሱም፡ 1ኛ በምእራብ ጎጃም፣ ከቡሬ በስተደቡብ ምእራብ አባይ ሸለቆ አካባቢ፣ 2ኛ በምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ከደብረ ማርቆስ በስተደቡብ ምእራብ በደብረ ኤሊያስ ወረዳ፣ አባይ ሸለቆ አካባቢ፣ 3ኛ አሁን በምስራቅ ጎጃም ዞን ፣ በመርጦ ለማሪያም፣ ግንደ ወይን፣ ሞጣ መስመር በአባይ ሸለቆ አካባቢ፣ 4ኛ በደቡብ ወሎ ወረኢሊና በሰሜን ሸዋ መርሃቤቴ ሚዳ ከተማ መካከል እና 5ኛ በመንዝ በእንሳሮ ከተማ አካባቢ ነው፡፡

በነዚህ በአምስቱም ቀጠናዎች ፣ እንደ ስሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎና ሰሜን ሸዋ ይፋት፣ አገዛዙ አልተሳካለትም፡፡ በርካታ ታጣቂዎችን ያጣ ሲሆን፣ “አህያውን ፈርቶ ዳዉላዉን” እንደሚባለው፣ ፊት ለፊት የሚገጥሙትን የአማራ ኃይሎች መቋቋም ሲያቅተው፣ ሰላማዊ ዜጎች ላይ በርቀት መድፍ በመተኮስ፣ የድሮን ጥቃት በመፈጸም አብያተ ክርስቲያናትን፣ ገዳማትን ማውደም ጀምሯል፡፡

#image_title

ሰሜን ጎንደር

======

በሰሜን ጎንደር የተደረገው ውጊያ በአገዛዙ ተሸናፊነት ለጊዜው ጋብ ብሏል፡፡ በዚያ ያሉ የመከላከያ መኮንኖች ውጊያዉን ከቀጠሉ እጣ ፋንታቸው መደምሰስ ስለነበረ፣ ሽማግሌዎችን በመላክ ፣ ስምምነት ፈጽመዋል፡፡ መሳሪያቸውን ደፍተው ወደ ካምፓቸው ገብተዋል፡፡

ሰሜን ወሎ

=====

በሰሜን ወሎ ቆቦና ራያ አካባቢ ይንቀሳቀስ የነበረው የምስራቅ አማራ ፋኖ ላይ ከጅምሩ ነበር ዘመቻ የጀመሩት የአብይ ታጣቂዎች፡፡ ምሬ ወዳጆን ለመያዝ ያደረጉት በርካታ ሙከራዎች የከሸፉባቸው ሲሆን፣ የምስራቅ አማራ ፋኖዎች፣ ከቆላማ አካባቢዎች ወደ ደጋውና ተራራማ አካባቢ፣ ወደ ምእራብ በመሻገር ፣ ለአገዛዙ ጦር እጅግ በጣም ከፍተኛ ራስ ምታት እየሆኑበት ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ የአገዛዙ ጦር በስሜን ወሎ አፋርን በሚያዋስነው አካባቢ ብቻ ተወስኖ ነው የሚገኘው፡፡ ከዚህም የተነሳ በስሜን ወሎ አንጻራዊ መረጋጋት ያለ ይመስላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ልዩ ዜና..... እነ ዶክተር ደብረጺዮን እና ጌታቸው ረዳ አሁንም በህይወት አሉ

ሰሜን ሸዋ ይፋት

========

ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ ውጊያ የተደረገበት አካባቢ የሰሜን ሸዋ ይፋት ነው፡፡ በማጀቴ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ደብረ ሲና፣ አንጻኦቂያ ገምዛ ፣ ራሳ ከፍተኛ ውጊያዎች ተደርገዋል፡፡ አገዛዙ በከባድ መሳሪያ እየታገዘ ፋኖዎችንና የአማራ ልዩ ኃይሎችን ትጥቅ ለማስፈታት ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራዎች ሊሳኩ አልቻለም፡፡ ያ ብቻ አይደለም ከፍተኛ መኮንኖችን ሳይቀር ብዙ ታጣቂዎችን አጥቷል፡፡ ብዙ መሳሪያዎችም በአማራ ኃይሎች እጅ ውስጥ ገብተዋል፡፡ብዙዎች የተማረኩ ሲሆን፣ ቀላል የማይባሉም አንዋጋም ብለው የአማራ ኃይሎችን ተቀላቅለዋል፡፡

ደብረ ኤሊያስ ፣ አባይ ሸለቆ

=============

አገዛዙ የአማራ ሕዝብዊ ግንባር መሪዎች፣ በደብረ ኤሊያስ አካባቢ አሉ በሚል የተሳሳተ ስሌት ነው፣ በደብረ ኤሊያስ እጅግ በጣም ከፍተኛ ጦር ነበር ያሰማራው፡፡ ደብረ ኤሊያስ ወለጋን የሚያዋስን የጎጃም ወረዳ ነው፡፡ ኦነጋዊው ሰራዊት ደብረ ኤሊያስ ያሉ ገዳማትን ለማጥቃት ሰራዊቱንና ከባባድ መሳሪያዎችን ያመላለሰው፣ ከጎሃጺዩን በደጀን፣ ሉማሜ፣ አምበር፣ ደብረ ማርቆስ፣ አማኑኤል ከተሞች አድርጎ ነው፡፡ ሆኖም በደብረ ኤሊያስ ፋኖዎች በብዛት የሉም፡፡ መከላከያ ብሎ ራሱን የሚጠራው የኦነግ ታጣቂ ቡድን ከህዝብ ጋር ነው እየተዋጋ ያለው፡፡

ተረኛውና ዘረኛው አገዛዝ፣ ወደ ደብረ ኤሊያስ ከ50 በላይ በኦራል የታጨቁ ወታደሮች እንዳሰማራ፣ ወታደሮቹም ግማሹ ሙትና ምርኮኛ፣ ከፊሉ ደግሞ ቁስለኛ ሆኖ የደብረ ማርቆስ ሆስፒታልን እንዳጨናነቁት እየተሰማ ነው፡፡ በአካባቢው ወደሚገኘው ደብረ ኤልያስ ገዳም የፋሺስቱ ወታደሮች ባደረጉት የከባድ መሳሪያ ድብደባ፣ በገዳሙ የሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን እንደ ወደመ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በቡሬ መስመር አባይ ሸለቆ

============

ሌላ ውጊያዎች የተደረጉባቸው አካባቢዎች ከቡሬ በስተደቡብ ምእራብ ባሉ፣ የተወሰኑ የምእራብ ጎጃም ዞንና የአዋኢ ዞን የአብይ ሸለቆ አካባቢዎች ናቸው፡፡ የአማራ ኃይሎች በዚህ አካባቢ በስፋት በመንቀሳቀስ፣ በአገዛዙ ታጣቂዎች የተቃጣባቸውን ጥቅት በብቃት ከመከላከል አልፈው፣ የማጥቃት እርምጃዎች በመውሰድ፣ በርካታ ቀበሌዎች መቆጣጠርና ህዝቡን ነጻ ማውጣት ጀምረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ስለ ዳዊት ከበደ ዘ-ሐበሻ ጁላይ 2013 ምን ጽፋ ነበር? አሁን ምን ሆነ?

መርጦ ለማሪያም/ ግንደ ወይን መስመር፣ አባይ ሸለቆ

=======================

ሞጣ፣ መርጦ ለማሪያም፣ ግንደ ወይን አካባቢም ከፍተኛ ዉጊያዎች ተደርገዋል፡፡የፋኖ መሪዎች በዚያ አሉ በሚል ነበር አገዛዙ ፣ ወታደሮችን በሰሜን በኩል ከባህር ዳር፣ በደቡብ በኩል ከጎሃጺዮን ደጀን፣ በምስራቅ በኩል ከወረኢሉ መካነሰላም እያስገባ፣ ከባባድ መሳሪያዎችን እየተጠቀመ ፣ “የፋኖ መሪዎች የታሉ” እያለ ህዝቡን እያሸበረ ያለው፡፡

በዚህ መስመር በተደረጉ ውጊያዎችም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሞተዋል፣ ተማርከዋል፡፡ ብዙዎችም አንዋጋም በሚል ጥለው ሄደዋል፡፡

በዚህ መስመር ነው፣ አንዲት እህት፣ ራሷን ለመከላከል፣ ቤቴን አላስደፍርም ብላ በሁለት የአገዛዙ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ የወሰደችው፡፡ ወደ ቤቷ ይመጣሉ፡፡ ምንም አይነት የፍርድ ቤት ማዘዣ አልያዙም፡፡ አማርኛ በደንብ መናገር አይችሉም፡፡ አመናጭከው አዋክቧት፡፡ “ባልሽ የታለ ?” አሏት፡፡ “ገበሬ ነው፣ እርሻ ላይ ነው” ትላቸዋለች፡፡ የባልሽን መሳሪያ አምጪ ይሏታል፡፡ “ለምን ?” ብላ ትከራከለች፡፡ አስገድደው ቤቷን ሰብረው ሊወስዱ፣ እርሷም ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ሲሉ፣ “ቆዩ፣ ይዤላችሁ እመጣለሁ” ትላቸዋለች፡፡ የባሏንም መሳሪያ ይዛ መጣች፡፡ ግን አላስረከበቻቸውም፡፡ “የባሌን መሳሪያማ አትወስድም” ብላ አጋደመቻቸው፡፡ የባሏን መሳሪያ ይዛ፣ ቤቷን ትታ ወደ ጫካ ሄደች፡፡

ወረኢሉ መርሃቤቴ መስመር፣ ካራ ምሽግ

===================

በኮምቦልቻ፣ ደሴ ከፍተኛ ጦር በማመላለስ፣ ዋና ማዘዣዉን ወረኢሉ በማድረግ ፣ የመርሃቤቴን ህዝብ ትጥቅ ለማስፈታት የተደረገውን ሙከራ እስከ አሁን አልተሳካም፡፡

ከወረኢሉ በጃማ፣ መራቤቴ(ሚዳ)፣ አለም ከተማ አዲስአበባ መስመር፣ የካራ ምሽግ የሚባል ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ቦታ አለ፡፡ በጃማና መራቤቴ (ሚዳ) ድንበር ላይ፡፡ ወያኔዎች ደርግን ያሸነቡትና ባለፈው ጦርነት ደግሞ፣ ወያኔዎች የተሸነፉበት ቦታ ነው። ይህን ቦታ በአሁኑ ወቅት ፋኖዎች ተቆጣጥረዉታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዜጎች ላይ ማንነታቸውን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም ጥቃት እንዲቆም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ

መከላከያ ጃማን አልፎ ፋኖ ያለበት ቦታ ለመድረስ ሞክሮ አልተሳካለትም፡፡ እስከ ጃማ ድረስ መከላከያ ኬላ ዘርግቶ ይፈትሻል። ሚዳ ላይ ፋኖዎች ይፈትሻሉ። ጃማ ከወረኢሉ 30 ኪሜ እርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ሚዳ ደግሞ ከወረኢሉ እስከ 90 ኪሜ ላይ ይሆናል።በዚህ መስመር ከወረኢሉ አዲስ አበባ 293 ኪሜ ነው።

በወረኢሉ ደቡብ ወሎን ጨምሮ፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ህብረተሰቡ እጅግ የመረረ ጥላቻ ነው እያሳያቸው ያለው፡፡ እንጀራ የሚሸጡባቸው ቤቶች መከላከያዎች ሲጠይቁ ጨርሰናል የሚል መልስ ይሰጣቸዋል፡፡ በአጋጣሚ እንጀራውን ካዪ ደግሞ 15 ብር የሚሸጥ እንጀራ 50 ብር ይሏቸዋል።

በእንሳሮ መንዝ

======

ሌላ ውጊያዎች የተደረገባቸው አካባቢዎች በእንሳሮ አካባቢ፣ በመንዝ ነው፡፡ ተረኛው አገዛዝ በእንሳሮ ባሉ ትምህርት ቤቶች ታጣቂዎችን ማስፈሩን በመቃወም ነበር፣ ህዝቡ መከላእክያን ውጡል፣ ልጆቻችንን አናስነካም ብሎ የተነሳው፡፡ ከዚህ ተቃውሞ ጋር በተገናኘም በአካባቢ በተነሳው የተኩስ ልውውጦች ፣ ህዝቡ ራሱን ለመከላከል ባደረገ ትንቅን በርካት የአገዛዙ ታጣቂዎች ሞተዋል፡፡

ማጠቃለያ

=====

አገዛዙ በብዙ የአማራ ክልል አካባቢዎች ውጊያ በህዝቡ ላይ ሲያደርግ፣ በሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች እያለፈ ነው፡፡ ህዝቡ በሁሉም ቦታ አንድ ሆኖ ተያይዞ መንቀሳቀስ መጀመር አለበት፡፡ የአገዛዙ ጦር ከኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ አድርጎ ወረኢሉ፣ ከባህር ዳር፣ አዴት አድርጎ ግንደ ወይን ፣ ከጎሃጺዮን ደጀን፣ ደብረ ማርቆስ፣ አማኑኤል አድርጎ ደብረ ኤሊያስ እንዴት ያለ ምንም ችግር ሊንቀሳቀስ ይችላል ????? የአገዛዙ ታጣቂዎች እንዳይንቀሳቀሱ ህዝብ መንገዶችን በሙሉ መዝጋት መጀመር አለበት፡፡ ለምሳሌ የደብር ማርቆስና የደሴ ወይንም የወረኢሉ ህዝብ ሆ ብሎ ወጥቶ ከተማዎችን ከተረኛው አገዛዝ ነጻ ቢያወጣ ፣ ህዝብን ለማሸበር፣ አብያተ ክርስቲያናትን ለማወደ በደብረ ኤሊያስና በመርሃቤቴ የተሰራው ጦር እጅ ከመስጠት ውጭ ሌላ ምርጫ አይኖረውም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share