ሚሊዮን ዘአማኑኤል(ኢት-ኢኮኖሚ)
ሎሚ ተራ ተራ ሎሚ ተራ ተራ፣ የማምዬን ነገር ጎረቤት አደራ!!!
መንግሥት ለተያዘው በጀት ዓመት 786.6 (ሰባት መቶ ሰማንያ ስድስት)ቢሊዮን ብር በጀት መመደቡ ይታወሳል፡፡ ከተመደበው በጀት ውስጥ ከ300 (ሦስት መቶ) ቢሊዮን ብር በላይ የበጀት ጉድለት እንደተከሰተና 40 (አርባ) ቢሊዮን ብር በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ያልተሰበሰበ የታክስ ገቢ የነበረ ሲሆን፣ ይህንን የበጀት ጉድለት ለመሙላት የግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭንና ( የገንዘብ ሚኒስቴር ሪፖርት እንደሚጠቁመው፣ የባለፈው 2014ዓ/ም በጀት ዓመት ሲጠናቀቅ ተጠራቅሞ የነበረው የግምጃ ቤት ሰነድ ዕዳ 317.6 (ሦስት መቶ አስራ ሰባት) ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፣ የ2015 ዓ/ምግማሽ አመት ሲጠናቀቁ ግን ወደ 315.4 (ሦስት መቶ አስራአምስት) ቢሊዮን ብር ዝቅ ብሏል፡፡) መንግባት+ የቀጥታ ብድርን 183.5 (መቶ ሰማንያ ሦስት) ቢሊዮን ብር ገንዘብ በማተም ጨምሮ የተለያዩ አማራጮችን ሊጠቀም ከርሞል፡፡ ሆኖም የብልፅግና መንግሥት የውጭ ብድርና እርዳታ በጦርነቱ፣ በስብዓዊ መብቶች ጥሰትና የሽግግር ፍትህ ስርዓት አለማካሄድ ምክንያት ከለጋሽ አገሮች ያገኝ የነበረው ብድርና ዕርዳታ ከ22 በመቶ ወደ 10 በመቶ መቀነሱ ታውቆል፡፡ እንዲሁም ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ በእድገትና እድል ድንጋጌ (አግዋ) ታገኝ የነበረው የውጭ ንግድ ገቢ አለመኖር የሃገሪቱን ኢኮኖሚ የእንፉቅቅ አስኪዶታል፡፡
- እኤአ በ2021 የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ላይ መንግሥት ብሔራዊ ባንክን በማዘዝ በአዲስ እንዲታተም ያደረገው የብር መጠን 83.5 (ሰማንያ ሦስት) ቢሊዮን ብር ሲሆን የተቀመጠውም ከባንክ ውጪ ከጦርአበጋዞቹ ቤተ መንግሥትና ክልል ግምጃቤት እንደሆነ ይጠረጠራል፡፡
- የብልፅግና መንግሥት በ2023 (በ2015 ዓ/ም) ግማሽ አመት 100 (መቶ) ቢሊዮን ብር ገንዘብ ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ ብድር (ገንዘብ በማተም) መውሰዱ ታውቆል፡፡ የተቀመጠውም ከባንክ ውጪ ከጦርአበጋዞቹ ቤተ መንግሥት ግምጃቤት የኢኮኖሚ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ በኢኮኖሚው ውስጥ እየናረ ለመጣው የዋጋ ንረት አንዱ ዓይነተኛ ምክንያት ይህ በየጊዜው እየታተመ ወደ ገበያ ውስጥ እንዲሠራጭ የሚደረገው በምርትና አገልግሎት ያልተደገፈ ሌጣ ብር መሆኑን የኢኮኖሚ ጠበብት ይስማማሉ፡፡
- በኢትዮጵያ 189 (መቶ ሰማንያ ዘጠኝ) ቢሊዮንብር ከባንክ ውጪ ያለ ከጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ፣ ከከንቲባዋ ቢሮ፣ በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች ጦር አበጋዞች የኦህዴድና ህወሓት ቢሮዎች ውስጥ የተቀመጠ ገንዘብ ከአምናው ጋር ሲወዳደር በ27 በመቶ እንዳደገ ተገልፆል፡፡ ነጋዴው ህብረተሰብም በባንኮች ላይ እምነት አጥተው እንደአቅሚቲ በግል ቤታቸው ካዝና ውስጥ ተቀምጦል፡፡
የአብይ አህመድ መንግስት ወደ ትግራይ ክልል ስድሰት ቢሊዮን ብር ልኮ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከቦንኮች ውስጥ ወጥቶ በህወሓት የጦር አበጋዞችና በሰዎች እጅ ገብቶ መቅለጡ ይታወሳል፡፡ በሃገሪቱ የገንዘብ ዝውውር ከባንኮች ወደ ህብረተሰቡ፣ ከህብረተሰቡ ወደ ባንኮች የነበረው የገንዘብ ዝውውር ኡደት ()እያደር በኢኮኖሚው ውስጥ መቆረጡን ያሳያል፡፡ ገንዘብ አስቀማጩ ህብረተሰብ ገንዘቡን ከባንክ አውጥቶ መጠቀም ባለመቻሉ የተነሳ፣ በኢትዮጵያ ባንኮች ላይ ህብረተሰቡ እምነት አጥቶል፡፡ በህወሓት በትግራይ ክልልና በኦሮሚያ ክልል በኦነግ ሸኔ የተዘረፉ ከሠላሳ እስከ አርባ የሚቆጠሩ ባንኮች በኢትዮጵያ ባንኮች ታሪክ ሪከርድ የበጠሰ መንግሥታዊ የውንብድና ተግባር በመንግሥትም በባንኮቹም የጋራ ስምምነት ስለዘረፋው ለህብረተሰቡ አንድም ቀን ተገልፆ አያውቅም፡፡ የተዘረፈው ህዝብ ያስቀመጠው ገንዘብ መሆኑን፣ ሠራተኛው ህዝብ ለጡረታ ያስቀመጠው ብር፣ ነጋዴው፣ አስተማሪው፣ወዘተ ያስቀመጡት ብር መሆኑን ዘንግተውታል፡፡ ህብረተሰቡ በመንግሥትና ባንኮች ላይ እምነት አጣ ማለት ደግሞ የስርዓቱ በስብሶ የመውደቂያው ሰዓት መቃረቡን ያመላክታል፡፡
መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለማሟላት፣ ብር የማተም የገንዘብ ፖሊሲ በኦሕዴድ / ብልፅግና ዘመን በከፍተኛ ደረጃ ተባብሷል፡፡ መንግሥት የበጀት እጥረቱን ሲያሟላ የቆየው በአገር ውስጥ ብድር፣ ከውጭ በሚገኝ ብድርና እርዳታ ነው፡፡ በአገር ውስጥ የመንግሥት ብድር የሚሸፍነው ከንግድ ባንክ በሚገኝ ብድርና ቀሪው በብሔራዊ ባንክ አማካይነት አዲስ ገንዘብ ታትሞ ለመንግሥት የመደበኛ ወይም የካፒታል በጀት መሸፈኛ እንዲውል በማድረግ ነው፡፡
ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2015 ዓ/ም፤ የአጠቃላይ የኢኮኖሚው እድገት ምጣኔ ያላገናዘበ (Excess Money Supply) የገንዘብ ፖሊሲ በኦነግ ኦሕዴድ / ብልፅግና ዘመን በከፍተኛ ደረጃ ተባብሷል፡፡ከጁን 30 ቀን 2021 እኤአ ድረስ፣ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ 2.4 (ሁለት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአገር ውስጥ ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት) ትሪሊዮን ብር እንዲሁም የውጭ አገር ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.29 (አንድ ነጥብ ሃያ ዘጠኝ) ትሪሊዮን ብር ሆኖል፡፡
ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2014 ዓ/ም፤የአገር ውስጥ የመንግሥት ዕዳ ከ449.7 (አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ብር ወደ 1.14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት) ትሪሊዮን ብር ተመንድጎል፡ በሌላ በኩል በአብይ ዘመን የሚገነባው የጫካው ከተማ ፕሮጀክት አንድ ትሪለየን ብር ወጪ የገንዘቡ ምንጭ ምስጢር ከኢትዮጵያ የብድር ግምጃ ቤት በብድር ስም የተመዘበረና ከአረብ አገር ንጉሶች በልመና የተገኘ ሊሆን እንደሚችል ይጠረጠራል፡፡
- ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2011ዓ/ም፤ የማዕከላዊመንግሥት ዕዳ7 (አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ብር ነበር፡፡
- በ2013 ዓ/ም የአገርውስጥ የመንግሥት ዕዳ 945 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተጠቅሷል። ከዚህ ውስጥ 525 (አምስት መቶ ሃያ አምስት) ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቆማት ያበደረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው፡፡ መንግሥት ተጨማሪ 495.3 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ከብሔራዊ ባንክ፣ በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ፣ ከመንግሥት ሠራተኞችና ከግል ሠራተኞች የጡረታ ፈንድና ተወስዶ ያልተከፈለ ዕዳ መሆኑን ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል፡፡
- ከመጋቢት 2010 እስከ 2014ዓ/ም የአገር ውስጥ ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት) ትሪሊዮን ብር መድረሱ ተገልፆል፡፡
- የመንግሥትልማት ድርጅቶች የአገር ውስጥ ዕዳ8 (ሦስት መቶ ሰማንያ ስድስት ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ እንዳለባቸው መረጃው በዝርዝር ያመለክታል፡፡ ብድሩ የተሰጠው ከኢትዮጵያ አየር መንገድና ከኢትዮ ቴሌኮም ወጭ ያሉትን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሚመለከት እንደሆነ ሰነዱ ያመለክታል፡ ከመንግሥት ልማት ድርጅቶቹን የተናጠል ዕዳ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር ያለባቸው የአዲስ አበባ የቤት ልማት መርሃግብር 50 (ሃምሳ) ቢሊዮን ብር እዳ፣ የስኳር ኮርፖሬሽን 70 (ሰባ) ቢሊዮን ብር እዳ፣ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል 300 (ሶስት መቶ) ቢሊዮን ብር እዳ፣ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን፣ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ወዘተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር ያለባቸው ድርጅቶች ናቸው፡፡
- መጋቢት 2015 ዓ/ም፤የአገርውስጥ የመንግሥት ዕዳ ከ7 (አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ብር ሲሆን የአገር ውስጥ ብድር ወደ 1.68 (አንድ ነጥብ ስድሳ ስምንት) ትሪሊዮን ብር ተመንድጎል፡፡ 31.5 ቢሊዮን ዶላር አድጎል፡፡ ከዚህ እዳ ውስጥ ማዕከላዊው መንግሥት ሃምሳ ዘጠኝ በመቶ ዕዳ ሲኖርበት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ደግሞ አርባ አንድ በመቶውን ይሸፍናሉ፡፡(በ2014 ዓ/ም የአገር ውስጥ ብድር 1.53 ትሪሊን ብር ወይም 29.4 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡)
የብልፅግና መንግሥት በ2015 ዓ/ም ግማሽ አመት 100 ቢሊዮን ብር ገንዘብ ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ ብድር (ገንዘብ በማተም) መውሰዱ ታውቆል፡፡ ይህውም የብልፅግና መንግስት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በ2015ዓ/ም የመጀመሪያ ሩብ አመት 60 (ስልሳ) ቢሊዮን ብር ብድር የወሰደ ሲሆን በሁለተኛው ሩብ አመት 40 (አርባ) ቢሊዮን ብር ብድር ሲወስድ በስድስት ወራት ውስት 100 (መቶ) ቢሊዮን ብር ብድር ወስዶል፡፡ በ2014ዓ/ም በጀት አመት መንግሥት 76 (ሰባ ስድስት) ቢሊዮን ብር ተበድሮ የነበረ ሲሆን ከ2015ዓ/ም ጋር ሲነፃፀር የ32 በመቶ ብልጫ አለው፡፡የገንዘብ ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የስድስት ወር የብድር ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰው ለሦስት አመታት ሲንከባለል የመጣው አጠቃላየወ 236.5 ቢሊዮን ብር መንግሥት በቀጥታ የወሰደው ብድር ወደ ረዥም ጊዜ ባንድ መቀየሩ ተጠቅሶል፡፡ መንግሥት ያለበት አጠቃላይ የረዥም ጊዜ ቦንድ ዕዳ ወደ 433.9 ቢሊዮን ብር ማደጉን በሪፖርቶ ተጠቅሶል፡፡ መንግሥት ለሠራተኛው የሚከፈለው ደሞዝ ካጣ፣ የውጭ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችት ከተመናመነ ለመንግሥት ቀይ መብራት ነው!!! መንግሥት የህዝብ የጡረተኛ ገንዘብን እየበላ ከመጣ፣ ህዝብ መንግሥትን መብላቱ አይቀሬ ነው!!!