May 5, 2023
7 mins read

በሚዲያ ጥፋት የተጠረጠሩ ታሳሪዎች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር ሊለቀቁ ይገባል

Detention ET 1 1

በፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት፣ በሚዲያ አባላትና በማኅበረሰብ አንቂዎች ላይ ያነጣጠረ የዘፈቀደ እስርና ወከባ ሊቆም ይገባል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችንና አባላትን፣ የሚዲያ አባላትንና የማኅበረሰብ አንቂዎችን ዒላማ ያደረገ እስር እና ወከባ በእጅጉ አሳሳቢ መሆኑን ገለጸ። ኢሰመኮ በተለያየ ዓይነት ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ከተያዙ ሰዎች ውስጥ በተለይ የሚዲያ አባላትን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን እንዲሁም የማኅበረሰብ አንቂዎችን (Activists) ጉዳይ በተመለከተ ክትትል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፣ ከእነሱም መካከል ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በቁጥጥር ስር የዋሉ፣ የሚዲያ አዋጁን (የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013) በሚጻረር መልኩ የታሰሩ፣ በተራዘመ ቅድመ-ክስ እስር ወይም ክስ ሳይመሠረትባቸው በእስር የቆዩ መኖራቸውን፣ በተወሰኑት ላይ የወንጀል ክስ ተመሥርቶ የነበረ ቢሆንም ክሱ በበቂ ማስረጃ የተደገፈ ባለመሆኑ በፍርድ ቤት ውሳኔ ውድቅ ተደርጎ ወይም በፖሊስ ውሳኔ ከተራዘመ እስር በኋላ በነጻ ወይም በዋስትና የተለቀቁ መኖራቸውንም ኮሚሽኑ ተመልክቷል።

ኮሚሽኑ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እስከ አሁን ድረስ በእስር ላይ ከሚገኙት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አመራሮችንና የሌሎችም ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት ላይ የሚደርሱ እንግልት እና እስሮችን ጠቅሶ መንግሥት የሰዎችን በሕዝባዊ ጉዳዮች ውስጥ የመሳተፍ መብታቸውን የሚገድቡ ተግባሮችን የመመርመርና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት ማሳሰቡ የሚታወስ ነው።  በቅርብ ጊዜ በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ያተኮሩ እስሮች እና ማዋከብ እናት ፓርቲን፣ በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲን እና የጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲን ይጨምራል፡፡

በዚህ ወር ውስጥ ብቻ ከታሰሩ የሚዲያ አባላት መካከል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆነው ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውን (አራት ኪሎ ሚዲያ) ጨምሮ ጋዜጠኛ ገነት አስማማው (የኔታ/መድሎት ሚዲያ)፣ ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ (ሮሃ ኒውስ/Roha News)፣ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው (ኢትዮ ሰላም)፣ ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ (የአማራ ድምፅ/Voice of Amhara)፣ ጋዜጠኛ በየነ ወልዴ (ጉራጌ ሚዲያ ኔትወርክ )፣ ጋዜጠኛ ሰናይት አያሌው (አሻራ ሚዲያ)  ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ (ኢ ኤም ኤስ) እንዲሁም በማኅበረሰብ አንቂነት (Activist) እና በሚዲያ ሥራም የሚታወቁት መስከረም አበራ (ኢትዮ ንቃት) ይገኙበታል፡፡ ከፊሎች በእስር ወቅት ተገቢ ላልሆነ አያያዝ የተዳረጉ፣ ከፊሎች ከዚህ በፊት ለተመሳሳይ እስር ተዳርገው የነበሩ እና፣ ከፊሎችም ከተለያየ ጊዜ መጠን እስር በኋላ የተለቀቁ ናቸው፡፡

መንግሥት የወንጀል ተግባሮችን ሁሉ የመከላከል፣ የመመርመርና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት፣ በሚዲያ አባላትና  የማኅበረሰብ አንቂዎች  ላይ የሚያተኩር እስር ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመደራጀትና  በሕዝባዊ ጉዳዮች የመሳተፍ መብቶች ላይ የሚያስፈራራ፣ የሚያሸማቅቅ እና  የሚገድብ ውጤት (chilling effect) እንዳይኖረው ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ ነው፡፡

በመሆኑም የመንግሥት የጸጥታ አካላት በፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት፣ በሚዲያ አባላትና በማኅበረሰብ አንቂዎች ላይ ካተኮረ እስርና ማዋከብ እንዲቆጠቡ፣ በወንጀል የተጠረጠሩና በበቂ ሕጋዊ ምክንያት በቅድመ-ክስ ሊታሰሩ የሚገባቸው ሰዎች በሚኖሩበት ሁኔታም በሕግ በተመለከተው መንገድ ብቻ በጥብቅ ጥንቃቄ አንዲፈጸምና የተጠረጠሩ ሰዎችን ሁሉ ከምርመራ በፊት ከማሰር እንዲቆጠቡ፣  በተጨማሪም በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 (የሚዲያ አዋጅ) መሠረት በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ወይም አካል፣ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ በዐቃቤ-ሕግ አማካኝነት ለፍርድ ቤት መቅረብ ያለበት መሆኑ በግልጽ የተደነገገ በመሆኑ፤ በዚሁ መሠረት እንዲፈጸምና በሚዲያ አማካኝነት ተፈጽሟል በተባለ ወንጀል ተጠርጣሪ የሆኑ ታሳሪዎች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲለቀቁ ኢሰመኮ ያሳስባል፡፡

በተጨማሪም የሚዲያ ሠራተኞች የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የማኅበረሰብ አንቂዎች ለሕጋዊና ሰላማዊ ሥራ ያለባቸውን ልዩ ኃላፊነት ኢሰመኮ አስታውሷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop