የኮነሬል አብይ የነፍስ ገበያ በኢትዮጵያ!!! አንድ ሐሙስ የቀረው ጊዜ የሠጠው ሲሶ መንግሥት!!!

ክፍል አንድ                     ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

ለዶክተር ዩናስ ብሩ ማኒፌስቶ እና ለአቶ ልደቱ አጀንዳ አመንጭ መራሽነትን ማጠናከሪያ የቀረበ የሃሳብ በረከት፡-

አሜሪካ መር አዲስ የነፍስ ገበያ በኢትዮጵያ ምድር፡-ኢትዮጵያ የነፍስ ገበያ  ከጦርነት ባለመላቀቆ አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ህዝብ ሞት፣ በመቶ ሽህ ወጣቶች አካላቸው ጉደለ፣ ብዙ ሚሊዮን ህዝብ ከቀየው ተፈናቀለ እንዲሁም  ሃገራችን የሃያ ስምንት ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት የኢኮኖሚ ውድመት  አስተናግዳለች፡፡ ከደቡብ አፍሪካ በተደረገ ኢትዮጵያና ትግራይ ክልል   የሰላም ስምምነት በኃላ  በተፈፀመ ክህደት ወያኔ ትጥቅ ሣይፈታ፣ ምርጫ ሳያካሂድና መከላከያ ትግራይን ሳይቆጣጠር ለቆ እንዲወጣ በማድረግ አሜሪካኖቹና አደራዳሪዎቹ ሴራ አዲስ ጦርነት በአማራ ክልል ህዝብ ላይ ሚሊዮኖችን ለመጨፍጨፍና ቁስለኛና ተፈናቃይ የማድረግ ሴራ   ተነድፎል፡፡ ኮነሬል አብይ ወልቃይትና ራያን ለወያኔ ለማስረከብ በድብቅ ተስማምቶል፡፡ በዚህም መሠረት የአማራን ልዩ ኃይል ትጥቅ ለማስፈታት፣ ፋኖና ሚሊሻውንም ትጥቅ ለማስፈታት ታቅዶል፡፡ አሜሪካና አደራዳሪዎቹ ያሉትን ሁሉ ፈፅሞ ብድር እንደሚያገኝ ቃል ተገብቶለታል፡፡ አብይ አህመድ መንግሥት ከህወሓት ጋር አብሮ የአማራን ህዝብና የኤርትራን ህዝብ ለመፋለም አቆብቁቦል፡፡ አሜሪካ መር አዲስ የነፍስ ገበያ በኢትዮጵያ ምድር ሌላ አውዳሚ ጦርነት ታቅዶል፣ የነፍስ ገበያ ፕሮጀክት ዋና ዓላማ በጦርነት ህዝብ ቅነሳ ማድረግ ነው፡፡ የዓለም ሚዲያ  ቢቢሲ የማይዘግበው፣ ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ ወዘተርፈ የሚሊዮኖችን ሞት የማይዘግቡበት የዘረኛ ዓለም በታሪክ አንድ ቀን ተጠያቂ ያደርጋቸል፡፡ የርዋንዳን ህዝብ የሚሊዮን ህዝብ እልቂት ልብ ይበሉ!!! የብልፅግና መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ቀውስ ሃገሪቱን ከፍተኛ እዳና የብድር ወለድ ጫና፣ የውጪ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆል፣ የመንግሥታዊ መሠረተ-ልማቶች ፕሮጀክቶች ወጪ መጨመርና በጊዜው አለመጠናቀቅ፣ የወጣቶች ሥራ አጥነት መጨመር እንዲሁም የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት  እንደቀጠለ ነው፡፡ የአብይ መንግሥት  ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና ከዓለም ባንክ ብድር ለማግኘት የማያገላብጠው ድንጊያ የለም፡፡ የአብይ ሦስቱ መንግስታዊ ምሶሶዎች ህግ አውጭ፣ተርጎሚና አስፈፃሚ ዘሞ በመፈራረስ ላይ ይገኛል፡፡ በዘር የተደራጁ አስርአንድ ክልላዊ የጦር አበጋዞች መንግሥቶች ተዋኛይ ሲሆኑ ዋና ተዋናዮቹ አንደኛ ኦነግ/ኦህዴድ/ሸኔ/ብልጽግና ኦሮሙማ መንግሥት፣ ሁለተኛ የህወሓት ወያኔ የትግራይ መንግሥት፣ ሦስተኛው ተገዳዳሪ ኃይል ሆኖ እየወጣ ያለው የፋኖ የአማራ መንግሥት ሲሆን አራተኛዎቹ ስምንቱ የእራሳቸው ልዩ ኃይል ያላቸው የክልል መንግሥቶች አፋር፣ ሱማሌ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሃረሪ፣ ሲዳማ (Sidama in 2019)እናደቡብ ምስራቅ (South West in 2021) ደቡብ ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ ክልላዊ መንግሥትነት የጠየቁ የጉራጌ፣ የወላይታ ወዘተ ህዝብ ገደላና እስራት የሚፈፅም የኮነሬል አብይ መንግሥት በነቢብም በግብርም በህገመንግሥት ስም ህገመንግስቱን የማይከተል የጋንግስተሮች ፖለቲካ የሚያራምድ መንግሥት ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉን አሳታፊ ሰላማዊ ትግል (peacefull and all inclusive) የትግል ወይም ህዝባዊ አመጽና እንቢተኛነት የትግል ሥልታችንን የሚመርጥልን  አንባገነኑ ኦነግ/ ኦህዴድ የብልፅግና መንግሥት መሆኑ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ህዝባዊው ትግል ሁሉን አሳታፊ ሰላማዊ ትግልና ህዝባዊ እንቢተኛነትና ህዝባዊ አመፅን ያካተተ አማራው  የኦሮሞ ደም ደማችነው!!! እንዳለው አማራውም ሲጠቃ ጉራጌው የአማራ ደም ደማችን ነው!!! እንዳለው ዓይነት አስራአንዱ የክልል መንግሥት ህዝብ በቀጣዩ ትግል እንደተሳትፎቸው ልክ እንደሚያገኙ ከአሁኑ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡

 

(I) አንባገነኑ ኦነግ/ ኦህዴድ የብልፅግና መንግሥት የኦሮሙማ የመሥፋፋት አባዜና ግጭት በሁሉም ክልሎች ላይ እየተፈጸመ በመሆኑ በኦሮሙማ ላይ ‹‹የፀረ-መሥፋፋት ግንባር›› መመሥረት

(II) አንባገነኑ ኦነግ/ ኦህዴድ የብልፅግና መንግሥት ‹‹የሃገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔር ብሔረሰቦች እና የህዝቦችን ሚዛናዊ ተዋዕዖ ያካተተ ይሆናል)  የሚለው አንቀፅ ሰውየው ኮነሬል አብይ የጦርኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ፣ ገብርዬው ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጆላ ገላልቻ ኤታማዦር ሹም በኦነግና ኦነግ ሸኔ ሠራዊት ከላይ እስከታች በኦሮሙማ የተሸሙ  ‹‹ከላይ ሰውዬው፣ ከታች ገብርዬው፣መኃል ያለው ንሻ ዝምብዬው!!!››ሆነውብን (ከዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ወርቃማ ቃለምልልስ የተወሰደ) በኦሮሙማ ዘር ላይ ያማከለ መከላከያ ሠራዊት በመሆኑ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ ይልሆነ በበኦነግ ኦሮሙማና በኦነግ ሸኔ ፖለቲካ የተጠመቀ አራጅ ቡድን አሸባሪነት የተፈረጀ በመሆኑ፤  በኢትዮጵያ የሚገኙ የክልሎች ልዩ ኃይል ትጥቅ ያለመፍታት ግንባር መፍጠርና መተባበር ግድ ይላቸዋል የአዲሲቶን ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በእኩልነት ለመመሥረት ይበጃልና ፡፡

 

(III) ትግላችን ‹‹ ማንኛውም ሰው ስብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር የአካል ደህንነትና የነጻነት መብት አለው›› በሚለው የህገመንግሥቱ አንቀጽ በህይወት የመኖር መብታችንን መጀመሪያ ለማስከበር እንታገላለን፡፡

 

(IV) ከ2010 እስከ 2015 ዓ/ም የኮነሬል አብይ የብልጽግና መንግሥት የግፍ አገዛዝ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ሞተዋል፣መቶ ሽዎች የአካል ጉዳተኘች ሆነዋል፣ ሚሊዮኖች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፣ ብዙ ሽዎች  ሴቶችና እናቶች ተደፍረዋል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፈው አምስት አመታት ተጠያቂነት  እንዲመጣ፤ ገለልተኛ የስብዓዊ መብቶች አጣሪ ኮሚሽን ገብተው የተፈፀመውን የዘር ፍጅት፣ የጦር ወንጀልና የስብዓዊ መብቶች ጥስቶችን አጣርተው ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ የሚታገል የኢትዮጵያዊ ኃይል በየክልሎቹ ማደራጀት፣ ወቅታዊ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ናቸው እንላለን፡፡

 

የኮነሬል አብይ የብልጽግና መንግሥት ልዑካን ባዶቸውን መጡ!!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ድንቁርና የሚድንም የማይድንም ሕመም ሊሆን ይችላል

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚንስትር እዮብ ተካልኝ ቶሊና፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ  ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ሹማምንት ጋር በአዲስ አበባ ቀጥሎም በዋ ንግተን ስለ ኢትዮጵያ ዘለቄታዊ የዕዳ ትንተና (debt sustainability analysis) ውይይት በማድረግ ብድር እንዲሰጣቸው እግር ላይ ወድቀው ነበር፡፡  ኢትዮጵያ በ2021እኤአ ለግሩፕ ሃያ ኮመን ፍሬም ወርክ (Group of 20’s Common Framework) ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገሮች የመንግስት እዳ ማሸጋሸግ መርሃ ግብር ጥያቄ አቅርባ ነበር፡፡ ሆኖም በኖቨምበር 2020 እኤአ  ተጀምሮ ለሁለት አመት በዘለቀው ጦርነት ምክንያት ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ህይወት ያሳጣውና ሚሊዮኖችን ከቀያቸው ያፈናቀለ ጦርነት በመከሰቱ ምክንያት የብድር ጥያቄው ተስተጎጎለ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት   ልዑካን ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ጋር በአካሄዱት ውይይት በትንሹ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲለቀቅላቸው ተማፅነዋል፡፡ እንደ (አይ ኤም ኤፍ) ትንተና መሠረት  የኢትዮጵያ መንግሥት እስከ 2026 እኤአ ድረስ ስድስት ቢሊዮን ዶላር  እንደሚያስፈልገው ተንብየዋል፡፡ WASHINGTON, April 13 (Reuters) – Ethiopia is in talks with the International Monetary Fund (IMF) to borrow at least $2 billion under a reform program, four sources familiar with the matter told Reuters….In this first debt analysis, the IMF calculated that Ethiopia is set to face a financing gap of at least $6 billion until 2026, according to two sources close to the negotiations. That would still leave a funding hole of roughly $4 billion over that period should the country succeed in securing the amount under discussion……………..() ()Exclusive: Ethiopia seeking $2 billion under IMF program, sources say/By Jorgelina Do Rosario/April 13, 2023

 

የኢትዮጵያ የብር የመግዛት አቅምን ማዳከም  (Devaluation)

አይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያ የብድር ጫና ክምችት፣ የዕዳ የወለድ ምጣኔ መጨመር፣ የውጪ ንግድ ገቢ መቀነስ፣ የውጪ ምንዛሪ ክምችት መመናመን የተነሳ (አይ ኤም ኤፍ) የመፍትሄ ሃሳብ መሠረት፤ ኢትዮጵያ  የብርን የመግዛት አቅም ሃምሳ በመቶ ማዳከም ይጠበቅባታል ይህን ካደረገችም የሁለት ቢሊዮን ዶላር ብድር እንደሚፈቀድላት ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ  የኢትዮጵያ የብር ምንዛሬ ተመን 53.42 ብር በአንድ የአሜሪካ ዶላር በባንኮች ውስጥ ሲመነዘር፣ በጥቁር ገበያ ደግሞ አንድ ዶላር  ከመቶ እስከ መቶ አስር ብር   ይመነዘራል፡፡ በዚህ መሠረት የአይ ኤም ኤፍ ምክረ ሃሳብ መሠረት የውጪ ምንዛሬው በነፃ ገበያ እንዲወሰን አዘዋል፡፡ A free-floating exchange rate occurs when a government allows the exchange rate to be determined purely by market forces and there is no attempt to ask the central bank to influence the external value of the exchange rate. በዚህ መልክ የብር መርከስ ውጤቱ ኢትዮጵያ በውጪ ንግድ የምትልከው ምርትና ሸቀጥ ዋጋቸው በእጥፍ ይረክሳሉ፡፡

 

ብሔራዊ ባንክ ገንዘብ ማተም (Money printing)

  • የብልፅግናመንግሥት እኤአ በ2021 የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ላይ መንግሥት ብሔራዊ ባንክን በማዘዝ በአዲስ እንዲታተም ያደረገው የብር መጠን 83.5 (ሰማንያ ሦስት) ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ በ2023 እኤአ( በ2015 ዓ/ም ) ግማሽ አመት 100 ቢሊዮን ብር ገንዘብ ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ ብድር (ገንዘብ በማተም) መውሰዱ ታውቆል፡፡ ከ2021 እስከ 2023እኤአ የብልፅግና መንግሥት ብሔራዊ ባንክን በማዘዝ በአዲስ እንዲታተም ያደረገው የብር መጠን 183.5 (መቶ ሰማንያ ሦስት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ሌጣ ብር አትሞል፣ በምርትና በገንዘብ ዝውውር ውስጥ ያልነበረ የወረቀት ብር ነው፡፡ በኢኮኖሚው ውስጥ እየናረ  ለመጣው የዋጋ ንረት አንዱ ዓይነተኛ ምክንያት ይህ በየጊዜው እየታተመ ወደ ገበያ ውስጥ እንዲሠራጭ የሚደረገው በምርትና አገልግሎት ያልተደገፈ ሌጣ ብር መሆኑን የኢኮኖሚ ጠበብት ይስማማሉ፡፡
  • በኢትዮጵያ 189 (መቶ ሰማንያ ዘጠኝ) ቢሊዮንብር ከባንክ ውጪ ያለ ከጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ፣ ከከንቲባዋ ቢሮ፣ በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች ጦር አበጋዞች የኦህዴድና ህወሓት ቢሮዎች  ውስጥ የተቀመጠ ገንዘብ ከአምናው ጋር ሲወዳደር በ27 በመቶ እንዳደገ ተገልፆል፡፡ ነጋዴው ህብረተሰብም በባንኮች ላይ እምነት አጥተው እንደአቅሚቲ በግል ቤታቸው ካዝና ውስጥ ተቀምጦል፡፡
  • የኢትዮጵያ መንግሥት እዳ ከጂዲፒ ጋር ሲነፃፀር “Ethiopia recorded a government debt equivalent to 57 percent of the country’s Gross Domestic Product in 2019.” Source: National Bank of Ethiopia

የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ ብድር ለልማት ወይስ ብድር ለጦርነት!!! የዕዳ ገበታ ማጋራትና

  • ከመጋቢት2010 እስከ መጋቢት 2014 ዓ/ም፤ የአጠቃላይ የኢኮኖሚው እድገት ምጣኔ ያላገናዘበ (Excess Money Supply) የገንዘብ ፖሊሲ በኦነግ ኦሕዴድ / ብልፅግና ዘመን በከፍተኛ ደረጃ ተባብሷል፡፡ከጁን 30 ቀን 2021 እኤአ ድረስ፣ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ4 (ሁለት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአገር ውስጥ ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት) ትሪሊዮን ብር እንዲሁም የውጭ አገር ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.29 (አንድ ነጥብ ሃያ ዘጠኝ) ትሪሊዮን ብር ሆኖል፡፡
  • መጋቢት 2015 ዓ/ም፤የአገርውስጥ የመንግሥት ዕዳ 68 (አንድ ነጥብ ስድሳ ስምንት) ትሪሊዮን ብር ተመንድጎል፡፡ 31.5 ቢሊዮን ዶላር አድጎል፡፡ ከዚህ እዳ ውስጥ ማዕከላዊው መንግሥት ሃምሳ ዘጠኝ በመቶ ዕዳ ሲኖርበት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ደግሞ አርባ አንድ በመቶውን ይሸፍናሉ፡፡(በ2014 ዓ/ም የአገር ውስጥ ብድር 1.53 ትሪሊን ብር ወይም 29.4 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡)
ተጨማሪ ያንብቡ:  እነሆ በሀገራችን አዲስ ጎሳ መፈጠሩ ተሰማ - 'ፌስዳቢ' | ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት

{1} ከውጪ የተላከ ገንዘብ (Remittance) ገቢ ቀን፡- በባህር ማዶ የሚኖረው ኢትዮጵያዊያን በሚልኩት ገንዘብ የሚያስተዳድሩት ህዝብ ሢሶ መንግስትነታቸውን ዛሬም አረጋግጠዋል፡፡ ከ1981 እኤአ እስከ 2018 እኤአ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከውጪ የተላከ ገንዘብ (Remittance) ድርሻ 6.9 በመቶ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት gross domestic product (GDP) እንደነበር ይታወቃል፡፡  Remittance accounted for 6.9% of Ethiopia’s GDP on average from 1981 to 2018 (WDI, 2020), and remittance is an extremely important source of foreign exchange for Ethiopia, perhaps larger than the export earnings of the country in its foreign exchange generation capacity.Jun 8, 2021 ከውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች  የወያኔን የግፍ አገዛዝ በመቃወምና የአብይን መንግሥት በመደገፍ በተግባር ወደ ሃገር ቤት የላኩትን ገንዘብ በመጨመር በ2013 ዓ/ም 4.3 (አራት ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ዶላር፣በ2014 ዓ/ም 5.6 (አምስት ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር በመላክና ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በማዋጣት ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ኮነሬል አብይ መንግሥት ከኢትዮጵያዊነት ወደ ኦነግነት የዘር ፖለቲካ ዶንያ በገቡ ጊዜ ዲያስፖራው ተቃወማቸው፣ ሸሻቸው እንዲሁም ድጋፉን ነሳቸው፡፡ ዲያስፖራው ከውጪ የሚልከው ገንዘብ ሰባ በመቶ እንደቀነሰና ወደ መንግሥት ካዝና እንዳይገባ በማድረግ የኢኮኖሚ እቀባ መንግሥት ላይ ቀጠለ፡፡ በዚህም መሠረት በ2015ዓ/ም ስድስት ወራት ውስጥ 1.72 (አንድ ነጥብ ሰባ ሁለት) ቢሊዮን ዶላር ብቻ እንደተገኘና በሚቀጥሉት ወራቶች እየነጠፈ እንደሚሄድ የተቃዋሚ አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ ዲያስፖራው ወገናችን ወደ ሀገር ቤት የሚልከው ገንዘብ ሃገራችን ከውጪ ንግድ ገቢ (ኤክስፖርት) እንደሚበልጥ ይታወቃል፡፡ እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ሆኖ አገልግሎል፡፡ ለዚህ ነው ዲያስፖራው ወገናችን ሢሦ መንግስት የሚባለው ለአንድ ሦስተኛው ህዝብ ቀለብ በመሸመት፣ ሸማ ገዝቶ በማልበስ፣ ወገኖቹን በማሳከምና በማስተማርና በሃገር ውስጥ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በማድረግ በሳይንስና ቴክኖሎጂ በማሸጋገር ወዘተ  ከመንግሥት ተብዬው የተሸለ ስብዓዊ ልማት በማፋጠን ለሃገር ኢከኖሚ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረጋቸው በሃገራቸው ጉዳይ ከማንም በላይ ያገባቸዋል እንላለን፡፡   የኮነሬል አብይ መንግሥት (ria Money Transfer send money to Ethiopia) ዶላር ፍለጋ በጨረቃ! ዓይነት በአሜሪካና በአውሮፓ  ከተሞች ውስጥ ለኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች አንድ ዶላር በመቶ አምስት ብር እየመነዘረ ሃገር ቤት ዘመዶቻቸው ገንዘብ እንዲልኩ ህገወጥ ሥራ ላይ ተጠምዶል፡፡ የዲያስፖራ አስተባባሪዎች ይሄንን የገንዘብ ህገወጥ ዝውውር ማስቆም ይገባቸዋል እንላለን፡፡

{2} በፊች ምደባ፣የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ደረጃ ሲሲሲ ኔጌቲቭ አሽቆልቁሎል! በዚህም የተነሳ አዲስ ብድር አግኝቶ ወለድ ለመክፈል በኢትዮጵያ ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች› በሚቀጥሉት ሁለት አመታት ውስጥ በፕራይቬታይዤሽን ከ25 በመቶ እስከ 55 በመቶ ድርሻ የሚሸጡት ካንፓኒዎች ለዓለም አቀፍ ንግድ ጨረታ ይቀርባሉ፣ በምዕራባዊያን የእዳ ወጥመድ ውስጥ የብልፅግና መንግሥት ተንበርክኮል፡፡የኢትዮጵያ

 

{3} የመንግሥት ግብርና ታክስ ገቢ ተሸመድምዶል (Ethiopia’s tax revenue)፡- የመንግሥት ግብርና ታክስ በሁለቱ አመት ጦርነት ወቅት በትግራይ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች አንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በተለይ ወለጋ እንዲሁም ኦነግ ሸኔ በሚቆጣጠራቸው  ቦታዎች የመንግሥት ግብርና ታክስ አልተሰበሰበም፡፡ በ2018/2019 እኤአ የኢትዮጵያ መንግሥት ከግብርና ታክስ ገቢ 9.8 (ዘጠኝ ነጥብ ስምንት በመቶ)  ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት Gross Domestic Product (GDP) ድርሻ እንደነበረው ይታወቃል፡፡ ከ2019 እስከ 2030 እኤአ የኢትዮጵያ መንግስት የታክስ ገቢን 18.2 (አስራ ስምንት ነጥብ ሁለት በመቶ) ከፍ ለማድረግ አቅደደዋል፡፡ መንግሥት በ2022/23እኤአ 450 (አራት መቶ ሃምሳ) ቢሊዮን ብር ከግብርና ታክስ ገቢ መሰብስብ አቅዶል ተፈፃሚነቱ ግን በአዲሱ ጦርነት ምክንያት አያስተማምንም፡፡ Despite the growth, officials see its GDP ratio leaves much to be desired and wants to push for sustained reforms to increase the tax base and administration to attain a tax-to-GDP ratio of 18.2% by the end of 2019/30……..Digitalising the tax payment system፡-According to the latest Ministry of Finance (MoF) information, the contribution of Ethiopia’s tax revenue to its GDP was 9.8% in the 2018/2019 fiscal year, which was the lowest, compared to other countries. To increase the country’s tax revenue, the Ministry has started to implement a digitalised e-tax filing system…..

The government has set a 450 Billion Birr revenues target for the fiscal year following an encouraging 20.6% jump in annual tax revenues in the preceding year.  የኮነሬል አብይ ሲሶ መንግሥት በ2015ዓ/ም 450 (አራት መቶ ኃምሳ) ቢሊዮን ብር ከግብርና ታክስ ገቢ ማግኘት አቅዶል፣ ሆኖም የኢትዮጵያ ብልጽግና መንግሥት የሚቆጣጠረው አንድ ሦስተኛ ግዛት ነው፡፡ የብልፅግና መንግሥት  የትግራይን፣ አማራንና አፋርን ክልላዊ መንግሥቶች አይቆጣጠርም፣ ግብርም አይሠበስብም፡፡ በአማራ ክልል የልዩ ኃይል ትጥቅ ለማስፈታት በተወጠነ ሴራ የተነሳ በተዛመተው  ህዝባዊ እንቢተኛነትና አመጽ  በአማራ ክልል ግብርና ታክስ የመሰብሰብ እቅድ አይሳካም፡፡ በኦሮሚያ ክልል ኦነግ ሸኔ ከህዝቡ ግብርና ታክስ ይሰበስባል፣ በወለጋ ዞኖች፣ በምስራቅ ሸዋ ዞን፣ በምስርቅ አርሲ ዞን፣ ሃረርጌ ዞን፣ ጉጂ ዞን፣ ሰሜናዊ ምዕራብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፣ ሰሜን ሸዋ ዞን እንዲሁም ደቡብ ምስራቅ ሸዋ ዞን የብልጽግና መንግስት ከከሠመ አመታት ተቆጥሮል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  "እርሱን ስሙት" ለሰይጣናዊ ዘረኛ መሪ ሲጠቀስ ዝም ማለት አልችልም

 

{4} የውጭ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችት መንምኖል (Ethiopia’s FX reserves)፡- የኢትዮጵያ የውጭ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችት 1.5 (አንድ ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ዶላር አሽቆልቁሎል፡፡ የገንዘብ ክምችቱ የአንድ ወር የገቢ ንግድ ውጪን ብቻ ሊሸፍን ቢችል ነው፡፡ የውጭ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችት ከተመናመነ ለመንግሥት ቀይ መብራት ነው!!! Ethiopia’s FX reserves have fallen to USD 1.5 billion, enough just to cover less than a month’s import bills but insufficient to satisfy debt commitments. According to Fitch’s latest outlook, published on December 20, 2022, the current account deficit will remain unchanged until 2023.Dec 24, 2022

 

{5} ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ቀንሶል (Foreign Direct Investment) በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ያላቸውን አስተዋፅኦ በካፒታል፣ በሙያ ክህሎት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ  ወዘተ  ያበረከቱትን ድርሻ  ከፍተኛ ነው፡፡ political stability and government policy commitment are the most important factors. Moreover economic factors such as labour, trade connection, size of the export sector, external debt, and market size of the countries are found to be significant determinants of FDI flows to African countries.

በኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት በ2018 አኤአ $3.36B (ሦስት ነጥብ ሠላሳ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር፣ በ2019 አኤአ $2.55B (ሁለት ነጥብ ሃምሳ አምስት) ቢሊዮን ዶላር፣በ2020 አኤአ $2.40B (ሁለት ነጥብ አርባ)ቢሊዮን ዶላር፣በ2021 አኤአ $4.26B (አራት ነጥብ ሃያ ስድስት)ቢሊዮን ዶላር፣ በባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ወደ ኢትዮጵያ ካፒታላቸውን በማስገባት ኢንቨስት አድርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ የፖለቲካ አለመረጋጋትና የደህንነት ስጋቶች የተነሳ የተከሰቱ የዘር ተኮር ግጭቶች በተለይም በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተው ጦርነት ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ቀንሶታል፡፡የውጭ ኢንቨስተሮች ሰላም ከሌለ፣ ገንዘባቸውን ስጋት ባለበት አካባቢዎች ኢንቨስት አያደርጉም፡፡ የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት አማራ ክልልን በጦርነት ለማጥቃትና ለማስገበር በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኦህዴድ ብልፅግና ከትግራይ ጦርነት የሚሊዮኖች እልቂት ምንም አልተማረም፡፡  የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ከአገር መውጣት ይጀምራሉ ኢኮኖሚው ይወድቃል፡፡ Insecurity and political instability associated with various ethnic conflicts – particularly the conflict in northern Ethiopia – have negatively impacted the investment climate and dissuaded foreign direct investment (FDI).Jul 29, 2022

 

{6} የባህር ማዶ እርዳታና ኦፊሽያል ዲቨሎፕመንት አሲስታንስ ድጋፍ  መቆረጥ (Foreign Aid and Official Development Assistance received)፡-በኢትዮጵያ የባህር ማዶ እርዳታ ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት (GDP) ድርሻ 9.3 በመቶ በ1982 እኤአ የነበረ ሲሆን በ2019 እኤአ ደግሞ 42.9 በመቶ እያደገ እንደሄደ በጥናት ተረጋግጦል፡፡ ኢትዮጵያ በየአመቱ ከ ሦስት እስከ አራት ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ታገኝ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዚህም መሠረት እንደ ናሙና በ2015 (3.238.9 ቢሊዮን ዶላር)፣ በ2016 (4.084.4 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2017 (4.124.8 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2018 (4.941.0 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2019 (4.810.0 ቢሊዮን ዶላር)የባህር ማዶ እርዳታ አግኝታለች፡፡ (The Global Economy.com) ድረ-ገፅ መረጃ ይገልጻል፡፡ How much of Ethiopia’s GDP is aid? It is clearly observed from the figure 2 on average the share of foreign aid to GDP showed increasing trend from 9.3% in 1982 to 42.9% in 2019; on the other hand there is slight fluctuation in GDP per capital growth rate over time, it is also evident that there is a rising trend from 0.9% in the year 1981 to 5.6% in …Jul 20, 2022.

ከኢትዮጵያ የሰሜኑ ጦርነት በኃላ  የባህር ማዶ እርዳታና ኦፊሽያል ዲቨሎፕመንት አሲስታንስ ድጋፍ በመአቀብ ተመታ፡፡ ኢትዮጵያ ጦርነቱን ካላቆመች የሚላስ የሚቀመስ ዶላር እንደማታገኝ ተፈረደባት፡፡ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት በ2023ዕኤአ 331 ሚሊዮን ዶላር ለስብዓዊ እርዳታ አበረከተ፣ ከሦስትና አራት ቢሊዮን ዶላር ወደ ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እንደ ተሸቆለቆለ መረጃው ይጠቁማል፡፡ የጦርነት መዘዙ ይሄ ነው አሁንም የፈረንጅ እርዳት ለማግኘት ካሻን ከጦርነት መታቀብ ግድ ይላል እንላለን፡፡ የኮነሬል አብይ መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የሚያካሂደውን ጦርነት በአስቸኮይ እንዲያቆምና በሠላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈታ እንጠይቃለን፡፡

 

‹‹ከላይ ሰውዬው፣ ከታች ገብርዬው፣መኃል ያለው ንሻ ዝምብዬው!!!››

 

Share