April 3, 2023
12 mins read

በኢንተርኔት ኢኮኖሚ ዘመን፣ የኦነግ ጦር አበጋዞች የኢንተርኔት አፈና ጃንጥላ በጨረቃ!!!

et economy 1 1 1 1

ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

የኮነሬል አብይ አህመድ አንባገነናዊ አገዛዝ የኢንተርኔት እቀባ ያብቃ! የጦር አበጋዞች የመረጃ ግብር ያብቃ! ስለ አርቴፊሻል ኢንቴሌጀንስ እያወራ ኢንተርኔት የሚያግድ፣ ስለ ሳይንስ ሙዜም እየገነባ ኢንተርኔት የሚያፈርስ፣ በአፍ የሰለጠነ በተግባር ያልዘመነ የበሻሻ  ሰው እንዲዘምን የልብ ንፅህናና የህሊና የበታችነት ደዌ ተላቆ በእኩልነት ያለአድሎ ህዝብን እንዲያስተዳድር እንፀልይለት፡፡ ትላንት በትግራይ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ሰው አልቆል፣ ነገ ደግሞ በአማራ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ሰው ለመጨረስ በዝግጅት ላይ ናቸውና ፈጣሪ ማስተዋል ይስጣቸው፡፡

በኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በ1894 እኤአ ተጀመረ፣ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ ሚኒሊክ የስልክ ቴክኖሎጂን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የዛሬ 129 አመታት በፊት አስፋፉ፡፡ “The introduction of telecommunications services in Ethiopia dates back to 1894. When Minilik II, the King of Ethiopia, introduced telephone technology to the country. ”

ከኢትዮጵያ ህዝብ ከ123 (መቶ ሃያ ሦስት )ሚሊዮን ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 20.86 (ሃያ ነጥብ ሰማንያ ስድስት)ሚሊዮን ህዝብ ሲሆን የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነት 16.7 (አስራስድስት ነጥብ ሰባት)በመቶ መሆኑን ጀነዋሪ 2023 እኤአ መሆኑ ተገልፆል፡፡ ከዓለም ዝቅተኛ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ያሉባት ሃገር ናት፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎት መስፋፋት ጠቀሚታው በህብረተሰቡ ውስጥ የተረጋገጡ ማስረጃዎችና አሃዞች እንዲሰራጩ፣ የኢንፎርሜሽን እውቀት ለተማሪዎችና አስተማሪዎች ብሎም ለግለሰቦችና ለህብረረተሰብ ይትረፈረፋል እንዲሁም የኢኮኖሚ እድገት   ያጎናፅፋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርኔት ኢኮኖሚ ዘመን ከመጣ ጀምሮ ለብዙ መቶ ሽህ ወጣቶችና ነጋዴዎች አዲስ የስራ መስክ ተከፍቶላቸዋል፡፡  የሞባይል የእጅ ስልኮች ሱቆች፣ ኢንተርኔት ካፌዎች፣ የኢንተርኔት የባንክ አገልግሎቶች፣ የማህበረሰብ ሚዲያ አገልግሎት ሰጪ አንቂዎች እንደ አሽን ፈልተዋል፡፡ የባንክና ፋይናንስ ዘርፍና የዓለም አቀፍ የንግድ አገልግሎቶችን በዘመናዊና ቀልጣፋ መንገድ አዘምኖል፡፡ There were 20.86 million internet users in Ethiopia in January 2023. Ethiopia’s internet penetration rate stood at 16.7 percent of the total population at the start of 2023. Kepios analysis indicates that internet users in Ethiopia increased by 520 thousand (+2.6 percent) between 2022 and 2023.Feb 13, 2023

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት በዝቅተኛ ደረጃ ለመስፋፋቱ ዋና ምክንያት የህወሓትና የብልፅግና ፓርቲ አንባገነን መሪዎችና የአንድ አውራ ፓርቲ አገዛዝ መስፈን የተነሳ ዴሞክራሲያዊ  መብቶችን የሚያፍኑ፣ ስብአዊ መብቶች የሚጥሱ፣ የፕሬስ ነጻነትን የሚጋፉ ዘረኛ ጠባብ ብሄርተኛ የጦር አበጋዞች በነፃ አውጭነት ስም የፖለቲካ ሥልጣን ከተቆጣጠሩበት ዘመን ጀምሮ የመለስ ዜናዊ ሃያ ሰባት አመታት አፈና ብሎም የአብይ አህመድ የአምስት አመታት የሰቆቃ ዘመን የኢትዮጵያ ህዝብ ከአለም ህብረተሰብ በኢንተርኔት አገልግሎት አፈና ከሠላሣ አመታት በላይ መቀጠሉ በታሪክ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያና በትግራይ ጦርነት በኢንተርኔት መዘጋት የተነሳ 146 (መቶ አርባ ስድስት) ሚሊዮን ዶላር ገቢ አጥታለች፣ በትግራይ አንድ ሚሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችም ከሥራ ተስተጎጉለዋል፡፡ በኢትዮጵያ በ2020እኤአ በኢንተርኔት አገልግሎት መቆረጥ የተነሳ 100 ሚሊዮን ዶላር የሃገራችን ኢኮኖሚ ገቢ አጥታለች፡፡ በ2021 እኤአ ደግሞ 164.5 ሚሊዮን ዶላር የሃገራችን በኢንተርኔት ኢኮኖሚ ገቢዎን አጥታለች፡፡  በኢንተርኔት አገልግሎት መቆረጥ የተነሳ 21.3 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ከዓለም ህብረተሰብና እውቀት ተቆራርጠው ከርመዋል፡፡ በ2022እኤአ  ኢንተርኔት አገልግሎት 8760 (365ቀናቶች)በመቆረጡ በሃገሪቱ የዲጂታል ክፍያዎች ገቢ ተጨናግፈዋል፣ ቢዝነሶች ከስረዋል፣ የሰብዓዊ መብት ተሞጋቾች በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩት የስብዓዊ መብቶች ጥሰት፣የዘር ጭፍጨፋ፣ የጦር ወንጀል ዶሴዎችን ሪፖርት እንዳይሰራጩ ተስተጎጉለዋል፡፡ In 2020, the country lost $100 million to internet outage which rose to $164.5 million in 2021, affecting 21.3 million users. There was no internet connection for a total of 8760 hours (365 days) in 2022, crippling digital payment systems, businesses, and efforts by human rights groups to use social media to document reported crimes against humanity and ethnic cleansing in Tigray, home to over 5 million people before the war………………………..(1)

የብልፅግና መንግሥት የኮነሬል አብይ አህመድ አንባገነን አገዛዝ የኢንተርኔት እቀባ ያብቃ፡፡ ኢትዮቴሌኮም ለህብረተሰቡ ኢንተርኔት አገልግሎት ሳይሰጥ የወር ክፍያ ማስከፈል ወንጀል ነው፡፡  የመረጃ ግብር ብዝበዛ ያብቃ እንላለን፡፡!!! በኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያዎች(Social-media-icons) እገዳ የፌስቡክ፣ ቲውተር፣ ዩቲዩብ፣ ኢንስታግራም፣ቲክ ቶክ፣  ወዘተ በአንባገነኑ ኮነሬል አብይ አህመድ አፓርታዳዊ አገዛዝ ላለፉት ሁለት ወራት ሃገሪቱን ህዝብ ከአለም አቀፍ የኢንተርኔት ትስስር ከዓለም ህብረተሰብ በመነጠል የህዝብን መብቶች በመጋፋትና ሃሳብን በነጻነት የመግለፅ መብቶችን ባለማክበር ፀረ-ዲሞክራሲያዊ አገዛዙ በመላ ዓለም መጋለጡን፣ የአምኒስቲ ኢንተርናሽናል የምዕራብና ደቡብ አፍሪካ ምክትል ሪጅናል ዴሬክተር ፍሌቪያ ማዋንጎያ አጋልጠዋል፡፡ “Ethiopian authorities have, for a month now, blocked people in the country from accessing selected social media platforms such as Facebook, Telegram, Tik Tok and YouTube. The authorities thus continue to violate people’s right to freedom of expression, which includes the freedom to seek receive and impart information.

የኢንተርኔት ማቆረጥ በተለይም የሶሽያ ሚዲያ መገኛኛ ዘርፎች የዜጎች መብትን ሃሳብን የመግለፅ ነፃነትን የሚጥስ ሲሆን ዜጎች መረጃ የማግኘት መብታቸውን ተነፍገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ- መንግሥትና ብሔራዊ ህጎች እንዲሁም ክልላዊና አለም ዓቀፋዊ ስምምነቶች ፊርማዎን ያኖረችበትን በጠራራ ፀሐይ ህግ የጣሰች ሃገር መሆኖ ለዓለም ተጋልጦል፡፡ ሃገሪቱ ባደረገችው ተደጋጋሚ  የኢንተርኔት እገዳ፣ የሚዲያ ነፃነትን መፃረር ሪከርድ መስበሮን አስመስክራለች፡፡ “Amnesty International urges the Ethiopian authorities to lift this blockade without delay and to end this culture of interfering with people’s right to express themselves and to seek and receive information.”

የብልፅግና መንግሥት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር በፈጠረው ጣልቃገብነት የተነሳ አገር አቀፍ አድማና ሠላማዊ ሠልፍ እንዳይጠሩ በመፍራት፣ በተፈጠረ ያለመግባባት  ቀውስ ከፌብሪዋሪ 9 ቀን 2023 እኤአ አንስቶ የኢንተርኔት ማቆረጥ፣የማህበረሰባዊ ሚዲያ  መዘጋት ተከሰተ፡፡ እንደ ሚዲያ ሪፖርት መሠረት በምስራቅ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ከተማ የኦሮሚ ክልል በመንግሥት የፀጥታ ኃይል የቤተክርስቲያን ምዕመናን በመግደላቸው  የተጀመረ ነበር፡፡ Since 2016 Amnesty International and other organizations have documented frequent internet shutdowns or restrictions during widespread protests and in conflict areas. The war-torn Tigray Region has been cut from any means of communication, including the internet, for almost two years.  The connectivity partially resumed after the Cessation of Hostilities (CoH) agreement was signed by the warring parties in November 2022. …………(2)

ከ2016እኤአ አምኒስቲ ኢንተርናሽናልና ሌሎች ድርጅቶች ያቆዩት ሠነድ መረጃ መሠረት ተደጋጋሚ የኢንተርኔት መቆረጥና መዘጋት ዋነኛ ምክንያት በሃገሪቱ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመጽና ህዝባዊ እንቢተኛነት ለመግታት ነበር፡፡ በጦርነት የተመታው ትግራይ ክልል ከምንም ዓይነት የኮሙኒኬሽን መገናኛ አገልግሎት ኢንተርኔት ጭምር ለሁለት አመታት ተቆርጦ ነበር፡፡ የኮሙኒኬሽን መገናኛ አገልግሎት  በከፊል የጀመረው ሁለቱ ተፋላሚዎች የጥላቻ ማስቆም ስምምነት Cessation of Hostilities (CoH) ከተፈረመ በኃላ ነበር፡፡

 

የኢንተርኔት አፈና ይቁም!!! የዲጅታል ቴክኖሎጅ ዘመን ወጣቶች ያረጁ የጃጁ ካድሬዎችን አስወግዱ!!!

በኢንተርኔት ኢኮኖሚ ዘመን፣ የኦነግ ጦር አበጋዞች አፈና ጃንጥላ በጨረቃ!!!

ምንጭ

(1) Internet shutdowns cost Ethiopia $146 million in 2022 By Faustine Ngila/PublishedJanuary 12, 2023

(2) Ethiopia: One month on, authorities must immediately lift blockade on selected social media access in the country.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop