ዓድዋ 127 – የዓድዋ ድል በዓል በአንጎለላ፣ አንኮበር እና ደብረ ብርሃን

 የዓድዋ ድል ሲነሳ ቀድመው በሚነሱት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ፊታውራሪ ገበየሁ፣ ራስ መኮነን . . . የትውልድ ምድር በሆነው ሸዋ 127ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ከነገ የካቲት 21 ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በድምቀት መከበር ይጀምራል።

ዓድዋ በሸዋ ከተሞች በተለይም በአንጎለላ፣ አንኮበር እና ደብረ ብርሃን በጉብኝት፣ በጎዳና ላይ ትርኢት፣ በኪነ-ጥበብ ዝግጅትና በፓናል ውይይት ሲዘከር ደስ ብሎት ማክበር ከፈለጉ በጠዋቱ ወደ ምስራቅ ይጓዙ።

ለዓድዋ 127

የካቲት 21 አንኮበር እንሄዳለን። ድንቅ ተፈጥሯዊ ገጽታዎች፣ ከአጼ ይኩኖአምላክ ዘመን እስከ ዳግማዊ ምኒልክ የተሰሩ ዘመን አይሽሬ ህያው ቅርሶች በአንኮበር ይጎበኛሉ። ውይይት ይደረጋል፣ በነገሥታቱ ቤተ መንግስት ደስታ ይሆናል።

የካቲት 22 አንጎለላ ነን። “ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ፣ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ” የተባለላቸው ዳግማዊ ምኒልክ የተወለዱት በዚህ ነው። “ግንባሬን ካልሆነ ስሸሽ ከኋላየ ከተመታሁ ስሜ አይታወስ” ብለው ከዓድዋ ጦርነት በፊት ውድ መስዋዕትነት የከፈሉት ፊታውራሪ ገበየሁ የትውልድ ቦታም ናት አንጎለላ።

በአንጎለላ ከሚደረገው ጉብኝት በተጨማሪ ልዩ የፈረስ ግልቢያ ትርኢት ይካሄዳል። በዚህ የፈረስ ግልቢያ ትርኢት ከአንጎለላ በተጨማሪ ከኦሮሚያ አጎራባች ወረዳዎች በሚመጡ ፈረሰኞች ዳግማዊ ምኒልክና የዓድዋ ጀግኖች ይወደሳሉ።

የካቲት 23 የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ቀን ነው። ደብረ ብርሃን ደግሞ ይሄን ልዩ ቀን በድንቅ መንገድ ለመዘከር ተዘጋጅታለች። በዚህ ቀን የዳግማዊ ምኒልክ ሀውልት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ይቀመጣል። ዋናው በዓልም በአጼ ዘርዓያዕቆብ አደባባይ ልዩ በሆነ መንገድ ይከበራል።

ይምጡ!

ዓድዋን ከእኛ ጋር ያክብሩ!

አዲስ አድማስ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያናደደ የፓትርያርኩ ንግግር ይፋ ሆነ! ሀብታሙ አያሌው አቡነ ማትያስ @Ahaz tube አኃዝ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share