በደም የጨቀዬው የሳሪዮስ መስቀል፣
ባልነበር ልዩነት ባልተሰራ በደል፣
መንጋውን ሰብስቦ ይላል እንበቀል።
የኦነግ ሲኖዶስ የጨበጠው መስቀል፣
ይላል ግደል!ግደል! ይላል ስቀል!ስቀል!
ከፍ ካለው ቦታ እራሱን አውርዶ፣
ቀሳውስቱን ገሎ ፣ምዕመናኑን አርዶ፣
ክርስቲያን ነኝ ይላል ክርስትናን ክዶ፣
የት ይሆን መድረሻው ከቶ ሄዶ ሄዶ?
መንበሩን እረግጦ ቤተስኪያን አርክሶ፣
ጽላቱን ወርውሮ፣ተቋሙን አፍርሶ፣
አትግደል ያለውን ትዕዛዙን ጥሶ፣
ሌላ ጽላት ይዟል በሰው ደም ለውሶ።
እኔስ አዘንኩለት ለኦሮሞ መንጋ፣
ሃይማኖቱን ጥሎ ሃይማኖት ፍለጋ፣
ለባእዳን እምነት እጁን ሲዘረጋ፣
እርስ በርሱ ሲላጋ፣ ሲጋደል ሲዋጋ።
ምን ይሰማው ይሆን አዚሙ ሲለቀው፣
ይኸ ጊዜ አልፎ ሲገፈፍ ጨለማው፣
ብርሃን ሲፈነጥቅ ሌሊቱ ሲነጋ፣
ከልጅ ልጆቹ ጋር ቁጭ ብሎ ሲያወጋ ?
የእብሪቱ ክምር እንደ እምቧይ ይናዳል፣
በታሪክ ሚዛን ላይ ትውልዱ ይፈርዳል፣
የጊዜ ጉዳይ ነው!
ሁሉም ሳይደበቅ ፊት ለፊት ይወጣል፣
ማቅ አልባሽ ማቅ ለብሶ ሃዘን ይቀመጣል።
አጋጣሚ ሆኖ በቦታው ባልገኝ፣
አሁን ግን እላለሁ እኔ እሱን አያርገኝ።
አገሬ አዲስ
የካቲት 1 ቀን 2015 ዓም(08-02-20230