ተሳቀናል ማለት የብሄር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ የተባለውን የወረደ የዘቀጠ ሃሳብ ፈርተናል ማለት ነው።
ብጹዕ አባታችን አቡነ አብርሐም በረከትዎ ይደርብን!! በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ እርስዎን ወደ ፊት ያመጣ ቅዱስ ሲኖዶስ የተከበረ የተመሰገነ ይኹን!
ወንድም እህቶቼ ሆይ! ገና ጅማሮ ላይ ነንና እንደ ኹል ጊዜው ቅዱስ ሲኖዶስ ባዘዘን መሠረት በንጋት በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናችን ተገኝተን ለቸር አምላክ ክብር፤ በሕብረት ኪዳናችንን አድርሰን፣ አስቀድሰን እና የወንጌል ስብከት አገልግሎት ተካፍለን ሰንበትን እናክብራት።
ቸር አምላክ ያየናልና ደስ ይበላችሁ!