March 2, 2023
10 mins read

አሁን ተረጋግጧል። ባንዳው የኦህዴድ ብልፅግና “የኢትዮጵያ መንግሥት” አይደለም። ሊሆንም አይችልም

330299294 757801602628806 8136974755935570526 n 1 1የሐገሩን ታሪካዊና ወሳኝ ድል፣ መላው አፍሪቃና የአለም ጥቁር ሕዝቦች ብኩራት በአደባባር እያከበሩት ያለውን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደጥንት ልማዱ እንዳያከብረው የከለከለ መንግሥት!! የድል መሪዎቹን ፎቶና የእነሱን ምስል የያዘ ልብስ እንድይለብስ የከለከለ፣ ያሰረና የገደለ ማንግሥት!! አድዋ ላይ ዘምቶ ሕዝቡን አንድ አድርጎ አዋግቶ በመጭረሻም በድል የተሰቀለውን ሰንደቅ እንዳይውለበለብ የከለከለ መንግሥት!! የድሉ ሐውልት በተገነባበት አደባባይ ድሉን ለመዘከር የወጣው ሕዝብ እያስቀደሰ በሚገኝበት ቤተክርስትያን ድረስ በመግባት በመርዝ ጭስ ያፈነና በጥይት እሩምታ የገደለ መንግሥት!! በእውነት ኢትዮጵያዊ ነው ወይንስ ፋሽስቱ ጠላት? ጣልያን “ኢትዮጵያዊ” አቆማዳ ለብሶ ለሦስተኛ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ተመልሶ ገብቷል? ያሰኛል። በፍፁም አያጠራጥርም። ይህ በጭራሽ “የኢትዮጵያ መንግሥት” ሊሆን አይችልም። የኦህዴድ ብልፅግና፣ እንደሚላላክለት የፈርንጅ ጌታው፣ “ኢትዮጵያ”፣ “ምኒልክ”፣ “ጣይቱ”፣ “ልሙጥ ባዲራ” የሚሉትን ቃላቶች፣ “ካፈ ቅቤው ልበ ጩቤው” አብይ አህመድ በስተቀር፣ እንደመርዝ የሚጠሉ የባንዳዎች ስብስብ ነው።እስካሁን ያልተረዳህ ብትኖር ቁርጥህን እወቀውና፣ ዛሬና ነገ ሳትል፣ “የሁለተኛ አድዋህን” ትግል አሁኑኑ ጀምር

 

አሁን የኦህዴድ አንኳር አላማ በጣም ግልፅ ነው።

የመላው የጥቁር ሕዝብ ገድል የሆነው አድዋ፣ ያሳፍረኛል ብሎ፣ የድል መሪዎቹ የምዬ ምኒሊክና የጀግናዋ የቴጌ ጣይቱ ሥም እንዳይጠቀስ የሚያደርግ መንግሥት “ኢትዮጵያዊ ነኝ” ለማለት ድፍረት አለው? የሚንልክም ሆነ የእቴጌ ጣይቱን ፎቶዎች የያዘ፣ ምስላቸውንም የለበሰና የሸጠ እያሰረ ያለ መንግሥት “ኢትዮጵያዊ ነኝ” ለማለት ድፍረት አለው?

የምዕራባውያንን ትእዛዝ ተከትሎ፣ ጥንታዊቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን ታሪክና መሰረት ለማፈራረስና ለማጥፋት እየሰራ ያለ ይህ መሰሪ መንግሥት “ኢትዮጵያዊ ነኝ” ለማለት ድፍረት አለው? በመሰረቱ ሰለ ዴሞክራሲያዊ መብቶች የኢፌድሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 29 እንኳን እንዲህ ይላል። ንዑስ አንቀጽ 1 ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል ይላል። ንዑስ አንቀጽ 2 ደግሞ ማንኛወም ሰው ያለምንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለፅ ነፃነት አለው። ይህ ነፃነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በፅሁፍ ወይም በህትመት፣ በስነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛወንም አይነት መረJአና ሃሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነቶችን ያካትታል ይላል። በተጨማሪም ንዑስ አንቀጽ 3 ለዴሞክራሲያዊ ሥራት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሃሳቦችና አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ፕሬስ በተቋሚነቱ የአሰራር የነፃነትና የተለያዩ አስተያየቶች የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የሕግ ጠበቃ ይደረግለታል። እንግዲህ ለራት ዓመታት ባይነውና በታዘብነው መሰረት ፈራጁም አሳሪውም ገዳዩም የኦህዴድ አምባገነናዊና አፓርታይዳዊ ሥርዓት ነው። ይህንን “ኢትዮጵያዊ መንግሥት” ነው የማለት እንክርዳድን የምታክል ብቃት አለው?

ለምን ጥቁር ለበሳችሁ እያለ ንፅሁሃን ኢትዮጵያዊያንን የሚያስር፣ ከሥራ የሚያባርር መሰሪና አምባገነናዊ መንግሥት በእውነቱ “ኢትዮጵያዊ ነኝ” ለማለት ድፍረት አለው?

ማንነትን (ብሄርን) ምርኩዝ በማድረግ ኦሮሞ ያልሆኑትን ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከኦሮምያና ከአዲስ አበባ የሚያፈናቅል፣ ለአመታት የኖሩበትን ቤታቸውን በግሬደር አፈራርሶ በሜዳ ላይ የሚጥል በጭካኔና በትቢት የተሞላ መንግሥት በእውነቱ “ኢትዮጵያዊ ነኝ” ለማለት ድፍረት አለው?

ትላንትና የአሮጊትና የአዛወንቶች ቤት አድሳለሁ፣ ወጣቶች የኔን አራያ ተከተሉ እያለ የተቀመጠበት ወንበር እስኪደላደል የደለለን አታላይ አብይ አህመድ ዛሬ በመላው አዲስ አበባና “ሸገር” ብለው ከሚገነቡት ለኦህዴድ ብልፅግና መሪዎችና ካድሬዎቹ የተካለለ አፓርታይዳዊ ክልል፣ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ያልሆነው ሁሉ ቤቱ በቡልዶዘር እየፈረሰ፣ የሞተው ሞቶ የቀረው ደግሞ ሜዳ ላይ ተወርውሮ ግማሹ ደግሞ በጅብ ተበልቷል። ታድያ ሸረኛው፣ አስመሳዩ፣ ቀጣፊውና አታላዩ አብይ አህመድ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ነው? ኦባንግ ሜቶ “ያገኘንው የብሄር መሪ እንጂ የኢትዮጵያ መሪ አይደለም” ብሎ ጨርሶታል።

በወለጋ የሚኖሩትን አማሮች “ሸኔ” በሚባል እራሱ የኦህዴድ ብልፅግና ባደረጀው፣ ባሰለጠነውና ባስታጠቀው ቡድን አማራውን በገፍ ያስጨፈጨፈ፣ ያስቃጠለ፣ ከእናት ማህፀን ሽል አውጥቶ ያስዘለዘለ፣ ይህም በቃኝ ሳይል በሺህ የሚጠጉ አማራዎች በማንነታቸው እየታረዱ ሳለ ዛፍ የሚተክል፣ የስንዴ እርሻ የሚጎበኝ “አረመኔና የድንጋይ ልብ ያለው” ጨካኝ መሪ በየትኛው መርሆ “ኢትዮጵያዊ ነኝ” የማለት ድፍረት አለው? ዛሬ ደግሞ በእጅ አዙር አማራን ሲይቃስጨፈጭፍና ሷፈናቅልለት የንበረውን ሸኔ በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዳይከሰስበት፣ እሱንም በክስ ውስጥ እንዳያስገባው በማለት ለእርቅ እንደራደር ይለዋል። ሕዝብን በሰቃቂና በኢሰባዊ መንገድ በማንነቱ የጨፈጨፈን ወንጀለኛ እንታረቅ የሚል የትኛው የአለም መንግሥት ነው። እስራኤሎች እንኳን እስካሁንም ድረስ የናዚ ገዳዮችን፣ እንኳን ሃገራቸው ውስጥ ይቅርና፣ የገቡበት ገብተው አድነው ለፍርድ ያቀርቧቸዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የሐገራችን ሕዝብ፣ በየትኛውም አካባቢና ክልል በግፍ የተጨፈጨፉበት፣ የተቆራረጡበት፣ የተቃጠሉበትና የተፈናቀሉበት ጊዜ የለም። ታድያ ማን ነው “መንግሥት አለን” ብሎ ለመናገር ድፍረት ያለው?

በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ሕግ የለም። ሕግ ማለት የኦህዴድ ብልፅግና መሪዎችና እነሱን ከላይ ሆኖ የሚዘውረው የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮ አስተያየትና ውሳኔ ሆኗል። እንደፈለጋቸው ያፍናሉ፣ ያስራሉ፣ ይገድላሉ፣ይፈታሉ። ፍርድ ቤትና ዳኞች ቢሮ ለማድመቂያና የሰፊውን ሕዝብ ሰብአዊ መብት ማፈኛ አካሎች በመሆናቸው ማንኛውም ውሳኔ የሚረጋው በኦህዴድ ብልፅግና

ደረጀ አዳኖ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

Go toTop