በውን የኢትዮጵያ የመከላከያ ሃይል በተኛበት ላረዱትና ለወጉት ወራሪዎች ሲል በአማራ ሃይሎች ላይ ቃታ ይስብ ይሆን? – ሰመረ አለሙ

አንዳንዴ የስነጽሁፍን አወራረድ በመልክ በመልኩ ለማስቀመጥ ከጽሁፉ ጽንሰ ሃሳብ በላይ አርእስትን መፈለግ ጊዜ ይወስዳል ምናልባትም ነጋ ድራስ ባይከዳኝ መሰሉኝ “አርእስት ፈልጉልኝ” የሚል መጽሃፍ የጻፉት፡፡የወያኔ ጦር በኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ድባቅ ተመትቶ ወደ ዱቄትነት ከተለወጠ በኋላ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መቀሌ እንዳይገባና ህወአቶች እንዳይጎዱ ከበላይ አካል ትእዛዝ ተሰጥቶ ያረዱት የመከላከያ ሃይል ላይ እልሁን ሳይወጣ እንደቋመጠ አቀርቅሮ ከርቀት ተመልሷል፡፡ ይህ ትእዛዝ በዶክተር አብይ ይሁን በዶ/ር አብረሃም በላይ፤በሙሉ ነጋ (የህወአት ቁልፍ ሰውና የመከላከያ ሚኒስቴር) ይሆን ወይም በኦሮሙማ የበላይ አካል ዉሳኔ እስክ አሁን ጥርት ያለ ግንዛቤ አልተገኘም፡፡

የኢትዮጵያን የመከላከያ ሃይልን ያረደ በዚህ አይነት በክብር ሲስተናገድ ማየት ሃገሬን ሃገሬን ለሚል ዜጋ ልብ ያደማል፡፡ ሃገር በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች አብይ አህመድ ድርድር በሚል ሰበብ ወደ ፕሪቶሪያና ወደ ናይሮቢ የአማራ ሃይሎችና አፋሮች ዋናው የጥቃቱ ሰለባ ሳይካተቱበት በመሄድ ድርድሩ ምን እንደሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይገለጽ በዚያኛው ተደራዳሪ ህወአት በዚህኛው ተደራዳሪ የህወአት የውስጥ ሰው ሬድዋን ሁሴን በመሆን በህወአት ፍላጎት ድርድሩን ቋጩት፡፡ ይህን ተከትሎም ታገሰ ጫፎና የፍትህ ሚኒስቴሩና የሃገር ፍቅር ስሜትና ቁጭት የማይስማቸው ሙትቻ ተሿሚዎች በመቀሌ የደብረጽዮንን ጉልበት ተሽቀዳድሞ በመሳም ዳግም የወከላቸውን ህዝብ አዋርደው ተመለሱ፡፡
ዛሬ ወደ ባህርዳርና ወደ ተለያየ የአማራ ክልል በመሄድ አማራ አንድም የአማራ ታጣቂ እንዳይኖር አገዛዙ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ይልቃል ከፍያለው ደግሞ ለዳግም ውርደት “ከትግራይ ወንድሞቻችንን ጋር እንደራደራለን” የሚል ማብራሪያ ሰጠ አይ ወንድሞች፡፡የትግራይ ፋሽስቶች የቀማነውን የአማራ መሬት ወደ ክልላችን ዳግም ካትተን ከኢትዮጵያ እንገነጠላለን በሚለው ግልጽ አቋማቸው እንደጸኑ ነው፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ አማራው ባልመረጣቸው በሌሎች ተመርጠው አማራውን በባርነት እንዲገዙት በተመደቡ ሰዎች አማራው መከራውን እያየ ነው (አገኘሁ ተሻገር፤ደመቀ መኮንን፤ግርማ የሽጥላ፤ሰማ ጥሩነህ ቀደም ሲል በረከት ስሞን ታደሰ ጥንቅሹ እያለ የመጣው ሁሉ የሚጭነው አሳፋሪ ስብስብ ነው)፡፡ በረከት ስሞን በአንድ ወቅት እንደነገረን ውስጣችው የሚረባ ሰው የለበትም አፈጣጠራቸውም አገልጋይ እንጅ መሪ እንዲሆኑም አልነበረም፡፡ እሱው ቀርጾ ስለሰራቸውም ይህንን አባባል መቃወምም አይቻልም እንግዲህ ይህ በሆነበት የአማራው የወደፊት እጣው በነዚህ ሰዎች ምን ሊሆን ይችላል ? ብሎ ማሰብ በጣም አስጨናቂ ሁኗል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  "የአሲምባ ፍቅር" - መጽሃፍ ቅኝት - በክንፉ አሰፋ

በፕሪቶሪያው ስምምነት የኦሮሙማው መንግስት ህወአት የጠየቀውን ሁሉ ተቀብሏል ህወዋት ወልቃይትና ጠገዴ ራያን የመሳሰሉ የአማራ ግዛቶችን ዋናው አጀንዳው አድርጎ ለመጠቅለል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ የአማራ ሃይሎች ሊቃወሙ ቢሞክሩይህንን በሃይል የማስፈጸም የመከላከያ ሃይሉ ስራ ይሆናል ተብሎ ይታመናል፡፡ በሌላ በኩል ህወአት ኤርትራንም መተናኮሉን አላቆመመ:: ካሁን በኋላ ህወአት ከኤርትራ ሃይሎች ጋር በቀጥታ አይዋጋም ውጊያን በተመለከት ስራው የተተወው ለመከላከያ ሃይሉ ነው የሚሞተውም ኢትዮጵያዊው ሃይል ነው፡፡ ይህች ነች ስምምነት ማለት የመከላከያ ሃይላችን ዋናው ስራው የህዋአትን ሃገረ መንግስትነት ተግባራዊ ማድረግና ወንድሞቹን መፍጀት ይሆናል ማለት ነው፡፡ በእርግጥ እነ አበባው ታደሰ የትላንቱን ረስተው ጦሩን እየመሩ ትላንት የታደገውን የአማራን ህዝብና የኤርትራን ሰራዊት ይፈጁት ይሆን? ጊዜ ይፍታው፡፡

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሃይል በተኛበት በጭካኔ ታርዷል ይህን አስመልክቶ የላከው የአብይ አህመድ መንግስት ይህ ወንጀል ከዜጎች አእምሮ እንዲጠፋ አጥብቆ እየሰራ ነው አሁን ላይ አራጆቹ ህወአቶች የታረዱ እንጅ የኢትዮጵያን የመከላከያ ሃይል ማረዳቸውን እንድንረሳው እነ ሬድዋን ሁሴን በርትተው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ እኛ ግን የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል በሚጠብቃቸው ከሃዲዎች የታረደበትን ቀን በየአመቱ ማክበራችንን እንቀጥላለን፡፡ የኦሮሙማው ሽመልስ አብዲሳም ጌታቸው ረዳን ጠርቶ ትላንት ምንም እንዳልተደረገ ሁሉ ፍቅር በፍቅር የሆኑበትን ምስል አጋርተዋል ይህን በማድረጋቸው የኢትዮጵያን መከላከያ ሃይል መክዳታቸውን ግን የተገነዘቡት አይመስልም፡፡ የአማራ ሚሊሽያ ፋኖ ልዩ ሃይል ከምንም በላይ የመከላከያ ሃይሉን ተከትሎ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ለሃገሩም ሆነ ለመከላከያ ሃይላችን ውድ ህይወቱን መስጠቱን በቦታው የነበሩ ዘጋቢዎች በተቀረጸ ምስል ሲያስቀሩልን የመከላከያ ሃይሉም ይህንን ውለታ እንደማይረሳ በወቅቱ ገልጿል ወደፊትም ትውልድ እንዲያውቀው በመጽሃፍ መልክ ይወጣል፡፡
ጠ/ሚኒስትሩም ሳይወደ በግድ ነብሱን ያዳኑትን የአማራ ሃይሎችን ገድል እየተናነቀውም ቢሆን በመጠኑ ገልጾታል፡፡ ትላንት የአማራ ህዝባዊ ሃይል አብይ ያስታጠቀውን የህወአትን ወራሪ ሃይል ገድቦ ባያቆመው አብይ እሬሳው ከቤተ መንግስት ተጎትቶ ህይወቱ በውርደት እንደ ጋዳፊና ሳዳም ሁሴን በተጠናቀቅ ነበር፡፡ ይህ ክፉ ጠ/ሚኒስቴር ጦርነቱ ሳያልቅ ጦሩን ከፋኖ ሲለየው “የድል ሽሚያን አቁሙ” ብሎ በመናገር ነበር የተገኘው ድል ላይ ውሃ የቸለሰበት፡፡ እዚህም ላይ ሳያቆም ምእራብ ትግራይ ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጦርነቱ በኋላ የጠራው ይኸው ጠ/ሚኒስቴር ነበር፡፡ በወቅቱ አብረሃ በላይ፤ ሙሉ ነጋ.፤ አብረሃ ደስታ ቃል ገብቶልናል ወልቃይትን ሊሰጠን ተስማመቷል ብለው ሲናገሩም ተደምጧል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በጠንካራ መሰረት ላይ እንድንቆም - ይርጉ እንዳይላሉ

ነገሩን ለማሳጠር የአማራ አጽመ ርስቶችን ለኦሮሙማና ለትህነግ ለረከሰ አላማ ሲባል ወልቃይትና ጠገዴ ሌሎች የአማራ መሬቶች ለትህነግ ሊሰጡ ተቆርጧል፡፡ ይህ የአማራ የህልውና ጥያቄ ስለሆን 10000 አማራን አንገት በስለት የቀነጠሰ የትግሬ ፋሽስት ወራሪ ሃይል ዳግም ወደ አጽመ ርስቱ ተመልሶ ከሚያላግጥበት የአማራ ሃይል በአንድነት ሞትን መርጧል ሳይወድ በግድም ተገድዶ የመገንጠል ጥያቄንም እንደ ሌሎቹ ሁሉ እያሰበው ይገኛል፡፡ በእርግጥ ቀደም ብሎ በውስጡ ያሉ እንቅፋቶችን ማስወገድ የመጀመሪያው ስራው ይሆናል፡፡ እንግዲህ የኦሮሙማን ፍላጎትና የትህነግን መሰሪ አላማ ለማሳካት ይህ ትላንት በትግሬ ፋሽስቶች የታረደው የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይልን ለማዳን ቀድሞ ህይወቱን በሰጠው በአማራ ሰራዊት ላይ መከልከያው ቃታ ይስባል? ይህ ወደፊት የሚታይ ይሆናል ከምክንያት አንጻር ሲታይ ግን የሚሆን አይመስልም ክትህነግ ወራሪ ሰራዊት ይልቅ የአማራው ሃይል በአስቸጋሪ ሁኔታ ከጎኑ ቁሟልና፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል የሃብታም አሽከር ሳይሆን ሃገርና ድምበርን የሚያስከብር ህዝባዊ ጦር በመሆኑ አሁን የሚገነገነውን ተንኮል በንቃት ሊከታተል ይገባል፡፡ ትላንት ለሞቱለት ወገኖቹ ክብር እንጅ ጥይት ስለማይገባቸው ቃታውን ወደ ውድ ወገኖቹ እንዳይስብ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡ ይህንን ሳያደርግ በኦነግ ተንኮል በነ ጄነራል አበባው ደባ ከተጠለፈ ዳፋው ከምንም በላይ ለራሱ ለጦሩ ሊሆን ስለሚችል ከወዲሁ ቢታሰብበት መልካም ነው፡፡ ጌታቸው ረዳ በብርሃኑ ጁላ፤በጫላ ደበሌ፤በነ አበባው ላይ ምን ያህል ያላግጥ እንደነበር ጎግሎ መመልከት ማንነታቸውን ስለሚያሳይ አሁንም ጦሩ እራሱን ከውርደት ሊጠብቅ ይገባዋል እንላለን ነገ ትህነግ ጦርነት መክፈቱ የማይቀር ነው ይህ በሆነበት መከላከያው ህዝባዊ ድጋፍ ቢፈልግ ህዝቡ ስራህ ያውጣህ ለማለት ይገደዳል፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
semere.alemu@yahoo.com

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሳኦል በሽታ - አስቻለው ከበደ

4 Comments

  1. የብልጽግናው ሰው አዲሱ ለገሰ ሩዋንዳን በማንሳት እኛም ሃገር እንዲያ ሊሆን ይችላል ይለናል። ባይረዳው ወይም ረስቶ ካልሆነ በስተቀር በዘር ሰዎች እየተለዪ በእሳት ሲጋዪ፤ በገደል ሲጣሉ፤ ከተወለድበት ምድር ሲፈናቀሉ ማየትና መስማት ከጀመርን 40 ዓመት እየተጠጋ ነው። ችግሩ በዘሩና በቋንቋው ለሚያሰላ ወስላታ ፓለቲከኛ የእርሱ ክልል ወይም መንደር ደህና እስከ ሆነ ድረስ ዓለም ሁሉ ሰላም ውሎ ያደረ ይመስለዋል። ሲጀመር የብሄር ፓለቲከኞች አስተሳሰብ ከአፍንጫቸው አይርቅም። ለዚያ ነው ዛሬ ላይ የሩዋንዳን እጣ ሊገጥመን ይችላል የሚሉት። አሁን በምድር ላይ ያለውንና የሚሆነውን የክፋት ጥግ እንዳላዩ በማለፍ ይመጣል ለሚሉት ያላዝናሉ።
    የሩዋንዳው መሪ ፓል ካጋሚ በተደጋጋሚ ጠ/ሚ አብይን የዘር ፓለቲካ እንደማያዋጣ አስረግጠው ነግረውታል። ግን በወያኔ ጽዋ የተቃመሰውና በቃል ጋጋታ ሰውን የሚያሰለቸው ጠ/ሚ ይህን ምክር እስከ አሁን አልሰማም። ዛሬ ላይ ቆም በማለት በትግራይ፤ በአማራ፤ በአፋርና በሰሜን ሽዋ እልፎችን የጨፈጨፈውና እንዲሁም ወደ ኤርትራ የተውሶ ሮኬት ያስወነጨፈው ወያኔ ከዚህ ሁሉ ጥፋትና እልቂት ያተረፈው ያው እንደ 50 ዓመቱ ልማድ ሰቆቃና ለቅሶ ብቻ ነው። አሁን ጌታቸው ረዳ አዋቀረ የተባለው የ27 ሰው ጥንቅር የሚያሳየን በጭራሽ ወያኔ ከትግራይ ህዝብ ጀርባ ለመውረድ እንደማይፈልግ ነው። ግን የጠራ አስተሳሰብ ሳይሆን ጠበንጃ በሚያራኩታት ትግራይ ለምን ብሎ መጠየቅ የጅብ ራት ያስደርጋል። እኔ የወያኔ መሪዎችን ሳስብ አንድ ነገር ይገርመኛል። ሥልጣንና ሃብትን በቃኝ አለማለታቸው። እድሜአቸው የገፉ አዛውንቶች አሁንም በስልጣን ኮረቻ ላይ ቁጭ ብለው የማይጨበጥ ህልም ለህዝባቸው ሲናገሩ መስማት እግዚኦ ያሰኛል። የማን ልጅ ነው ከህዋላና ከፊት እየተተኮሰበት የሞተው? አካለ ጎዶሎ የሆነው? የተሰደደው? የወያኔ ባለስልጣናት? ጭራሽ። የድሃ አርሶ አደር ልጆች እንጂ። ወያኔ ይቅር የማይባል የአረመኔ ስብስብ ነው።
    የአዲስ አበባ የብልጽግና መንግስት ጥሉ ከአማራ ጋር እንጂ ከወያኔ ጋር አይደለም። አሁንም አሜሪካ በሰጠችው ትዕዛዝ መሰረት የአማራ ታጣቂዎችን ትጥቅ አስፈታለሁ ማለቱ የቱን ያህል የደነቆረ እንደሆነ ያሳያል። ሰው እኮ ትጥቅ የሚያወርደው መተማመንና ሰላም ሲኖር ነው። በፕሪቶሪያና በናይሮቢ ተፈጻሚ ይሆናል የተባለውን ጉዳይ በትግራይ ሳያስተገብር እናንተ ይህን አርጉ ያን አርጉ ማለት ተጃጅሎ ማጃጃል ነው። ወያኔ በታሪኩ ሰላምን አያውቃትም። ወያኔ ሳይከስም በምድራችን ሰላም ይኖራል ማለት ውሸት ነው። አሁን ተመረጡ የተባሉት የትግራይ ጊዜአዊ አስተዳደር አባላት ከኋላ የሚገፏቸው የተንኮል ቋቶች ድብቅ የወያኔ የቀድሞ ባለስልጣኖች የውጭ አጋሮቻቸው ናቸው። በራስ አስቦ፤ አቅዶ፤ በራስ ተማምኖ መስራት በሃበሻ መሬት ውስጥ የለም። ይህም በሽታ ለብልጽግናው መንግስት ተጋብቶበት በዚህም በዚያም ሰውን ዘብጥያ እያወረደ ባማሩ ቃላት ይሸንግለናል። እውነቱ ሲፈተሽ ወቸው ጉድ የዚህች ሃገር መጨረሻዋ ምን ይሆን ያስብላል።
    የዛሬ አምስት ዓመት ገደማ የተዘፈነላቸው፤ ዲያስፓራው እንደ ጣኦት ያያቸው ጠ/ሚሩ ቆይተው አፍቃሪ ኦሮሞ መሆናቸው የተቃመሱትን የፓለቲካ ሸፍጥ ያሳያል። ፓለቲካ በወሬ አይመራም። ፓለቲካ ምድር ላይ በሚገኘው የጊዜው ክስተት ይመዘናል። ግን አፓርታይድ ለሰፈነባት ለአሁኗ የሃበሻ ምድር መጠራጠር፤ መካሰስ፤ መታሰር፤ መፈታት፤ መደብደብ፤ መገደል፤ ቤት ማፍረስ፤ መደስኮር ወዘተ. የሚስተናገድባት የእብድ ምድር ሆናለች። ባጭሩ ዓለማችን በተለያዪ ጉዳዮች ትግል ላይ ናት። የዚህ ሁሉ ውጤቱ ግን እንኩሮና አሻሮ ብቻ ነው። 70 ዓመት ሙሉ የተለፋበት የሩሲያው ፓለቲካም በአንድ ጀንበር ነው ፍርክርኩ የወጣው። ሰው እንዴት ከዓለም ታሪክ አይማርም። አሁን ራሷን የዓለም ቁንጮ አድርጋ የምታየው አሜሪካ ከ30 ቲሊሪዪን በላይ በእዳ የተዘፈቀች ( 12 ዜሮ ከቁጥሩ በህዋላ ይታከልበት)፤ የቀድሞ የበላይነቷ የተሸረሸረባት፤ በሃገሯ ውስጥ እልፍ ችግር የተቆለለባት ሃገር ናት። በቅርቡ Hate in the Homeland: The New Global Far Right by Cynthia Miller-Idriss ሳነብ የተረጋገጠልኝም ነገር የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች የሚለው አባባል ነው።
    ስለሆነም አሁን ጠ/ሚሩ ከአማካሪዎቹ ጋር የአማራ ልዪ ሃይልን ለማፍረስ መጣሩ በአሜሪካ ታዞ ነው። እኔ በመሰረቱ ሁሉ ነገር ሰላም ከሆነና ወያኔና የአማራ ሃይሎች ሰላም ካወረድ የኦሮሞ ታጣቂዎችም ትጥቅ ከፈቱ የትጥቁ ብዛትና ጋጋታ ዛሬ ላለው የድሮን ውጊያና ስልት ምን ሊረባ? ያው ሰፈር ለማስጨነቅና ቡራ ከረዪ ለማለት ካልሆነ በስተቀር። ግን የኢትዮጵያ ሰራዊት ለሃገሪቱ ህዝቦች ሰላምና ዋስትና የሚሰጥበት ብልሃትና መንገድ ተመቻችቷል? እንደምናየው ከሆነ ውሸት ነው። ግራም ነፈሰ ቀኝ የብልጽግናው (የድህነቱ) መንግስት በቅድሚያ የፕሪቶሪያውንና የናይሮቢውን ስምምነት ቢያስተገብር ለቀረው የወደፊት እቅድ ጠቃሚ ይሆንለት ነበር። ግን በነጭ ሃይል እየተገፋ ታዞ ለሚኖር መንግስት በራስ ማሰብ ከባድ ነው። አንድን የክልል ሃይል ትጥቅ አስፈትቶ ሌላውን በርታ ማለት ግን ያው የብልጽግናው አባል አቶ አዲሱ እንዳለው ከአሁኑ የባሰ እልቂትና መገዳደልን ያመጣል።

  2. የፋኖ አጉል እብጠት በቅጭኗ መርፌ እንደፈነዳ ፊኛ ሆነ? ያዉም ባንድ ቀን! በመጨረሻ ኢትዮጵያ ካንዠበባት ሽብርና ለከት የለሽ አሸባሪዎች ነፃ ወጣች። ለዚህ ያበቃን የኢትዮጵያ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!

  3. Mesay በቅጭኗ መርፌ ፈንድቷል ማለት ነው? የህወአትስ? እስቲ ይሄንንም ጊዜ ይፍታው ሁኔታህ ግን አንተም ተንፈስ ያልክ ትመስላለህ ምን ያህል እንዳስጨነቀህ ጽሁፍህ ያሳብቃል፡፡ ፋኖ ማለት ሩሲያ ነው ከጠፋም ብቻውን አይጠፋም፡፡

  4. የፈራነው አልቀረም ለገደሉት ሲል ህዝቡ ላይ ተኮሰ እንዲህ ያለ ወንጀለኛ ጦር ከአካባቢው እንዲወጣ መፍቀድ አግባብ አይደለም ህዝብን የሚኪላከል ሳይሆን ወንጀለኛን የሚከላከል ነውና፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share