የፕሪቶሪያ ስምምነት:- ውጫሊያዊ ወይስ አልጄርሳዊ? (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

ስምምነቱ ከሀገራዊ ዘላቂ ሰላም አኳያ  

በዚህ ጽሑፍ የፕሬቶሪያውን ውል አጠቃላይ መንፈስ፣ ዓላማና መዘዝ ለማሳያ አንድ አንቀጽ ላይ ብቻ እናተኩራለን።

የሥልጣን ውዝግቡ ማእከል የተደረገውና ጦርነቱ ሁለንተናዊ ጉዳት ያደረሰበት፣ የሰላም ስምምነት ተብዬውም ሌላ ዙር አደጋ የጋረጠበት የአማራ ሕዝብ በድርድሩ ሊወከል ይገባል ብለው የሚከራከሩ አካላት ትክክል መሆናቸውን ከሚያሳዩት የፕሬቶሪያ ውል አናቅጽ ውስጥ አንቀጽ 10 ቁጥር 4 ዋነኛው ነው።

ይህ አንቀጽ በወያኔ በጉልበት ተወስደው በጭቆና ሥር የኖሩትን የአማራ (የጎንደርና የወሎ) መሬቶች ተመልሰው ለወያኔ የሚተላለፉበትን አግባብ የሚያመቻች ነው። ታድያ ተማስሎሹ ነጻነትን አሳልፎ እንደሰጠውና ለጦርነት በር እንደከፈተው የውጫሌ ውል (አንቀጽ 17) ነው ወይስ ጦርነትን ድል አድርገው አልጄርስ ሄደው ድሉን በሽንፈት እንደለወጡበት የአልጄልርስ ስምምነት? የሚል ጥያቄ ይጭርብናል።

አወዛጋቢ አካባቢዎችን በተመለከተ የተጻፈው የፕሪቶሪያ ውል አንቀጽ እንዲህ ይለናል።

Article 10

 1. The Parties commit to resolving issues of contested areas in accordance with the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia* ወያኔ ሆን ብሎ የፈጠረውን ችግር ለመፍታት ችግሩ እንዳይፈታ አድርጎ በቋጠረበት በራሱ በወያኔው ሕግ ይዳኝ ብሎ የመፍረድን ነገር፣ ተንኮል፣ ክፋት ወይስ ንቀት እንበለው? በቀላል  ቋንቋ  ዘራፊ ተዘራፊ በተዘረፈው  ንብረት ሲጣሉ ውዝግቡ በዘራፊው  ሕግ ይዳኛል እንደማለት ነው።

 

Kenyan President Uhuru Kenyatta (L), Redwan Hussein (2nd L), Representative of the Ethiopian government, African Union Horn of Africa envoy and former Nigerian president Olusegun Obasanjo (2nd R) and and Getachew Reda (R), Representative of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), look on after the signing of a peace agreement during a press conference regarding the African Union-led negotiations to resolve conflict in Ethiopia at the Department of International Relations and Cooperation (DIRCO) offices in Pretoria on November 2, 2022. (Photo by PHILL MAGAKOE / AFP)

አፍሪካ ጫፍ ሄደው አጽራር በጠያራ

ወልቃይት ጠገዴ ራያና ሁመራ፣

ነጻ እንደማይቆዩ ነገሩት ላማራ

የተዋለበትን ውሉን ሳያጣራ 

ሰላም መጣ ብሎ አያብዛ ዳንኪራ

ሰከን ብሎ ያስብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ

ውጫሌ ነው ውሉ ደግሞ አልጄርሳዊ*

 

(*የውጫሌ ውል ከጦርነት በፊት የተዋዋሉት የባርነት ውል ሲሆን፣ የአልጄርስ ውል ደግሞ ከድል በኋላ የተዋዋሉት የሽንፈት ውል ነው) ውሉ በአማራ ሕዝብ ላይ ባርነትን፣ ጭቆናን፣ ከርስት መፈናቀልን የሚያስከትል ነው ስንል ለትግሬ ሕዝብ ይጠቅማል ማለት አይደለም። ከአማራ ርስት ቀምታችሁ ወደ ትግራይ ከልሉልን፣ እኛን እየወሰዳችሁ፣ እያስታጠቃችሁ በአማራው መሬት ላይ አስፍሩን ብሎ ሕወሃትን ጠይቆ አይደለምና የተስፋፊነቱ ክሥተት የተፈጸመው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለብአዴን መኖር የሚከፈለዉ መስዋዕትነት ስንት ነዉ ?

እርግጥ የጎሳ አፓርታይዱ ሥርዐት ፈርሶ አንቀጽ 39ኝም ተወግዶ ሌላ የፖለቲካ አከላለል ቢተገበር፤ ወልቃይትም ሆነ ራያ ወደ ሱዳን እና ኬንያ አይካለሉ እንጂ በሌላ በየትኛውም ኢትዮጵያዊ አስተዳደር ሥር ቢደረጉ ብርቱ ተቃውሞ አይነሳም። የጎሳ አፓርታይዱ ሥርዐት ግን አንድም ክልሎቹ ተገንጥለው ሀገር ለመሆን የሚንደረደሩ በመሆናቸው ከትግራይ ጋር መገንጠል የማይፈልጉትን እነዚህን አካባቢዎች በግድ ትግራይ ውስጥ ማካለሉ አግባብ ስለማይሆን፤ ሁለተኛም በማንነት ፖለቲካ ላይ በተመሠረተው በዚህ ሥርዐት ማንነታችንን ይበልጥ የሚገልጸው የጎንደርና የወሎ አማራነት ነው እያሉ በትግሬ ማንነት በግድ ተጨፍለቁና ለተጨማሪ የባርነት አገዛዝ ተንበርከኩ ማለቱ ግፍ ስለሚሆን ፍትሐዊ ሰው ሁሉ በጽኑ ሊቃወመው የግድ ይላል።

ለሥልጣን ሲባልና ማን ጌታ ማን ሎሌ እንደሆነ ለማሳየት ይህን ያክል ደም አፋሳሽ ጦርነት ከተካሄደ ለፍትሕና   ለነፃነት   ሲባል ጦርነት አይካሄድም   ብ ሎ ማሰብ የዋህነት  ነው።  የድርድሩ ውጤት ቅጽበታዊ ሰላም የሚያመጣለት ሰውና አካባቢ፣ የተወሰነ እፎይታ የሚሰጠው አካል አይኖርም ማለት አይደለም። በዋናነት ግን ዛሬን ለመሻገር ብቻ እና ድርድሩን ካባሸሩና ከተሳተፉ አካላት ጥቅም አኳያ ብቻ የተደረገ የሰላምን መሠረት የሚያናጋ “የቀጠሮና የቋጠሮ ውል” ነው።

ስለዚህ እንደ ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ወይም እንደ ውጫሌ ውል ብዙ ደሳስ በሚሉ ቃላትና አናቅጽ የታጀበው   የሰላም ስምምነት ተብዬው የፕሪቶሪያ ሰነድ፣  የድሉን  የነጻነት  እድል ያመከነ፣   ለሌላ ግጭትና  ጦርነት መሠረት የጣለ አልጄርሳዊ ሰነድ ነው።  በትግራይና በአማራ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በቀጠናው ሌላ ዙር ቀውስ የሚጠራ እንጂ እንደተደሰኮረለት ለዘላቂ ሰላም መሠረት የሚጥል አይደለም።   ስምምነቱን  በተመለከተ  መልካም አናቅጹን እየጠቀሱ  ጉንጭ  አልፋ ክርክር   ማንሳቱ ቁም  ነገር የለውም።  ከላይ እንደተባለው  የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትም የውጫሌ ውልም ቁልፍ የባርነት እና የሀገር ክህደት አናቅጾቻቸውን እጅግ ብዙ በሆኑ በሚያማምሩና በሚያማልሉ አናቅጽ ነው የመሸጓቸው፣ የሸፋፈኗቸው፣ የከበቧቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የደብረ ብርሃኑ ስብሰባ ብልጽግና በሰሜን ሸዋ ዞን ጨርሶ እንዳበቃለትና እንደተንኮታኮተ የሚያስተምር ነበር

ምናልባትም መጀመሪያስ ከአደራዳሪዎቹ ኢትዮጵያ ጠል (ራስ ወዳድ) ባእዳን ስፖንሰሮች እና እነሱ ካሳደጓቸው አሸባሪና ባንዳ ተደራዳሪዎች ዱለታ  እውነት የዘላቂ ሰላም ውል ሊገኝ  ይችላልን? ብለን መጠየቅ ይኖርብናል። ምእራባውያን  በሰላም ድርድሮች፣ በሕገመንግሥት ረቂቆችና በመሳሰሉት ውሎች ውስጥ ቆይተው የሚፈነዱ ፈንጂዎችን ቀብረው  ሀገሮችን በእርስ በእርስ ጦርነት የመዝፈቅ የበሰለ ልምድ ያላቸው ናቸው። በድርድርና በማረጋጋት ስም የገቡባቸው ሀገሮች ወይ ይፈርሳሉ ወይም ለማያባራ እርስ በእርስ ጦርነትና ውዝግብ ይዳረጋሉ። ይህም በአብዛኛው የሚተገበረው በስምምነት ውል ተብዬዎቹ ሰነዶች ውስጥ በተንኮል ጥበብ በሚቀመመው ቋንቋ ነው።  በአደራዳሪነት ስም ገብተው ያፈረሱት ሀገር ሁለት ደርዘን ይሞላል።

እዚህ ላይ ሳይጠቀስ የማይታለፈው የምእራባውያን የተንኮል ጥበብ ድርድሩን ያቀናበሩት እነሱ ሆነው እያሉ ፎቶው ላይ አንድም ቦታ አለመታየተቻው ነው። ሁሉም የድርድር ፎቶ አፍሪካውያንን ነው የሚያሳየው። አንድ የሶሻል ሚዲያ ኮመንት ይህን የድርድሩን ፎቶ እንቆቅልሽ “ዝንጀሮዎቹ ብቻ ፎቶ የተነሱት ቺምፓንዚዎቹ የት ሄደው ነው?” ብሎ በትክክል ገልጾታል። እኔ በመጨመር “ገመሩ ዝንጀሮስ የት ነበር?” እላለሁ። የማያጠያይቀው ጉዳይ ግን ራሱ አቢይ አህመድም በቃሉ እንደመሰከረው የድርድሩ  ውል  ኦህዴድ  ላይ የማይፈልገውን  ነገር የጫነበት  ሳይሆን  በሚፈልገው  ልክ  የተሰፋ  ከረጢት  ነው።  ለዚህም ኦህዴድ/አቢይ አህመድ  የወልቃይት፣  ጠለምት፣  ሁመራና  ራያን  መሬት  ለወያኔ  ለማሰረከብ   አመቱን  ሙሉ  ሲፈጥረው  የከረመውን  መደላድልና  ያካሄደውን መንገድ ጠረጋ ልብ ይሏል።

 1. አረቂያሙን የወያኔ ቡችላ አገኘሁ ተሻገርን  ይህ ውሳኔ ሄዶ ሄዶ የሚወሰንበት የፌደሬሽን ምክር ቤት ወንበር  ላይ መሰየሙ
 2. ይህንንውሳኔ በብርቱ ይቃወማሉ ተብለው የሚታሰቡትን የአማራ ፋኖዎች ሲያሳድድ፣  ሲያስርና ሲገድል መክረሙ  (ዛሬም እያሳደደ መሆኑ)
 3. በዚህምአይቀሬው ድርድር ሲመጣ አማራን የሚወክል ሐቀኛ ተቋም እንዳይኖር አበክሮ መሥራቱ
 4. ነጻለወጡት አካባቢዎች የማንነት ጥያቄ ሕጋዊ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን መቆየቱ
 5. ከሕወሃትነጻ የወጡትን የአማራ አካባቢዎች የባጀትና የመንግሥት አገልግሎት መንፈጉ
 6. ወያኔ ጠለምትና ራያን ይዛ እንድትቆይ በማድረግ በነዚህ አካባቢ ያሉ አማራዎችን እንድታወድም  ማመቻቸቱ
 7. ሕገመንግሥቱ የሚሻሻልበትን እድል ዘግቶ መቆየቱ
ተጨማሪ ያንብቡ:  አገዛዙ ለሰላማዊ ሰልፉ ዕውቅና የሰጠው ፈጽሞ አማራጭ ስላልነበረው ነው - በእኔ አመለካከት!

እናም ወገኖች እፎይታን አብዝተን ስለናፈቅነው ብቻ አይናችንን ጨፍነን ልንሞኝ አይገባም። ደርግ ሲወድቅ እፎይታን ከመናፈቃችን ብዛት የባርነት እና የሀገር ፍርሻ ወጥመዱ ሲዘረጋ ሁሉ ልብ አላልነውም። አቢይም ሥልጣን ላይ ሲወጣ በእፎይታ ፍለጋ ማእበል ውስጥ እጅግ ብዙ ወጥመዶች ሲዘረጉብን ሳናስተውል ቀርተናል። “ዘላቂ ሰላም ምንትሴ” በሚል አስመሳይ ሰነድ የዘላቂ ሰላም መሠረት በክህደት ሲናድም እንዲሁ በእፎይታ ፍላጎት ብቻ እየናወዝን ሳንመረምር እንዳለ መቀበል አይገባንም።  ጦርነት  መቆሙ  ደስ ይላል።  ለሌላ ጦርነት  መሠረት የሚጥል፣ የትናንቱን የሀገር ፍርሻ መንገድ የሚያስቀጥል ከሆነ ግን ርቀት አያስጉዝም።

እውነት ግን ኢትዮጵያችን ከነዚህ አሸባሪ ስታሊኒስት ድርጅቶች (ኦህዴድ፣ ኦነግ፣ ሕወሃት፣ ብአዴን ወዘተ) እና ከሕገ አራዊቱ የእልቂትና የፍርሻ ሰነዳቸው ነጻ የምትሆንበት ዘመን ቅርብ ይሆን?

______

*ሞገስና ኤርምያስ ኢትዮ 360 ላይ በዚህ ዙሪያ ባደረጉት ሰፊና አስተማሪ ውይይት ይህን አንቀጽ 10.4 በተመለከተ ግን የተሳሳተ አተረጓጎም (ከቋንቋው አቀማመጥ ውጭ) ሲያንጸባርቁ ነበር። ይኸውም resolving issues of contested areas የሚለው “ውዝግብ የሚነሳባቸውን ጉዳዮች ማለት ነው፣ መሬትን በቀጥታ አይመለከትም ወይም አወዛጋቢ ጉዳዮችን ሁሉ መሬትንም ጨምሮ ማለቱ ነው” ብለዋል። እንደዚያ እነሱ እንዳሉት ቢሆን የቃላቱ አቀማመጥ የሚሆነው እንደሚከተለው ነበር

The parties commit to resolving contested issues in accordance with….. ወይም= The parties commit to resolving contested matters in accordance with…..

በውጫሊያዊው የፕሬቶሪያ ውል የተቀመጠው ግን በቀጥታ የመሬት ውዝግብን የሚመለከት ነው። ይሁን እንጂ ትርጉሙ አሻሚ ከሆነም እንደሚመቸው አጣምሞ የመተርጎም መብት የሚኖረው ሥልጣን ላይ ያለው ነው። ሥልጣን ላይ ያለው ደግሞ ፍላጎቱን በግልጽ ቋንቋ ሲያስቀምጥ እና እንዳልነው ለትግበራውም መንገድ ሲጠርግ የከረመ ነው። ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያን በተመለከተ።

እዚህ ላይ የቦርከና ኤዲቶሪያል የፕሬቶሪያን ስምምነት “postponing the war” ብሎ የገለጸበትን ቋንቋ ዘላቂ መፍትሔ ብሎ እስካቀረበው የመደምደሚያ ጥቆማ ጭምር ወድጄለታለሁ።

 

 

 

 

6 Comments

 1. ወገኖቼ ጊዜ አናጥፋ። ሃበሻ ሰው ሲስቅ የሚያለቅስ፤ ሰው ሲያለቅስ የሚስቅ ነው። አሁን እንሆ የወያኔውና የብልጽግናው የስምምነት ጉዳይ ገና ከመቀመጫው ሳይነሳ ሸኔና ኦነግ በጥምር ጥቃት ከፍተው ሸኔ ነቀምትን እያተራመሰ ሲሆን ኦነግ ደግሞ አሶሳ ላይ ይገኛል። ይህ የሚያሳየው የሃበሻውን የፓለቲካ ከንቱነት ነው። ሸኔ ነቀምት እስኪገባ እንዴት ባለ መልኩ ነው የጸጥታ ሃይሉ ከመግባታቸው በፊት መረጃ የሌለው? ወይስ የከተማው ኗሪ ሁሉ ታጣቂ ሸኔና ኦነግ ሆኗል። ለዚህ ነው የኢትዮጵያ ፓለቲካ አንድ ጋ ሲያስሩት ሌላ ጋ የሚፈታው። ዛሬ በኢትዮጵያ የስልጣን መሰላል ላይ እንደ ኦሮሞዎች የሚፈነጭ የለም። ልክ ወያኔ እንዳደረገው እነርሱ ደግሞ በወረፋቸው ሁሉን በሚባል መልኩ ስልጣኑን ይዘውታል። የሚያሳዝነው ግን ያም ሆኖ አለመስከናቸው ነው። ለምን ቢባል የኦሮሞ አክራሪ ፓለቲከኞች ፍልሚያ ከኢትዪጵያ ጋር በመሆኑ ነው። ሌላው ደግሞ ኢትዮጵያ እያለ በቀጣፊዎች ይገደላል፤ ይሳደዳል፤ ይራባል። አይ ሃገር!
  በወያኔና በብልጽግና በፕሪቶሪያ ተፈረመ የተባለው ስምምነትም ለጊዜ መግዣ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ እንጂ ወያኔና ክፋት ፍቺ ቢያደርጉ ወያኔ ከባህር እንደ ወጣ አሳ ትንፋሹ ይወጣል። ተንኮልና ወያኔ ተለያይተው መኖር አይችሉም። ወያኔዎች ከሰው ልጅ ባህሪ የወጡ እጅግ አረመኔና ጨካኞች ናቸውና። ስለዚህ በሰበባ ሰበቡ ስምምነቱን በማዘግየትና መሳሪያቸውን እንዳለፈው በመቅበር ሲልላቸው ከተቀበረበት እያወጡ ሂድ አማራና አፋርን ግደሉ ማለታቸው አይቀሬ ነው። የዚህ የአሁኑ ሸኔና ኦነግ የጥምረት ጥቃትም ወያኔን ለማዳን ተብሎ የተደረገ ድርጊት ነው። ፍትጊያው ግድያውና ማፈናቀሉ ይቀጥላል። የሚያስፈራው ኦሮሞዎች ከወያኔም የከፉ ሊሆኑ ይችላሉና። መለኪያ የለሽ ግፍ አፍሳሾች! ሽግግራችን ከክፋት ወደ ክፋት አይደል እንዴ የሚሸጋገረው? በሰሜን መልሶ ማቋቋም፤ የፈረሰውን መጠገን ወዘተ የሚባለው ሁሉ መልሶ አፍራሽ ሳይፈርስ ዝም ብሎ በደንበር ገተር የሚደረግ ተመልሶ ተዘራፊና ፈራሽ ጉዳይ ነው የሚሆነው። መልሶ ማቋቋም የሚሻውም የሰሜን ህዝብ ብቻ አይደለም። ብዙዎች ሜዳ ላይ በወያኔና በኦሮሞ አጥቂዎች ወድቀዋልና!
  የውጫሌው ስምምነት በሸፍጥ የተደረገ ሲሆን የአልጀርሱ ደግሞ ቆይቶ ባድሜ ለእኛ ሆኗል በማለት የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስዪም መስፍን ሰውን በውሸት ያስጨፈረበት የፓለቲካ ስሌት ነው። የደ/አፍሪቃው የወያኔና የብልጽግና ስምምነትም በእኔ እምነት ሥር ሰዶ ህዝባችን በሰላምና በጤና አብሮና ተባብሮ ይኖራል ብዬ አላምንም። ይህን ጉዳይ ከጀርባ ሆነው ወያኔና ሌሎች ተቃዋሚ ሃይሎችን የሚሾፍሩት ሁሉ ያውቁታል። ወያኔ በጦር ሜዳ ላይ ስለተወቀጠና እነርሱም የራሳቸውን ሰራዊት ልከው ለመታደግ ባለመቻላቸው የመጣ የሰላም ድርድር እንጂ ወያኔ አምኖበት አይደለም። በሰሜን፤ በደቡብ፤ በምስራቅና ምዕራብ ፍትጊያው ይቀጥላል። ታሪክ ራሱን እየለወጠና እየደገመ፤ የቆመውን እየቀበረ፤ ቆሜአለሁ እኔ ብቻ የሚለውን በቁሙ እንቅልፋም እያደረገ ልክ እንደ በፊቱ ታሪካችን በዚህ በዚያም ጠብ የለሽ በዳቦ አይነት ፍልሚያዎችን ስንገጥምና ስናጋጥም ስንገዳደል እንኖራለን። ሌላው ሁሉ አጉል ተስፈኛ መሆን ነው። አጉል ተስፈኝነትም ብልሃት አልባ የቀን ቅዥት ይሆናል። በቃኝ!

 2. ልጅ ተስፋ

  አስተያየትህ በአገራችን ለዘመናት የሆነውንና አሁንም እየሆነ ያለውን ግዙፍና መሪር እውነታ የሚገልፅ በመሆኑ ሚዛናዊ ህሊና ያለው ሰው ሁሉ ሊረዳው እንደሚችል ለመገመት አያስቸግርም።
  በሌላ በኩል ግን፦
   ምንም እንኳ ለሆነውና እየሆነ ላለው ሁለንተናዊ ቀውስ የህወሃት ፖለቲከኞች የእራሳቸው ትልቅ ድርሻ ያላቸው መሆኑ ግልፅ ቢሆንም እነርሱን ብቻ የመክሰሱና የማውገዙ የፖለቲካ አካሄድ የትም አያደርስም።

   ኦነግና ሸኔ አንድና አንድ የፖለቲካ ፍጡሮች ሆነው ሳለ ሸኔና ኦነግ በሚል የተለያዩና የተለያየ ዓላማ ያላቸው በሚያስመስል አገላለፅ መግለፅ አሳሳች ስለሆነ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ይመስለኛል ።

   ኦህዴድ በሚቆጣጠረው (በሚዘውረው) የቤተ መንግሥቱ ፖለቲካ አማካሪነት፣ አምባሳደርነት፣ ሚኒስተርነት፣ በፓርላማ ተብየው አባልነት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ገዥነትና ምክር ቤት ተብየ አባልነት ፣ በላቀ የወታደራዊ ማእረግ (ፊልድ ማርሻልነት) ፣ በገንዘብ ተቋማት ተቆጣጣሪነት ፣ በጥላ ወጌ (የስለላ መረብ) ጠርናፊነት ፣ ወዘተ ተሰማርቶ ከተቻለ የኦሮሙማ ፖለቲካ የበላይነት የሚቆጣጠራት ኢትዮጵያን ለመግዝትና ለመዝረፍ ፣ ይህ ካልሆነ ግን “ታላቋን አገር ኦሮሚያን ‘ ለመመሥረት ሌት ተቀን እየቃተተ ያለውን እና በአራት ዓመታት የተረኝነት አገዛዙ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ የመከራና የውርደት ዶፍ እያወረደ የቀጠለውን እጅግ አደገኛ የኦሮሙማ ቡድን በስሱ እያሄሱ በህወሃት ላይ የመረባረቡ ጉዳይም ትኩረትየሚሻ ጉዳይ ይመስለኛል ።
   ይህ እስካልሆነ ድረስ ነገረ ፖለቲካችን ሁሉ ውሃ ቅዳና ውሃ መልስ ወይም ቆሻሻ ውጣና ቆሻሻ ግባ (garbage in garbage out) ሆኖ ይቀጥላል የሚል ሥጋት አለኝ።

 3. TG – እንዳትሳሳት በኢትዮጵያ ፓለቲካ የክፋቱን ቁንጮ ወያኔ ይውሰድ እንጂ ሌሎችም ባለወረፋዎች ህዝብን በማመስ ላይ እንደነበሩና እንዳሉ የጠፋኝ አይምሰልህ። እይታዬ ወያኔን ብቻ የተጫነ ከመሰለህ ምንም ማድረግ አልችልም። የክፋት ሁሉ መሰረቱ እነርሱ ናቸውና። አንተ ኦሮምማ ብለህ የምትጠራቸው ቢሆነ የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚዎችና በእነርሱ የተቃመሱ ግፈኞች ናቸው። ምንም ቢደረግ ምንም የኢትዮጵያ ፓለቲካ አሁንም ወደፊትም ያው የወረፋ ዘረፋ እንጂ ትርፍ እንደማያመጣ ለሃገር ቆመናል የምንለው ሰዎች እንኳን ግልጽ በሆነው እይታ ላይ መተማመን ያቃተን መሆናችን አመላካች ነው። ባጭሩ በሃበሻው ምድር ለውጥ ማለት የጠገበን ገፍትሮ የተራበን በስልጣን ላይ ማውጣት ማለት ነው። ለሃገርህ፤ ለባንዲራህ፤ ለሃይማኖትህ የሚለው ጡርንባ ሁሉ በፊት የሰማነውና ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚደረግ ብልሃት ነው። ከላይ የዘረዘርካቸው የስልጣን እርከኖች ወያኔ በኦሮሞ ብሄርተኞች መተካቱን የሚያሳይ ድርጊት ነው። የአሁኑን በአይን አይቶ፤ በእጅ ዳስሶ ከበፊቱ ጋር ለማገናዘብ Blair Thomson -Ethiopia: The Country That Cut Off Its Head: A Diary Of The Revolution የሚለውን መጽሃፍና በተጨማሪም Ethiopia at bay by John H. Spencer ማገላበጡ ይጠቅማል።
  ባጭሩ ስለ ወያኔ ስናወራ ሌሎች የጥፋት ሃይሎች በፊትም ዛሬም ያደረጉትን የመዘንጋት ፍርሃት የለኝም። ሥራቸው በግልጽ ይታያልና። የእኔ እይታ አጠፋ የተባለው ሰው ሁሉ እንደ ሞሶሎኒ ተዘቅዝቆ ይሰቀል አይደለም። እሱን እኔ ሳልላቸው ኦሮሞዎቹ ያለምንም ፍርድ ሰውን ዘቅዝቀው ሰቅለዋል። የእኔ ምልከታ ለሚሰቃየው ህዝብ እናስብ ነው። ሌላው ሁሉ እንተም እንዳልከው ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ነው። አሁን እንሆ ወያኔ ልብ አግኝቶ ህዝባችን ሰላም ካገኘ የኦሮሞው እንዘጥ እንዘጥ በፍጥነት ሥፍራ የሚይዝ ይመስለኛል። አንድን ቁማርተኛ በሌላ ቁማርተኛ እየተካን ግን እስከ መቼ እንኖራለን? ወያኔ በሰላም አብሮ ለመኖር ጉዞ ከጀመረ ስለ ወያኔ ክፋትና ተንኮል መጻፋችን ለፈሰሰ ወተት ማልቀስ ስለሚሆን ይቆማል። ተስፋ አድርጋለሁ ሥጋትህ በጥቂቱም ቢሆን በዚህ ምላሽ እንደሚያገኝ። በቃኝ!

 4. ከህወሓት ተፈጥሮ ውጭ ግን በደረሳቸው ሽንፈት እጃቸውን እንደመስጠት ነውና እንዳይመለሱ ለመንግስት አንጻራዊ ድጋፍ እንጂ ቀዳዳዎችን ማስፋት ለኦነግ ሸኔ እንዲሁም የህወሓት ሸኔ ለመመስረት በር መክፈት ሊሆን ይችላል። አንድ ብሎ ሁለት ሰዎስት እንጂ ወደ ኃላ አይኬድም። ህዝብ የመረጠው መንግስት አለ ሙሉ ውክልና አለው፣ በትችት ማስፈጸም እና ወደ ሌሎች ጉዳዮች ለመድረስ ይጠቅማል። እኔ እኛ ካልመራን የትም ኣላደረሰም። ታሪኮች የየራሳቸው ታሪካዊ ማሕደር አላቸው።

 5. ሳስበው ሳስበው የአማሮች ነገር ይገርመኛል። አልፎ ተርፎም ያሳዝነኛል።

  ለምን ይገርመኛል ፧ ለምን ያሳዝነኛል፧ ላስረዳ።

  እስኪ T.G. የጻፈውን ኣስተያየት ተመልከቱ፤ አማራው ከትህነግና ከኦሆዴድ ብልጽግና የሚያገኘው ነገር የለም ይለንና መፍትሄ ስንጠብቅ ስጋቱን አካፍሎን ውልቅ ይላል። ሰውየው አማራ መሰለኝ። አማሮች በሙሉ አማሮች የአማራን የመረረ ስቃይ አሳምረው ከተነተኑ በኋላ የመፍትሄ ነገር ሲጠየቁ የለንበትም ወደማለት ያልፋሉ። ምክንያቱም በቁርጥ አማራ ክኦሮሞ መገላገል የሚችለው ራሱን በነጻነት ሲያስተዳድር ብቻ ነው ማለት ሃገሪቱን መክዳት ይመስላቸዋል። አማራ የራሱ የመከላከያ ሃይል ኖሮት ኣማሮችን ክኦሮሞና ሌሎች መጠበቅ ካልቻለና የኢኮኖሚ ነጻነቱን ከኦሮሞ መቀማት ካልቻለ በሰላም መኖርም ሆነ ማደግ አይቻለውም። T.G ይህን ሃሰት የምትል ከሆን ሃስብህን አካፍለኝ።

  አንድ ወዳጄ ከቀናት በፊት ይህን ጽፎ ነበር።

  ” ይህ የአማራ ህዝብ የኮንፌደሬሽን ጥያቄ ወሳኝ መሰለኝ። በኦሮሞ አስተዳደር ስር የአማራ ህዝብ የተሟላ ሰላምና ደህንነት አንዲሁም የኢኮኖሚ እድገት ሊረጋገጥ አይችልም። በኮንፌደሬሽን በነጻነት መሪዎቹን መምረጥ፥ ሰላምና ደህንነቱን ማስጠበቅ በኢኮኖሚ ማደግ ይቻለዋል። እስከኣሁን እንደታየው ከሆነ መሪዎች ተብዬዎቹ ኦሮሞዎች ሲጠሩዋቸው (አቤት) ሲልዃቸው (ወዴት) ባይ ናቸው። ከኦሮሞ ቁጥጥር ውጭ የሆነ አመራር የአማራን ህዝብ ሊያስመነድገው ይችላል። ከኦሮሞ ቁጥጥር ውጭ የሆነ አመራር ባለው የብሔር ፌደራሊዝም ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ያለፉት ሰላሳ አምስት ዓመታት ያረጋገጡት ይህንኑ ነው።

  የብሔር ፌደራሊዝም ይቆይ ቢባል እንኴ የተሻለ የሚሰራው በፕሬዚዳንታዊ ስርዓት እንጂ አሁን ባለው ፓርላሜንታዊ ስርዓት አይደለም የሚልው ክርከር አሳማኝ ነው።

  ለማንኛውም የአማራ ህዝብ መጪ እድል የሃገሪቱን መጪ እድል ይወስናል። ለዘለቄታው ከትግራይ ፣ ከኤርትራ፣ ክአፋርና ብንቫንጉል ጋር በኮንፌደሬሽን ታሳስሮ ወደፊት የሚራመድበት ኦሮሞ ደቡብን ይዞ የሚያነክስበት ጎዳና ይታየኛል።”

  ወዳጄ ባለው በሙሉ ባልስማማም አማራ ከኦሮሞ ቁጥጥር ነጻ አስካልወጣ ድረስ ስቃዩ አይቆምም፣ እድገትም አይኖረውም ባይ ነኝ። በጀመረው ሂደት ኦሮሞም ራሱ ክጨቋኝነት ወጥቶ ነጻ ሊሆን አይችልም። እና ለሁላችንም ነጻነት የአማራው ነጻነት ቁልፍ ነው የሚባለው ለዚህ ነው። በዚህ መንገድ ሄዳችሁ ሁላችንንም ነጻ አድርጉን።

  አሁን መገረሜና ማዘኔ ገባህ?

 6. አሁንገና –

  በግርጌ ማስታወሻ ላይ ሰለሞገስና ኤርምያስ ያልከው ትክክል ነው። የስምምነቱ አንቀጽ 10.4 በቀጥታ የሚመለከተው ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያን ነው። ጉዳዩ አማሮችን ያስቆጣል በሚል ፍራቻ ይመስላል ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ ለትግርይ ይመለሳል ከማለት ይልቅ በአንቀጹ ሸፋፍነው አልፈውታል።

  ሥልጣን ላይ ያለው (መንግስት)_ _ _ ፍላጎቱን በግልጽ ቋንቋ ሲያስቀምጥ እና _ _ _ ለትግበራውም መንገድ ሲጠርግ የከረመ ነው ያልከው በከፊል ትክክል ነው። እውነት ለመናገር መንግስት ፍላጎቱን በግልጽ ቋንቋ አስቀምጦ አያውቅም። ነገር ግን ውዝግቡ በህገመንግስቱ መሰረት እነደሚፈታ ሲናገር ቆይቷል። አሁን የተለወጠ ነገር የለም። ትሕነግም አቌሙ ይኀው ነው። ወደትግበራ ለመግባት መንገድ ጠረጋው አብቅቶ አሁን እውን ሊሆን ነው።

  የሚግርመው ነገር ዛሬ የሆነ ዜና የአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ላይ ጥሩ ልማት እየሰራ ስለሆነ እያስተዳደረ እንዲቆይ ተወሰነ በሚል ቱልቱላ ሲነፋ ሰማሁ። በሞግዚትነት ያስተዳድር ማለት ነው። ሲያለማ ቆይቶ ጊዜው ሲደርስ ለትግራይ ያስረክባል ማለት ነው። በግፍ ላይ ግፍ _ _ _

  የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ በህገመንግስቱ መሰረት ይፈታል ማለት ለትግራይ ይመለሳል ማለት አንደሆን ብዥታ ሊኖር አይገባም። በህግ ጉዳይ የትግራይ ጭንቅላት የሆነው ጌታቸው ረዳ በህገመንግስቱ መሰረት ማለት የትግራይ ክልል እንዳለ ወደነበረበት መመለስ (Status quoi ante) መሆኑን ተናግርሯል። መንግስት ይህን አልተቃመም።

  የአማራ ክልል ህገመንግስት ራሱ ወልቃይት ጠገዴን ምዕራብ ትግራይ በሚል ይገልጸዋል። ይህ ህገመንግስት አልተሻሻለም። እና አማራ ክልል ራሱ የተቀበለው ጉዳይ ነው።

  ጎበዝ ተስፋ ቁረጡ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share