March 31, 2023
17 mins read

ከሸፍጥ ነፃ የሆነ ህዝበ ውሳኔ ይልቅ ፣ ፖለቲካዊ ሤራን ማጫጫስ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እጅግ ይበዛል – መኮንን ሻውል

images 2 1
#image_title

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ልዩ ኃይልና ወጣት እና ጤነኛ ሚሊሻዎች ወደ መከላከያ ሠራዊት እንዲቀላቀሉ የሚያደርግ ህጋዊ  አዋጅ ሳይወጣ እና የክልልች ያበጠው ጡንቻ ሳይላላ ፣ ወልቃይት ና ራያን በትግራይ ክልል ውሥጥ በመመለሥ ነፃ ና ገለልተኛ የሆነ ሪፈረንደም ማድረግ የሚቻል አይመሥለኝም ።

images 2 1

ነፃና ገለልተኛ ህዝበ ውሳኔ በማድረግ ዜጎች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩት ከጠብ መንጃ ነፃ ሆነው ያለፍርሃት ያለአንዳች ተፅእኖ ግልፅ ፣ ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ የህነ የህዝበ ውሳኔ ድምፅ ለመሥጠት የሚያሥችል ግልፅ ና ገለልተኛ መድረክ ሲኖር  ብቻ ነው ። እኔ አውቅልሃለሁ በሚሉት ኮሚኒሥታዊ አካሄድ ትላንት ወልቃይትና ራያ በትግራይ ክልል ሥር ነበሩ ።

እርግጥ ነው ፣ ከጦርነቱ በፊት ወልቃይትና ራያ በትግራይ ክልል ሥር ነበሩ ። ከ1983 ዓ/ም በፊት ግን አልነበሩም ። ከዘመነ ወያኔ በፊት በዘመነ

112393298 capture

ደርግ በጎንደር ክፍለሀገር ሥር እንደነበሩ ይታወቃል ። ከዘመነ ደረግ በፊትም የጠበቀ እና ከአካባቢያቸው   ባህል ጋር የተዋሃደ ማንነት  ነበራቸው ።  ህኖም ትላንት በኃይል  አሥተዳደራቸው ሥለተወሰነላቸው ዛሬም ዜጎችን ያለፈቃዳቸው “ ኃይል ይግዛቸው ። “ ብዬ ሃሳብ ለመሥጠት አይዳዳኝም ። ይሁን እንጂ ያለአሻጥር ፣ በነፃ ና ግልፅ በሆነ መድረክ የሚያሥተዳድራቸውን ክልል ወይም “ ረሥ ገዝ አሥተዳደር  “ ራሳቸው ይወስኑ ። ልዩ የፊደራል ክልል  የመሆንም መብት እንዳላቸውም መዘንጋት የለብንም ። በዘመነ ከፋፍሊት የሆነውም ይኸው ነው ።

በበኩሌበነገራችን ላይ ፣  ” ዘመነ ከፋፍልቲን” አገር እንደ ዳቦ የሚቆራርስ እና ለተራው ህዝብ የማይጠቅም የቆዳ ማዋደድ እና ጋብቻ ከልክል በመሆኑ ነፍሴ ይጠየፈዋል ። ኤርትራን ያሳጣንም ይሄ ግትር አቋም ነው ። የግድ ጨካኝ መሪ ያሸንፋል ብሎ ነገር በዛሬው ዓለም የለም ። ሃያል እና ጅምላ ጨረሻ የባዮሎጂ ጦር መሣሪያ ካለህ አንድ አገርን ለማጥፋት ትችላለህና ! በእኛ ሁኔታ ይህንን የሚያደርግ አቅም የለንም ። ከዓለም የምንበልጣቸው አገሮች 24 ናቸው ። በድህነት 25ኛ አገር ነን ። የዛሬ ታሪካችንን ከጎግል መጎልጎል ይቻላል ።  ዕውቀት እንደ ሠፈር ብቅል ሆናለችና ማንም ለማወቅ የፈለገ የተማረ ሰው ሥለ እኛ አገር ክፉና በጎ ሁኔታ ለማወቅ የታሪክ ምሁራንን መጠየቅ አያሥፈልገውም ።

ኤርትራዊያንን ከጉያችን የቀማን ፣ የአንደ እናት ልጆችን የለያየን የቀዝቃዘው ጦርነት ሤራ ነው  ። ካፒታሊስት አሜሪካ ከመሰሎቿ ከአውሮፓውያኑ ጋር በማበር ፤ ሶሻሊስቷን ሩሲያ አሥራ አንድ አገር አድርጋ ሥትበታትናት ፣ በ1982 የደርግ ፍፃሜ እውን መሆኑ ተረጋግጧል ። ደርግ የሶሻሊዝም አቀንቃኝና የአሜሪካን ኢምፐርያሊዝምን ክፉኛ መጥላቱን  በአብዮት አደባባይ ሦሥት በቀይ ቀለም የተሞሉ ጠርሙስችን በመከሥከሥ በተጨባጭ ያረጋገጠ ነበርና ! ( ፊልሙን ዛሬ በእዝን ልቦናዬ ሣሥታውሰው የጓድ መንግሥቱ ኃይለማሪያም  ወኔ ያሥደንቀኛል ።

ዛሬ የኃያሏ አሜሪካ ጡንቻ ተገዳዳሪ ቢኖረውም ፣ አሜሪካ የዜጎቿን ጥቅም ለማሥጠበቅ ሥትል የማትወጣው ዳገት እንደሌለ ቆም ብለን ማሰብ ይኖርብናል ። እንዲህም ሲባል አሜሪካ የብልሃት ፖለቲካን የማይመርጥ መንግሥት የላትም ብለን አናምንም ።

113784322 50fcca72 0151 4681 9bb3 9f8baa98a148 1

በኢትዮጵያ ውሥጥ የተረጋጋ ጠንካራ ህግ አሥከባሪ መንግሥት እንዲኖር  የአሜሪካ መንግሥት ይፈልጋል ። ከወቅቱ ሥልጣኔ ጋር የማይራመድ የህፃን ጨዋታን የመሠለ ኢ_ዴሞክራሲያዊ ድርጊትንም አይደግፍም ።  በመላው ኢትዮጵያ ግጭቶች ጠፍተው ዜጎች እንዳሻቸው በዜግነታችው በአገራቸው ምድር ሁሉ ተዘዋውረው የሚሠሩበት  አውድ ቢፈጠር እጅግ ደሥ ይላቸዋል ። እነሱም መዋለ ነዋያቸውን በኢትዮጵያ ላይ ያለፍርሃት በማፍሰስ ህዝቡን ጠቅመው የአገራቸውን ዜጋ ተጠቃሚ የሚያደርጉት ሠላም ሲኖር ብቻ እንደህነ ያምናሉ ። ከዚህ እምነታቸው ተነሥተው ነው ፣ ዛሬ እያራመድነው ያለውን የቋንቋና የዘር ፕለቲካ የማይደግፉት ።

የእኛ ፖለቲካ ለህብረት ፣ ለአድነት ፣ ለወንድማማችነት ና ለመልካም ጓደኝነት ፍፁም የተመቸ አይደለም ። ዜጎች ተከፋፍለው ፣ ተለያዬተውተነጣጥለው ፤ ልክ እንደባላንጣ በጎሪጥ እየተያዩ ይህቺን አጭር ህይወት እንዲኖሩ የሚያሥገድድ ነው ።

ለዚህም ነው ዛሬ አማራ ያለመደበትን  ” አማራ ነኝ ” ብሎ የተደራጀው ። እርግጥ  ኢትዮጵያ 80 ቦታ እንዳትቆራረጥ የአማራ  በአማራነት መደራጀት ይጠቅማል  የሚል ሃሳብ በምሁራን ዘንድ አለ  ። በዘር እና በቋንቋ መደራጀት እና የፖለቲካ ፖርቲ መሆን በህግ እሥካልተወገደ ጊዜ ድረስ አማራ በአማራነቱ በወጉ መደራጀት ግዴታው ነው ።

ይህን የምለው  በሚገባ የተደራጀ እና የታጠቀ ከ 20 ሚሊዮን የማያንስ ወጣትና ጎልማሳ አማራ ካለ ማንም ጉልበት አለኝ ብሎ በዘር   የተደራጀ እና የታጠቀ ህዝብ ሊጨፈጭፈው  እንደማይችል ሥለተገነዘብኩ ነው ። ይህም ብቻ አይደለም እንደ ጨው ዘር በመላው ኢትዮጵያ የተበተነው እና በጋብቻ የተዋለደው  ህብር  ኢትዮጵያዊ ዜጋ ( ጎሣዬ፣ነገዴ፣ብሔር ብሔረሰቤ … ይኼነው ለማለት የሚቸገር ፤ ልክ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ልጆች  የበዙ ዜጎችን  አማራ ክልል ካለው ጋር   ሥትደምሩ ኢትዮጵያ በፍፁም ልትበታተን እና ሥሞ ሊጠፋ ከቶም እንደማይችል ትገነዘባላችሁ ። ) ሲደማመር  የአማራ ህዝብ ብዛት  በትንሹ  ከ 45  ሚሊዮን በላይ ይሆናል ። …. እናም  ይህ ትልቅ ህዝብ የኢትዮጵያ መመኪያ መሆኑ መዘንጋት የለበትም ።

ከዚህ እውነት አንፃር ህዝብን ከህዝብ ጋር ከማጫረስ ፤ ወንድምና እህታማማቾችን ፈጣሪ በፈጠረውና ነገ በሚቀበሩበት መሬት የእኔነው እያሉ እንዲጫረሱ በማድረግ ፤ በህዝብ እልቂት አትራፊ እሆናለሁ  በማለት በቀቢፀ ተሥፋ ከመዳከር ይልቅ ፣ ቆም ብሎ በማሰብ ፣ ለእውነተኛ ፍትህ በመወገን ፣ በዛ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ ከሸፍጥ ነፃ የሆነ ህዝበ ውሳኔ ቢደረግ መልካም ነው ። ከህዝቡ ውሳኔ በፊት ሸፍጡ ከቀደመ እና ፖለቲካዊው  ሤራ ከተጫጫሰ  ተመልሰን ወደማጡ መግባታችን እና እንደአገርም ክፉኛ እንደምንጎዳ ከወዲሁ መገንዘብ ይኖርብናል ።


ኧኩኩሉ !?

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

” ፀረ ለውጥ ! ” ነህ ብትሉኝም_እኔ ግን አይደለሁም ፤
በትላንት አቋሜ ላይ ነኝ ትግሌን ፤ አላቋረጥኩም ።
በቀቢፀ ተሥፋ ከእናንተ ጋር አልቦዝንም
እያልኩ “ኩኩሉ ! አልነጋም ! “
በከንቱ ጊዜዬን አልገድልም ።
“ በነጋ ! አልነጋም ! “ …
ዘላለሜን በጨለማ ውሥጥ አልዳክርም ።
በነጋ አልነጋም የድበብቆሽ ጫዋታ
ሁሉም በየነገዱ ተደብቆ ሲያምታታ
እያየው ነው ዛሬም ከ27 ዓመት በኋላ
የሰው ልጅ እንደአውሬ እየዘረፈ ሲበላ ።
” ፀረ ለውጥ ! ” ነህ ብትሉኝም ፤
እኔ ግን አይደለሁም ፤
በለውጥ አቋሜ ላይ ነኝ ፤ ትግሌን አላቋረጥኩም ።
የምረካ አይደለሁም በቁሥ ክምር በመሥከር
የአኩኩሉ ጫዎታችሁ ቢቆም ከምር እደግፋችሁ ነበር ።
ድብብቆሽ ጫዎታ ውሥጥ ሆናችሁ ፤ ኩኩሏችሁ ካላባራ
አልነጋም ወይ እያለ ህዝብ ብርሃን ለማየት ሲጣራ
አንደበቱ ሞት ጠራበት በቋንቋው ሥላወራ
የአኩኩሉ ጫወታው ለካ ደብቋል ቢላዋና ካራ ።
” ፀረ ለውጥ ! ” ነህ ብትሉኝም_እኔ ግን አይደለሁም ፤
በለውጥ አቋሜ ላይ ነኝ ፤ ትግሌን አላቋረጥኩም ።
የምረካ አይደለሁም እንደ ጎሰኞች ቁሥ በመከመር
የአኩኩሉ ጫዎታችሁ ቢቆም ፤ አብሬ በቆምኩ ነበር ።
ለውጥነው አትበሉኝ ፤ ከቶም ባልተለወጠ ነገር
ፖለቲካውን እሥከ አንገት ተዘፍቃችሁበት በዘር
ለውጡ ሁሉን አቃፊ አሣታፊ ተራማጅ ሥትሉን ነበር ።
ኧረ እንዲህ ነው እንዴ የመደመራችሁ ነገር ?
” ፀረ ለውጥ ! ” ነህ ብትሉኝም_እኔ ግን አይደለሁም
በለውጥ አቋሜ ላይ ነኝ _ ትግሌን አላቋረጥኩም ።
የምረካ አይደለሁም እንደ ጎሰኞች ቁሥ በመከመርየአኩኩሉ
ጫዎታችሁ ቢቆም ፤ አብሬያችሁ በቆምኩ ነበር ።
ለጅብና ለአህያ ፤
ለነብርና ለሚዳቋ ፤
ለአይጥና ድመት ፣
ለእባብና ገበሎ …
ለአራዊት እና እንሥሣ ሁላ
ፈፁም ምቹ የሆነ _ ለሰዎች በሟላ
በዘር እየከፋፈለ _ ሰውን ከሰው ጋር የማያጣላ ።
ቢሆን ኖሮ ለውጡ ያደረበት ፈርሃ እግዜር
የሚያኗኑረን በአንድነት _ ሰብዓዊ መብታችንን በማክበር
እኔም ከልቤ ለውጡን በደገፍኩት ነበር ።
” ፀረ ለውጥ ! ” ነህ ብትሉኝም_እኔ ግን አይደለሁም ፤
በለውጥ አቋሜ ላይ ነኝ _ ትግሌን አላቋረጥኩም ።
የምረካ አይደለሁም እንደ ጎሰኞች ቁሥ በመከመር
የአኩኩሉ ጫዎታችሁ ቢቆም ፤ አብሬ በዘመርኩ ነበር ።
በቃል በወሬ ቀረ ፤ ትላንት የታቀደው አሻጋሪ መርከብ
እርስ በእርስ ስንተላለቅ ፤ በጥይት ስንደባደብ ።
እኔም አዝኜ ማቅ ለበስኩ ፤ እውነት በሐሰት ሥትቀበር
ወንድም ወንድሙን ገድሎ ሲያቅራራ ያለማፈር ።
” ፀረ ለውጥ ! ” ነህ ብትሉኝም_እኔ ግን አይደለሁም ፤
በለውጥ አቋሜ ላይ ነኝ _ ትግሌን አላቋረጥኩም ።
የምረካ አይደለሁም እንደ ጎሰኞች ቁሥ በመከመር
የአኩኩሉ ጫዎታችሁ ቢቆም ፤ አብሬያችሁ በታገልኩ ነበር ።
አብዮት ቢሆን ኖሮ አሉኩኝ አኩኩሉን የሚያሥቀር
እግዜር ያደረገው አይነት ከኖህ ጋር በትብብር ።
በሃቅ ፣ ሥለሃቅ በመቆም ፤ ኖህ እጅግ ፀንቶ በእምነቱ
ያኔ ! ያኔ ! ድሮ !እግዜር ተቆጥቶ ፤ ዶፍ ሲያወርድ በፍጥረቱ
ዝናብን ያለማቋረጥ ሲያወርድ በቀን እና በለሊቱ
ኖህ ፣ አስቀድሞ አውቆ ነበር ሥለ ሥር ነቀል አብዮቱ ።
ፍጥረታትም እንዳይጠፉ ሁሉን መርጦ በመርከቧ በማሳፈር
የራሱን ፃድቅ ወገኖችም በውስጦ በመደመር
በአብዮቱ እንዳይጠፉ በፈጣሪ መርከብ አስጠልሎ
ይኸው እሥከዛሬ አለን ህይወትን አሥቀጥሎ ።
ያኔ በእግዜር አብዮት ፤ በሆነው እጅግ ሥር ነቀል
ፈጣሪ አቅዶ ነበርና አዲስ ትውልድ ለማብቀል
ፍጥረታቱ እና የኖህ ትውልድ በመርከቧ ተጠልሎ ተረፈ
የእግዚአብሔር አብዮትም በውሃ ፍጥረታትን ሁሉ ቀሰፈ ።
እናውቃለን በዛ አብዮት ኖህ ዳቢሎስን በፀሎቱ ታግሎ እንደጣለ
ሰው ሁሉ ይጠፋል ያለው ሤጣን እራሱ በኖህ መርከብ እንደተገደለ
እናውቃለን ፣ ኖህ ከፈጣሪ አብዮት ጋር ተባብሮ ህይወትን እንዳስቀጠለ ።
” ፀረ ለውጥ ! ” ነህ ብትሉኝም_እኔ ግን አይደለሁም ፤
በለውጥ አቋሜ ላይ ነኝ _ ትግሌን አላቋረጥኩም ።
የምረካ አይደለሁም በቁሥ ክምር በመሥከር
የአኩኩሉ ጫዎታችሁ ቢቆም ፤ አብሬያችሁ በቆምኩ ነበር ።

የደራሲው ማስታወሻ
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
Godmyc1955godmyc@gmail .com አድራሻዬ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Aklog Birara PhD zehabesha
Previous Story

የውጭ እርዳታና ድጎማ ለቀን ጂቦች አመች ሁኔታ ይፈጥራል – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

68878853 1 1
Next Story

የታገሰ ጫፎ ሌባ ጣት፤ ያማራ ውርደት ዘላለማዊ ምልክት

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop