ወደነገ ለመድረስ፣ ዛሬን ማለፍ ግዴታ ነው። ዛሬ! አማራ በሕዝብ አመፅ የተደገፈ የትጥቅ ትግል ከማድረግ ውጭ አማራጭ የለውም።

ትላንት ልዩ ሃይልህ ፈርሷል። ዛሬ የኦህዴድ ብልፅግና የፖለቲካ ተሿሚው ብርሀኑ ጁላ ፍኖህን አጠፋዋለሁኝ ብሏል። ነገ ሚሊሽያህ ይፈርሳል አትጠራጠር። የሚነግሩህን ሁሉ እየተገበሩት ነው። ተነገወዲያ ደግሞ አንተን ክልልህ የኦህዴድና የወያኔ መፈንጫዎች ትሆናላችሁ። ወጣቱ ዛሬውኑ ተነስተህ ከፋኖ፣ ከሚሊሽያውና ከልዩ ሃይሉ ጎን በመቆም ህልውናህን መታደግ አማራጭ የሌለው ግዴታህ ነው።

ልዩ ህይሉና ፋኖውን ትጥቅ ከማስፈታት ባሻገር፣ በመቶ የሚቆጠሩ የአማራ ልሂቃን ታፍነው ታስረውል (አንተ የምታወቀው በሚድያ ይተዘገቡትን ጥቂት ታዋቂዎችን ብቻ ነው)። ጌታቸው ረዳ ያለውን አትርሳ “ከአማራ ልሂቃኖች ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን” ብሏል። ኅወሃትና ብልፅግና የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፆች ናቸው። ብልፅግና ውስጥ አሁን የተሰገሰጉት የቀድሞ የኅወሃት ባለስልጣኖችና አሁን መንበሩን የሚቆጣጠሩት የቀድሞ የኅወሃት ካድሬዎች ናቸው።  አሉ የሚባሉና በመቶ የሚቆጠሩ የአማራ ጋዜጠኞችና የማህረሰብ አንቂዎች እሰር ቤት ታጉረዋል። በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ወጣቶች በየስር ቤቱና በየበረቱ ታጉረዋል። ታድያ ያንተስ እጣ ፈንታ ምን የመስልሃል? ትግልህ አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው።

አማራ ሆይ! መጀማሪያ መታገል ያለብህ ከጥንት ጀምሮ ከሚያስገድልህ ዋና ጠላትህ የብአዴን ባንዳ ነው። ከክልልህ ጀምሮ እስከፌዴራል መንግሥት መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉትን የትላቱንና (በወያኔ ግዜ) የዛሬውን (በኦህዴድ ብልፅግና) መሪዎችህን ተመልከታቸው። አንድ ቀን እንኳን ያንተ መፈናቀል፣ መጨፍጨፍ፣ መንደድ፣ መሰቀልና መሰደድ አሳስቧቸው ያውቃል? ካልጋህ ላይ ሆኖ ደምህን እየመጠጠ ያለው ይህ የብአዴን ትኋን እያለ አንተ “ዳውን! ዳውን አብይ!” ብትል ምን ፋይዳ አለው። መጀመሪያ ቤትህ ውስጥ ያለውን ጠላት ማጥፋት ያለብህ። ዛሬ ይህ ተላላኪውና ባንዳው የቤት ጠላትህ፣ የልዩ ሃይልህንና ፋኖህን አስጨርሶ ሊጨፈጭፍህ ተዘጋጅቷል። እሱ ከአለቆቹ ጋር አ/አበባ ተቀምጦ፣ ዙርያህን በጠላቶችህ አስከብቦ እየፈጀህ ነው። ልዩ ሃይልህን በመንግሥትና በሸኔ ታጣቂዎች ትብብርና መናበብ አስከብቦ እየረሸነልህ ነው። ነገ የሚልሽያህን ትጥቅ ያስፈታል። ተነገ ወዲያ ደግሞ በየቤትህ እየገባ ትጥቅህን ይቀማል። ሚስትህን ይደፍራል። ልጅህን ያርዳል። ሀብትህን ይቀማል። ይህን በህልውናህ ላይ ያንጋጠጠብህን ሀቅ እያየህ ከታለልክና ካንቀላፋህ፣ ክብርህንና ቤተስብህን ከማዋረድ አልፎ የመጪው የአማራ ትውልድም ታሪካዊና የማትረሳ ተውቃሽ ትሆናለህ።

አማራ ጭምብልህን አውልቅ። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ጆሮ ዳብ አትበል። ነግ በኔ ነውና የማይቀርልህ እጣ ፈንታህ ነው።

የዛሬ አመት ገደማ፣ ጄኔራል ፃድቃን ታጣቂዎችሁን ሰብስቦ፣ ብርሃኑ ጁላና አቢይ “እናንተ ከኛ ጋር ከተስማማችሁ፣ የኤርትራንና የአማራን ጉዳይ ለኛ ተውት። ሁለቱንም እናስወጣቸዋለን ብለዋል” ብሎ ተናግሮ ነበር። በዚያን ጊዜ ይህ መረጃ ትንሽ አቧራ አስነስቶ፣ ብርሃኑ ጁላ ሚድያ ላይ ቀርቦ “ይህ ሕዝብን የማወናበድ የተሰራ የጠላት ወሬ ነው” አለ። ሀቁ ግን ይህ ነው። የኤርትራ ጦርም ወጥቷል። ወያኔም ትጥቁን አልፈታም። የአማራ ልዩ ሃይል በህይል እየፈረሰና በየጎዳናው እየተረሸነ ነው። የፋኖና የሚሊሽያው ትጥቅ ማስፈታትና ፍጅት በኦህዴድ ብልፅግና አጀንዳ ላይ የተቀመጠ ቀጣዩ ወሳኝ እርምጃ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሌንጮ ለታ – ታሪክ ሊሰሩ ወይንስ ታሪክ ሊጽፉ…?

አማራ ጭምብልህን አውልቅ። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ጆሮ ዳብ አትበል። ነግ በኔ ነውና የማይቀርልህ እጣ ፈንታህ ነው።

እንዴት ነው ሐገሩን በሙሉ ከዳር እስከዳርና መሀል ሐገር ድረስ እያተራመሰ ያለው ሸኔ፣ ሕዝብን እየጨፈጨፈ፣ መንግሥት ከጉዳይ ሳይቆጥረው በምትኩ ግን እራሴን ልከላከል የሚለውን ሕዝብ ትጥቁን አስፈትቶ በገፍ ለማስጭረስ ቆርጦ የተነሳው። ለምንድነው በመቶ ሺህ የሚቆጠር የመከላከያ ሃይል አሰማርቶ ትግራይን ወደትቢያ ያፈረሰ፣ መላወን የአማራ ግዛቶች ሳምንት ባልሞላ ጊዜ የተቆጣጠረ፣ አጣዬን ለአስረኛ ጊዜ የወረረን፣ ወለጋ ውስጥ በአለም ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ጭካኔ ሕዝብን እንደ ሽንኩርት የጨፈጨፈን የሸኔ ሰይጣን ለአምስት ዓመት ሙሉ ዝም አለው? አሁንስ፣ የአማራን ከተሞች በሙሉ ከብቦ በየቀኑ እየጨፈጨፈ እያለ፣ የአማራን ሕዝብ ህልውና ለማስከበር ክልልሉ ያደራጀውን ልዩ ሃይል ማፍረስ አስፈላጊ የሆነበት? እውነተኛ የሕዝብ መንግሥት መጀመሪያ የሕዝብን ጠላት ማስወገድ እንጂ፣ የሕዝብን ጠላት እያጠናከረና ተባባሪ እየሆነ፣ በዚያወ ልክም ይሕዝን “አልሞት ብቃይ ተጋዳይ” መብት በመቀማት ለልቂት መዳረግ አይደለም። በግልፅ የዘር ማፅዳት ተግባር ለማካሄድ ካልሆነ በቀር።

አማራ ሆይ! የመቃብርህ ጉድጓድ ተቆፍሮ አልቋል። ቆፋሪዎቹም ትላንትና በወለጋና በመተከል በጅምላ ያስቀበሩህ፣ ዛሬ ደግሞ በገዛ ክልልህ ያለተከላካይ ሊይስጨርሱህ የተሰለፉት የብአዴን አመራሮች ናቸው።

የትኛው የአማራ አመራር ነው በየሥፍራው ለሞቱትና ለሚሞቱት አማሮች ተቆርቋሪ የሆነው? የትኛው የብአዴን አመራር ነው የልዩሃይሉ ካምፑ ደረስ ተክቦ ሲጨፈጨፍ ድምፁን ያሰማ? የሞተው አንድ ትግሬ ቢሆን፣ የተገደለው አንድ ኦሮሞ ቢሆን ግን ከህወሃትም ሆን ከኦህዴድ የሚመጣው ጩኸት ሐገሩን ያናውጠው ነበር። በርግጥ የብአዴን አመራር ከአማራ ብሄር የመጣ ነው?

አማራ ሆይ! እንዴት ነው ይህ ሁሉ ሴራ ለአንተ ሚስጥር የሆነበት?

የኦህዴድ ብልፅግና ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ዘመቻውን ለማካሄድ ቅድመ ቅስቀስቃወን አጠናቋል። የኦህዴድ የብልፅግና መንግሥት በአብይ አህመድ በኩል፣ ያውም መላው የሐገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች በተገኙበት ፓርላማ፣ የጥላቻ  ዲስኩር እየሰበከ ባለበት፣ አዳነች አቤቤ ሽመልስ አብዲሳ፣ አዳነች አበቤ አማራውን በይፋ እንደ መጤ ቆጥራ “መንግሥት ሊገለብጡ የመጡ” “ከውጭ የመጡ” እያለች (እሷ እራሷ ከባሌ ፈልሳ እንደመጣች ስትይገነዘብ) ጥላቻን ስታቀነቅን፣ ሽመልስ አብዲሳ የነፍጠኛን (የአማራን) አከርካሪ ሰብረናል፣ ጠላቶቻችንን (አማራዎችን) አንገት አስደፍተናል እያለ በገሃድ የዘር ጭፍጨፋ ቅስቀሳዎችን እያስተጋባ ባለብት ወቅትና፣ እናዲሱ አረጋ ያለፈውን የሩዋንዳንና የአሁኑን ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ እያመሳሰሉ የዘር እልቂቱ ሊከሰት እንዲሚችል ድርሰት በሚፅፉባት ወቅት፣ እንዴት ንፁህ አምሮ ያለው አማራና የቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን ታላቅ የእልቂት ዘመቻ ጆሮ ዳባ ብሎ ይቀመጣል? ይህ የእልቂት ዘመቻ በእያንዳንዱ ሐገር ወዳድ ብሄር ብሄረሰብ ላይ የመጣ ከፋፋይ፣ አጋዳይ፣ አግላይ፣ የአንድን ብሄር ጥቅም ብቻ ለማስከበር የተቀነቀነ፣ ከቅኝ ገዥዎች ፍላጎት የከፋ፣ አፓርታይዳዊ ተንኮልና ስርዓት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እውነተኛ ማንነት ሲገለጥ (በይበቃል ያረጋል ረታ)

አማራ ሆይ! እንዴት ነው ይህ ሁሉ ሴራ ለአንተ ሚስጥር የሆነበት?

የአማራ ሕዝብ ሆይ! በፅንፈኛና በአክራሪ የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮ የሚዘወረው የኦህዴድ ብልፅግና፣ በኮሎኔል ገመቹ በኩል በራሱና በሶሽያል ሚድያ በተደጋጋሚ አጀንዳውን አሳወቆሃል። “ሸዋ፣ ጎጃም፣ ጎንደርና ወሎ የአማራ መሬት አይደለም። ከሁሉም ቦታ አማራን ሁሉ አፅድተን ወደ ደብረብርሃን እንሰበስባቸዋለን” ብሎሃል። “የሰሜን ሕዝብ” ማለትም “የሴሜቲክ ህዝብ” ትግሬውንና አማራው፣ ኤርትራንም ጨምሮ “የአቢሲንያ ቅኝ ገዢዎች” ናቸው ብሏል። የኦህዴድ ብልፅግ  መራሹ መንግሥት “እኛን የምትመስል ኢትዮጵያ ከመፍረስ ውጭ ሌላ አማራጭ የላትም” ብለውናል። ኮሎኔል ገመቹም ማንኛውም በኦሮምያ ክልል የሚኖር ኢትዮጵያዊ የኦሮሞ ዜኘት እንዲኖረው እናደርጋለን (ኦሮማዊ እናደርገዋለን ማለቱ ነው)። ግልፅ ነው? የዛሬ 500 አመት እፍኝ ከማትሞላ ቦታ ተንቀሳቅሶ ይህን ሁሉ የኢትዮጵያ መሬትን ዛሬ የያዘው ይህ አክራሪ ቡድን እንኳን፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ “መጤ” ተብሎ አይታወቅም። እነዚህ አክራሪዎች ግን በሺህ ለሚቆጠር አመታት የቆየውን ሕዝብ “መጤና የአቢስንያ ቅኝ ገዢዎች” ይሉታል።

ዛሬ እንዳጋጣሚ አማራ ስላልሆንክ ያልተፈናቀልክ ወይም ቤትህ ያልፈረሰ ትግሬ፣ ሲዳማ፣ ሱማሌ፣ ወላይታ፣ ሃድያ፣ ጉራጌ፣ ወዘተ፣ የአፓርታይድ ስርዓት ይምረኛል ብለህ ካሰብክ ተሳስተሃል። እያንዳንዳንድህ በኦህዴድ ብልፅግና አፓርታይድ መዝገብ ላይ ሰፍረሃል።

ጥንታዊ የኢትዮጵያ ሐይማኖትን ለማፍረስ ጎጠኛ ቡድን አቋቁሞ ቤተክስርትያናትን የሚሰብርና ምእመናኑን የሚገድል፣ በነፃነት የመልበስን መብት በመግፈፍ (ለምን ጥቁር ተለበሰ? ለምን የምኒልክንና የጣይቱን ምስል የያዘ ልብስ ተለበሰ? ወዘተ) ብሎ በስልጣን ኮርቻ ላይ ያወጣወን ሕዝብ በገፍ የሚያስርና ከሥራ የሚያባርር (በተለይ አዳነች አበቤ የምትመራው መዘጋጃ ቤትና አህመድ ሺዴ የሚመራው የገንዘብ ሚንስቴር)፣ ለምን በየጊዜው ጅኞች አባቶቹ የተዋደቁለትን አረጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ያዝክ በማለት የሚያስርና የሚረሽን አስፋሪና ነውረኛ አማባገነናዊ የአንድ መንደር መንጋ የሚዘውረው የኦህዴድ ብልፅግና ለመሆኑ ሰለ ነፃነት የማውራት ብቃትና ሞራል አለው?

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዘገየ ፍትህ ከተነፈገ ፍትህ ይቆጠራል!  (ከገብረ ኣማኑኤል)

ይህን የድንጋይ ዘመን ትርክት እያመጣ፣ ለአውሮፓወያን ጠላቶቻችን ብዝበዛና ምዝበራ ተጠቂዎች እንድንሆን፣ በአሥርተ አመታት በተደጋጋሚ አንድ ጊዜ ወደፊት ስድስት ጊዜ ደግሞ ወደ ኋላ እንድንራመድ የሚያደርጉን፣ ከስማቸው ፊት የልሂቃን ማዕረግ የለጠፉ እውቀት አልባ የጭንጋፎችን ሰብስብና፣ ታሪክን የሚያጨቀዩ አክራሪ የኦሮሙማ ስብስቦች ናቸው። እነዚህን አክራሪዎችና የኢትዮጵያ ጠላቶች ከሰላማዊው፣ ከሃገር ወዳዱና፣ ከቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በአንድነት ተሳስሮና ተዋልዶ ከሚኖረይ የኦሮሞ ሕዝብ መለየት ያስፈልጋል። ሁላችንም፣ በአንድም ሆነ በሌላ ምክኛት ኦሮሞነት አለብን።

የዋሁ የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ፣ የኦህዴድ ብልፅግናና አክራሪው “ኢትዮጵያን ጠል” የኦሮሙማ ስብስብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እያቀያየመህና ክፉኛ እንድትጠላ እያደረገህ መሆኑን ጠንቅቀህ እወቀው። “ጆሮ ለባለቤቱ ቡዳ ነው” እንደሚባለው ላታውቀው ትችላለህ። ግን ከጎረቢትህ ተቀራረብና ተማከር። የኢትዮጵያ ሕዝብ የተዋለደና ለዘመናት ተካፍሎ እየበላ የኖረ ጨዋ ሕዝብ ነው።  ይህ እየበጠበጠን ያለው የዛሬው የሐገራችን ነቀርሳ፣ የውጭ ጠላቶችን አላማ ግብ ለማድረስ፣ አንተን ከዘመናት ወንድምና እህቶችህ ጋር አጣልቶ፣ የሐገሪቷን ሃብትና ንብረት በዝብዞ፣ እሱን ወደቀጠረው ውጭ ሐገር ነገ ኮብላይ ነው። አሁንም እዚያው ንብረት እየገዛና እየተደራጀ ነው። በአንተ ሥም እንዳይነግድ አድረገው።

የኦሮሞ አክራሪ ብሔረተኞች እንደተረኛ፣ የሌላው ብሔር ጫንቃ ላይ ወጥተው በምንም አይነት መልክ ኢትዮጵያን ሊመሩና ሊያስተዳድሩ ብቃት የላቸውም። ይሄ “የኬኛ” አስተሳሰብና አመለካከት መንገዱን በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚሳሰናክለው ጥርጥር የለውም። በመጀምሪያ ደረጃ ወያኔን ለማወረድ የተደረገው ትግል፣ የአንድን ዘር የበላይነትን ለማክሰምና በምትኩ ደግም ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝቦች በእኩልነት የሚወክል ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ለማቋቋም ነበር። ወያኔ እንኳን፣ ለሃያ ሰባት ዓመት ሲገዛ “ሁሉን ለኔ” በገሃድ አላለም። በወያኔ ጊዜ ማንኛወም ኢትዮጵያዊ ወደፈለገበት ቦታ ያለስጋት መዘዋወር ይችል ነበር። ወያኔ ከወረደ አምስት ዓመት እንኳን ሳይሆን ከመሥመር የወጣ ይህ “የኬኛና” አፓርታይዳዊ የተረኛነት ሴራና ቅጥ ያጣ የፖለቲካ ቁማር በአጭሩ መቀጨት እንደሚያስፈልገው የማያጠራጥር ሐቅ ነው። ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመጥን መንግሥት መመስረት ግዴታችን ነው። ይህንን አስመሳይና መሰሪ ቡድን መቶሎ ማጥፋት ያስፈልጋል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ። ኢትዮጵያን እየበላት ያለው ነቅርሳ በሕዝባችን ትግል የነቀላል።

 

ደረጀ አያኖ

ሚያዝያ 7 ቀን 2015 ዓ/ም

 

2 Comments

  1. ይህ ጸሃፊ ከፊት ተሰልፎ ክላሹን አንግቦ የትጥቅ ትግሉን የሚመራ ከሆነ ጥሩ ነው። ለዚህም ግብ ፕሮግራም እና እቅድ ያስፈልጋል። ይህንን የሚመራ ድርጅትም ያስፈልጋል። “ሙያ በልብ” ማለትም ያስፈልጋል። ባለፈው አንድ ወጣት (ቲሊሊ የምትባል ከተማ መሰለኝ) ፊት ፊት ሰልፍ እየመራ መፈክር ሲያወርድ “ዘመነ ካሤ ይፈታ፣ ካልተፈታ ወደ ትጥቅ ትግል እንገባለን” እያለ ደጋግሞ ሲፎክር አይቼው ወደ ትጥቅ ትግል መሄድም በአዋጅ ሆን እንዴ ብዬ ታዝቤ ዝም አልኩ። ጸሃፊው እንደው ዝም ብሎ ወጣቱን የማነሣሳት ፉከራ ከሆነ “it is not fair” ማለቱ ይበቃል። ምክንያቱም “አይሰራም!” የማይሰራው ደግሞ 40 ሚሊዮን የሚሆነው የአማራ ህዝብ silent majority አይፈልገውም። ቢፈልግማ ኖሮ “የልዩ ሃይል ፖለቲካ” እንደዚህ በቀላሉ እና በአጭር ጊዜ ዉስጥ አይዘጋም ነበር። እንደው ለመምከር ያህል [ከትግራይ ልምድ በመንሳት] በትጥቅ ትግል መንገድ ሄዶ ክልሉን ሥርዓተ አልባ ከማድረግ ይልቅ ሶስት አመት ታግሶ ህዝብ አንቅቶ/ቀስቅሶ ብልጽግና የሚባል ፓርቲን ከአማራ ክልል ጠራርጎ ማስወጣቱ አይሻልም? ቢያንስ ተጨማሪ ብዙ ነፍስ እንዳይጠፋ እና ንብረት እንዳይወድም ያደርጋል። እንዲያውም በርግጠኝነት በትጥቅ መሞከሩ ብልጽግናን ከሶስት ዓመት በላይ የመቆየቱን እድል ይሰጠዋል። ከዚህ በኋላ በጉልበት መንግስት መቀየር እንደማይቻለው ሁሉ፣ በሥልጣን ያለ ገዢ ፓርቲም አይን ያወጣ [እንደ ምርጫ 97] ኮሮጆ ግልበጣ ማድረግ አይችልም። በቃ አይችልም!

  2. እረ ብርሃኑ አይመጣም ስራውን ለአገኘሁ ተሻገር፤ለደመቀ መኮንን፤ግርማ የሽጥላ፤ሰማ ጥሩነህ፤ተመስገን ጥሩነህ ይሰጠዋል እነዚህ ሰዎች ከብርሃኑ ጁላ/ነጋ /ከአብይ/ከሽመልስ/ከሌንጮ/ዲማ ነገዎ/ከቀጀላ መርዳሳ፤ዳውድ ኢብሳ በተሻለ ደረጃ አማራውን ያጠፉለታል፡፡ የነዚህ ሰዎች ፍራቻ ትህነግና ኦነግን እንጅ አማራውን ለማጥፋት አምበሳ ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share