መቃብር ብቻ ሆንሽ!! – ያሬድ መኩሪያ

/
መቃብር ብቻ ሆንሽ!!
”””””””””””””””””””””””””””””
አይሞቅም አይበርድም፣ቢዘሩ ያበቅላል
ምቹ ነው ለመኖር፣ብሩክ ነው ምድሩ
ሰዉ ግን  ተርቧል፣ደህይቷል ታርዟል
የኑሮ ፎርሙላ፣ጠፍቶት ቅጥ አንባሩ::
በሰው ደካማነት፣ጠልቆ ያለማሰብ
እንስሳ ይመስል፣በለመደው መኖር
ተተብትቦ ታስሮ፣ዝሎ ተሽመድምዶ
ሰው የመሆን ፍሬው፣ክብረቱ ተዋርዶ
እንደ አባይ ፏፏቴ፣ቁልቁለቱን ወርዷል
ማረፊያውን አቶ፣ባየር ላይ ተንሳፏል::
በምንም ነገር ላይ፣እውነት ሚባል የለም
ሀሰትና ሀኬት፣ሁሉም አርቴፊሻል
በሸፍጥ በታጠረ፣በዚህ ብኩን አገር
በሐቅ ቅን ልቡና፣ላብን እንጠፍጥፎ
አስቦና ታግሎ፣ሰው መሆን ይከብዳል::
ኢትዮጵያ ዕድልሽ፣ባከነ አልቀና!
ኢትዮጵያ ምድርሽ፣ጠፍ ዋለ አለማ!
ልጆችሽ ኮብልለው፣ወተው ተንከራተው
ያሉትም ደኸይተው፣ዛክረው ተንገላተው
ሥራ አልተሰራብሽ፣በጥበብ አልደመቅሽ
ለወጪ ወራጁ፣ለነባሩ መጪው
አስከሬን ማረፊያ፣መቃብር ብቻ ሆንሽ!!::
    ~ ***•°•***°•°***•°•****~
#image_title
ጎሰኝነት የሴጣን ጨዋታ ነው
ይህ ነገር መቅረት ይገባዋል!
ምድሩ ብሩክ ነው ጫርጫር
አርጎ ቢዘራ ያበቅላል
በማለት ማንነታችንን ለነገረን
አባታችን ብላቴን ጌታ ጸጋዬ ገብረመድኅን
አባታዊ ተግጻጸ ምክር መነሻ የተጫረ::
ሕይወት ሚያብብ ሚለመልምባት ሰው ልጅ ሙሉ በኩልሄ ጨዋ የተከበረ ኑሮ/ዲሰንት ላይፍ ሚኖርባት ሳይሆን ያስከሬን ማረፊያ መካነ መቃብር/ግሬቭ ያርድ ብቻ ለሆነች ምድር
መዘከርያ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ሚያዚያ ፲፪/፳፻፲፩ ዓ.ም
April 20/2019
ቅዳሜ)05:13 ለሊት(ሚኪ.ላ/አ.አ
©ያመጌዕ
ተጨማሪ ያንብቡ:  መንግሥት መንገደኞች ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ከተማ የመግባት መብታቸውን እንዲያስከብር - ኢሰመጉ

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share