በአማራ ሕዝብ፣ ማህበራዊ ፣ አኮኖሚያዊ ፣ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ደህንነትና ሁለገብ ተቋማት ላይ በተወሰኑ ስግብግብ ፣ ለኔና ለኔ ብቻ በሚሉ“ኬኛዎች” የሚደርሰውን ግፍ አይቶ እንዳላዩ በዝምታ ሳይቃወሙ ማለፍ “ነግ ለኔ” የሚያስብል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።
ለመላው የኢትዮጵያ ሰፊ ሕዝብ ይህን ሕገ ወጥ አካኣድ እንዲያጤነው ፣ እንዲያስቡበት ፣እንዲመክርበትና “ሳይቃጠል በቅጠል” እንዲሉ የአበው ምክራዊ ሃሳቦችን መሰረት አድርገን እኛ የአማራ ህዝቦች መልዕክታችን ለማስተላለፍ እንወዳለን።
ኢትዮጵያዊያን በተለይም የአማራው ሕዝብ ክርስቲያኑ ሆነ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የመንግስት መዋቅራዊ የስርዓት ሂደትን ፣ አፈፃፀምና ውቅር አስረግጦ ስለሚያውቅ በዘመናት መካከል የተመሰረቱ የመንግስት አስተዳደሮችንና የስርዓት መዋቅሮችን በሰከነ መልኩ እንዲዘልቁና ለሃገር ዘላቂ ሰላም ሲባል ከበላይ የሚወርድ ትዕዛዛትን ፣ መመሪያዎችንና ጥሪዎችን ቀና ሆኖ ይቀበላል ፣ ይፈፅማል ፣ ያስፈፅማል።
ይህን መሰረተ ሃሳብ ተንተርሶ በአለፉት የዐፄ ኃይለሥላሴ ፣ የደርግን ሆነ የኢሕአዴግ የመንግስት የአስተዳደር ዘመናት ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብና የአማራው ማህበረሰብ ችግሮችና ድክመቶች ሲታዩ ወደ ከፋ ደረጃ ከመድረሳቸው በፉት እየነቀሰ በማውጣት በጭዋነትና በጥበብ ይተቻቸዋል።
እሰየው የሚያስብሉ እምርታዎች ካሉም ደግሞ ዕፁብ ድንቅ ናቸው በማለት ህይወቱን መግፋት የኢትዮጵያዊያን ብሎም የአማራ ህዝብ ባህላዊ ውቅር ፣ ቱፊትና እሴት ነው።
ግፉ ፣ ጭቆና፣ ሌብነቱ ወዘተ ዐይን አፍጥጦ እስካልመጣበት ድረስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆነ የአማራው ሕዝብ ከሃይማኖት ትብዕሎችና ከአምላክ በወረዱለት የእግዚአብሄር ትዕዛዛቶች ጋር በይበልጥ የተቆራኘ በመሆኑ “መንግስት የሚቆመው ሆነ የሚሻረው በእሱ በኃያሉ ፈጣሪ ፈቃድ ነው” ብሎ የሚያስብ አስተዋይና ታጋሽ ሕዝብ በመሆኑ ለነገሮች ሁሉ ግብታዊ የሆነ ምላሽ አይሰጥም።
ጭቆናው፣ ተንኮሉ፣ ሻጥሩ፣ መገደሉ ፣ መታሰሩ መሰል ግፎቹና መከራዎቹ ከአፍ እስከ ገደፉ ደርሰው የመጨረሻው መዳረሻ የመኖር እና የአለመኖር ክስተቶች እሰከአላጋጠሙት ድረስ የአማራው ህዝብ ጉዳቱን ፣ ቁስሉን ፣ መገፋቱንና መንገላታቱን “የውሻ ቁስል” ነው ብሎ በአርምሞና በመቻል ለሃገር አለመፍረስ ሲባል ታግሶ በትዕግስትና በታጋሽነት የሚያሳልፍ ታላቅ ሕዝብ ነው።
መንግስት ግን የሕዝብን ትዕግስት ፣ ዝምታና ሆደሰፊነት ንቆና ወደጎን ብሎ ከተጨማለቀ ፣ ከተግማማና ከፏነነ የአፀፋ የእንቢ ባይነት ምላሽ የመስጠቱን አካሄድ ያውቅበታል፣አሳይቶትማል።
ይህ እውነታና ኩነት በደርግም ሆነ በኢሕአዴግ የመውደቂያና የመንገዳገድ ወቅትና ክራሞት የታዩ የቅርብ ጊዜ ትዝታዎች መሆናቸው የሚታውቅ ነው።
ታሪክ እንደዘገበው ቀደም ባሉት ዘመናት ማለትም በ16ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ የኦሮሞ ተስፋፊ ኃይል በአፄ እዮሃስ ፣ በአፄ በካፋና በእትጌ ምንትዋብ ዘመነ መንግስት ወቅት እስከ ጎንደር ድረስ ዘልቆ እንደነበር ይታወሳል።
በነዚህ ያለፉት ዘመናት የሃገሬው ህዝብና አፄዎቹ በዚያ ዘመን የኦሮሞን የመስፋፋት ግስጋሴ ለመግታት በጥበብ ፣ በጋብቻ በማስተሳሰር ፣ በማዛመድና በማቀራረብ በጋራ ለመኖር ሲባል ታላቅ መስዋዕትነት ከፍለው እንደነበር የሚታወቅ ነው።
ነገር ግን አልጠግብ ባዩ የኦሮሞ ተስፋፊ ብድን ይህን የእርቅ አሳቤና አብሮ ተዋልዶ የመኖርን ትብዕል እንደ ፍራቻና ማጎብደድ ቆጥሮ በጎንደር ቤተመንግስት ዙሪያ የአማረኛን ቋንቋ ወደ ኦሮሞኛ ለመቀየር ጥራዝ ነጠቅ የወረደ እሳቤ አሳይቶ ነበር። ነገርግን ይህ ዋልጌነቱና ድፍረቱ ያበሳጫቸው ሆደ ሰፊዎቹ በዘመኑ የነበሩ የጎንደር ዐፄዎች የዚህ ህሳቤ ያለውን የኦሮሞ ሹምና ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ቀጠውታል። ከዚያም በዐፄ ቲዎድሮስ ዘመነ መንግስት የኦሮሞ ተፅዕኖ ፍርክስክሱ እንዲወጣ ተደርጎ ለዘመናት ታዛዥ ሆኖ እንዲዘልቀ እንደተደረገ የታሪክ ማህደራት ያሳያሉ።
የኦሮምማው የብልፅግና መንግሥት ከሕውሃት መራሹ ወራሪ ኃይል ጋር ሲፋለም “ የመከላከያ ሰራዊቱ ከጀርባ ተመታ ፣ ሕግ ማስከበር ፣ ኢትዮጵያ አትፈርስም ፣ የበቃ ጦርነት ዘመቻ ወዘተ “ በሚሉ ውስጣቸው በመርዝ በተለወሱ የሴራ ፖለቲካ የአሻጥር ሽረባዎችና ዱለታወች ከአያቶቹ የወረሰውን የመስፋፋት ትብዕል እንደገና እውን ለማድረግ ይቻለው ዘንድ የኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በርሱ እዲጨፋጨፈ እንዳደረገ መላ ሕዝቡ የሚያውቀው የቅርብ ጊዜ ክሳቴ ነው።
መሰሬው የኦሮሞ ብልፅግና በሕውሃት በኩል ይታዩ የነበሩትን የግለኝነት ስሜት ፣ የአልጠግብ ባይነትና የወራሪነት ደካማ ጎኖች በማነብነብና በማጉላት እንዲሁም በወያኔ የጭቆና ቀንበር ስር የነበረውን የኢትዮጵያዊያንና በተለይ የአማራውን ሕዝብን ቁስል አጉልቶ በማውጣትና በማመርቀዝ መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዳር እስከ ዳር በተንኮል እንዲነሳሳ በማድረግ ወንድም ከወንድሙ እርስ በርሱ እንዳናረት ና ደም እንዲቃባ አድርጓል ። ይህ የአረመኔነትና የአረማውያን ክዋኔ የታሪክ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ እንዳለፈና መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅር የማይለው ታላቅ በደል እንደተፈፀመ ሊታውቅ ይገባል እንላለን ።
ብልፅግና ይህን ያደረገው ደግሞ የስልጣን ወንበሩን ለዘለቄታው ለማደላደል ሲሆን ወደድንም ጠላንም፣ ገብቶንም ሳይገባን የዚህ የሴራ የፖለቲካ ሻጥር ሰለባዎች ሆነን እንደሰነበትን መላው ሕዝብ ሊረዳው ይገባል።
ብልፅግናዎች ብዙ እውነትና ሃቅ ያዘሉ የሚመስሉ ስበከቶችን እየሰበከ ሲያደናብረን ፣ቃዥቶ ሲያቃዥን፣ የቀቢፀ ተስፋ ህልሙም አንቀንቃኞች አድርጎን ከርሟል።
ሕዝብን ከህዝብ በማጋጨትና በማናቆር ደም እንደጎርፍ እንዲፈስ ብልፅግና ይህን ርካሽ ተግባር ሆን ብሎ እንደፈፀመው መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊገነዘበውይገባል። እንላለን።
የሰሜኑን ማህበረሰብ ዕምቅ የዕምነት የጋራ ቱፊት ብጥስጥሱን ለማውጣት ፣ ለዘመናት ያካበተውን የኢትዮጵያዊነት ስሜት ለማደብዘዝ ፣ ለመናድ ፣ የገዥነት ህሳቤውን ወደተገዥነት ድባብ ጎተቶ ለማውረድ በኦሮምማ ውቅር የተረዳጀው ብልፅግና ብዙ እርቀት መጓዙን ልብ ይሏል።
አማራው ከቀደምት አያቶቹ የወረሰው “የአትንኩኝ ባይነት ፣ የእንቢ ለሃገሬ ፣ ለደንበሬ፣ ለኢትዮጵያዊነቴና ለአይማኖቴ” የሚለውን ትብዕሉና ማንነቱ እንደ ጉም እንዲበን ተረኞቹ የኦሮሙማ ባለሥልጣኖች ከውጭ ጠላት ሃገራት፣ የአማራው ህዝብ ታሪካዊ ገናናት ከማይዋጥላቸው፣ ከአዲሶቹ የኮሎኒያሊዝም አቀንቃኞች አሜሪካና አውሮፓውያን ኃይሎች ጋር በመሆን ባላፉት አምስት ዓመታት ኢ- አሉታዊ ስራዎች እንደሰራ ፣ ደባና ሴራ ሸርቦ ይጓዙ እንደነበር ቢዘገይም አሁን ሕዝብ ገብቶት በቃህ እያለው ይገኛል።
ያም ሆነ ይህ በቅርብ ጊዜ “ሕግ ማስከበር በሚል” መፈክር ከሕውሃት መራሹ ኃይል ጋር የተከወነው ጦርነት “ የታሰበው አሻጥር እንዳልታሰበ ሆኖ ለአማራ ሕዝብ ትልቅ ሲሳይ ፣ ድል እና የነፃነት ካባ አንዲላበስ አድርጎታል።
ወልቃይት፣ ጠገዴ ፣ ጠለምትና ራያ ከ28 ዓመታት የህወሃት ወራሪነት ፣ ሕገ ወጥ አገዛዝና ቀንበር ነፃ ወጥተው ወደ አፅም እርስት ባለቤቶቻቸው የአማራ ሕዝብ ጋር ተመልሰው ተቀላቅለዋል።
ይህ ድል ደግሞ የተበሰረው በአማራ ልዩ ኃይል ፣ በፋኖና የአካባቢ ሚኒሻ የጀግነት ተጋድሎ ፣ በወልቃይት ፣ ጠለምት ፣ ጠገዴና ራያ አፅም እርስት አስመላሽ ቡድኖች የተቀናጀ ትንቅንቅ ፣ መስዋእትነትና የጋራ የትግል ጥምረት ነው።
የአማራ ሕዝብ “ ውለታን የማይረሳ በመሆኑ” ሰሞኑን የተፈጠረው ፈር የለቀቀ ድፍረት አካሃድ እንዳለ ሆኖ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልን ውለታ መርሳት ስስትነት ነው ብሎ ያምናል።
ከህውሃት ጋር በተደረገው እልህ አስጨራሽ ጦርነት የአማራ ልዩ ኃይል፣ የፋኖና የአማራ ሚኒሻ ተጋድሎና ገድል የመከላከያ ኃይሉን ከማስደመም አልፎ በኦሮሙማው የብልፅግና ሹማምንት አድናቆትን በማትረፉ ለሽልማትም እንደበቃ የሚታወቅ ነው። ተደ
የብልፅግና የስልጣን እርካብ ዘመን እንዲሰነባብት ትልቁን ሚና የተጫወተው የአማራ ፋኖ ፣ ልዩ ኃይልና ሚኒሻ መሆኑ የማይታበል ሃቅና እነብልፅግናም የዛሬውን አያድርገውና ውስጠ ህሊናቸው ይህን ሃቅ ያውቁታል።
ይህ የአማራ ልዩ ኃይል ፣ ፋኖና ሚንሻ ታአምራዊ የፍልሚያና የተጋድሎ ብቃት ብልፅግናን አስደንብሮታል ፣ ብርክ ብርክ ብሎታል አስደንግጦታልም።
ይህ እውነታ “ለኛ ሥልጣን መሰንበት ያሰጋናል “ የሚለው የብልፅግና አጓጉል ስሜትና ቅዥት ጣራ ላይ ደርሶ ከልፍስፍሱ የአማራ ብልፅግና ጋር በመተባበር ፋኖን ለእስርና ለእንግልት እንዳበቁት ሁሉ የአማራን ልዩ ኃይልን ለማፈራረስ ከግማሽ ሚልዮን ሕዝብ በላይ ከአስጨረሰው ህወሃት ጋር ብልፅግናዎች ዳግም ጋብቻ ፈፅመው በአማራ ሕዝብ ላይ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም ጀምረዋል ።
ይህ አካሄድ ግን ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚሆንባቸው ጥርጥር የለውም።
በብልፅግናና በህወሃት ያልተቀደሰ ጋብቻ ሊከወን የታሰበው የአማራን ልዮ ኃይል ፣ ፋኖና ሚንሻን የማፈራረሱ እቅድ የበስተጀርባ ዋና ዓላማ ወልቃይት ፣ ጠገዴን፣ ጠለምትና እራያን ለትግራይ ህወሃት የደም ካሳ በመክፈል መልሶ ለማስረከብና የትግራይን ሕዝብ ይቅርታ ለማግኘት የታሰቦ የጉማ ክፍያ ለመክፈል መሆኑ ሳይታለም የተፈታ እውነታ ነው።
ከዚህ ባሻገር ይህ ሰሞነኝው የብልፅግና ቅጥ ያጣ ድፍረትና የድንብር ጉዞ የደቡብ አፍሪካውን የጨረባ ስምምነት ሕጋዊ ለማስማሰል የሚያደርጉት ሻጥርና ተንኮል መሆኑን መላ የኢትዮጵያ ፣ የአማራ ህዝብ ፣ የወልቃይት ፣ ጠለምት ፣ ጠገዴና ራያ ሕዝብ ሊያውቅ ይገባል እንላለን።
“በውኃላ የመጣ ዐይን ያወጣ ” እንዲሉ እጁን ይዞ መብላት ፣ መጠጣት ፣ የኑሮ ዘየና የዘመናዊነት ትብህልን ያስተማረን የአማራ ወንድም ሕዝብ መዳፈር ፣ መግፋትና ማዋከብ ዋጋ የሚያስከፍል እንደሚሆን አትጠራጠሩ እንላለን።
በህወሃት የ27 የግፍ፣ የመከራና የሰቆቃ ዘመናት እንዲሁም በአለፉት አምስት ዓምታት በብልፅግና አደናግሮ የሚያደናግር የአስተዳደር ፣የብልጣብልጥነት፣ የመሰሬነትና እኩይ አመራር በአማራው ህዝብ ላይ ከዚያም አልፎ ፣ በወልቃይት ፣ ጠለምት ፣ ጠገዴና የራያ ሕዝብ ላይ የደረሰው ግፍና በደል መላ የአማራን ሕዝቡ እንደ ብረት እያጠነከረውና አይበገሬ እያደረገው እንደመጣ ሊታወቅ ይገባል እንላለን።
ኋላ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ እንዲሉ እነ ብልፅግናን አደብ ግዙ እንላቸዋለን።
ሁሉም ያልፋል ብሎና በትዕግስት ተክዞ ከተቀመጠ አንበሳ ጀርባ ላይ የዝንጀሮ መቀመጥ ለጊዜው አንበሳው አይነሳም በሚል እሳቤ ዝንጀሮ ቢያፏልላትና ብታሽካካም አያ አንበሳ የተነሳ ጊዜ ግን ዝንጀሮን እኔን አያድርገኝ እንላታለን።
ተዘራ አሰጉ
ከምድረ እንግሊዝ