April 17, 2023
1 min read

ጥቁር ወተት፤ነጭ ኑግ – ያሬድ መኩሪያ

abiy Geday merz
#image_title

ጥቁር ወተት፤ነጭ ኑግ

“””””””””””””””””””””””””””””
በሰው ደም ታጥቦ ጨቅይቶ
ሲ,ዖልን ፈጥሮ በምድር
አማን ሠላም  ነው ይልሀል
ይሄ ወደረኛ፣ወንበር አፍቅር
ጡር ማይፈራ፣የዘመን ቁር::
ወተት ጥቁር ነው፣ኑግ ነጭ
እያለ ቀጥፎ ወስልቶ
ጭቦው ሲገለጥ፣ሲታወቅ
ዳግም ስህተቱን፣ይደግማል
ያን! ጭቃ ጅራፉን፣በመምዘዝ::
   ~***•°•***•°•*** ~
ከመቀላመዳቸው ለማይታቀቡ
ከስህተታቸው ለማይታረሙ
መንቻካ፣ችኮ፣ልዝብ፣ዐይን አውጣ
የዘመን ጉድ፣መደዴዎች
መዘከርያ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ሚያዚያ ፬/፳፻፲፫ ዓ.ም
April 12/2021
ሰኞ)12:27(መድኃኔዓለም/አ.አ
©ያመጌዕ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop