March 31, 2023
15 mins read

የታገሰ ጫፎ ሌባ ጣት፤ ያማራ ውርደት ዘላለማዊ ምልክት

68878853 1 1

ሁለት ዓይነት አዋራጆች አሉ፡፡  አንደኛው ዓይነት አዋራጅ፣ ታግሎህ ካሸነፈህ በኋላ ባሸናፊነቱ በመታበይ የሚያዋርድህ አዋራጅ ነው፡፡  ሁለተኛው ዓይነት አዋራጅ ደግሞ ባንተው በራስህ ትግል አሸናፊ ከሆነ በኋላ፣ ባሸናፊነቱ የተደላደለ ሲመስለው፣ አንተኑ ራስህን የሚያዋርድህ አዋራጅ ነው፡፡

ወያኔ በተወሰነ ደረጃ አንደኛው ዓይነት አዋራጅ ነው፡፡  በተወሰነ ደረጃ የተባለበት ምክኒያት ደግሞ፣ ወያኔ እስከተወሰነ ደረጃ የደረሰው በራሱ መስዋእትነት ቢሆንም፣ አማራን በስፋት ሊያዋርድ ከሚችልበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው ግን ባማራ ጫንቃ ታዝሎ አራት ኪሎን ከተቆጣጠረ በኋላ በመሆኑ ነው፡፡  ለዚህ ደግሞ የወያኔ የጦር ሹሞች የነበሩት እነ ጀነራል ተፈራ ማሞ ቋሚ ምስክሮች ናቸው፡፡

አማራ ወያኔን አዝሎ አራት ኪሉ ያስገባው ደግሞ ደርግ ይውደቅልኝ እንጅ በሚለው ክፉ አባዜው ነው፡፡  ያማራ ሕዝብ ትልቁ ድክመት ሙሉ ትኩረቱን የሚያደርገው ጠላቱን በመንቀል ላይ እንጅ ነቅሎ ለሱ የሚበጀውን በመትከል ላይ አለመሆኑ ነው፡፡  ወያኔን ነቅሎ ጭራቅ አሕመድን በመትከል ከእሳት ወጥቶ ረመጥ የገባውም በዚሁ ወያኔ ትውደቅልኝ እንጅ በሚለው ክፉ አባዜው ነው፡፡  አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ተብሎ የተተረተውም፣ ጀግኖች በመስዋእትነታቸው በሚነቅሉት ጠላት ላይ ባንዳ ስለሚተከልበት ነው፡፡

ባጠቃላይ አነጋገር አማራን ለመጨፍጨፍ የሚነሳ ማናቸውም ቡድን በራሱ በአማራ ሕዝብ በነቂስ ለመደገፍ ማድረግ ያለበት የጊዜውን ያማራን ጠላት በጽኑ በማውገዝ ያማራ ወዳጅ መስሎ መቅረብ ብቻ ነው፡፡  ወያኔም ኦነግም ያደረጉት ይሄንኑ ነው፣ ወያኔ ደርግን በማውገዝ፣ ኦነግ ደግሞ ወያኔን በማውገዝ፡፡  ያማራ ሕዝብ ከዚህ ከፉ አባዜው እስካልተላቀቀ ደረስ ደግሞ ከእሳት እወጣለሁ እያል ረመጥ መግባቱ፣ በራሱ መስዋእትነት ስልጣን ላይ በሚያወጣው ቡድን መጨፍጨፉ ይቀጥላል፡፡  ያማራ ሕዝብ ሙሉ ትኩረቱን የሚያደርገው በሚነቅለው ላይ እንጅ በምትኩ በሚተክለው ላይ ባለመሆኑ፣ ከኃይለሥላሴ እጅ ለመውጣት ታግሎ ደርግ እጅ ገባ፣ ከደርግ እጅ ለመውጣት ታግሎ ወያኔ እጅ ገባ፣ ከወያኔ እጅ ለመውጣት ታግሎ ኦነግ እጅ ገባ፡፡  ይህ እኩይ ሰንሰለት አነግ ላይ ካልተበጠስ ደግሞ፣ ያማራ ሕልውና ያበቃለታል፡፡  ያማራ ሕዝብም የሕልውናውን ትልቅ ጥያቄ ውስጥ መውደቅ በደንብ ስላወቀ፣ አማራዊነቱን ከፍ በማድረግ ይህን እኩይ ሰንሰለት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመበጠስ ቆርጦ ተነሳስቷል፡፡  ስለዚህም ላማራ ሕዝብ አሁን የሚያስፈልገው የመይሳዊ ካሳ ዓይነት ዳግማዊ ቴድሮስ ብቻ ነው፡፡  ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ፣ የጭራቅ አሕመድ መምጣት ላማራ ሕዝብ ጠቅሞት ከሆነ፣ የጠቀመው ዳግማዊ ጭራቅ አሕመድ እንዳይፈጠር ምሎና ተገዝቶ እንዲነሳሳ ማድረጉ ነው፡፡

ወያኔ በተወሰነ ደረጃ አንደኛው ዓይነት አዋራጅ ቢሆንም፣ ኦነግ ግን ሙሉ በሙሉ የሚመደበው ከሁለተኛው ዓይነት አዋራጅ ነው፡፡  ኦነግ የሚያወቀውና የሚታወቀበት ጨለማን ተገን አድርጎ ተከላካይ አልባ ሕፃናትንና አረጋውያንን በሜንጫ በማረድና በገደል በማንኮታኮት ብቻና ብቻ ነው፡፡  ኦነግ ድል ማደረግ ቀርቶ በታሪኩ አንድም ጊዜ መሣርያ ከታጠቀ ባላንጋራ ጋር ፊት ለፊት ገጥሞ አያውቅም፡፡  የኦነግ ሠራዊት ቁጥሩ ህልቆ መሣፍርት ቢሆንም፣ ባንድ ሙቀጫ የሚወቀጥ ተልባ ነው፡፡  ወያኔው ሰየ አብርሃ ኦነግን ከሳንቲም አንቆጥረውም በማለቱ ምንም አልተሳሳተም፡፡  ጭራቅ አሕመድ የሸኔ ሠራዊቱን እንደ ተምች አብዝቶ አስካፍንጫው ቢያስታጥቀውም፣ የሺዋ ፋኖ ብቻ የዶግ ዐመድ እንደሚያደርገው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

ወያኔ የወደቀው “ወያኔ ትውደቅልኝ እንጅ” በሚለው አባዜው ያማራ ሕዝብ ጉሮሮውን ስላነቀው እንጅ ቄሮ መንገድ ስለዘጋበት አልነበረም፡፡  ቄሮንማ በጭስ ብቻ አስበርገጎ ገደል እንደሚያስገባው ደብረ ዘይት ላይ በግልጽ አስመስክሯል፡፡  ቄሮ በተሰለፈ ቁጥር ከባድ እርምጃ ወስዶበት የማያውቅውም፣ አለንጋ የሚበቃው መንጋ መሆኑን ስለሚያውቅ ነበር፡፡  ባሕር ዳር ላይ ግን ባንድ ጀምበር ብቻ ካምሳ በላይ ወጣቶችን በመጨፍጨፉ ያተረፈው ቢኖር ውድቀቱን ማፋጠን ብቻ ነበር፡፡

ስለዚህም ለጭራቅ አሕመድ ስልጣን መያዝ ወሳኙን ሚና የተጫወተው ያማራ ትግል ነው ቢባል ማኮስመን እንጅ ማጋነን አይሆንም፡፡  ያማራን ውርደት እጅግ ሲበዛ አንጀት አቁሳይ የሚደርገውም፣ ውርደቱን የሚፈጽመው ይህ ባማራ መስዋእትነት ስልጣን ላይ የወጣ ኦነጋዊ ጭራቅ መሆኑ ነው፡፡

ያማራ ሕዝብ በጭራቅ አሕመድ የተዋረደውን ያህል በሌላ በማንም አልተዋረደም፣ ወደፊትም አይዋረድም፡፡  ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ አይዋረዱ ውርደት ያዋረደባቸውን አያሌ ምሳሌወችን መጥቀስ ይቻላል፡፡  ከሁሉም ያማራ ውርደት ምሳሌወች ውስጥ መቸም የማትረሳዋ ግን ታገሰ ጫፎ በዲባቶ (Doctor) ደሳለኝ ጫኔ ላይ የቀሰራት ሌባ ጣት ናት፡፡

ታገሰ ጫፎ አፈጉባኤ ስለሆንኩ፣ የፓርላማውን ስነስርዓት አስከብራለሁ ይላል፡፡  ላማራ የሚቆርቆሩ እንደራሴወች ጥያቄ ሲጠይቁ ግን ከኦንጋውያን እንደራሴወች ጋር አብሮ እያፌዘ፣ እየሳቀና እየተሳለቀ አስከብራለሁ የሚለውን ስነስርዓት እሱ ራሱ ያፈርሳል፡፡  በቶሌ ለተጨፍጨፉት አማሮች የደቂቃ የሕሊና ጸሎት እንዲደረግላቸው ሲጠየቅ ግን፣ ላፍታም ሳያቅማማ ሌባ ጣቱን ወደ ጠያቂው በመቀሰር ጠያቂውን ስነስርዓት ብሎ ገሰጸው፡፡  ደቂቃ ቀርቶ ሰከንድ እንደማይፈቅድለት ነገረው፡፡  ይህ የሚያሳየው ደግሞ ጥያቄው እንደሚጠየቅ አስቀድሞ አወቆ፣ በታዘዘው መሠረት ጥያቄውን ለማስቆም ተዘጋጅቶ ይጠባበቅ የነበረ መሆኑን ነው፡፡  ታገሰ ጫፎን ያዘዘውና የሚያዘው ደግሞ ሌላ ማንም ሳይሆን ጌታው ጭራቅ አሕመድ ነው፡፡

ጭራቅ አሕመድ ይወድቃል፣ መውድቂያውም እየተቃረበ ነው፡፡  እጣ ፍንታው ደግሞ ከጋዳፊ እጣ ፈንታ እጅግ የከፋ ይሆናል፣ መሆንም አለበት፣ እንደሚሆንም ጥርጥር የለውም፡፡  ያን ጊዜ ደግሞ ታገስ ጫፎ በሂወት ኖረም አልኖረም፣ አማራን ያዋረደባት ሌባ ጣቱ ተቆርጣ፣ ላማራ ልጆች ዘላለማዊ ማስተማርያ ትሆን ዘንድ፣ ያማራን ሕዝብ በወያኔና በኦነግ መጨፍጨፍ ለዘላለም ለመዘከር በተሠራ ልዩ ቤተመዘክር (Amhara Holocaust Museum) ውስጥ ለዘላለማዊ ትዕይንት መቀመጥ አለባት፡፡

አጼ ምኒሊክ ባልሠሩት ሥራ ጡት ቆራጭ ተባሉ፡፡  ፋኖ ደግሞ ባልሠራው ሥራ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ አማሮችን አረዶ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ካፈናቀለው ከጭራቅ አሕመድ ሸኔ ጋር እኩል (እንደውም በከፋ ደረጃ) ሽብርተኛ ተባለ፡፡  የጭራቅ አሕመድን ሸኔ አንድም ቀን ስሙን ጠርታ የማታውቀው አሜሪቃ፣ የምዕራብ አውሮጳ ሎሌወቿን በማስተባበር ፋኖን በዘር አጥፊነት ለማስወንጀል የፀጥታውን ምክርቤት ካስር ጊዜ በላይ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራች፡፡  ይህ ሁሉ የሚያሳየው ደግሞ ምዕራባውያንና የነሱ ቡችሎች የሆኑት ወያኔና ኦነግ አማራን በጠላትነት የፈረጁት ባማራዊ ማንነቱ መሆኑን ነው፡፡  ስለዚህም ያማራ ሕዝብ አደረገውም አላደረገውም በማንነቱ በሚጠሉት በምዕራባውያንና የነሱ ቡችሎች በሆኑት በወያኔና በኦነግ መከሰሱ መቸም ቢሆን አይቀርለትም፡፡  ባደረገውም ባላደረገውም መከሰሱ የማይቀርለት ከሆነ ደግሞ ላማራ ሕዝብ የሚበጀው አድርጎት ቢከሰስ ነው፡፡

ስለዚህም ያማራ ሕዝብ ሆይ ማንነትህን ለማስከበር ስትል፣ በወያኔና በኦነግ ላይ ማድረግ ያለብህን ሁሉ ያለ ምንም ርህራሄ ማድረግ አለብህ፡፡   ጭራቅ አሕመድ ሸኔን አሰማረቶ ልጆችህን በሜንጫ ሲያርድብህ፣ አንተ ደግሞ የሱን ሸኔ ከነ ጀሌወቹ በጎራዴ አወራርድለት፡፡  ጭራቅ አሕመድ ልጆችህን ጎጆ ውስጥ ዘግቶ ሲያቃጥልብህ፣ አንተ ደግሞ የሱን ሸኔ ከነጫካው አንጨርጭርለት፡፡  ጭራቅ አሕመድ ልጆችህን የጅብ ራት ሲያደርግብህ፣ አንት ደግሞ የሱን ሸኔ ያሞራ ምሳ አድርግለት፡፡  ጭራቅ አሕመድ ካህንህን በጥፊ ሲመታብህ፣ አንት ደግሞ የሱን ደጋፊ አባገዳ በቃሪያ ጥፊ ወልውልለት፡፡

የፈሪ ብትር ሆድ ይቀትር እንዲሉ፣ ጭካኔና ፍራቻ ቀጥተኛ ወደረኛ (directly proportional) ናቸው፡፡  ጨካኝ፣ የጨካኝነቱን ያህል ፈሪ ነው፡፡  ኦነግ በዚህ ደረጃ ጨካኝ የሆነው፣ በዚሁ ደርጃ ፈሪ ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህም ያማራ ሕዝብ ሆይ፣ አነግን ሳይወድ በግዱ ወደ ጠርንጴዛ የምታመጣው፣ ለሚያደርግብህ እኩይ ድርጊት ሁሉ አስር እጥፍ እያስከፈልክ፣ አኩይ ድርጊቱ ይበልጥ የሚጎዳው እሱን ራሱን መሆኑን በተግባር ስታሳየው ብቻ ነው፡፡  መክረኸው፣ መክረኸው ስላልሰማህ፣ በመከራ ምከረው፡፡  ዳግማዊ ጭራቅ አሕመድና ዳግማዊ ታገሰ ጫፎ መወለድ ቀርቶ እንዳይጸነሱ የምታደርገው በዚህና በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop