March 30, 2023
11 mins read

ይድረስ ለእነ “ብለን ነበር” በሙሉ! – ጥላሁን ፅጌ

የዛሬ አንድ ዓመት ደሴ ነበርኩ። የአማራ ምሁራን መማክርት በደሴ ባዘጋጀው ጉባኤ የመሳተፍ ዕድሉ ነበረኝ። ወቅቱ ከጦርነት በመጠኑም ረፍት ያደረግንበት በጠላቶቻችን ወረራ ተፈፅሞባቸው የነበሩ የአማራ ክልል ከተሞች ከደረሰባቸው ውድመትና ዝርፊያ ለማገገም የሚጥሩበት ነበር። ደሴ አንደኛዋ የጠላት ወረራ ሰለባ ነበረች።

በወሎ ዩኒቨርስቲ የተካሄደው የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ በተጀመረበት ዕለት አንዲት ጉስቁል ያለች ሙስሊም እናት በአንዲት ሴት ተደግፋ ወደ መድረክ መጣች። ይህች እናት አማራን እናጠፋለን ብለው ወረራ የፈፀሙብን ጠላቶች ሰለባ ከመሆኗ በፊት ትዳር መስርታ፣ ቤት ሰርታ እና ልጆች ወልዳ ከደሴ ከተማ ትንሽ ራቅ ባለች የገጠር መንደር ውስጥ ትኖር ነበር።

ወደ መድረኩ ከወጣች በኋላ ሁሉ ነገሯ እንደተሰበረ በሚገልፅ ሁኔታ መናገር ጀመረች። የህወሓት ታጣቂዎች “ወደ ቀያችን መጡ፣ ከልጆቼ ፊት አስገድደው ደፈሩኝ፣ ባለቤቴን ከቤት አውጥተው ጫካ ወስደው ገደሉት፣ አስከሬኑን በጅብ ተበልቶ የተቦጫጨቀውን ልብሱን ብቻ አገኘነው” አለች። አዳራሹ ከከፍተኛ ባለስልጣናት እስከ የተለያዩ የዩኒቨርስቲ መምህራን እና ሌሎች ተጋባዦች ተሞልቷል። በህይወቴ በጣም ብዙ ሰው በቃል መግለፅ የሚከብድ ጭንቀት ውስጥ ገብቶ ያየሁት የዛን ቀን ነው። ያኔ ይህች ምስኪን እናት የስነልቦና ድጋፍ በሚያደርግ ማዕከል ውስጥ ነበረች።

አማራ ወደጦርነት የገባው አለመግባት ስለማይችል ብቻና ብቻ ነው። ለሶስት አስርት አመታት የተከማቸ በደል ካደረሱበት፣ ተቋማዊ እና ስርዓታዊ የሆነ የዘር ማጥፋት ከፈፀሙበት፣ የወልቃይትና ራያን የአማራ ማንነት በጉልበት ከደፈጠጡበት እና ዛሬ ለአማራ ዘርፈ ብዙ አደጋዎች መጋለጥ ምክንያት የሆነን ስርዓት ከተከሉት ታሪካዊ ጠላቶቹ ጋር ነው። ይሄንን የዘመናት ብሶት በውስጡ አምቆ የኖረን ህዝብ ከአምስት አመታት በፊት ማንም ለማያውቀው አቢይ የሚባል ቆሻሻ ግለሰብ ብሎ ጦርነት እንደገባ የሚያስቡ ሰዎችን ነፍሴ አብዝታ ትጠየፋቸዋለች።

ከላይ መግቢያ ላይ እንደጠቀስኳት የአማራ እናት አይነት በደሎች በብዛትና በጭካኔ ተፈፅመዋል። በማይካድራ በጭና በወሎ በሸዋ ሺህዎች በጅምላ ተገድለው ተቀብረዋል። ቀደም ሲልም መከላከያ ውስጥ የነበሩ የአማራ የጦር መኮንኖች እየተመረጡ ተጨፍጭፈዋል። በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት አውድመውብናል። ዘርፈውናል። ከታዳጊ እስከ አዛውንት ከመነኩሴ እስከ የካህናት ሚስቶች በቡድን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል። ይህ ሁሉ በደል የተፈፀመው ፀረ አማራነት ውሳጣቸው ዘልቆ በገባ ጠላቶቻችን ነው። አማራ ወደጦርነት እንዲገባ ያስገደደው እውነታም ይሄ ነው።

ጦርነትን መቃወም አንድ ነገር ነው። የህዝብን Cause መቀማት ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው። በግሌ ከሶስት እና አራት አመታት በፊት ከጦርነት ጉሰማዎች ይልቅ ሰላማዊ አማራጭ ያላቸውን ሰዎች ደግፌያለሁ። የኢህአዴግ መፍረስ እና የምርጫው መራዘም የፈጠራቸው አለመግባባቶች ጦርነት ውስጥ ሊከቱን ይችላሉና እንነጋገር ሲሉ የነበሩ የልደቱ አያሌው አይነት ሰዎች ሀሳባቸው Reject መደረግ የለበትም ብያለሁ። አምኜበትም ነበር።

ህወሓት በማንነቴ ላይ ጦርነት ሲያውጅ ግን ሰላም ይበጃል እያልኩ የማላዝንበት አንድ ፐርሰንት ምክንያት ሊኖረኝ አይችልም!! ወቅቱ ልዩነት ቢኖረን እንኳን ቅድሚያ አደጋ ላይ ለወደቀው ህዝብ የምንስጥበት ነበር። ለአማራ interest loyal የሆኑ ሁሉ ህዝባቸው አደጋ ላይ በነበረበት ወቅት በየፊናቸው ታግለዋል። ጠላትን ፊትለፊት ከመግጠም እስከ ሀብት ማሰባሰብ ከፕሮፓጋንዳ እስከ የSocial Media ዘመቻዎች ሁሉም ህዝቡን አግዟል። ከህዝብ interest ይልቅ ለግላዊ ego ቅድሚያ የሰጡት ደግሞ ህዝብን በሚከፋፍል አጀንዳ ተጠምደው ነበር። አልተሳካላቸውም እንጅ።

ወልቃይት እና ራያ ቁራጭ መሬቶች ናቸው ማለት ይቻላል። ለእኔ ግን አንድም ከጎረቤት ሀገራት ጋር መገናኛ ኮሪደር ሌላም የምግብ ዋስትና መሰረት መሆን የሚችል የጅኦኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ታሪካዊ ሀብቶቻችን ናቸው። ከፍ ሲልም ለሶስት አስርት አመታት ይጠፋ ዘንድ የግፍ መዓት የተፈፀመበት የአማራ ማንነታችን ምሰሶዎች ናቸው። እነዚህ አካባቢዎች የደም ዋጋን የሚጠይቁ የህዝብ Quest ናቸው። ለዘመናት ከፍተኛ መስዕዋትነት ተከፍሎባቸዋልም። ወደፊትም በዚሁ አግባብ Secure የሚደረጉ ይሆናል።

ዛሬ ላይ የራያ እና ወልቃይት አካባቢዎች በጎንደር በተዘጋጀው የመላው አማራ የስፖርት ጨዋታዎች ተካፋይ መሆን ችለዋል። ለረዥም ጊዜያት የማንነታችን ክፋይ ሆነው በርቀት ስናያቸው የነበሩት ወልቃይት እና ራያ ደም እና አጥንት በገመዳቸው ክሮች ከሰውነታችን ጋር ተሰፍተዋል። ክሩ ደብዝዞ ቆዳችን እስኪጎላ ድረስ ደግሞ እለት በእለት እንከባከባቸዋለን። የተከፈለው መስዕዋትነት ቀላል አይደለምና!

አንዳንድ ጊዜ የህዝቡን ሀቀኛ እና ፍትሃዊ Cause ሆን ብለው abandon ያደረጉ አካላት ለህዝብ ብለው የሚያዘምቱት ጦር ስሌለላቸው ደስ ይለኛል። ህልውናችን በእነዚህ አይነት ሰዎች እጅ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ህወሓትን ያህል ጠላት በሁለት ሚሊዮን ትግሬ አማራን ሲያስወርር ምን ልንሆን እንደምንችል ሳስበው ዝግንን ይለኛል። ገብቶት ይሁን ሳይገባው ከሚግተለተል የፌስቡክ ግሪሳ ውጭ ምንም የላቸውም። ምስጋና ለክብሩ ሟች ለሆነው የጦር ገበሬ ይድረሰውና እንደታቀደልን አልጠፋንም!! አከርካሪያችን እንዳልተሰበረ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ሲሉት እንደኖሩትም አርቀው እንዳልቀበሩን አሳይተናል።

ተገድደን በገባንበት ጦርነት እንደ ህዝብ ብዙ ጉዳቶችን አስተናግደናል። በተፈጥሮው አውዳሚ የሆነው ጦርነት ካደረሰብን ውድመት ባሻገር በህዝባችን መስዕዋትነት የተገኘውን የጦርነት ድል በፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ ለመድገም ተግዳሮቶች አጋጥመውናል። ከውስጥ አስተዳደራዊ እና አሻጥር ከውጭ ደግሞ የምዕራባውያኑ ከአማራ በተቃራኒ መቆም ዋነኛ ተግዳሮቶች ናቸው። እነዚህ ክፍተቶች ላይ ጠንክሮ መስራት እና የዲፕሎማሲያዊ ኪሳራዎችን Rectify ማድረግ ቀጣይ የቤት ስራዎቻችን ናቸው።

አማራ ዛሬም ረፍት የለሽ ህዝብ ነው። የኦህዴድ ፋሽስታዊ ስርዓት ከባድ አደጋ ጋርጦብናል። ህወሓትም active threat ነው። እንደ ህዝብ ህልውናችንን ማስጠበቅ የምንችለው ለህዝብ interest loyal ሆነን ስንገኝ ብቻና ብቻ ነው። እኔ ፖለቲካዊ ወዳጅነቴን የምሰጠው ለህዝብ ጥቅም ታማኝ ለሆኑት ብቻ ነው። የምንጋራው እንጅ የምንከፋፈለው ስጋት እንደሌለ ማወቅ ያስፈልጋል። ይሄ ስጋት እኔን አይመለከትም ያኛው ስጋት ለእኔ ስጋት አይደለም የሚል እሳቤ ያላቸው ሰዎች የሚያራምዱት አቋም ዘርፈ ብዙ አደጋ ለተጋረጠበት ወገናችን መቼም አይጠቀሙንም። አንድያቸውን ጠላት የሆኑት ሀይሎች ይሻሉናል። አማራ ዛሬም ነገም የጠላቶቹን ጥቃት እንደአመጣጡ መመለስ አለበት የሚለው አቋሜ መቼም አይለወጥም። በጠላቶቻችን ዓላማ እና ፍላጎት ዙሪያም የClarity ችግር የለብኝም።

Tilahun Tsige ፔጅ የተወሰደ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop