በህገመንግስቱና በሽግግሩ ቻርተር ይሁን ቢባል እንኳ (ቢባል እንኳ ነው እያልኩ ያለሁት) ወልቃይቶችና ራያዎች የአማራ ህዝብ አካላት ከመሆን የሚያግዳቸው አንዳችም ነገር የለም!!!

ፋስሽስቱ ህወሐት በወቅቱ የነበረውን ወታደራዊ ጡንቻና የፖለቲካ የበላይነት ተጠቅሞ የወላቃይት ጠገዴ አማራዎችን ማንነት እና መኖሪያ ቦታ ይለፈቃዳቸውና ያለፍላጎታቸው ዘርፎ ወደትግራይ ክልል ጠቀለለ። በዚህ ጊዜ ህገመንግስት የሚባል ነገር አልነበረም። ወልቃይቶች ግን ዃላ ላይ ሀገመንግስቱ ሲፀድቅ ስለወሰን አከላለል ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች ቀድመው የተረዱ ይመስል “አሰፋፈራችን፣ ባህላችን፣ ቋንቋችን፣ ወጋችን፣ ልምዳችንና ታሪካዊ ትስስራችንና ስነልቦናዊ ውቅራችን አማራ ሆኖ እያለ እንዴት ወደትጋራይ እንካለላለን” ብለው ሲቃወሙና ሲታገሉ ኖረዋል።

በወቅቱ ሁኔታዎች ወደነበሩበት ይመለሱና ሁሉም በህግ አግባብ ይታዩ የሚሉ ጥያቄዎች ቢቀርቡም ህወሐት ሊሰማ አልፈቀደም። ጭራሽ ጥያቄ የሚያነሱትን መግደል፣ ማሰር፣ ማሳደድ፣ ማፈንና ማፈናቀል ስራየ ብሎ ተያያዘው።

እንዳለመታደል ሆኖ ህወሓት የማንነት ዝርፊያውን ሲፈፅም በአማራ ክልል በኩል ይህን ፋሽስት ሃይል የሚገዳደር የተደራጀ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ሃይል ባለመኖሩ ምክንያት የወልቃይቶች አፈና ለሰላሳ አመታት ቀጠለ።

መጨረሻ ላይ ግን ራሱ ህወሐት በለኮሰው ጦርነት ራሱ ተቃጥሎ የዘረፈውን ማንነት ጥሎ ሸሸ። በዚህ ጊዜ አማራዎቹ ወልቃይቶች ማንነትና መኖሪያ ቦታ በእጃቸው ገባ። That is what is known as ” status quo ante.”

በነገሬ ላይ ከዚህ ጋር ያያያዝኩት  ፅሁፌ የሚያጠነጥነው በዚህ ዙሪያ ነው።

 

መሰረት ተስፉ (Meseret.Tesfu@Yahoo.Com)

 

ሀወሐትና የህወሓት ጉዳይ አስፈፃሚዎች ወልቃይትና ራያ በህገመንግስቱ መሰረት የትግራይ አካላት ናቸው ሲሉ እንሰማለን።

በዚህ ጉዳይ ላይ ያለኝን ሃሳብ በግልፅ ከማቅረቤ በፊት ግን ስለወልቃይት ጠገዴና ራያ ታሪካዊ ዳራ የተወሰነ ነገር ለማለት ወደድኩ:: እንደሚታወቀው ከ1984 ዓ.ም በፊት ወልቃይት ጠገዴ officially በጎንደር፤ ራያ ደግሞ በወሎ ስር የነበሩ ቦታዎች ናቸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ህወሃት “ታላቋን ትግራይን” ለመመስረት በነበረው ህልም ምክንያት በአንድ በኩል ግዛት ለማስፋፋት ለም መሬቶችን የትግራይ አካል ለማድረግ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከውጭው አለም ጋር ለመገናኘት የሚያስችለው ኮሪዶር ለማግኘት በማሰብ እዚህም እዛም ማማተሩ አልቀረም። ስለሆነም በትጥቅ ትግሉ ወቅት በተለይ ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ወልቃይት ጠገዴ መስፋፋት መጀመሩ ይታወቃል።

በዚህ ረገድ ያለውን እውነታ ግልፅ ለማድረግ ያህል የተወሰኑ ነጥቦችን ማንሳት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። በትጥቅ ትግሉ ሂደት ረዘም ላለ ጌዜ አባላቱ በሚለብሷቸው ካኔትራዎችና በሚዘጋጁ አንዳንድ ፅሁፎች ላይ ይታተም የነበረው የትግራይ ካርታ ወልቃይት ጠገዴንና ራያን አይጨምርም ነበር። ህወሃት በግዛት መስፋፋቱ የፀና አቋም መውሰድ ከጀመረ በኋላ ግን እነዚህን ፅሁፎችና ካኔትራዎች ድራሻቸውን እንዳጠፋቸው ሁኔታውን የሚያውቁ የሚመሰክሩት ሃቅ ነው።

የህወሃት የቀድሞ አመራሮች የነበሩት እነአቶ አብራሃም ያየህም ደርግ ሊወድቅ አከባቢ ባደረጉት ቃለመጠይቅ የህወሃትን የግዛት መስፋፋት እቅድ በዝርዝር ገልፀውት እንደነበር ማስታወስ ተገቢ ነው። እነዚህ አመራሮች በወቅቱ ባደረጉት ቃለመጠይቅ ህወሐት የትግራይ አካል ያልሆኑትን ወልቃይት ጠገዴንና ራያን፤ አልፎም እስከ አልውሃ ምላሽ ቆርጦ ወደ ትግራይ የማካለል ህልም እንደነበረው በግልፅ ማስረዳታቸውን የሚያሳይ ዩቱብ ፈልጎ ማዳመጥ ይቻላል። ይህ ተስፋፊ የሆነ ፍላጎት ትክክል እንዳልነበረ እነአቶ አብራሃም ያየህ አፅኖት ሰጥተው እንደገለፁት አስታውሳለሁ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እባብ ለእባብ፣ ይተያያል በካብ – በወንድሙ መኰንን፣ ለንደን

ኋላ ላይ ትጥቅ ትግሉ ተጠናክሮ ቀጠለና በአስራ ዘጠኝ ሰማንያ ሶስት ዓ.ም ደርግ ከስልጣን ሲወገድ ተጠናቀቀ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ለሃያ ሰባት አመታት ሁሉም የሃገሪቱ እጣ ፋንታዎች የሚወሰኑት በህወሃት አመራሮች መሆኑ ላብዛኞቻችን ግልፅ ነው ብየ አምናለሁ። በነዚያ ሃያ ሰባት አመታት ውስጥ ህወሃቶች ግልፅ አመራር ሰጥተው ይቅርና ካፋቸው አንድ ቃል ቢወጣ እንኳ እንደፈጣሪ ቃል የሚከበርበት፣ ምጣድ አቀብሉን ቢሉ ሞግዱን ረሳችሁት የሚል መልስ የሚያገኙበት፣ ገርፈውም ሆነ ገድለው ራሳቸው የሚጮሁበት እንዲሁም ያሻቸውን ነገር ሁሉ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲፈጠር የሚችሉትን ሁሉ አድርገው በጊዜው ተሳክቶላቸው ነበር።

በመሆኑም ደርግ ወድቆ ህወሐቶች በበላይነት ሃገሪቷን እንደተቆጣጠሩ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ሲያልሙት የነበረውን ሁሉ ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ። ተግባራዊ ካደረጓቸው እቅዶች አንዱና ዋነኛው ወልቃይት ጠገዴንና ራያን ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ Officially ወደ ትግራይ እንዲካለሉ ማድረግ ነበር። ማካለሉን ተግባራዊ ባደረጉ ማግስት ደግሞ ከተዋጊዎቻቸው የተቀነሱ (በወቅቱ አጠራር Demobilized የተደረጉ) አባሎቻቸውንና ሌሎች አከባቢዎች ይኖሩ የነበሩ ተጋሩዎችን በማስፈር ዴሞግራፊውን ለመቀየር የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል።

ህወሃቶች ይህን ለማድረግ ያስቻላቸው በወቅቱ የነበራቸው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጡንቻ እንጅ ህጋዊ መንገድ አልነበረም። የ1984 አ.ም ቻርተርና በተለይ ደግሞ ዃላ ላይ የፀደቀው ህገመንግስት “ክልሎች የሚዋቀሩት በህዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ ማንነትና ፍላጎት ነው” ይላሉ እንጅ የሄ አከባቢ አማራ ነው፣ ያኛው ደግሞ ትግራይ ነው የሚል ድንጋጌ አላስቀመጡም።

የወልቃይት ጠገዴም ሆን የራያ ነዋሪዎች ቋንቋችን፣ ባህላችን፣ ስነልቦናዊ ውቅራችን፣ ጂኦግራፊያዊ አሰፋፈራችንና ማንነታችን የሚተሳሰረው ከአማራ ህዝብ ጋር በመሆኑ መካለል ያለብን ወደ አማራ ክልል እንጅ ወደ ትግራይ ክልል አይደለም ብለው በፅናት እየተቃወሙ ነው ወደ ትግራይ እንዲካለሉ የተደረጉት።

ህወሃቶች ወልቃይት ጠገዴንና ራያን ከላይ በተገለፀው ኢ-ፍትሃዊ መንገድ ወደ ትግራይ እንዲካለሉ ካደረጉና የነዋሪዎቹን ማንነት ከነጠቁበት ጊዜ አንስተው ተቃውሞ ማቅረብ የጀመሩት  የወልቃይትና የራያ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በሌሎች አከባቢዎች የሚኖሩ አማራዎችና ኢትዮጵያውያንም ነበሩ።

ህወሃቶች ወልቃይትንና ራያን በሃይል ወደ ትግራይ እንዲካለሉ ማድረጋቸው ሳያንስ ጭራሽ የቦታዎቹ ባለቤት የነበሩት አማራዎች ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውን፣ ወጋቸውንና ልምዳቸውን እንዳይጠቀሙና እንዳያከብሩ መከልከል ጀመሩ። ለምሳሌ የየአከባቢዎቹ አማራ የሆኑ ነዋሪዎች አማርኛ ዘፈኖችን እንዳያዳምጡ፣ የአማራ ክልል የእግር ኳስ ክለቦችን እንዳይደግፉ፣ የነሱንም ማሊያዎች እንዳይለብሱ፣ ቀይ ቢጫ አረንጓዴ ቀለማት ያሉበትን ሰንደቅ አላማ እንዳይጠቀሙ ሲከለከሉ እንደነበር በተለያዩ ጊዚያት ምርር ብለው ገልፀዋል፤ አሁንም ሲገልፁ ይደመጣሉ። ይህ ለምን ይሆናል ብለው የጠየቁ አማራዎችም ተገድለዋል፣ ተደብድበዋል፣ ተሳድደዋል፣ ንብረታቸው ወድሟል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ኢሕአዴግ ፖለቲካውን የሚመራው በዕዝ ነው እንጂ በሃሳብ የበላይነት አይደለም" - አቶ ሃብታሙ አያሌው

በዚህ መልክ ግፍና ሰቆቃ በአጠቃላይም ኢ-ፍትሃዊ የሆነ ተግባር የተፈፀመባቸው አማራ የሆኑ የሁለቱም አከባቢ ነዋሪዎች ተሰባስበው የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በማቋቋም አደረጃጀቶቻቸውን አጠናክረው መብቶቻቸውንና ፍትህን ለማስከበር ጥረት ማድረጋቸው አልቀረም። ኮሚቴዎቹ ፍላጎታቸው ምን እንደሆነ ለህዝብ በማሳወቅ ህጋዊ ጥረት ማድረግ ቢጀምሩም በህወሃት ሳንባ ሲተነፍሱ የነበሩት ሁሉም የመንግስት ተቋማት ግን ፍትሃዊ የሆነ ምላሽ ሊሰጧቸው አልቻሉም። እንዲያውም ማንነታቸውን ለማስመለስ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን እነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ለማጥፋት ህወሃት ገዳይ ቡድን ወደ ጎንደር መላኩ ይታወቃል።  ይሁን እንጅ በጎንደር ህዝብና በራሳቸው በነኮሎኔል ደመቀ ጀግንነት የህወሐት የአፈና ሙከራ እንደከሸፈ በታሪክ የተመዘገበና ሁሉም ሰው የሚያውቀው ሃቅ ሆኖ አልፏል። በነገራችን ላይ እነኮሎኔል ደመቀ ከጎንደር ህዝብ ጋር ሆነው የህወሐትን ጠለፋ ያከሸፉባት ሃምሌ አምስት ዃላ ላይም ህወሐትን ለመጣል እርሾ ሆና እንዳገለገለች እገረመንገዴን ለማስታወስ እወዳለሁ።

ከዚህ ጎን ለጎንም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎችና በውጭም የሚኖሩ አማራዎች የወልቃይት ጠገዴንና የራያን ህዝብ የማንነት ማስመለስ ጥያቄዎች ፍትሃዊነት እውቅና ሰጥተው ከጎናቸው በመሰለፍ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል። ድምፃቸውን ማሰማት ብቻ ሳይሆን በያሉበት የድጋፍ ኮሚቴዎችን በማቋቋም በሃሳብ፣ በገንዘብና በቁሳቁስ ለማጠናከር ጥረት ማድረጋቸው ይታወቃል። በተለይ ብአዴን ውስጥ የነበርን በርከት ያልን ታጋዮች ደግሞ ወልቃይትና ራያ ወደ ትግራይ ከተካለሉበት ኢ-ፍትሃዊነትና ፀረ ዴሞክራሲያዊነት ጋር እያያያዝን የህወሃትን ተስፋፊነት በመግለፅ በመድረክም ሆነ ከመድረክ ውጭ ፊት ለፊት ለመታገል ሞክረናል።

በአስመላሽ ኮሚቴዎቹ በተለይና እነሱንም በሚደግፏቸው ሌሎች አማራዎችና ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ ሲነሱ የነበሩ የማንነት ማስመለስ ጥያቄዎች ፍትሃዊ ምላሽ ሳያገኙ ለውጥ የሚባለው ነገር መጥቶ ህወሃቶች መቀሌ ሄደው ተወሸቁ። በዚህ ጊዜ የኮሚቴዎቹና የነዋሪዎቹ ጥያቄዎች እየጎሉ እንደመጡ የተለያዩ የዜና አውታሮች ዘግበዋቸዋል። መንግስትም ጥያቄዎቹን በሚገባ አይቶ አግባብነት ያለው መልስ እንደሚሰጥ ቃል እንደገባ የዜና ዘገባዎቹ አመላክተዋል።

ህዝቡ በአስመላሽ ኮሞቴዎቹ እየተመራ የመንግስትን ህጋዊና ፍትሃዊ  የሆነ መልስ እየተጠባበቀ ባለበት ወቅት ግን ህወሃቶች ሰሜን እዝን ከጀርባው ወግተው የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ሚዛን በማዛባት ኢትዮጵያን ለነሱዳን ወረራ ያጋለጠ እጅግ በጣም አሳፋሪና አሳዛኝ ድርጊት በመፈፀም የማይረሳ የታሪክ ጠባሳ ጥለው አልፈዋል። በዚህ ብቻ ግን አላበቁም። በወልቃይት ጠገዴና ራያ የፈፀሙት የማንነት ዘረፋ ሳይበቃቸው ይባስ ብለው ሌላ ተጨማሪ ዘረፋ ለማካሄድ በአማራ ይዞታዎች ላይም ጥቃት ሰነዘሩ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ''ዛሬም ታለቅሳለች!'' - ወቅታዊ ግጥም ከፊሊጶስ

ደግነቱ ከህወሃት ስግብግብ ባህሪና ከፍተኛ የሆነ የጦርነት ዝግጅት በመነሳት ጥቃት ይፈፀምብኛል ብሎ ሲያስብ የነበረው የአማራ ህዝባዊ ሃይል በየአከባቢው በተጠንቀቅ ቆሞ ክልሉን ይጠብቅ ስለነበረ ልክ ጥቃቱ እንደተፈፀመ ወዲያዉኑ በመሰባሰብ መከላከል ካደረገ በኋላ ከመከላከያና ከልዩ ሃይል ጋር ተባብሮ መልሶ በማጥቃት የህወሃትን የወረራ ሙከራ ማክሸፉ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

የአማራን ህዝባዊና ልዩ ሃይል እንዲሁም የመከላከያን መልሶ ማጥቃት መቋቋም ያልቻለው የህወሃት ዘራፊ ቡድን ነጥቋቸው የነበሩትን የወልቃይት ጠገዴንና የራያን አከባቢዎች ብዙም ሳይቆይ ጥሏቸው እግሩ ወዳመራው አቅጣጫ የሸሸ መሆኑ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። በዚህ ጊዜ የማንነት ዘረፋ የተፈፀመባቸው የወልቃይትና የራያ ነዋሪዎች ማንነታቸውን መልሰው በእጃቸው ለማስገባት ቻሉ። ነዋሪዎቹ ማንነታቸውንና መኖሪያወቻቸውን መልሰው በይዞታቸው ስር ካስገቡ በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ይህንኑ በሆታና በጭፈራ በአደባባይ አበሰሩ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በራሳቸው ተነሳሽነት ማንነታቸውን ያወጁት የየአከባቢዎቹ ነዋሪዎች “ከትግራይ እንዲኖረን የምንፈልገው መልካም ጉርብትና እንጅ የትኛውንም አይነት አስተዳደር አይደለም” በማለት ፍላጎታቸውን በአደባባይ እየገለፁና እያሳወቁ ይገኛሉ።

ይህን የህዝቦች ፍላጎት መሰረት በማድረግም የአማራ ክልል ህዝባዊ ሃይልና የክልሉ መንግስት የሚችለውን ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛል።

ከላይ የተቀመጡትን ሁኔታዎች ጠቅለል ሲደረጉ በሽግግሩ ቻርተርና በህገመንግስቱ ይታይ ቢባል እንኳ ወልቃይትና ራያ የአማራ እንጅ የትግራይ አካላት ሊሆኑ ፈፅሞ አይችሉም። ምክንያቱም ከላይ በተራ ቁጥር 8 እና 9 ላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት እነዚህ አከባቢዎች በጉልበት ወደትግራይ የተጠቃለሉት የህዝብ አሰፋፈርን፣ ቋንቋን፣ ማንነትን፣ ስነልቦናዊ ውቅርን/ትስስርንና የህዝብ ፍላጎትን ግምት ውስጥ ባላስገባ መንገድ ባለመሆኑ ነው።

በዚህ አግባብ ሲታይ የህወሓት ሰዎች ወልቃይትና ራያ ላይ ያደረጉት የመሬት ማካለል ከመሰረቱም ቢሆን ፉርሽ (Void Ab Initio) መሆኑን በሚገባ መረዳት ያስፈልጋል። በመሆኑም ፈረንጆቹ Restitution እንደሚሉት የወልቃይትና የራያ ነዋሪዎች ማንነታቸውንና መኖሪያዎቻቸውን ካስመለሱ በኋላ በሙሉ ፍላጎታቸው ተነሳስተው ወደመረጡት የአማራ ክልል መጠቃለላቸው ተፈጥሯዊ መብታቸው መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። የሚቀረው ይህን ያፈጠጠ እውነታ ህጋዊ እውቃና እንዲኖረው ማድረግ ነው። ለዚህ ደግሞ የሁላችንም ርብርብና ተሳትፎ ወሳኝ ነው እላለሁ።

ይህ በመሆኑ ምክንያት ማንነቴ ተገ’ፏል የሚል ሌላ አካል ካለ ደግሞ ጥያቄውን በህጋዊ መንገድ አቅርቦ መፍትሄ ከመፈለግ የሚያግደው አንዳችም ገደብ አይኖርም።

 

11 Comments

 1. በህገመንግስቱና በሽግ ግር ቻርተሩ መሰረት ክሆንማ ወላቃይት ጠገዴ ወደ ትግራይ ሂያጅ ነው።

  ክርክርህ በታሪክ ወላቃይት ጠገዴ የማን ነበረ የሚል ጥያቀ አንስቶ የአማራ በሚል የሚመልስ ነው። በጦር ሃይል በህወሃት የተወሰደ ወላቃይት ጠገዴን በአማራ ትግል ወደአማራ በማስመለስ የአማራን ይዞታ ማረጋግጥ ይቻላል ወይ የሚለውን ጥያቀም በትክክል በማለት ትመልሰዋልህ። ከህገመንግስት አንጻር ያነሳሀው ነጥብ ቢኖር ወላቃይት ጠገዴ ወደ ትግራይ የተካለለው ህገመንግስቱ የሚጠይቀውን የህዝብ አሰፋፈርን፣ ቋንቋን፣ ማንነትን፣ ስነልቦናዊ ውቅርን፨ት ስ ስ ርንና የህዝብ ፍላጎትን ግምት ውስጥ ባላስገባ መንገድ ባለመሆኑ ነው የሚለው ብቻ ነው።

  ከላይ የተነሱትን ነጥቦች አንድ በ አንድ እን ያቸው። ታሪክ ሁኔታዎችን ለመረዳት ጠቃሚ ቢ ሆንም የሚያነሳ ውዝግብ ወይም ፍሬ ጉዳይ አንደ በህግ ከታሰር በኋላ አግባብነቱ ምንም ነው። በተለይም ህግመንግስት ዋና ወዲያ ወዲህ የማያዋዛ ሰነድ ነው። መክበር አለበት፣ ካልተከበር ከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ ይከተላል። አና አንድ ውዝግብ በህገመንግስት መሰረት ይፈታል ከተባል ማጣፊያው አጭር ነው። እንዳለ መቀበልን ይጠይቃል። በታሪክ ወላቃይት ጠገዴ ከ አማራ ጋር መሆኑ ህግመንግስቱ በስራ ላይ ከዋለበት ጊዘ ጀምሮ ተለውጧል ለማለት ይቻላል። በዚህ ላይ ወልቃይት ጠገዴ ምፅራብ ትግራይ ተብ ሎ ካርታ ተሰርቶ በትግራይ ክልል ስር ገብቶ በትግራይ ሀገመንግስት ውስጥ ሲጻፍ የ አማራ ክልል ምን አደረገ ቢባል መልሱ ምንም የሚል ነው። እንዲያውም የአማራ ክልል በትግራይ ክልል ሀገመንግስት መወ ረት የተሰራውን ካርታ ተቀብሎ የራሱን ክልል ሀገመንግስት አውጥቶ ካርታ ሲሰራ ምፅራብ ትግራይ ከሚባልው እንደሚዋሰን አሳውቌል። ይህ የ አማራ ክልል ሀገመንግስትና ካርታ እስከዛሬ አልተለወጡም። በፊት ህወሃት ስላማይፈቅድ መለወጥ አልተቻለም ቢባል እንኴ ባለፉት ሁለት አመታት ያለተለወጠበት ምክያት ምንድነው፡ ያለጥርጣሬ ሁኔታውን አምኖ በመቀበል ነው የሚል ክርክር ያስነሳል። አሁንም የ አማራ ክልል ሀገመንግስቱንና ካርታውን ካልቀየረ በሀገመንግስት መሰረት ወላቃይት ጠገዴን ማጣቱ አይቀርም። በዚህ ሁኔታ የአወዛጋቢ አክባቢ ጉዳይ በህገመንግስቱ መሰረት ይፈታል ሲባል አክባቢው ቀድሞ ወደነበረበት ወደትግራይ ይመለሳል ማለት ነው። ቀድሞ በትግራይ ሰር ምፅራብ ትግራይ ይባል የነበረው ወደትግራይ ተመልሶ ምፅራብ ትግራይ ይሆናል ማለት ነው። ____

  በጦር ሃይል በህወሃት የተወሰደ ወላቃይት ጠገዴን በአማራ ትግል ወደአማራ በማስመለስ የአማራን ይዞታ ማረጋገጥ ተችሏል የሚለውም አማራ ክልል ሀገመንግስቱንና ካርታውን እስካልቀየረ ድረስ ድርጊቱ ህገወጥ ተደርጎ ሊወሰድና ወላቃይት ጠገዴ ወደትግራይ ሊባል ይችላል። በሃይል ማያዝ ይዞታን ሕገወጥ እንጂ ሕጋዊ አያደርገውም። የህዝብ አሰፋፈርን፣ ቋንቋን፣ ማንነትን፣ ስነልቦናዊ ውቅርን፨ት ስ ስ ርንና የህዝብ ፍላጎትን ግምት ውስጥ ባላስገባ መንገድ የተካሄደ የሚለው ክርክርም ቢሆን አሁን ብዙም ጠቀሜታ ያለው ክርክር አይመስልም። በሰላስ ምናምን ፃመታት ሁኔታዎች እጅግ ስለተለዋውጠዋል። ማን በብዛት ነበረ ወይም አለ የሚለው ብዙም ችግሩን ለመፍታት ኣይጠቅምም።

  ደግነቱ ግን የፕሪቶሪያው ስምምነት የተፈረመው የሕወሃት አሸባሪነት ፍረጃ ከመነሳቱ በፊት በመሆኑ ሰራ ፈጻሚው አካል የተወካዩች ምክር ቤት ፍረጃውን ሳያነሳለት በርሱ ፍላጎት ያደረገው ስልሆነ በህግ ከተሰጠው ስልጣን በላይ ሄዷል። ስለሆነም ተፈጻሚነቱ ህጋዊነት ይጎድለዋል። ይህም ቢሆን የአማራ ክልል ሀገመንግስቱንና ካርታውን ቶሎ መቀየር አለበት። አለበለዚያ ወላቃይት ጠገዴ አኦሮማይ ማለት ነው።

 2. ወዳጄ ህጉን ተወው ባለፉት 50 አመታት በኢትዮጵያ ምድር በህግ የተከናወነ ምንም ነገር የለም፡፡ አብይ ከትግሬዎች ከሚጣላ ካሁን በኋላ ባህርዳርና ጎንደርን እስከ ነብሱ ለትግሬዎች ቢሰጥ ይቀለዋል፡፡ እነ አገኘሁ ተሻገርም ጎንደር ይዘውት ሂደው የሆኑትን መታመስ ሳትመለከት አትቀርም አሁን ህጉን ትተህ ለነጻነቱ የሚሞት የአማራ ህዝብ ማደራጀት ነው የሚጠበቅብህ፡፡ሁፉም ምኑም ቀረርቶውም ያልተሞከረ የለም ህዝቡ አሳምነውን፤ምግባሩን፤ዘመነ ካሴንና ፋኖ ልጆቹን አስበልቶ የተቀመጠ ነው እውነቱ መነገር አለበት፡፡ የትግሬ ነብሰ በላዎች ምቾታቸውን ጥለው ጫካ ገብተዋል አቦይ ስብሃቱ እስክ መዋስሉና ሺሻው በዚህ እድሜው ጫካ ገብቷል ጎበዝ ከዚህ አለመማር ግብዝነት ነው፡፡ ተደራጅ፤መክት ነው መልእክቱ መሆን ያለበት ፡፡ ተላላኪ ብአዴንም ሁነው አንድ በአንድ በወረንጦ እየተለቀሙ እንዴት በውርደት እንደ ተባረሩ ተመልክተናል ምንጠራው ይቀጥላል፡፡ በእርግጥ ምንጠራው አቶ ደመቀና አገኘሁ ተሻገርን ላይነካ ይችላል፡፡ መርሃ ጻድቅን የመሰሉ የህግ ምሁር ብ አዴን አብይን ሊያስቀይሙብኝ ይችላሉ ብሎ ከስራቸው አንስቷቸዋል ጥፋታቸው ለአማራው መታገላቸው ነው፡፡

 3. ስለ ወያኔ ክፋት ስንናገር የሚከፋቸው ጅላጅሎች ወያኔን ከሥር መሰረቱ የማያውቁ የቀን ተሰላፊዎች ብቻ ይመስሉኛል። አሁን እንሆ በዚህም በዚያም የሚናፈሰው የድርድር ወሬ እየቆየ መልሶ ግጠሙን እንግጠም የሚሉ ሁኔታዎች እየታዪ ነው። ለምሳሌ የጠ/ሚሩ አማካሪ 70 % የትግራይ መሬት በመከላከያ ቁጥጥር ስር እንደሆነ ተናግሯል። ቀጥሎም መከላከያ በተቆጣጠራቸው ስፍራዎች እህልና መድሃኒት ለህዝቡ እየደረሰ ነው በማለት ላይ እያለ በጎን የወያኔ አፈቀላጤ ጌታቸው ረዳ ደግሞ ይህ ሁሉ ውሸት ነው በማለት ያው እንደ ተለመደው ለተከፋይ ወሬ አናፋሾቻቸው ድምጽን አሰምቷል። ይህ ሁሉ ግን ጠብ ፍለጋ የሚደረግ ስልት ነው። ሲጀመር በምንም የሂሳብ ስሌት 70% የትግራይ መሬት በመከላከያ እጅ ነው ብሎ ለመናገር ይከብዳል። በሌላ መልኩ ለወያኔ ወርቅ አንጥፈህለት ጮማና ውስኪ ብትግተውም አሜን ብሎ ነገሮችን የመቀበል ባህሪ የለውም። ስለሆነም ክሱ እና መካሰሱ ይቀጥላል። የሰላሙም ጉዳይ ይጓተታል፤ እየተጓተተም ነው። በዚህም በዚያም ብሎ ወያኔ ውሉን ንዶ እንደገና ውጊያ ሊከፍት ይችላል። የተካኑት በግፍ ነውና!
  እኔን የበለጠ የሚገርመኝ የወያኔ ወታደሮችና የኢትዮጵያ ወታደሮች ሲጋራ ተለዋወጡ፤ ምግብ አብረው ቆረሱ፤ ሙታናቸውን በጋራ ቀበሩ የሚሉት ወሬዎች ናቸው። ትላንት ታንክና መኪና የነዳባቸው የሰሜን እዝ ሰራዊት እንዴት ነው እነዚህን ድርቡሾች አምኖ የሚያቀርባቸው። የጠ/ሚሩ መንግስት ከሰላሙ ጉዳይ ባሻገር ተለዋጭ እቅድና ፕላን ለትግራይ ከሌለው ዳግመኛ በወያኔ ሊሸወድ እንደሚችል ይታየኛል። የምድሪቱን ታህታይና ላዕላይ መዋቅር የምትገነባው ዳግመኛ እንዳይፈርስ ዋስትና ሲኖር ብቻ ነው። ከናይሮቢም ሆነ አዲስ አበባ ላይ ሆኖ ይህን ለትግራይ ህዝብ አረግን ያን ጨመርን ከማለት የውጭ ጋዜጠኞች ገብተው ነገሩን እንዲታዘቡ መፍቀድ የበለጠ ፍሬ ይኖረዋል። የተራበው፤ የተጠማው፤ ሃብት ንብረቱ የወደመበት የአማራና የአፋር ህዝብም እንዳይታዘብ የብልጽግናው መንግስት እነርሱን እየዘለለ ለትግራይ ይህን አደረኩ ያን ሰራሁ ማለቱን ቢገታ መልካም ነው። ያለበለዚያ ሌላ ግጭት ቀስቃሽ ነገር ሊያመጣ ይችላል። ለነገሩ አሁንም እኮ በኦነግ ሸኔና በመሰል ሃይሎች ህዝብ እየተሰቃየ ነው። ይህ ነው እንግዲህ የሃበሻው ፓለቲካ አንድ ጋ ቋጠርኩ ስትል ሌላ ጋ ያፈተልካል የምለው።
  ወልቃይትና ራያን አማራ አይደላችሁም ትግሬ ሆኑ ማለት ተመልሳችሁ ወደ ባርነት ወደ ስደትና መከራ ግቡ እንደማለት ነው፡ ይህ የሚታሰብም አይደለም። ግን የፓለቲካ አንድ መሳሪያ ከፋፍሎ መግዛት ነው። ለዚህም ነው ወያኔ በኢትዮጵያ በክልል ከፋፍሎ የአፓርታይድ ስርዓት የመሰረተው። የዶ/ር አብይ መንግስትም ያው ከወያኔ ጆኒያ አፈትልኮ የወጣ በመሆኑ ይህን የከፋፍለህ ግዛው ስልት ተጠቅሞ ወልቃይትና ራያን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል። ያኔ ምን እንደሚፈጠር አሁን መገመት አይቻልም። ባጭሩ እኔ ወያኔ ትጥቅ ይፈታል፤ ለሰላም እጅን ሰጥቶ አርፎ ይቀመጣል ብዬ አላምንም። በዚህም በዚያም እያፈነገጡ በትግራይ መሬት ሰላም እንዳይኖር የባሩድ ሽታ እያሸተቱና ሰው እያሸበሩ ለመኖር የሚያስቡ ይኖራሉ ባይ ነኝ።
  ባጭሩ ህገመንግስቱና የሽግግሩ ቻርተር የሚባለው ጉዳይ የማደናገሪያና የተንኮል ሃሳብ ማጣፈጫ ቅመም እንጂ በይዘቱም ሆነ በሌላው መልኩ የሃገራችን ችግር ከሚያባብሱት አንድ ጉዳይ ይህ ህገመንግስት ተብዬው ነው። በተንኮል ተጠንስሶ በተንኮል ብዕር የተከተበ ፉርሽ ህገመንግስት ነው። ያው ዛሬም የወያኔን ክፋት ስንጽፍ ብግን የምትሉ ካላችሁ ብገኑ። ሥራቸውን አይቶ 48 ዓመት ያደረሱትን ጥፋት ለይቶ ላወቀ ግን ነገሩ ከሚያልፍ ወንዝ የተጨለፈ የፓለቲካ ጸበል ሳይሆን እውነትን የተላበሰ የወያኔ የገመና ታሪክ ነው። አንድ ግጥም ላካፍልና ይብቃኝ። የተጻፈው በ 2011 ነው የደራሲው ስም የለበትም። ግጥሙ እንሆ
  በወያኔ አገዛዝ፤ በወያኔ ቀንበር
  የካቴናው ስርስር የኮረንቲው ንዝር
  የመቀመቅ ፍዳው የጨለማው እስር
  የሰቆቃው ንረት የአውሬዎቹ ምንዝር
  እንዴት እንደ ሆነ እንዴት እንደነበር
  ፍትህ በሌለበት ለዳኛ ከመንገር
  ጠበቃ ከማቆም ዕማኝ ከመደርደር
  ይኸው የኛ ፎቶ ታሪኩን ይናገር።

 4. I Mognu

  ሳስበው ሳስበው የአማሮች ነገር ይገርመኛል። አልፎ ተርፎም ያሳዝነኛል።

  ለምን ይገርመኛል ፧ ለምን ያሳዝነኛል፧ ላስረዳ።

  እስኪ Tesfa. የጻፈውን ኣስተያየት ተመልከቱ፤ አማራው ከትህነግና ከኦሆዴድ ብልጽግና የሚያገኘው ነገር የለም ይለንና መፍትሄ ስንጠብቅ ስጋቱን አካፍሎን ውልቅ ይላል። ሰውየው አማራ መሰለኝ።

  አማሮች በሙሉ አማሮች የአማራን የመረረ ስቃይ አሳምረው ከተነተኑ በኋላ የመፍትሄ ነገር ሲጠየቁ የለንበትም ወደማለት ያልፋሉ። ምክንያቱም በቁርጥ አማራ ክኦሮሞ መገላገል የሚችለው ራሱን በነጻነት ሲያስተዳድር ብቻ ነው ማለት ሃገሪቱን መክዳት ይመስላቸዋል።

  አማራ የራሱ የመከላከያ ሃይል ኖሮት ኣማሮችን ክኦሮሞና ሌሎች መጠበቅ ካልቻለና የኢኮኖሚ ነጻነቱን ከኦሮሞ መቀማት ካልቻለ በሰላም መኖርም ሆነ ማደግ አይቻለውም። Tesfa ይህን ሃሰት የምትል ከሆን ሃስብህን አካፍለኝ።

  አንድ ወዳጄ ከቀናት በፊት ይህን ጽፎ ነበር። ” ይህ የአማራ ህዝብ የኮንፌደሬሽን ጥያቄ ወሳኝ መሰለኝ። በኦሮሞ አስተዳደር ስር የአማራ ህዝብ የተሟላ ሰላምና ደህንነት አንዲሁም የኢኮኖሚ እድገት ሊረጋገጥ አይችልም። በኮንፌደሬሽን በነጻነት መሪዎቹን መምረጥ፥ ሰላምና ደህንነቱን ማስጠበቅ በኢኮኖሚ ማደግ ይቻለዋል። እስከኣሁን እንደታየው ከሆነ መሪዎች ተብዬዎቹ ኦሮሞዎች ሲጠሩዋቸው (አቤት) ሲልዃቸው (ወዴት) ባይ ናቸው። ከኦሮሞ ቁጥጥር ውጭ የሆነ አመራር የአማራን ህዝብ ሊያስመነድገው ይችላል። ከኦሮሞ ቁጥጥር ውጭ የሆነ አመራር ባለው የብሔር ፌደራሊዝም ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ያለፉት ሰላሳ አምስት ዓመታት ያረጋገጡት ይህንኑ ነው። የብሔር ፌደራሊዝም ይቆይ ቢባል እንኴ የተሻለ የሚሰራው በፕሬዚዳንታዊ ስርዓት እንጂ አሁን ባለው ፓርላሜንታዊ ስርዓት አይደለም የሚልው ክርከር አሳማኝ ነው። ለማንኛውም የአማራ ህዝብ መጪ እድል የሃገሪቱን መጪ እድል ይወስናል። ለዘለቄታው ከትግራይ ፣ ከኤርትራ፣ ክአፋርና ብንቫንጉል ጋር በኮንፌደሬሽን ታሳስሮ ወደፊት የሚራመድበት ኦሮሞ ደቡብን ይዞ የሚያነክስበት ጎዳና ይታየኛል።”

  ወዳጄ ባለው በሙሉ ባልስማማም አማራ ከኦሮሞ ቁጥጥር ነጻ አስካልወጣ ድረስ ስቃዩ አይቆምም፣ እድገትም አይኖረውም ባይ ነኝ። በጀመረው ሂደት ኦሮሞም ራሱ ክጨቋኝነት ወጥቶ ነጻ ሊሆን አይችልም። እና ለሁላችንም ነጻነት የአማራው ነጻነት ቁልፍ ነው የሚባለው ለዚህ ነው። በዚህ መንገድ ሄዳችሁ ሁላችንንም ነጻ አድርጉን።

  አሁን መገረሜና ማዘኔ ገባህ?

 5. I mognu ጽሁፍህ እንደ ምስጢረ ስላሴ ረቀቀ ከአጻጻፍ ረቂቅነትና ቃላት አጠራረብ ጉዳህን ስንመረምረው ዲማ አለቃ ክንፉ ዘንድ ወንበር ተስጥቶህ ቅኔ ታስተምር እንደነበር እናውቀዋለን ከሚሉ ሰዎች ሲነገር ይደመጣል። አሁን አሁን ላይ ደግሞ እውቀት ሰርጾብህ የብሄር አወቃቀር ፕሬዚዳንታዊ ቢሆን ጥሩ ለውጥ ያመጣል ነው የምትለን። እንግዲህ ምን ይባላል አንተ ከዚህ ብልጽግና ከዚያ አረጋዊ በርሄና አብረሀ በላይ ፣ብርሀኑ ነጋ ከወምበሩ እዚች ምስኪን አገር ላይ አላግጡ የእውነት ብርሀን እስኪፈነጥቅ ድረስ።

 6. Areru

  ስለ እኔ ቅኔ አስተማሪነት ከመዘላበድ ይልቅ ምነው ጊዜህን አማራውን ከትህነግና ከኦሆዴድ/ አማራ ብልጽግና እንዴት እንገላግለው ለሚለው ጥያቄ መለስ ብታፈላልግ?

  እኔ አማራ አይደለሁም። ያም ሆኖ “የአማሮች ነገር ይገርመኛል፣ አልፎ ተርፎም ያሳዝነኛል” ማለቴ ለራሴ በማሰብ መሆኑን አልደብቅህም።

  ከላይ ያልኩትን ልድገመው።

  “አማራ ከኦሮሞ ቁጥጥር ነጻ አስካልወጣ ድረስ ስቃዩ አይቆምም፣ እድገትም አይኖረውም . . . ። በጀመረው ሂደት ኦሮሞም ራሱ ክጨቋኝነት ወጥቶ ነጻ ሊሆን አይችልም። እና ለሁላችንም ነጻነት የአማራው ነጻነት ቁልፍ ነው የሚባለው ለዚህ ነው። በዚህ መንገድ ሄዳችሁ ሁላችንንም ነጻ አድርጉን።”

  የምለውና ፍላጎቴ አሁን ገበህ?

  አረጋዊ በርሄ፣ አብረሀ በላይ ፣ብርሀኑ ነጋ በሚል ቁዘማ ግዜ ከምታባክን በአማራ ነጻ መውጣት ላይ አትኩር ። የተፋጠጥከው ክትህነግና ከኦሆዴድ/ አማራ ብልጽግና ገር መሆኑን እትርሳ። ባልሆነው ባልሆነው ነሁልለህ የኛንም ነጻ የመውጣት ትግል አትፈታተን።

  እሻፈረኝ ካልክ “ወጊድ ብለናል ፣ መንገድ ልቀቅ”

  “ቶሽሽሽ” ማለት ይሻል ይሆን?

 7. አረሩ (Areru)

  ስለ እኔ ቅኔ አስተማሪነት ከመዘላበድ ይልቅ ምነው ጊዜህን አማራውን ከትህነግና ከኦሆዴድ/ አማራ ብልጽግና እንዴት እንገላግለው ለሚለው ጥያቄ መለስ ብታፈላልግ?

  አረሩ (Areru) ነኝ አልክ? እስከነተረቱ “መልክ ጥፉ ፣ በስም ይደግፉ” ይባል የለ? ወሸከሬ።

  እኔ አማራ አይደለሁም። ያም ሆኖ “የአማሮች ነገር ይገርመኛል፣ አልፎ ተርፎም ያሳዝነኛል” ማለቴ ለራሴ በማሰብ መሆኑን አልደብቅህም።

  ከላይ ያልኩትን ልድገመው።

  “አማራ ከኦሮሞ ቁጥጥር ነጻ አስካልወጣ ድረስ ስቃዩ አይቆምም፣ እድገትም አይኖረውም . . . ። በጀመረው ሂደት ኦሮሞም ራሱ ክጨቋኝነት ወጥቶ ነጻ ሊሆን አይችልም። እና ለሁላችንም ነጻነት የአማራው ነጻነት ቁልፍ ነው የሚባለው ለዚህ ነው። በዚህ መንገድ ሄዳችሁ ሁላችንንም ነጻ አድርጉን።”

  የምለውና ፍላጎቴ አሁን ገበህ?

  አረጋዊ በርሄ፣ አብረሀ በላይ ፣ብርሀኑ ነጋ በሚል ቁዘማ ግዜ ከምታባክን በአማራ ነጻ መውጣት ላይ አትኩር ። የተፋጠጥከው ክትህነግና ከኦሆዴድ/ አማራ ብልጽግና ገር መሆኑን እትርሳ። ባልሆነው ባልሆነው ነሁልለህ የኛንም ነጻ የመውጣት ትግል አትፈታተን።

  እሻፈረኝ ካልክ “ወጊድ ብለናል ፣ መንገድ ልቀቅ”

  “ቶሽሽሽ. . . ” ማለት ይሻል ይሆን?

 8. Gubda Negn

  “ደግነቱ ግን የፕሪቶሪያው ስምምነት የተፈረመው የሕወሃት አሸባሪነት ፍረጃ ከመነሳቱ በፊት በመሆኑ ሰራ ፈጻሚው አካል የተወካዩች ምክር ቤት ፍረጃውን ሳያነሳለት በርሱ ፍላጎት ያደረገው ስልሆነ በህግ ከተሰጠው ስልጣን በላይ ሄዷል። ስለሆነም ተፈጻሚነቱ ህጋዊነት ይጎድለዋል።”

  ከፍ ብሎ ያስፈርኩትን በሚመለከት ማብራሪያ ለጠየቃችሁኝ መልሴ ከታች መልሴ ከታች ሰፍሯል።

  የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ – አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፸፮፨፪ሺ፲፪

  ሙሉው አዋጅ ይኀው ፡ https://www.lawethiopia.com/images/latest%20proclamations/1176%20A%20PROCLAMATION%20TO%20PROVIDE%20FOR%20THE%20PREVENTION%20AND%20SUPPRESSION%20OF%20TERRORISM%20CRIMES.pdf

  ለምንነጋገርበት ጉዳይ አግባብነት ያላችው አንቀጾች ፡

  አንቀጽ ፲፰ – ድርጅትን በአሸባሪነት የመሰየም ሥልጣን

  ፩- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብር ወንጀል ውስጥ የተሳተፈ ድርጅትን በአሸባሪነት ለመሰየም ይችላል፡፡

  ፳ – የውሳኔ ሀሳብ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት

  ፪ – የሚኒስትሮች ምክር ቤት በፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የቀረበውን በአሸባሪነት የመሰየም የውሳኔ ሀሳብ ሲያጸድቀው ለህዝብ ተወካዮችምክር ቤት ያቀርባል፡፡

  ፳፪ – በአሸባሪነት የመሰየም ውጤት

  ፩ – በዚህ አዋጅ መሰረት በአሸባሪነት የተሰየመ ድርጅት ስያሜው ተፈጻሚ ከሚሆንበት ጊዜ ጀምሮ የሚያደርጋቸው ግንኙነቶች እና እንቅስቃሴዎች ህጋዊ ውጤት አይኖራቸውም፡፡

  ፪ – በአሸባሪነት የተሰየመው ድርጅት ህጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት የሆነ እንደሆነ እና በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፯ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሠረት በፍርድ ቤት እንዲፈርስ ያልተደረገ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ድርጅቱ እንዲፈርስ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማመልከት አለበት፡፡

  ፫ – በአሸባሪነት የተሰየመ ድርጅት ንብረት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመንግስት የሚወረስ ይሆናል፡፡ ንብረቱ እንዲወረስ ትዕዛዝ የመስጠት ሂደት ወቅት የሚኖረው ክርክር ድርጅቱ ከመሰየሙ በፊት በቅን ልቦና ከድርጅቱ ጋር ግንኙነት ያደረጉ የሶስተኛ ወገኖችን ጥቅም የተመለከተ ብቻ ይሆናል፡፡

  ፬ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፫) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ከሽብር ወንጀል ጋር የተገናኘ ንብረትን ወይም የአሸባሪ ድርጅትን ንብረት ወይም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፱ ንዑስ አንቀጽ (፪) መሰረት ንብረቱ የሚወረስ ድርጅትን በሚመለከት የተሻሻለው የፀረሙስና ልዩ የሥነ ሥርአትና የማስረጃ ህግን ጨምሮ ሌሎች ንብረትን ስለመያዝ፣ ስለማገድ ወይም መውረስን የሚመለከቱ ህጎችን መሰረት የሚመራ ይሆናል፡፡

  ፳፬ – ከስያሜ ስለመሰረዝ

  ፩ – የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአሸባሪነት ተሰይሞ ያለ ድርጅት ስያሜው እንዲሰረዝለት የውሳኔ ሀሳብ ለሚንስትሮች ምክር ቤት ሊያቀርብ ይችላል፤ ምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳቡን ሲቀበለው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል፡፡

  ፪ – የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በመቀበል፤ ከአሸባሪነት ስያሜ ድርጅትን ለመሰረዝ ይችላል፡፡

  ፫ – በዚህ አንቀጽ መሰረት አሸባሪ ድርጅትን ከስያሜ ለመሰረዝ የሚቻለው ድርጅቱ የሽብር ወንጀል መፈጸሙን ያቆመ እና በዚህ ዓይነት ድርጊት ውስጥ ሊሳተፍ የማይችል ስለመሆኑ የታወቀ እንደሆነ ነው፡፡

  ፳፮ – ከስያሜ መሰረዝ ስለሚኖረው ውጤት

  ፩ – የድርጅት የአሸባሪነት ስያሜ መሰረዝ፤

  ከአሸባሪነት መሰረዙ ተፈጻሚ ከሚሆንበት ጊዜ በፊት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፪ መሰረት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ምንም ዓይነት ውጤት አይኖረውም፡፡ ስለሆነም የተወረሰ ንብረትን እንዲመለስ መጠየቅን ጨምሮ ያደረጋቸው ግንኙነቶች ህጋዊ ሆነው እንዲቆጠሩ ለመጠየቅ አይችልም፡፡

  ፳፰- ውሳኔን ይፋ ስለማድረግ

  ፩ – የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድርጅትን በአሸባሪነት ሲሰይም ወይም ከአሸባሪነት ስያሜ ሲሰርዝ፤ ውሳኔውን አገር አቀፍ ተደራሽነት ባለው ጋዜጣ እና ሌላ አግባብነት ባለው የብዙሐን መገናኛ መንገድ ለህዝብ ይፋ ማድረግ አለበት፡፡

  ፪- በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሰረት ምክር ቤቱ ይፋ የሚያደርገው ውሳኔ እንዳስፈላጊነቱ ድርጅቱ
  ስለተሰየመበት ምክንያት፣ ስያሜው ተፈጻሚ ስለሚሆንበት ሁኔታ እና መሰል ጉዳዮችን መያዝ አለበት፡፡

  ፳፱ – አሸባሪ ድርጅትን መምራት

  ፩- ማንኛውም ሰው በአሸባሪነት ተሰይሞ ያለን ድርጅት በአጠቃላይ ወይም የድርጅቱን አንድ ክፍል በኃላፊነት የመራ እንደሆነ ድርጅቱን በመምራቱ ብቻ ከሰባት ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡

  ፵፩- የአስፈጻሚ አካላት ተጠያቂነት

  ፩- በዚህ አዋጅ የተመለከተ ወንጀልን የመከላከል፣ የመመርመር ወይም የክርክር ሂደትን የማስፈጸም ኃላፊነት የተሰጠው ማንኛውም ሰው የተሰጠውን ኃላፊነት ህግን በመተላለፍ የፈጸመ እንደሆነ እንደመተላለፉ ዓይነት እና እንዳስከተለው ጉዳት ዓይነት በዲስፕሊን፣ በፍትሐብሔር እና በወንጀል
  ተጠያቂ ይሆናል፡፡

  አንቀጾቹ ግልጽ ናቸው። አስፈላጊ ክሆነ ወደፊት አንቀጽ በ አንቀጽ እመለስበታልሁ።

  እስከዚያው በዚህ ተዝናኑ።

 9. የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፸፮፨፪ሺ፲፪ ፳፪ – በአሸባሪነት የመሰየም ውጤት የሚገልጸው አንቀጽ ፳፪፩ – ፩ – በአሸባሪነት የተሰየመ ድርጅት ስያሜው ተፈጻሚ ከሚሆንበት ጊዜ ጀምሮ የሚያደርጋቸው ግንኙነቶች እና እንቅስቃሴዎች ህጋዊ ውጤት አይኖራቸውም ይላል፡፡
  ግንኙነቶች እና እንቅስቃሴዎች የፕሪቶሪያውንና የናይሮቢውን ስምምነት ይጨምራል። አንደኛው ውገን የኢትዩጵያ መንግስት ስለሆነ ስምምነቱ ህጋዊነት ያገኛል ማለት አይደለም። እንዲያውም መንግስት የአሸባሪነት ስያሜን በተወካዩች ምክር ቤት ከማስነሳቱ በፊት ያደረገውም ስምምነት ቢሆን ሕጋዊነት የለውም። አና ፕሪቶሪያም ሆነ የናይሮቢ የተደረጉት ስምምነት ተብዬዎች ከህግ አንጻር ዎጋ ያላቸው ማናቸውንም ተስማሚ ወገኖች የሚያስገዹ ሰነዶች አይደሉም። የፖለቲካ ሰነዶች ሊባሉ ግን ይችላሉ። ስልሆነም ብልጽግናም ሆነ ትሕነግ ስምምነት ተፈራርመናል እያሉ የሚወሻክቱት በባዶ ሜዳ ነው።

  ከ አዋጁ እንደሚታየው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሸባሪነት ስያሜን ለመሰረዝ ይችላል። የመሰረዝ ጥያቄውን የሚያቀርበው የሚኒስትሮች ምክር ነው። ብልጽግናም ማድረግ ያለበት ህወሃት ከ አሸባሪነት እንዲሰረዝ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ ስረዛው ሲወሰን ወደስምምነት ንግ ግር መግባት ነው። ይህም ሆኖ አዋጁ ከአሸባሪነት መሰረዙ ተፈጻሚ ከሚሆንበት ጊዜ በፊት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ምንም ዓይነት ውጤት አይኖረውም፡፡ ይህ ማለት ትሕነግ የአሸባሪነት ስያሜ ቢነሳለትም በወንጀልና በሌሎች ጥፋቶች ከመጠየቅ አይችልም ማለት ነው።

  የሚያሳ ዝነው ነገር የፍት ህ ሚኒስትሩ ከስምምነቱ በፊት አንድም ቃል ስለዚህ የህግ ጥያቄ አለመተንፈሱ ነው። መንግስት የዚህ አይነት ስምምነት መፈራረም የሚችለው በህገመንግስቱ መሰረት የዜስቸኴይ ጊዜ ደንብ አውጥቶ ቢሆን ነበር።

 10. I_Mognu – የውስልትና ፓለቲካ ይሰለቻል። የፈጠጠውን እውነት እያዪ ሰው ላይ እንደ ሙጫ መለጠፍ አላዋቂነት ነው። አንተ ዓለሙ ሁሉ ይገማል ስትል የግድ አብራችሁ እኔን ምሰሉ ማለት ያሰለቻል። ሲጀመር ብልጽግናና ወያኔ አንድ ኮሮጆ ውስጥ የነበሩ በዚህም በዚያም የታሰረውን ሊፈቱ ሲታገሉ በብልጽግና ስም አፈትልኮ የወጣው የኦሮሞዎች ስብስብ ለአማራ ህዝብ መልካም ያደርጋል ብዪ አላስብም። የምናየውና የምንሰማው ነገርም ክፋት ተንኮል መግደል ማሳደድ ነው። የጠባብ ብሄርተኞች ችግር ይህ ነው። ለእኔ ብቻ። በሽታቸውን የሚያድን ምድራዊ ሃይል የለም። ስለሆነም በእኔ ጽሁፍ ዙሪያ የምትሰነዝረው እይታ የተንሻፈፈ መሆኑን አንባቢ ይረዳል። ዝም በል። ዝምታ ወርቅ ነው። በቃኝ!

 11. I_Mognu መልካም ብለሃል መቼም ያገሬ ሰው አዋቂ ነው አንድ አባባል አለው፡፡ ጦጣ ፊቷን በመከለሏ ብቻ መላ አከላቷን የከለለች ይመስላታል የሚል ብሂል አለው፡፡ እንዲህ ያለ መድረክ ባይኖር የመሳደብ ሱስህን በምን ትወጣዉ ነበር?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share