መዝቀጥ እንደ አብይ አህመድ – እውነቱ ቢሆን

<..እኛ አገር ማፍረስ ከፈለግን ማን ነው የሚያስቆመን? የሚያቆመን አለን?..> ከህግ በላይ የሆነው አብይ ባለፈው ሳምንት  ለሙቱ ፓርላማ ከተናገረው የተወሰደ

(እውነቱ ቢሆን)

በአለም ላይ መቋጫ በሌለው ውሸት ተጀቡኖ እልቂትን እየደገሰና ለራሱ ህዝብ ሞት ደስታን እየፈጠረ ስለ ራሱ ታላቅነት ብቻ ቅዠት እየቃዠ የሚኖር በቁሙ የዘቀጠ እንደ አብይ አህመድ ያለ ሰው ተፈልጎ አይገኝም፡፡

የወያኔ 27 አመታት አገዛዝ በህዝቡ ትግል ተሽቅንጥሮ ወያኔ ከመሀል አገር ተባርሮ ወደ መቀሌ ሲሄድ አጨናባሪው አብይ አህመድ  ደመቀ መኮነንንም ፣ ገዱ አንዳርጋቸውንና ለማ መገርሳንም “ቁጩ” ሰርቷቸው አብይ በመሪነት ቦታ ላይ ተቀመጠ፡፡ ድራማው ታሪካዊ ነበር፡፡ የአማራ ክልል ህዝብ ያኔም በወያኔ ተንገሽግሾ ስለነበረ ሲሆን ብዙ በደሎችና ግፎች ደርሰውበታል፡፡ ወያኔ በህዝብ ትግል ተሽቀንጥሮ ከማእከል ሲባረር የአማራ ክልል ህዝብ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ  ለአብይ አህመድ ከማንም ቀድሞ ደስታውን  በይፋ ገለጸለት፡፤ በውጭ አገራትም በተለይ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ዲያስፖራው ንቅንቅ ብሎ ወጥቶ አብይን ደግፎ ደስታውን ገለጸ፡፡ ያ ሁሉ የአብይን ማንነት ካለማወቅና የወያኔን ድርጊት ከመጥላት የመነጬ ነበር፡፡ አይፈረድበትም፡፡ እዚህ ላይ “” አረሱት”” በሚል መጠሪያ ዘፈኑ የሚታወቀውን አርቲስት ፋሲል ደመወዜ ለአብይ አህመድ ያኔ የገጠመውን ግጥም እንመልከት፡፡

<< አሼሼ አሼሼ ……አብይ መጣልን ከመሼ>>

ታዋቂው አርቲስት ፋሲል ደመወዜ ይህንን ግጥም የያዘ ዜማ ለአብይ አህመድ ያኔ ከመዝፈኑ ከአመታት በፊት ወያኔ ከአማራው በጉልበት ወልቃይትንና ራያን ወስዶ ወደ ትግራይ ከልሎት ስለነበረ የያኔውን  የአማራን ህዝብ ሲሰሰቃይ የነበረበትን ሁኔታ ለመግለጽ የገጠመውን የሽለላ ግጥም አሁንም ላንሳ፡፡ ግጥሙ ይህ ነበር፡፡

<< አረሱት ያውም የእኛን መሬት ያውም የእኛን እጣ ……..        እነርሱ ምን ያርጉ ከእኛ ሰው ሲታጣ>>>

ጥላሁን ገሰሰ በዜማው እንዳለው አንዳንድ ነገሮች ይገርማሉ፡፡አሁንም ይሄዉና ራያና ወልቃይት ዳግም በተረኛው ኦሮሙማም ጊዜ የእልቂት መንስኤ ሊሆኑ ጫፍ ደርሰዋ፤ል፡፡ አንድ ነገር ግን በእርግጠንነት መናገር ይቻላል;፡፡ ነብይነት አይደለም፡፡ ወልቃይትና ራያ ቢፈልግ በካሽሚርነት ይመሰል፡፡ ቢፈልግም በጋዛ ሰርጥነት ይመሰል፡፡ አንድ ነገር ግን እርግጥ ነው፡፡ አማራው ምንጊዜም እነዚህን እጅግ ለም የሆኑ ታሪካዊ ርስቶቹን ለወያኔ አሳልፎ አይሰጥም፡፡ በፈለገው ስርአት ትግሉና ዉጊያው የፈለገውን ጊዜ ይውሰድ እንጅ መሬቶቹ የአማራ ርስቶች ሆነው ይቀራሉ፡፡

 

አብይ አህመድን ህዝቡ እንዴት ያየዋል የሚለውን እንፈትሽ፡፡ እንዳው በሞቴ አብይን ምን ትሉታላችሁ?? አታላይ፣ አጭበርባሪ፣ ውሸታም፣ ቁጭ በሉ፣ ምስኪን፣ ጥሩ ልብ ያለው ግን አቅመ ቢስ፣ ተስፈኛ፣ ፈላጭ ቆራጭ ድክታተር፣ ግጭት ጠማቂ፣ ሰው ጠል፣ እውር ድንበሩ የጠፋበት ግራ የገባው ባተሌ፣ ሰይጣን፣ ጋኔን፣ ደም የጠማው አውሬ፣ ራሱን ጠልፎ የጣለ መካሪ የለሽ መሪ፣ ጥጋብ የነፋው ዱርዬ፣  እናቶች የሚጸልዩለት ጥሩ ሰው፣ ሀይማኖተኛ፣ ምሁር፣ ሩህሩህ፣ ጨካኝና አረመኔ  ሰው…… ወዘተ???  የፈለጋችሁትን ደርድሩ፡፡

በአገሪቱ ውስጥ መሬት ላይ ካለው ተጨባጭ፣ የሚታይና የሚዳሰስ እውነታ አንጻርና ከ120 ሚሊዮኑ ኢትዮጵያዊያን  ከሚገፉት የመከራ ኑሮና የመከራ ህይወት አንጻር ህዝቡ ስለ”መሪ” ተብየው ስለአብይ አህመድ ስብእና ምን ይል ይሆን??  ከአገሪት  ውድቀትናተስፋዋ የቸለመባት አገር ከመሆን አኳያ ብዙሀኑ ኢትዮጵያዊ ህዝቡንም አገሪቱንም ለዚህ ያበቃትን አብይ አህመድን ምን ይለው ይሆን??

ህዝቡ  የውሸት ቋት በሆነው በስም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሚባለው በተግባር ግን የኦሮሙማው ብልጽግና ቴሌቪዥን  ፕሮፓጋንዳ ማሽን በሆነው <<የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን>>በየቀኑ አብይ የሚለውን ስም ሲሰማና ምስሉን በየቀኑ እንዲያይ ስደረግ ህዝቡ ምን ይል ይሆን??

ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጧል ቢሆንበትም ህዝቡ የትናንቱን የወያኔ የስቃይ ጊዜ ከአሁኑ የኦሮሙማ የእልቂትና የገሀነም ወቅት ጋር ሲያያወዳደረው አሁን በመኖርና ባለመኖር መካከል ሆኖ የሚያቃትተው ህዝብ ስለ ኦሮሙማ፣ ስለኬኛ ፖለቲካና የስቃዩ ሁሉ ምንጭ ስለሆነው ግለሰብ ስለ አብይ አህመድ ምን ይሰማው ይሆን?

የህዝቡ ቁጥር በመቶኛ ቢስላና አብዛኛው ህዝብ ምናልባትም 90% እና ከዚያም በላይ ያለው ህዝብ አብይን የት ይመድበዋል ብላችሁ ትገምታላችሁ?? ታሪክስ??

አለም ብዙ ድክታተሮችን አይታለች፡፡ ታሪክም ይህንኑ መዝግባ ይዛለች፡፡ ለዚሁም የጀርመኑ ሂትለርና የጣሊያኑ ሙሶሎኒ ዋና ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ሌሎችም ነበሩ፡፤ አሁንም አሉ፡፡ በመሰረቱ ድክታተር የሆነ ሰው ከስሩ ያሉት ሰወች የሚሰግዱለት እንጅ ሀሳብ አቅርበው የሚያማክሩት፣ እንዲያ ሲልም አይበጅም፣ ይቅርብህ፣ አይሁን የሚሉት ፣ግፋ ሲልም በሀሳብ የሚሞግቱት አይደሉም፡፤ በጭራሽ!!

አብይ አህመድ ስብእናው የዘቀጠ ብቻ ሳይሆን ሰው የሆነ ፍጡር ይፈጽማቸዋል ተብለው በማይገመቱ አሰቃቂና ሰቅጣጭ የወንጀል ስራወቹ ተጨመላልቆና ገምቶ የከረፋ ሰው ነው፡፡ ግድያንን በሚለከት ካስገደላቸውታዋቂ  ሰውች ውስጥ ብቻ ጥቂቶቹን እንጥቀስ፦ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ፣  ጀኔራል አሳምነው ጽጌ፣ ዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ አቶ ምግባሩ ከበደ፣ ጀኔራል ጸአረ መኮንን፣  አቶ አዳሙ ረታ ወዘተ (አብዛኛው አማራወች) ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ሰወች ለስልጣኔ ያሰጉኛል ብሎ ራሱ በቀጥታ ያስገደላቸው እንቁ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ ስለነዚህ ታዋቂ ሰወች አሟሟት እስካሁን ምን ተደረገ??ምን ማታራት ተካሄደ?? ምንስ እርምጃ ተወስደ???  ውሾን ያነሳ ዉሾ ሆኖ ቀረ፡፡ እርሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ የተካሄዱት በአገርና በህዝብ ላይ  የተካሄዱት ዘግናኝ ድርጊቶች ብዙ ናቸው፡፡ ምሳሌ አፈናን በሚመለከት አንድ ምሳሌን ብቻ እንጥቀስ፦ ምስኪን የሆኑ ከ19 በላይ የአማራ ሴት ዩኒቨርሲቲ ተማሪወች በአማራነታቸው ታፍነው እርሱ በሚመራው የአክራሪ ኦሮሙማወች አንዱ ክንፍ  እንዲወሰዱ አስደርጎ እስከዛሬ ድረስ እነዚያ ሴት ተማሪወች ወሬያቸው ተዳፍኖ እንዲቀር አድርጓል፡፤

በሚስቱም በኩል ሆነ በራሱ በኩል ከውስጥም ይሁን ከውጭ ምንጩ እንደኤትና ከየት እንደእሆነ ያልተገለጸ አጠቀቀሙም ብሄራዊ ባንኩም ሆነ የአገሪቱ ገንዘብ ሚኒስቴር ያልመዘገበው የማያውቀውና የማይቆጣጠረው ከፍተኛ ገንዘብ ይግበሰበሳል፡፡ ዘራፊነቱንና፣ በተለያዩ የኬኛወቹ ክንፎች በመንጋወች አዘራፊነቱን፣ ጨፍጫፊ አስጨፍጫፊነቱን በሚመለከት ብዙ መረጃወችና ማስረጃወች ተሰደረው የፍርድ ቀንን እየተጠባበቁ ነው፡፡ እርሱ ግን በወንጀል ስለመጨመላለቁ አሁን ላይ ዘግይቶ  የባነነ ቢመስልም አሜሪካ “”ጥላ ጠለላ”” ሆና ታድነኛለች በሚል ተስፋቢስነት ሙልጭ ብሎና ጠቅልሎ ወደለየለት አገር ሽያጭ ገብቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  መንጋነት እና ፓለቲካል በግ’ነት ተነጣጥለው አይታዩም ( አባታጠቅ  ምንዳሁነኝ )

አገሪቱ ከድንበር 50 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ዘልቆ በሱዳን ተወርራ፣ የእርስ በእርስ እልቂቱ በየቀኑ መቶወችንና ሽህወችን እየበላ፣አሁንም ዜጎች በማንነታቸው እየተለዩ እየተገደሉ እየተፈናቀሉ ቤቶቻቸው ባላያቸው ላይ በሽመልስ አብዲሳ አፍራሽ ቡድን ቤቶቻቸው እንዲፈርስባቸው እየተደረገ አብይ አህመድ ግን አሁንም አይኑን በጨው ታጥቦ ወጥቶ ኢትዮጵያ አትፈርስም ይለናል፡፡ አብይ አህመድ ግን ኢትዮጵያ አድጋለች ፣ተመንድጋለች በልጽጋለች፣ዲሞክራሲን አስፍናለች ለሁሉም እኩል ሆና በእኔ አገዛዝ  ምቹ አገር ሆናልናለች ይለናል፡፡ ይህ ሁሉ ሀሰት ነው፡፡ ፍብረካ ነው፡፡  ውሸት ነው፡፡ ማታለል ነው፡፡ ሰውየው ግን ትናንትም ዛሬም በሀሰት ይቀደዳል ፣ እንደገናም አንድ ቦታ ላይ ድንገት ይከሰትና  እንደ አቡጀዲ ጣቃ በውሽት “ይተረተራል”፡፡

ስለመተርተሩ አንዲት የቅርብ ቀናት ገጠመኝን ላንሳላችሁ፡፡ ባለፈው ሳምንት በአማራውላይ የሚሰራው ግፍ ሞልቶ የፈሰሰ መሆኑን ህዝቡ በቁጣ ለመግለጽ የህዝብ የተቃውሞ ሰልፍ በተጠራበት እለት በጎንደር ከተማ  ፋሲሊደስ ቤተመንግስትን በአስወጊው ግለሰብ በዲያቆን ዳናኤል ክብረት አስጎብንነት ጉብኝት ሲያደርግ የተናገረው ትንሽ ፈገግ ያስኝ ነበር፡፡አብይ በቦታው ላይ እንዲዚህ አለ፡፡ “….’አባቶቻችን የሰሯቸውን የታሪክና የስልጣኔ አሻራወችእያለ   ሲዘረዝር የአክሱም፣ የዛጉየና የፋሲለደስ ብሎ ሶስቱን ከጠቀሰ በኋላ የፋስሊደስ ቤተመንግስት ሲሰራ እነ እንትና ከዚህ እነ እንትና  ከዚያ መጥተው ተሳትፈዋል ብሎ ገለጸ፡፡ ኦሮሞም በወታደርነት በጥበቃ ተሰማርቶ አስተዋጾ አድርጓል >> ብሎት አረፈው፡፡ ከዚያስ ለምን “”አባቶቻችን”’ ብሎ ጅምሮ በኦሮሚያ ላሰሩት የስልጣኔና የታሪክ አሻራወች አልገለጸም?? ምሳሌ በተስፋየ ገብረአብ የልብወለድ ታሪክ እነጃዋር ስላስሩት የአኖሌ ሀውልትና ሌላም ሌላም የታሪክ አሻራወች ካሉ እርሱ ራሱ ስለመጣበት ክልል መግለጽና መጥቀስ ነበረበት፡፡እውነቱ ግን የእርሱ አባቶች የአክሱምም ሆነ የዛጉየ እንደዚሁም የፋሲሊደስ ስልጣኔወች ወቅትና አሻራወች ላይ ተስትፎ አልነበራቸውም ሳይሆን በቦታው ላይ አልነበሩም፡፡ ሀቁ ይሄ ነው፡፡

ወደ ርእሳችን እንመለስ፡ አብይ በአመዛኙ በሆዳሞቹ የአማራ ሹመኞች እሽኮለሌ ባይነት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ የስልጣን ኮርቻ ከመቆናጠጡ በፊት “እርካብና መንበር” በሚለው መጽሀፉ ላይ ስልጣን እንዴት በሴራ፣ በተንኮልና በማጭበርበር እንደሚያዝ ጽፏል፡፤ በዚህ መልክ አንዴ ስልጣን ላይ ከተወጣም በኋላ እንዴት አድርጎ ህዝብን በዘርና በጎሳ ለያይቶ፣ በምላስ አታልሎ፣ በቁራሽ ስልጣንና በማይረባ ጥቅም ደልሎ፣ አንዱን ከአንዱ ከፋፍሎ፣ በጉልበት ረግጦ፣ እርስ በእርስ አናክሶና፣ አባልቶ የአገዛዝ ዘመንን ማራዘም እንደሚቻል ተንትኖ ጽፏል፡፡ አሁን እየሰራ ያለው ያንን ነው፡፡

አብይን << ..ይህ ለአንተም በስልጣንህ መቆየት፣ ለአገሪቱም አንድ መሆንና ለህዝቡም ኑሮ የሚበጅ ድርጊት፣ እቅድና እርምጃ አይደለምና ይቅርብህ አታድርገው …>> ብሎ የሚመክረው አንድም ነጻ አእምሮ ያለው ሀቀኛና ሚዛን የሚደፋ ሰው በአጠገቡ የለም፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት አብይ ራሱ ይህ አይነቱ ሰው በአጠገቡ እንዳይኖር አስቀድሞ አሳምሮ ሰርቷልና ነው፡፡

ስለሆነም አብይ በዙሪያው የኮለኮላቸው በሁለት ምድብ ተከፍለው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ በትልቁ ምድብ ውስጥ ያሉት በኦሮሙማ አክራሪነት የተሰባሰቡ አደገኛና ተረኛ የኬኛ ጅቦችን ሲሆን በአናሳ ቁጥር በሁለተኛዋ ምድብ ውስጥ ደግሞ ውርውር የሚሉት  ሆዳም የአማራ ሹመኛ ተብየወቹ ናቸው፡፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉት ከየክልሉ የሰበሰባቸውና በብልጽግና ፓርቲ ማህበር “”ጠበልተኞች”” ያደረጋቸው እዚህ ግቡ የማይባሉ ለማናጆነት ከየክልሉ በኮታ የሰበስባቸው ናቸው፡፡

በኩርፊያ ርቆ የቆየው የትግራዩ የወያኔ ቡድን መደረግ ካልነበረበት ሰቅጣጭ ጦርነት በኋላ አሁን ወደ ኦሮሙማ መስመር ለመግባት እየተዘጋጄ ነው፡፡ ወያኔ በዚሁ የማስመስልም ይሁን ወይንም ሌላ ምርጫ የማጣት ሁኔታ ተግድዶም ሆነ ወድዶ ባሰላው ስሌቱ ወደ ፌደራል መንግስት አካልነቱ እየተመለሰ ይመስላል፡፡

ይህ ክስተት አብይ አህመድ ኢትዮጵያ ተመልሳ ወደ ዱሮው ጥንካሬዋና የነጻነት ቀንድል የመሆን አገርነቷ እንዳትመልለስ የሚጥረው የምእራቡ አለም ዋና ተጠሪ በሆነችው  በአሜሪካ ቀጥተኛ ትእዛዝ  ከወያኔ ጋር የፈጸመውን አሳፋሪ የፕሪቶርያ ስምምነት  ይበልጡኑ በሚያሳፍር መልኩ ስምምነት ተብየውን በአገርና ህዝብ ላይ የተሰራ ፌዝ ይበልጡኑ አፈር ከድሜ ያስገባ ክስተት ነው፡፡

ወያኔ የእስካሁኑ በሀይል የአማራ መሬቶችን በሀይልመልሶ የመውሰድ ሙከራወች ሁሉ ስላልተሳኩለት ምሳሌ ቅራቅር ላይ የገጠመው የአማራ ሀይሎች ድል አድራጊነት>>  በፌደራል መንግስት “የሰላም እርምጃወች ”በሚለው የማጨናበሪያ አንቀልባ ታዝሎ የአማራ ህይልን ትጥቅ በማስፈታት የአማራ ርስቶች የሆኑትን ወልቃይትንና ራያን መልሶ ለመውሰድ አቆብቁቧል፡፡

አብይ አህመድ የአማራን ሀይል ድጋፍ በሚሻበት ወቅት ብቅ ብሎ  “ቤገምድሬ” ለራሱ አያንስም ይለናል፤፡ እጅግ ሰቅጣጭና እጅግ ዘግናኛ የሆነውን  በሳምሪ ታጣቂወች  በአማራወች ላይ በማይካድራ የተፈጸመውን የወያኔ ጭፍጨፋን በሚመለከትም አብይ አህመድ ሲያብራራ “የማይካድራው ጭፍጨፋ ማንም ያላልተናገረለት፣ ማንም ያልዘገበውና የማያነሳው በታሪክ ወደር የሌለው ጭፍጨፋ ነው” ይለናል፡፤ አብይ ጅኒው ሲመጣበት ብቻ ሳይሆን አለቆቹ አሜሪካኖቹ<< .. “ ዋ ” ያችን የምታውቃትን የወንጀለኝነት ፋይልህን እንመዛትና…> ሲሉትና  ወይንም ይሉኛል ብሎ ሲንቦቀቦቅ ደግሞ ወልቃይትንና ራያን ለወያኔ ለማስረከብ በ31 ዙር ስልጥኖና የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ያልታጠቃቸውን ከተዋጊ አውሮፕላኖች ውጭ ያሉትን እጅግ ዘመናዊ መሳሪያወች እስከ አፍንጫው ድረስ የታጠቀውን ከ300 ሽህ በላይ የኦሮሞ ልዩ ሀይል ጫፉ እንዳይነካ ተደርጎ የአማራ ልዩ ሀይል እንድፈርስ ወስኗል፡፡ ውሳኔውንም ለመተግበር እንደ ጀኔራል አበባው ታደሰ ያሉት አሳፋሪ የአማራ ጄነራልንና መሰሎቹን ልኮ  አማራውን ትጥቅ ለማስፈታት እየሰራ ነው፡፡

የአማራ ህዝብ ሆይ፦  ወልቃይትና ራያ ታሪካዊ  ርስቶችህ ናቸውና ወያኔወች  በዉጊያ ሞክረውህ ሳይሳካላቸው ሲቀር በእጅ አዙር ትጥቅህን ፍታና ርስቶችህን ወያኔወች ይውሰዷቸው የሚሉህን ዘወር በሉ በላቸው፡፡ ወልቃይትና ራያ የአማራ ርስቶች መሆናቸውን ሚሊዮን የታሪክና የተግባር ማሳያወች አሉ፡፡ ሲጀመር ወልቃይት ብሎ፣ ተከዜ ብሎ፣ ግጨው ብሎ  የትግሬ የቦታ ስም የለም፡፡ ራያ ብሎ፣ አለማጣ ብሎ ፣ ኮረም ዋግ፣ኦፍላ ወዘተ  ብሎ የትግሬ የቦታ ስም የለም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያው ሄዝቦላ!! ‹‹የጥቅምት 24/2013 የሽብር ጥቃት 1ኛ ዓመት መታሰቢያ›› ክፍል 1 - ቴዎድሮስ ጌታቸው

ይህንኑ የሚገልጽና በራይም በወልቃይትም ቦታውቹ በታሪክ የአማራ መሆናቸውን ገላጭ (SELF EXPLANATORY) የሆኑ ሁለት የህዝብ ግጥሞችን ላንሳላችሁ፦

በራያ ኮረምና አለለማጣ በኩል፦  

አለማጣ ዉዬ መልሼ አለማጣ  —  በበሽታዬ ላይ በሽታ ላመጣ

በወልቃይት በኩል፦

አገራችን ኩል መስክ  ወንዛችን ተከዜ  —-   ማን ነው የሚነካን እምቢ ያልን ጊዜ

ስለዚህ የአማራ ልዩ ሀይል ሆይ፦ የአማራ ሚሊሽያ ሆይ፡ የአማራ ፖሊስና ሌላም የአማራ ታጣቂ ሆይ፦ ፋኖን አይሞክሩትም፡፡ አንተ ራስህ የአማራ ህዝባዊ ሀይልን ለመቀላቀል አመቺ ወደሆነው ወደፋኖነት ከመግባትህ በፊት እነርሱ እንደ አሁኑ ሙከራቸው ቀድመውህ ትጥቅህን ሊያስፈቱህ ከመጡ ለማንም ትጥቅህን እንዳትፈታ፡፡ ጀነራል አበባውም ሆነ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለአንተ ከወያኔም ከኦሮሙማ የባሱ ጠላቶችህ ስለሆኑ አሳፍረህ መልሳቸው፡፡ እምቢ በላቸው”” እንመለስም ካሉም ዋጋቸውን በቦታው ስጣቸው፡፡

የአውሬው አብይ አህመድ ፋኖን የመፍራት አባዜ ስሙን ለመጥራት ከመፍራት አንስቶ የአማራን ክልል ወደ ሶስትና ከዚያም በላይ ከፋፍሎ ለማዳከም ያቀደ ስለሆነ የአማራው ልዩ ሀይል ትጥቅ ማስፈታትና  ብተና ወደዚያ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የኦሮሙማ ግስጋሴ በአማራው በሀይል ሊገታ ግድ ይለዋል፡፡ አለበለዚያ የኦሮሙማ አማራን የማጥፋት እቅድ መቆሚያ የለውም፡፡ ይህ ካልተመከተ ቀጥሎስ አማራ የሆነ ሁሉ ከአዲስ አበባ ይውጣ ወይንም ዜግነቱን ወደ ኦሮሞ ይቀይር የሚል ጉድ ሊመጣ ይችላል፡፡

አስታዉሱ፦ የአማራውን እምብርት የሆነውን ወሎን ለሁለት ከፍሎ ሰሜን ወሎን ደቡብ ትግራይ ደቡብ ወሎን ሰሜን ኦሮሚያ የማድረጉ ህልማቸው አሁን በትግ-ሬኦሮሞ ጥምረት ወደፊት የሚገፉበት ይሆናልና ከወዲሁ ጥንቃቄና ዝግጅት ይደረግ፡፡ ጥንቃቄው የአማራ ሆዳም ሹመኞችን በያሉበት ከማጽዳትና ይህንኑ የሚያስፈጽም ተወርዋሪ የአማራ ሀይል ከማዘጋጀት ይጀምራል፡፡ የአማራ ህዝብ ደጀንነትአስተማማኝ ነው፡፡ ህዝቡ ችቦው እስከሚለኮስና ፊሽካው እሰክሚነፋ ድረስ እንጅ አማራው በመሽቀዳደም ወያኔንም ሆነ ኦሮሙማን በአንድ ግዳጅ ጠርርጎ የመምታት አቅምና ወኔ አለው፡፡

ወደ አብይ አህመድ የስልጣን ማማ ምርኩዞች ማንነት እንመለስና በትንሹ እንቃኛቸው፡፡

በስልጣን ማማው በአንደኛው ምድብ ውስጥ ያሉት ጠባብና ጎጠኛ የሆኑ የኦሮሙማ አቀንቃኞችንና ክፍልፋዮችን በቅርበት ሲፈተሽ ውስጣቸው ይህንን ይመስላል፡፡አሁን በገዥው ፓርቲ ውስጥ ያሉት የኦሮሞ ብልጽግና (የበፊቱ ኦዴፓ) አመራሮች፣በኦነግ፣ በኢፌኮና በኦነግ ሸኔ እና በሌላም ስሞች የተደራጁ  ይገኙበታል፡፡ ውጭ ያሉት ደግሞ አንደኛዉኑ”” እየሱስ ክርስቶስ [ዋቃ ይሉታል]  ኦሮሞ ሆኖ ነው የተፈጠረው”” ከማለት የሚጀምሩ እንሰሶች ናቸው ማለት ይቻላል፡፤ ምሳሌ ጽጋየ አራርሳንና ህዝቄል ጋቢሳን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በጥቅሉ እነዚህ የኦሮሙማ ፍልስፍና {ኦሮሞ ከሁሉም የበላይ ነው የሚል እሳቤ} ክፍልፋዮች በአንድ ዛፍ ስር ሆነው አንድ የሚያደርጋቸው ዋና ጉዳይ አለ፡፡ ይህም በኢትዮጵያዊነት መቃብር ላይ የኦሮሞን አገርነት መመስረት ነው፡፡ ይህ እሳቤ አንዳንዴ ኢትዮጵያዊነትን እያከሰመ ሄዶ የሚወለደው ኦሮሙማ በሁሉም ዘርፍ የበላይ የሆነበት የኦሮሞ ኢትዮጵያን ማዋለድ ማለትን ይመስላል፡፡ ይህ እሳቤ የኦሮሙማ ክፍልፋዮች የተቀረውን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደነዝዙበት ሴራና በማር የተለወዘ መርዛቸው ነው፡፤ መደመር፣ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ ሁሉ ኬኛ ..።ወዘተ  መርዙ የተቀመመባቸው ኬሚካሎች ናቸው፡፡

እነዚህ የአገር ውስጦቹ የኦሮሙማ ክፍልፋዮች ከሞላ ጎደል የሚያካትቷቸው ኦቦዎች ከአብይ አህመድ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ የሚለዩ ይምሰል እንጅ በመሰረታዊ ጉዳዮች አንድ ናቸው፡፡ በዝርዝሩ ውስጥ አለቃቸው አብይ አህመድ ለተቀመጠበት ወንበር ሲቃዡ የሚያድሩትንም ያካትታል፡፤ እነዚህም ኦቦ ጃዋር ሙሀመድ፣ መራራ ጉዲና፣ ዳውድ ኢብሳ የ ሚጠቀሱ ናቸው፡፡በዚህ ምድብ ውስጥ የስብስቡ አስኳል ሆነው እየሰሩ ካሉት መካከል ግርማ ብሩ፣ ሌንጮ ባቲ ፣ሌንጮ ለታ፣ ለማ መገርሳና ድማ ነገዎ ወዘተ…… ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ ከነዚሁ ውስጥ አሁን በስልጣን ላይ ያሉትን ለይተን ስንመለከት  ሽመልስ አብዲሳ፣ አዳነች አበቤ፣ ምርኮኛው አምሳ አለቃ በርሀኑ ጁላ …ወዘተ የመሳስሉት አውሬውን መሪያቸውን አብይ አህመድን ከላይ ማእክከል አድርገው እጅግ በሚያሳፍር በማያባራ አገር አፍራሽና እልቂት ቀስቃሽ በሆኑ ስራወች ተጠምደው ይገናሉ፡፡አዳነች የዲስ አበቤን ገንዘብ ትBኦጠቡታለች፡፤ ሽመልስ መላው ኦሮሚያን ይለጥጣል; በውንድሙ በኩልም ሚሊዮነር ሆኗል፡፡

በአውሬው አብይ አህመድ በዘራቸውና አብዛሀኛወቹ ያለችሎታቸው ተመርጠው በተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች  በወታደሩና በደህንነት መስሪያ ቤቶች፣ የህይል አዛዦች የደህንነት ሀላፊወች የሚንስቴር፣ የኮሚሽንና የተለያዩ የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች አብይ የመደባቸው በኦሮሞነት የመረጣቸውን ምርጥና አክራሪ ኦሮሞወችን ነው፡፡ በአሳፋሪ ሁኔታ ከላይ እስከታች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚሰራው ዘርን መሰረት ያደረገ ቅጥርና የቅጥር መስፈርት፣ ማፈናቀልና ስምሪት ገንዘብ ዘረፋ፣ በተለይም የዶላር የውጭ ምንዛሬ የጥቁር ገበያ የጦፈ ንግድ እጅግ አይን ያወጣ ሆኗል፡፡

እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን አንድ ሀቅ አለ፡፡ በወያኔ መሩ የቁጥር አንድ የኢህእደግ ዘመን የፌደራል መንግስት የሀላፊነት ቦታወችና የፓርላማ ወንበሮች የመሳስሉት  ራሱ አሰራሩ ስህተት ቢሆንም ይያዙ የነበሩት ወያኔ በቀመረው በህዝብ ብዛትና አወካከል ስሌት ነበር፡፡ አሁን አውሬው አብይ አህመድ  ከወያኔ በባሰና አይን ባወጣ ማጭበርበር ብልጽግና ፓርቲ የሚል ማታለያና አዲስ የማታለያ ቀመር ፈጥሮ አሰራሩን ወደ ኦሮሙማ እንዲያጋድል አንሻፍፎ በመቅረጽ ፓርላማውን ጨምሮ ሁሉንም ስልጣን ኦሮሙማ ጠቅልሎ እንዲይዘው አድርጓል፡፡

ያለማጋነን ወያኔ ራሱም ቢሆን ዘረኛና ዘራፊ የነበረ ቢሆንም በንጽጽር ከኦሮሙማ ሽህ ጊዜ ሳይሆን ሚሊዮን ጊዜ ስለሚሻል”” እምዬ ወያኔ ማረን እባክህ”” የሚያሰኝ ጊዜ ላይ ተደርሷል፡፡

አብይ በሚመራው የኦሮሞ ብልጽግና ውስጥ ያሉት የኦሮሙማ ባለስልጣናት አገሪቱን የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ አስገብተው ለጊዜው እሳቱና እልቂቱ እነርሱንና የእነርሱን ዘር ስላልፈጀ ብቻ  <<አብያችንን አትተቹ!!  አለበለዚያ እንደ ሩዋንዳ የእርስ በእርስ ጦርነት በኢትዮጵያ ውስጥም ይነሳል” እያሉ በማላዘን ላይ ናቸው፡፡ እስኪ ማን ይሙት አሁን የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ያለን ህዝብ እንዲያ ብሎ ማስፈራራት ምን ማለት ነው?? ህዝቡ ከዚህ በላይ ምን እንዳይመጣበት ነው ልሊያስፈራሩት የሚሞክሩት??  ህዝቡ በዘሩ ተለይቶ እየተጨፈጨፈ? ህዝቡ በዘሩና በእምነቱ  ተለይቶ ከስራ እየተባረረ?? ያለ ፍርድ እየታሰረ፣ በላዩ ላይ ቤቱ እየፈረሰ፣  ወደራሱ ዋና ከተማ አትገባም እየተባለ፣ ከዚህ ልቀቅ መጤ ነህ እየተባለ ከዚህ ውጭኦርሙማወች  ለምንድን ነው  የእርስ በእርስ ጦርነት ታስነሳላችሁ የሚለው ማስፈራሪያ??

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መርህ በባህር ዳር ያካሔደው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 1,2, 3 & 4

ከኦሮሙማ አቀንቃኞች በተጨማሪ ሁለተኛው የአብይ አህመድ የስልጣን ባላ/ መሰላል በዋናነት የአማራ ሆዳም ሹመኞች ናቸው፡፡ እነርሱ በአንድ ቅርጫት ውስጥ የሚገኙና ዱሮም የወያኔ አሁንም የኦሮሙማው አሽከሮች ስለሆኑ ትንታኔ አያስፈልጋቸውም፡፡   በቁጥርና በማንነትም በቀላሉ ተለይተው የሚታወቁ ናቸው፡፡

ከወያኔወች እጅጉን በከፋ አካሄድ አገር እየጎዳና ህዝቡንም ወደ ውድቀት እየወሰደ ያለው የኦሮሙማው ገዥ ፓርቲ በአገሪቱ ውስጥ የችግሮቹ ሁሉ ምንጭ የሆነውን የተፈበረከ የህዝብ ቁጥር ብዛትና በዘር ላይ የተመሰረተ ፌደራላዝምን ይበልጥ ለራሱ ጥቅምና “”የሁሉ ኬኛ”” መወጣጫ መስላሉ አድርጎ እየተጠቀመበት ነው፡፡  የውጭ ታዛቢወችም ያሉበት ትክክለኛና  ሀቀኛ የህዝብ ቆጠራ ቢደረግ  እውነቱ ቁልጭ ብሎ ይወጣና የአገሪቱን ግማሽ ችግር ይፈታ ነበር፡፡ በዘር ላይ ያልተመሰረተ ሀቀኛ ፌደራሊዝምም ቢካሄድ ቀሪዎቹን ችግሮች ይፈታ ነበር፡፡ ዳሩ ግን “”ነበር”” ሆኖ ቀረ እንጅ እስካሁን ስላልሆነ አካሄዱ  የአገሪቱ መጥፊያ መጨረሻ ደረጃ ላይ አድርሷታል፡፡መድረሱን የሚያረጋግጥ ሆኗል፡፡

አገር 50 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ዘልቆ በሱዳን ተወርራ፣ የእርስ በእርስ እልቂቱ በየቀኑ መቶወችንና ሽህወችን እየበላ፣ ሰወች በማንነታቸው እየተለዩ እየተገደሉ እየተፈናእሉ ቤቶቻቸው ባላያቸው ላይ በዘር በተደራጀ ቡድን እንዲፈርስባቸው እየተደረገ አብይ አህመድ ግን አሁንም ኢትዮጵያ አትፈርስም ይለናል፡፡ አብይ አህመድ ግን ኢትዮጵያ አድጋለች ፣ተመንድጋለች ዲሞክራሲን አስፍናለች ለሁሉም እኩል ሆና በእኔ አገዛዝ  ምቹ አገር ሆናልናለች ይለናል፡፡ምናምን  ይቀባባና ይወጣል ፡፡ ከዚያም ይቀደዳል ፣ እንደገናም እንዴ አቡጀዲ/ ጣቃ ይተረተራል፡፡ ዛሬም ነገም ይሄው ነው፡፤ህዝቡኮ አብይን አታሳዩን ድምጹን አታሰሙን ፈጣሪ ይገላግለን ብሎ ሰውየውን አንቅሮ ተፍቶታል፡፡ ዉሸት ማታለልና መዋረድ የየእለት የማንነት መገለቻወቹና የሰልቹ ስራውቹ ሆነዋል፡፡ ታዲያ ይህ መዝቀጥ አይደለምን??

እኔ መዝቀጥ እንደ አብይ አህመድ ስላችሁ አንዳችሁ ተነስታችሁ መንዘርጠጥ እንደ አዳነች አበቤ ወይንም ማሽቃበጥ እንደ አማራ ብልጽግና መላላጥ እንደ ትህነግ ወይንም ሌላ ሌላ ልትሉ ትችሉ ይሆናል፡፡ ትክክል እሳቤ ሊሆንም ይችላል፡፤ እነዚህ የኦሮሙማ ክፍልፋዮችና የአማራ ሆዳም ሹመኞች ባይኖሩ ኖሮ አብይ እንደዚህ  ወደለየለት አውሬነት አይቀየርም ነበር ትሉ ይሆናልም፡፡ በእኔ እይታ ነገሩ ከዚህም በላይ ነው፡፡ አብይ ሳያውቃት፣ ሳይፈቅዳትና ሳያሰላት የምትዘረፍ ንብረት፣ የምትወረር ቦታ፣ የምትደገስ የእልቂት ድግስና የምትገደል  የንጹሀ ሰው ነፍስያ የለችም፡፡ እርሱ ራሱ የችግሮቹ ሁሉ ጠንሳሽ፣ የእልቂቶቹ ሁሉ ጠማቃና መሪ ነው፡፡ ገና ዱሮ ምክንያቱን በመጽሀፉ ላይ መጻፉም ለእርጉሙ ሰውየ ማለትም ለአብይ አህመድ የአገዛዙ ስልት ነው፡፤ የሚያምንበት ዘዴው ነው፡፡ ቀመሬ ብሎ የዘረጋው የእሳቤው ዉጤት ነው፡፡

አብይ አህመድ በኦሮሞ ህዝብ ስም ከላይ ሆኖ ሊትዮጵያ ህዝብ ድብቅ የሆነና በምርጦች ምርጥ የአክራሪ ኦሮሙማወች  ስብስብ ሀሳብ አመንጭነትና መካሪነት እየታገዘ ነገር ግን ከኢትዮጵያ ካዝና በውጭ ምንዛሬ ጭምር ከፍተኛ ደመወዝ እየተከፈላቸው በመካሪነት ከላይ ሆኖ አገር እያጠፉ  ያሉት በኬኛ ፖለቲካ በተለዬ ሁኔታ በጥቅም  የተሳሰሩ የጅቦች መንጋወችን  አቆራኝቶ በማሰማራት ነው፡፡ምሳሌ፦ኦቦ  ግርማ ብሩ ዩአንዲፒ ለአገሪቱ ለልማት  ከሚመድበው የውጭ ምንዛሬ ከፍተኛወርሀዊና ቋሚ የወር የዶላር ደመወዝተኛ ነው፡፡  ይህ መሰሉ  ወንጀልና ህገወጥ ድርጊት  የባንኮች ዝርፊያን ጨምሮ የከተማ ቦታወችንና  አፓርትመንቶች ወረራን፣ በጎረቤት ክልሎች የተለያዩ ወረዳወችንና ከተሞችን ወረራን፣ የህገ ወጥ የውጭ ምንዛሬ ንግድን፣ ታዋቂ ሰዎችን ማፈንን፣በአዲስ አበባ በታሪክ ቅርስነት የተመዘገቡ ክመቶ የሚበልጡ ቅርሶችን ማውደምን በምትኩ ቦታወቹንን ለምርጥ የኦሮሙማ ባለሀብቶች መስጠትን ያጠቃልላል>> አንድ ምሳሌ ብቻ እንጥቀስ፦ታዋቂውና በአይነቱ ለከተማዋ ምትክየለስ የጤናን አገግሎትይሰጥ  የነበረውን የአንበሳ ፋርማሲን አፍርሰው ለኦቦ አመንቲ የንግድ መደብር ህንጻ መስሪያ ቦታውን ሰጥተውታል፡፤ ፤ሌላም ብዙ እየፈረሱ ያሉና በታሪካዊነታቸው እንዳይፈርሱ ተመዝግበው ተይዘው በጉልቤው ኦሮሙማ የፈረሱ ቦታወች አሉ፡፤ ህዝቡ በነቂስ ያውቃቸዋል፡፤ አታፍርሱብን ብሎ ጮኋል፡፡ ግን የስማው የለም፡፡ ሸገር ብለው በሰየሙት የአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ የሚደረገው ዘርን መሰረት ያደረገ አረመኔያዊ ድርጊት ህጻናትን በጅብ እስከማስበላት የደረሰ መሆኑን  አለም ያወቀዋል፡፡

የአብይ ስብእና በእኩይነት የተሞላ፣ በማይረካ ፍላጎት የታጨቀ፣በማይሆን ቅዠትና ምንጊዜም ሊሳካ የማይችል ቅዠት እንደሆነ ያለፉት 5 አመታት ድርህጊቶቹ በቂ ማሳያወች ናቸው፡፡ የአብይ አህመድ በሰው ደም የከረፋና የቆሸሸ ስብእናን የተላበሰ ሰው ነው፡፡ አብይ መርህየለሽ ነው፡፤ፍላጎቱ  ይህንንም ያንንም በመከጅል አንዱንም ማሳካት ያልቻለ ልጓም የለሽ ነው፡፡ አንዱንም ቅዠቱን እስካሁን አላሳክም፡፡ መቀሌን በሻሻ አድርገናታል ከማለት ጀምሮመቀደድ አይሰለቸውም፡፡   ይዋሻል ፣ ይቀደዳል፣ ይበጠረቃል የሚላት ሁሉ በውስጧ አንድትም ቅንጣት እውነትነት የላትም፡፡በአፉ  የሚናገረው፣ በምላሱ የሚሰብከው ሌላ ሲሆን በተግባር  የሚተገብረው ደግሞ በተቃራኒው ሌላ ነገር ነው፡፡ በሁሉም ቅትፈቶቹና ምላሳምነቱ ሌላ ፣መሬት ላይ ያለው የሚታየው እውነታ ሌላ፡፡ይህ አይነት ክስተት የሚከሰተው በስህተት፣ ለአንድ ወቅት ብቻ ወይንም በአጋጣሚ አይደለም፡፤ በተደጋጋሚና ሁልጊዜም ያው ነው፡፤ ማታለል፣ ማጭበርበርና መዋሽት፡፡

ለማጠቃለልም ህዝቡኮ አብይን አታሳዩን ድምጹን አታሰሙን ፈጣሪ ይገላግለን ብሎ ሰውየውን አንቅሮ ተፍቶታል፡፡ህልቆ መሳፍርት የሌላቸው ዘረነቱና ወንጀለንነቱ እንዳለ ሆኖ  ህዝብን በዉሸታምነት ማታለሉ ብቻውን  ሰውየዉን በህዝቡ ዘንድ የተዋረደ አድርጎታል፡፡ይህ ታዲያ  መዝቀጥ አይደለምን??

የሰውየው ስብእናም ሆነ ማንነቱ ከማንምና ከምንም የከፋና የከረፋ በወንጀል የተጨመላለቀ መዝቀጥ ነው፡፡

 

3 Comments

  1. ጽሁፉ የአብይ አህመድን ማንነት በደንብ ገልጦታል፡፡ ኦሮሙማ አያምንም እንጅ በወንጀል መጨማመላለቁን ያሳያል ጽሁፉ፡፡ አንድ ነገር ብቻ ልጨምር፦
    ማን ነው በመንግስት ከፍተኝና ስልጣን ላይ ሆኖ የዶላርን ጥቁር ገበያ በተለይ ከውጭ በዶላር እየተቀበለ አገር ውስጥ በእጥፍ በብር እየከፈለ ያለው?? ራሱ አብይ አህመድ ነውን?? ወይንስ ሊስላ ሚሚስትር ወይንም ሌላ ፡፡ ነገሩ ጉድ ነው፡፡ ምክንያቱም ምንዛሬው በባንክ ለአንድ አሜሪካን ዶላር 54 ብር ሲሆን ከዚያው ከውጭ አገር አንዱን ዶላር ወስደው በብር 105 እና ከዚያም በላይ በባንክ የሚከፍሉ አሉ፡፤ ኢትዮጵያ ውስጥም የሁለቱም የብር ክፍያ የሚፈጸመው በባንክ ነው፡፡ የዶላር አላላኩ ግን አንደኛው ወደአገሪቱ አክካውንት ሲገባ ሌላኛው አላላክ ወደግለሰብ ሂሳብ ገብቶ በዚያው ሰምጦ ይቀራል፡፡
    ይህንን ሌብነትና የአገር ወንጀል ላይ በጣም ላይ ካሉት የመንግስት ሀላፊወች ውጭ ሌላ ማን ሊያደርገው ይችላል??
    ጽሁፉ ይህንን ቢነካካው ጥሩ ነበረ፡፡

  2. እናነተ: የአማራ: ኤሊቶች: በእልህ: ሀገሪቷን: ወደ ማስፈረስ: ደርሳችሇል: ሀገሩን: የሚወደውን: አቢይን: ኦሮሞ: ነው: ብላችሁ: ሠላም: ነስታችሁት: በናንተ: ስሕተት: ሰውዬውን: እልህ: ውስጥ: ከተታችሁት: አያችሁት: እሱን: በእንደዚህ: ዓይነት: እልህ: አውርዳችሁት: ማንስ: እንደ: ኢትዮጵያ: ሆኖ: ይቆምላችሇል:ማንነስ:ማስተዳደር:ፈለጋችሁ?ሕዝብ: የመረጠውን: እናንተ: በጉልበት: ልታወርዱት: ፈለጋችሁ: እልህ: ውስጥ: ከተታችሁት: እነ: ክርስትያን: ታደለ: በዚህ: ሁኔታችሁ: ሀገሪቷ: ቋፍ: ላይ: ነው: ያለችው::ማስተዋሉን: ይስጣችሁ: አቢይን: ለቀቅ: አርጉት::

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share